|
የትግራዋይ ሞት ለማደብዘዝ አማራን መግደልና አማራን እንደ እንቁራሪት ማጯጯህ አስፈላጊ ነው
ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 04-22-21
መንደርደሪያ፥ የትግራይ መሬት እና ወያነ ትግራይ ለወራሪው ኃይል የማይፈታ ህልምና ቅዠት (nightmare) ሆኖበታል። ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ከኢምሬት፣ ከካርቱምና ከመቃድሾ አስተዳደሮች ጋር ለዓመታት ከመከሩበትና ከተዘጋጁበት በኋላ የሰሜን ዕዝ ተጠቃ በሚል ሐሰተኛ ውንጀላ ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈቱት የዘር ማጥፋት ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት ውድመትና ብረሰት ቢያደርስም፥ ጦርነቱ በተጀመረው በጥቂት ቀናት ውስጥ ግቡ ሳይመታ ተኮላሽቷል፣ ከሽፏልም። አሁን እየተደረገ ያለ ጦርነት ታድያ ትግራዋይ ለማንበርከክ ሳይሆን አይጥፍቶ የማጥፋት ተልዕኮ ላይ መሰማራታቸው መሆኑን ልብ ይሏል። አንድም፥ የጦርነቱ ቀስቃሾችና ለኳሾች አንድ የቁማር ሱስ የተጸናወተው ቁማርተኛ ሰው ያለውን ሁሉ ከተበላና ካራገፈ በኋላ በመጨረሻም የተበላውን ለማስመለስ ሚስቱን አስይዞ የሚቆምረውና ዕድሉን የሚሞክረው የበገነና የታወከ ባለ አመል ቁማርተኛ ይመሰላል። ይህ ማለት፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ከውርደትና ከሽንፈት ተርፈው ለድርድር የሚያበቃ ቁመና ይዘው ለመገኘት፤ አንድም፥ ከገቡበት ለመውጣት እየተደርጉት ያለ ጦርነት ለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በተጨማሪም፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈቱት የዘር ማጥፋት ጦርነት የሚያቆሞውና ሊያቆም የሚችለው ትግራይዋይ በይግባኝ ሳይሆን በጀግንነቱ ታፍሮና ተከብሮ የሚኖርባት አገር ስትፈጠር ብቻ ይሆናል። ከዚህ ውጭ ሊኖር የሚችለው ማንኛውም ዓይነት አማራጭ መንገድ የትግራዋይ ሃሳብና እምነት ሊሆን አይችልምና።
አንድም፥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ ሆነ የዐቢይ አህመድ ዓሊና የኢሳይያስ አፈወርቂ ትግራይንና የትግራይን ህዝብ ፈጽሞ የማብረስና የማውደውም ዘመቻ እንዳያይና የተቃውሞ ድምጹን እንዳያሰማ ያደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ መሬትና በተጋሩ ላይ ምን እየተደረገ እንዳለ ስለማይውቅ ሳይሆን በዋናነት ኢትዮጵያውያን በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ስር የሰደደ የመረረ ጥላቻና የምቀኝነት ውጤት ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ፥ ድስትና ማንኪያ፣ አህያ እንቁላል፣ አሸዋና በርበሬ፣ ሊጥና ወጥ እየገለበጠ የሚሰርቅ፣ የሚያጓግዝ፣ የሚዘርፍና የሚመነትፍ ሌብነት የማይገልጸው፤ ቀሚስ የለበሰች ሁሉ የሚያስነውር ወራዳ ህሊና ቢስ ሠራዊት አሰማርቶ ትግራይን ሲያበርስና ሲያወድም የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍና ሲገድል ኢትዮጵያውያን ሳያዩና ሳይሰሙ ቀርተው ሳይሆን የኢሳይያስ አፈወርቂንና ሠራዊቱን የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው! ሲሉ በደስታ ስለ ተቀበሉት ብቻ ነው። ይህን ዓይነቱ ለየለት ሰይጣዊ ጥላቻና ምቀኝነት በሚገባው መንገድ ተገቢ ስፍራውን ሳያገኝና ፈጽሞ ሳይጸዳ፣ ኢትዮጵያውያን ትግራዋይ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ሳያውቁና ሳንተዋወቅ ተድበስብሶ የሚፈጸም ዕርቀ ሰላም ተመሳሳይ ጥፋት እንዲፈጸምብን የመፍቀድ ያህል ነው የሚሆነው።
እውነት ነው፥ ኢምሬቶች ለትግራይ ህዝብ እርዳታ እንሰጣለን በሚል ሽፋን አሻንጉሊታቸው ከገባበት አዘቅት ለመውጣት ያስችለው ዘንድ አገልግሎት ላይ የሚውል የጦር መሰሪያ የእርዳታ መሸፈኛ ልባስ እየሸፈነች በህገ ወጥ መንገድ ዐቢይ አህመድ ዓሊን ማስታጠቅ ቀጥላበታለች፤ ለልማት የሚውል አካፋና ዶማ በመስጠት ሳይሆን ቦምብና ጥይት በማስታጠቅና በመቸብቸብ ተምትተዳደረው ራሽያም የጦር አማካሪዎችና ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች (Russian Private Military Companies/RPMCs) ልካለች፤ ይህ ሁሉ ግን የዐቢይ አህመድ ዓሊ ከገባበት ጉድጓድ የሚያተርፈው ሳይሆን የገባበት ጉድጓድ ጥልቀት የሚጨምር ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ አብቅቶሎታል። ከእንግዲህ ወዲህ የጠጠር ወርዋሪና የኮኮብ ቆጣሪ ጥንቅላ፣ የከራማትና የምዋርተኞች ልመና፣ የሊቀ ጳጳሱ ዕጣን ሆነ ግባ በለው የሠራዊት ጌታ ካንተ ጋር ነው እያሉ በንጹሐን ደም መፍሰስ ደስ የሚሰኙ የጴንጤ ጸሎት አያድነውም፣ የሚመልሰው ነገርም የለም። ርግጥ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአፉ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! እያለ ስልጣኑን ለማደላደልና ለማስጠበቅ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው ክህደትና በደል በተለይ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የሰራውንና የማይፈጸመውን ክህደትና ወንጀል ኢትዮጵያውያን የማወቅ አቅሙና አጋጣሚው ቢኖሯቸው ኖሮ ሰውዬውን አጋድሞው ያርዱት ነበር ብቻ ሳይሆን፥ ሰባት ትውልዱ በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመቃብር ስፍራ እንዳይገኝ ሰላማዊ ውቅያኖስ አውጥተው እንደሚጥሉት አንዳች ጥርጥር የለኝም።
የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የንስሃ አባቱ የኢሳይያስ አፈወርቂ አሳች ምክር
መንደርደሪያ፥ የመረጃ ተፋሰስ በመቆጣጠርና የኢንተርኔት አገልግሎት በመቆራረጥ፣ የትግራይ ሴቶች በአሰቃቂ ሁኔታ በማስነወር፣ ከተሞችን በእሳት በማጋየት፣ ፍብሪካዎች በመንቀል፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማውደም፣ አብያተ ክርስቲያናት በማፈራረስ፣ ቅድሳት መጻህፍት በማቃጠል፣ ካህናቶችን በማረድና ወጣቶችን በመረሸን፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ታጣቂዎች በከተሞች በማፍሰስና በማሰማራት ትልቁም ትንሹም ትግራዋይ ደም ያለው ሁሉ በማሸበርና በመግደል ትግራይን እቆጣጠራለሁ፣ የትግራዋይ ሥነ ልቦና አሰብራለሁ፣ የትግራይ ህዝብ አንበረክከዋለሁ፣ አልፎም ተርፎም፥ የዓለሙ ማህበረሰብም ቢሆን የምፈልገውን ትርክት አስኮመክመዋለሁ ብሎ በማመን እህልና መድሃኒት ጨምሮ ትግራይ ከማንኛውም ዓይነት ሰብአዊ አገልግሎቶች በማገት ህዝብን እንደ ህዝብ እያጸዳ ያለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በዚህ ሰይጣናዊ ተግባሩ በጸና ቁጥር አወዳደቁ የከፋ እንደሚሆን ትምህርት እየወሰደ ለመሆኑ የኢቲቪ፣ የኢዚአ፣ የፋናና የዋልታ የተምታታና የተውረገረገ ውሎዎች መመልከት በቂ ነው።
በርግጥ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሰሜን ዕዝ ተነካ በሚል ሐሰተኛ ክስ፥ በላይ በሰማይ ኢምሬት፣ በሰሜን ኤርትራና ሱማሊያ፣ በደቡብና በምዕራብ አማራ አፋር ሱማሌ ኦሮሞ እንዲሁም የፌዴራል ሰራዊትና የፖሊስ አባላት አሰባስቦና አስተባብሮ በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈተው ሚልዮኖች ያፈናቀለና በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ንጽሐን ተጋሩ ህይወት የበላ (እየበላም ያለ) ጦርነት ዓላማ አሁን ለሁሉም ግልጽ ነው ተብሎ ይታመናል። የትግራይ ህዝብ እንዲጨፈጨፍ፣ እንዲገደል፣ እንዲበርስና እንዲያልቅ፣ ሀብት ንብረቱን እንዲወድምና እንዲዘረፍ የተፈለገበት በርካታ ምክንያቶች መካከል፥ ከራማው ዲና ሙፍቲ በይፋዊ መግለጫው ምናልባት ሰው አይጠይቅም እንጂ እያንዳንዱ ኤርትራዊ ቢጠየቅ ከኢትዮጵያ ጋር የተለዩበትን ቀን አያከብሩትም፣ አይወዱትም፤ በኢትዮጵያ በኩልም ተመሳሳይ ስሜት ነው ያለው ሲል እንደተናገረው ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙትን ወረራ ዓላማ ለዓለም ግልጽ አድርጓል። እውነት ነው፥ የከራማው የዲና ሙፍቲ የምዋርት ንግግር እውነት ነው ብሎ የሚቀበልና ሐቅ የሚመስለው በጥላቻና በምቀኝነት የሰከረ የኢትዮጵያ ህዝብ በቁጥር ቀላል አይሆንም፤ ቢሆንም ግን፥ ሐቁ ከራማው ዲና ሙፍቲ እንዳለው ሳይሆን፥ ኤርትራ እንደ ተወለደች የቀጨጨችና የበከተች አገር ብትሆንም ኤርትራና ኤርትራውያን ግንቦት 24 የነጻነት ቀን በማለት በደማቅ አከባበር የሚያከብሩት ሀገራዊ በዓል እንዳለ፣ ኤርትራ እንደ አገር ለማቆም በተደረገው የህዝብ ድምጸ ውሳኔም (referendum) 98.9 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ ይሁንታውን ሰጥቶ ያቆማትና በይፋ ነጻነትዋን ያወጀች አገር መሆኗን ማወቁ አስፈላጊ ነው። ስለ ኤርትራ ለኤርትራውያን በመተው እዚህ ላቆምና ወደ ዋና ነጥቢ ግን ልመሰል።
መያዣ መጨበጫ የሌለው ወሬ ሲያወራ ጸሐይ የምትጠልቅበት ኢሳይያስ አፈወርቂና የበከቱ የአማራ ልሒቃን ምክር ሰምቶ፤ አንድም፥ እናቴ የኢትዮጵያ 7ኛ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኛለች በማለት የኢትዮጵያ ንጉሥ ለመሆን ሲያኮበኩብ በለኮሰው እሳት በአሁን ሰዓት መላ ሰውነቱ ተያይዞ የሞት ጣር እያሰማ የሚገኘው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወያነ ትግራይ ጀርባው ላይ እያሳረፈበት ያለ በትር ሊሸከመው ከሚችለው በላይ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሊጫወተው ያሰበውን ጌም ከአፉ ተነጥቆ ወያነ ትግራይ በውስጥም በውጭም እጅግ በተሻለና ፈጣን በሆነ አደረጃጀት አሰላለፉን አሰማሮ ለክብሩና ለሉዓላዊነቱ መቆም በመቻሉ ጌሙን ከመብላቱ በላይ የጌሙን ህግ ወደ መጻፍ ተሸጋግሮ የሜዳው ባለቤትና ዳኛ ለመሆን በቅቷል። ይህ የወያነ ትግራይ ነባራዊ ሁኔታ ታድያ፥ በኢሳይያስ አፈወርቂ፣ በዐቢይ አህመድ ዓሊና በአማራ ልሒቃን ሰፈር ላይ ከፍተኛ የሆነ ግራ መግባት፣ መቃወስና መናጋት፤ ብሎም ተጨባጭ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሽንፈትና ኪሳራ ለማስመዝገብም አስችሎታል። ይህን ሐቅ ለማየትና ለመመልከት ታድያ የወዳደቁት ታንኮችና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንደ ቅጠል የረገፈው የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊት ለመቁጠር ትግራይ ጦር ግንባር ድረስ መውረድ ሳይጠይቀን የወራሪው ኃይል የሠራዊት አለቆችና የፖለቲካ ሹማምንት በአንዲት ጀንበር ውስጥ የሚናገሩት ነገር ሁሉ ዱላ ቢያቀብሉት እርስ በርሱ የሚጋጭና የተተረማመሰ መግለጫዎች ልብ ማለት ብቻውን በቂ ነው። ሌላው ቀርቶ፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድና ዓሊና የአማራ ልሒቃን ወያነ ትግራይ ፊት ለፊት ሊገጥሙ ቀርቶ አዳዲስ የትግራኛ ዘፈኖች በሰሙ ቁጥር መደናበርና ግራ መጋባት፤ ከዚህ የተነሳም ውሃ የማይቋጥር ድንገታዊ መግለጫዎችና የፈጠራ ዜናዎች ለመሰራጨት ሲገደዱ እየተመለከትን ነው።
ይህ በተለምዶ ጴንጤ አንድም የብልጽግና ወንጌል ተብሎ የሚታወቅ በክርስትና እምነት የተወገዘ አስተምሮ የሚያራግብና ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምዶች የሚያራምድ የክርስትና ክንፍ የሆነ የእምነት ተቋም አማኝና ፓስተር ነኝ የሚለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ የንስሃ አባት የሆነው ኃይማኖት የለሹ የኤርትራ የዕድሜ ልክ ገዢ የኢሳይያስ አፈወርቂ ምክር የአንዲት ማለዳ ቁርስ ይሆን እንደሆነ ነው እንጅ ምሳ አልያም እራት ሊሆን እንደማይችል ላለፉት ሃያና ሠላሳ ዓመታት በግሃድ የታየ የኤርትራና የኤርትራውያን የድንቁርና፣ የጨለማ፣ የኋላቀርነት፣ የትምክህት፣ የድህነት፣ የእጦት፣ የችጋር፣ የልመና፣ የስደት ብሎም የጥፋትና የእልቂት መንገድ እውነተኛና ተጨባጭ ምስክር ነው። በመሆኑም፥ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ሹማምንቶቹ የራሳቸው ህዝብ ከማወናበድና ከማታለል አልፈው ለዓለም ማህበረሰብ ሳይቀር ሲዋሹና ሲሸመጥጡ እጅ ከፈንጅ በመያዛቸው ውርደቱ ከራሳቸው አልፎ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ የምዋርተኞች፣ የምቀኞችና የነፍሰ ገዳዮች አገር እንደ አገር የወራዶችና የወስላቶች አገር ለመሆኗ በአደባባይ አስመስክሯል።
ኢሳይያስ አፈወርቂ፥ ዓመት አልፎ ዓመት በተተካ ቁጥር አንዲት ለእናትዋ በሆነችው የኤርትራ የቴሌቪዥን መስኮት በዓመት ሁለት ጊዜ ብቅ እያለ ለረጅም ለሰዓታት በሚሰጠው መቋጠሪያ የሌለው፣ የማይጨበጥ፣ አሰልቺና ተደጋጋሚ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ዓይነቱ ቃለ ምልልሶች ከመስጠት ያለፈ በተጨባጭ የሦስት ሚልዮን ኤርትራውያን ህይወት መለወጥ የተሳነው የአፍአ ፈላስፋ መሆኑን ያረጋገጠ፣ በዓለም መድረክ የተገለለና የተናቀ ሰው ከመሆኑ በላይ በቀጠናው ህልውናቸው ባይታይም ግን የማይታጡ አካላት ተባራሪ ኬብሎችና ሰነዶች እንደሚያመላክትቱም ሰውየው ምንኛ የተናቀና ፈጽሞ የተተወ ለመሆኑ ኢሳይያስ አፈወርቂ snag አንድም በራሱ ጊዜ የሚንጋዳል የቆነቆነ ዛፍ ተብሎ እንደሚገለጽም ይታወቃል። ሌላው ቢቀር፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ በግለሰብ ደረጃ ሆነ እንደ መንግስት የሚጠቅም ዓይነት ሰው ቢሆን ኖሮ ከምንም በላይ ኤርትራና ኤርትራውያን የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጤናማ አእምሮ ባላቸው ዜጎች ዘንድ የሚያከራክር አይደለም። ዳሩ ግን፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ ለመልካም ነገር ያልታደለ ፍሬ አልባ በለስ ከመሆኑ በላይ ስልጣን ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለኤርትራውያን ሆነ ኤርትራን የሚያዋስኑ የጎረቤት አገራት ሰላም ማጣት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ይሄው ድፍን ሣላሳ ዓመታትን አስቆጥሯል። ይህ ሰው ከእሾህም የተለየ የሰው እሾህ ሆኖም ሰውና አገርን የደም እምባ ሲያደማና ሲያስለቅስ ከርሞ በአሁን ሰዓት ደግሞ የሰው አገር ሰው በማስጨነቅ ላይ የሚገኝ አረመኔም ነው።
መጽሐፍ፥ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል እንዲል ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መተሻሻቱና መዳራቱ ለመልካም ነገር ተጠቃሚ ሳይሆን ያደረገው እንደውም በአንጻሩ ሰውየው የበሽታው ተሸካሚ አድርጎ የውርደት መንገድ እንዲያቀጥነው አድርጎታል። እንደ አገር መሪ ሳይሆን፥ ጌታውን ሲያይ ጭራውን እንደሚቆላ ውሻ መቁነጥነጥና መሽኮርመም ልዩ መለያው ያደረገ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር አንድ መዓድ መካፈል ከጀመረ ዕለት ጀምሮ ይሄው ኢትዮጵያ እንደ አገር ሰላምዋን ሙሉ በሙሉ አጥታ የኤርትራ የጨለማ፤ የስደት፣ የውርደት፣ የኪሳራ፣ የውድቀት፣ የኋላቀርነት፣ የድህነትና የችጋር መንገድ ከተያያዘችውም ከራርማለች። መቼ ይሄ ብቻ፥ አገሪቱ በአሁን ሰዓት ተሽጦ ዋጋ እንደማያወጣ ዕቃ በዓለም መድረክ ክፉኛ የተገለለች፣ የተተወችና የተናቀች፤ ትልቁም ትንሹም የተጸየፋት አገር ለመሆንዋ ባለ አእምሮ የማይስተው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
እዩኝ እዩኝ ያለች ማሽላ አንድም ለወፍ አድም ለወንጭፍ
ኢሳይያስ አፈወርቂና መንግስታቸው ለአማራ ያለው ያላቸው አመለካከት ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በአንድ ወቅት ኢሳይያስ አፈወርቂ፥ የሚከተለውን ብለው ነበር፤ ይኸውም፥ ከአማራ ጋር አይደለም አብሮ መስራ አብሮ መለመንም አይቻልም ሲሉ ለአማራ ያላቸው ንቀት የገለጹት በአደባባይ ነው። ቀይ ባህርና አሰብ ላይ ተነተርሶ ሲያበቃ እያዛጋ እንዲውል፣ የጉሮሮ ላይ ስንጥር ሆኖ አቅም ያሳጣቸው ትግራዋይ የሚባል ህዝብ በአንድም በሌላም መንገድ ገለል ያለላቸው እንደሆነ ኢሳይያስ ከኢትዮጵያ የሚሹትን ሁሉ ለማግኘት አማራን በቀላሉ ሊያንበረክኩት እንደሚችሉና ለአማራና ለአህያ መድሃኒቱ ዱላ ነው! ብለው እንደሚያምኑ ጠንካራና ጥልቅ ገምጋማቸውን ያሰፈሩት እኔ ሳልሆን ትላልቅ የምዕራቡ ዓለም ተቋማት የቆየ የሰንድ ማህደር ነው። ይህ በእንዲህ ሆኖ ሳለ ግን ኢሳይያስና አማራ ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ መዝመታቸው እንግዳ ነገር ባይሆንም በአማራ ልሒቃን እየተዋጠ የመጣውን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ቡድን በቀጥታም በተዘዋዋሪም አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለው ኢሳይያስ አፈወርቂ በቀጠናው ያለው ፍላጎትና ተልዕኮ ግን በቀላሉ የሚታለፍ ሊሆን አይገባም በማለት ባለሞያዎቹ አስተያየታቸውን ሲሰነዝሩ እየተስተዋለ ነው።
እውነት ነው፥ በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች እየታየ ያለ ሰልፍና እየተሰማ ያለው ጩኸት መንስኤው በአማራና በኦሮሞ ልሒቃን መካከል ያለውን መከፋፈል ወደ ህዝብ መውረዱ ብቻ ሳይሆን፤ ጎንደርና ጎጃም ሽዋና ወሎ እየተባባለ አንዲት ቀን ተስማምቶ የማያውቀውን የአማራ ልሒቅ መካከል ያለው የእርስበርስ መባላትና መጠላለፍ መሆኑም ሊዘነጋ አይገባም። እግዚአብሔር በሴኬም ሰዎችና በአቤምሌክ መካከል ክፉ መንፈስ በመልቀቅ በክፉ አድራጊዎች ላይ ፍርድን እንዳደረገ እንዲሁ በራሳቸው ጊዜ ያነደዱት እሳት ተመልሶ እነሱን የሚበላ እሳት መሆኑም የማይቀር ነው። በርግጥ፥ እዚህ ላይ መታወቅ የሚገባው አንኳር ነጥብ ቢኖር እዚህም እዚያም በመላ አገሪቱ ላይ እየታየ ያለ ሁከትና የእልቂት ማዕበል ብዛት እኩል ተዋናዮችም በርካታ መሆናቸውንና በዐቢይ አህመድ ዓሊ ሙሉ ሥልጣን የምትተዳደር አገር እንደሌለች ይህ ሁነኛ ማሳያ ነው። አንድም፥ ከቀበሌ እስከ ካቢኔ የተሰገሰገውና የተቀመጠው ሹም ሁሉ ከራሱ ውጭ ማንንም እንደማይሰማና ሁሉም በአቅሙ ያሻውንና የወደደውን የሚያደርግበት፣ ኢትዮጵያም መንግስት አልባ አገር ለመሆንዋ ይህ ምስክር ነው።
ከዚህ ቀደም የአማራ ህዝብ እንደ ከብት እያጋደመ እያረደ ያለው ሌላ ማንም ሳይሆን የአማራ ልሒቃን ናቸው (http://aigaforum.com/amharic-article-2020/the-amahara-elites-are-killing-the-amhara.htm) በሚል ርእስ በሰፊው እንደጻፍኩት የአማራ ልሒቃን የአማራ ህዝብ ልብ ለማሸነፍ፣ ከጎናቸው ለማስለፍና ምኒልካዊት ኢትዮጵያ የመፍጠር ህልማቸውን ለመሸጥ ካሴሯቸው ሴራዎችና ተግባራዊ ካደርጓቸው ዕቅዶች መካከል አማራን በመግደል አማራን ማስቆጣት፣ ተመልሶም ስለ አማራ መጮህና ማልቀስ አንዱ ነው። ቤንሻንጉልና (መተክል) ኦሮሚያ ለዚህ እኩይ የአማራ ልሒቃን ሴራ መሳካትም ተመራጭ ክልሎች በመሆን አገልግሏል እያገለገሉም ይገኛሉ። ይህ አማራን በመገደል አማራን እንደ እንቁራሪት የማጯጯህ የአማራ ልሒቃን ሴራ ከሌሎች በርካታ ሴራዎች ሲነጻጸር በአፈጻጸሙ በአመዛኙ በአማራ ልሒቃን አቅም ሊከናወን የሚችል ሴራ ሲሆን ግቡ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለመዋጥ፣ ወደድክም ጠላህም ያለንህ እኛ ብቻ ነን! እኛ ያልንህ ትሰማና ታደርግ እንደሆነ ትሰነብታለህ አሻፈረኝ ያልክ እንደሆነ ደግሞ ይሄው እያየኸው ነው እያሉ የገዛ ራሳቸው ህዝብ በጠራራ ጸሐይ እያሳደዱና እያፈናቀሉ፣ እየጨፈጨፉና እየገደሉ እንደ ቁራ እያስጮኹት ያለውን ህዝብ እንደ ባንዴራ እያውለበለቡ ለማስፈራራትና የሚፈልጉትን ለማግኘት የንጹሐን የአማራ ክልል ተወላጆች ደም መጠቀሚያ ማድረጋቸው ነው። ከተሳካላቸው ደግሞ፥ የፌዴራል ስርዓቱ ለዚህ ሁሉ እልቂትና ደም መፋሰስ ተጠያቂ በማድረግ አሃዳዊ ስርዓት መልሶ መትከል ነው። ቀለል ባለ አማርኛ፥ ሞተ አለቀ እየተባለ ደሙ በከንቱ እየፈሰሰ ያለው የአማራ ክልል ተወላጅ ዋና መሃንዲስ ሌላ ማንም ሳይሆን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ካላቸው ምኞት የተነሳ የገዛ ራሳቸውን ህዝብ በመግደልና ለመጨፍጨፍ ተማምለው የወጡ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ናቸው። ፊታቸው ወደ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሲያዞሩ ደግሞ፥ ተዋቸው ይጩሁ፣ መገናኛ ብዙሐን ሰልፉን ይዘግቡት፣ በትግራይ መሬት በተጋሩ ላይ እየፈጸምከው ያለኸው ዘር የማጥፋት ዘመቻ በዓለም መድረክ ያገኘውን ሽፋን ለማብረድ ይጠቅማል፣ ማፈናፈኛ ያሳጣህ የዓለም ማህበረሰብና መገናኘ ብዙሐን በአማራ ሰለፍ መላምት እየሰጠ ይጠመድ! እያሉ የትግራዋይ ሞት ለማደብዘዝ አማራን መግደልና አማራን እንደ እንቁራሪት ማጯጯህ ስራችን ብለው ተያይዘውታል። ያም ሆነ ይህ ግን ከነተረቱ፥ እዩኝ እዩኝ ያለች ማሽላ አንድም ለወፍ አድም ለወንጭፍ እንደሚባለው ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በራሳቸው ጊዜ ያስቆጡት ህዝብ ከቁጥጥራቸው ውጭ ሆኖ ተመልሶ እንደሚውጣቸውና እንደሚበላቸው የታወቀ ነው።
E-mail: mahbereseytan@gmail.com
Back to Front Page |