Back to Front Page

የአማራ ህዝብ እንደ ከብት እያጋደመ እያረደ ያለው ሌላ ማንም ሳይሆን የአማራ ልሒቃን ናቸው

የአማራ ህዝብ እንደ ከብት እያጋደመ እያረደ ያለው ሌላ ማንም ሳይሆን የአማራ ልሒቃን ናቸው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል (ስትራቴጂስት) 12-28-20

 

የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ በነበረበት ዘመን አንድ ኤልሳዕ የተባለ ብርቱ ነቢይ ከሎሌው ጋር በዶታይን ሰፍሮ ነበር። በተደጋጋሚ ሽንፈት የቀመሰ የሶሪያ ንጉሥ፤ አማካሪዎቹ፥ የሽንፈቱ ምክንያት ንጉሱ በር ዘግቶ በጓዳ የሚመክረውን ምክር ለእስራኤል ንጉስ የሚናገር ነቢይ ስላለ ነው ብለው ስለ ነገሩት ንጉሱ የተባለውን ሰው ይዘው እንዲያመጡለት ትዕዛዝ ይሰጣል። የሶሪያ ወታደሮች በሌሊት ከተማዋን ከቧት አደሩ። ማልዶ የተነሳ የኤልሳዕ ሎሌ የሚያየው ነገር ማመን ስላቃተው ወደ ኤልሳዕ መጥቶ፥ ጌታዬ በቃ አለቀልን፣ ሞትን ዋጡን ሲል የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ይነጫነጫል። የኤልሳዕ ምላሽ ግን አስደናቂ ነበር። አንተ ሰው እንዴት አይገባህም? ይህ ሁሉ ዘመን ከእኔ ጋር ኑረህና የእግዚአብሔር ተአምራት በዓይንህ አይተህ እንዴት እንደዚህ ትርበደበዳለ? እንዴትስ በአምላክህ አትታመንም? እንዴት አይገባህም? ብሎ አልተቆጣውም፤ አላመናጨቀውም፣ ጣል ጣልም አላደረገው። ኤልያስ ያደረገው ቢኖር አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ነበር ጸለየለት።

 

Videos From Around The World

ዘንድሮ፥ በመበታተን አፋፍ ላይ የምትገኘው በላተኛይቱ ኢትዮጵያ ግራ ያልተጋባ ሰው ይኖራል ብሎ ማመን የሚከብድ ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዜጎች በመላ በምድሪቱ እየሆነ ስላለ ነገር ተምታቶበታል። በርግጥ፥ በተራው ዜጋ ላይ ቀርቶ የአገሪቱ መንግስት ነኝ ብሎ የሚያምን ድንገተኛ ፖለቲከኛው አቢይ አህመድ ዓሊ ሳይቀር የገባበት ጉድጓድ ጥልቀት በውል የተረዳ ሰው አይደለም። እንዴት አይገባው? ብሎ መፍረድም አዳጋች ነው። በመሆኑም፥ ግራ የተጋባና እየተምታታበት ያለ ተራ ዜጋው ብቻ ሳይሆን አንዱን ለመገንባት ሌላውን ማፍረስ ላይ የተጠመደው አደጋ ጣዮ አቢይ አህመድ ዓሊ ጭምር ነው።

 

በጥቂቱ ወደኋላ ልመልሶት። ከጥቂት ዓመታት በፊት በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ የተነሳ ውልደ ቀዳማዊ ኢህአዴግ የነበሩ ብአዴንና ኦሆዴድ ካርታ በመቀባበል በህወሓት መሪዎች ላይ በማሴርም የህወሓት መሪዎች በመገፍተር ወደ ስልጣን መጡ። የሦስተኛ ዓለም ፖለቲካ ትንግርት ነውና ኦሆዴድ እቺ ባቄላ ካደረች ሲል ገና በጥዋቱ ብአዴንን በርግጫ ብሎ ብቻውን መንገዱን ማቅጠን ተያያዘው። ከዚያ በኋላ ብአዴን ስሙን ቀይሮ ብቅ ቢልም ታሪኩን መቀየር ሳይችል ስለቀረ ባለተራውን ኦዴፓ ተላላኪ ሆኖ ለማገልገል ተስማማ። የአማራ ልሒቃን ማመን ነፋስን መከተል ነው! ብለው የሚያምኑ የኦሮሞ ሰዎች የአዴፓ ወዶ ገብተን እንዲሁ በቀላሉ አልተቀበሉትም። ታማኝ ታላላኪዎች ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው አዴፓዎች ጓዶቻቸውንና የስራ ባለደረቦቻቸው በጠራራ ጸሐይ ገድለውና አስገድለው አቢይ አህመድ ዓሊ ለሚመራው ኦዴፓ ባቀረቡት ገጸ በረከት ፍርፋሬ ከመልቀም ተገላግለው ጥግ ላይ ተቀምጠውም ቢሆን በኦዴፓ መዓድ ላይ ለመካፈል ዕድል አገኙ።

 

አዴፓዎች - ኦዴፓ ጃስ ባላቸው ቁጥር እንዳበደ ውሻ መጮህና መክለፍለፍ ተያያዙት። የምላስ አርበኛ ከመሆን ያለፈ ሓሙቱ ስልነበራቸው ግን የተለመደውን ቀረርቶና ሽለላ አሰምተውና ፎቶ ግራፍ ተነስተው ከመመለስ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራቸው። አንድ ሲባል ሁለት ዓመት አለፈ። በተላላኪነት የታመነ አዴፓ አድጎ ቀስ በቀስ መርዙን መርጨት ጀመረ። ኦዴፓዎች የፈሩት አልቀረም። አዴፓዎች ገሰገሱና ሰውየው ከጓዶቹ ገነጣጠሉት። ቀድሞውኑ በማንነት ቀውስ ሲናጥ የነበረ ሰው (አቢይ አህመድ ዓሊን) ለብቻው ነጥለው አቢይ ሺህ ዓመት ይንገስ! ሲጨመሩለት ጨርሶ ተሳከረ። እመራዋለሁ ከሚለው ህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ የመሆኑ ነገር ሲያሳስበው ደግሞ፥ በዚህ ሰዓት ትግራይን ብትወጋ ቀድሞ ከነበረህ ክብር ይልቅ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትከበራለህ፣ ትነግሳለህ፣ ከፍ ከፍ ትላለህ ሲሉት ጥሬው እውነት መስሎት ያጣው ክብርና ጭብጨባ ለመመለስ በሐሰት ክስ በትግራይ ላይ ጦርነት ከፈተ። የትግራይ ህዝብና የትግራይ ከተሞች ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር በከባድ መሳሪያና ከዓረብ ኢምሬት ባገኘው ድሮን አወደማቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ለሞትና ለስደት ዳረጋቸው። የአማራ ልሒቃን ምኞት ለጊዜው የተሳካ ይመስላል።

 

የአማራ ልሒቃን ሦስት ዓመት ሙሉ አምጠው የአቢይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጉያ ላይ ተወሽቀው፤ የአፋርና የሱማሌ ስፍር ቁጥር የሌላው ሰራዊት አስከትለው የትግራይ ህዝብ በአራት አቅጣጫ ከበው ከወረሩ በኋላ (ለጊዜው)፤ ይሄው ዛሬ ደግሞ ቀን ቀን ከእሱ ጋር (ከዐቢይ አህመድ ዓሊ) እጥፍ ዝርግት እያሉ ሲያሸረግዱና አቧራ ያልነካው የአቢይ አህመድ መቀመጫ ሲጠርጉ ይውላሉ፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እንደ ይሁዳ ወጣ እያሉ ማስክ አጥልቀው ጨለማን ተገን በማድረግ የገዛ ወገኖታቸውን እንደ ዶሮ ሲያርዱና እንደ ደን ሲመነጥሩ ጨለማው ይነጋባቸዋል። በማለዳ ተነስተው ደግሞ ሰው መስለው ለአማራ ህዝብ እንደሚቆረቆሩ ሲያለቃቅሱ፣ ሲሸልሉና ዘራፍ ማለት ስራችን ብለው ተያይዘውታል። በነገራችን ላይ፥ በአሁን ሰዓት አቢይ አህመድ አየር ላይ የማንሳፈፍ የአዴፓዎች አጀንዳ በውል ተጀምሯል። አንባቢ ይህ ሁሉ ክፋትና ሴረኝነት ለምንድ ነው? የአማራ ልሒቃን ዓላማ ምንድ ነው? በማለት ጥያቄ ያነሳ ይሆናል። እዚህ ላይ ወደ ምክንያቶቹ በቀጥታ ከመግባቴ በፊት የአማራ ልሒቃን የክህደት፣ የሌብነትና የምቀኝነት ተፈጥራዊ ባህሪይ ምናልባት የማያውቅ ዜጋ ያለ እንደሆነ በግርድፉ ለማስታወስ እወዳለሁ።

 

የአማራ ልሒቃን ማንንም የማይበጅ ያርጀና ያፈጀ መሳፍንታዊ አስተሳሰብ አራማጆች ከመሆናቸው በላይ ሰዎች ጨረቃ ላይ ቤት ሰርተው በሚኖሩበት 2020 ዓ/ም ላይ ሆነውም የሰማኒያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የድምር ውጤት የሆነችው ኢትዮጵያን የመምራት መለኮታዊ ስልጣን ያለንና የሚገባን እኛ ብቻ ነን! ብለን የሚያምኑ የበከቱ ጸረ ሰላምና ጸረ ዕድገት የትውልድ ነቀርሳዎች ናቸው። እንደ እባብ ጉልበታቸው ምላሳቸው ላይ የተሰነቀረችው የአማራ ልሒቃን ምኞትና ፍላጎት አንድና አንድ ነው። ይኸውም፥ ቀደም ሲል እንደገለጽኩት ሌላውን ረግጠውና አስገብረው፣ አንድ ሃይማኖት አንድ አገር! የሚል የደንቆሮ ዘፈን የምታስተጋባ ጨፍላቂ ኢትዮጵያ መልሶ ማምጣትና እነሱ ጌቶች ሌላውን ባሪያ፣ እነሱ አጥማቂ ሌላው ተጠማቂ፣ እነሱ ደረጃ መዳቢዎች ሌላው ፍርፋሬ ለቃሚ፣ እነሱ የዜግነት ሴርተፊኬት ሰጪዎችና ነሺዎች ሌላው ተመጭዋች ሆነው እዘዝ በገላየ እያሉ እየተንፈላሰፉ በሌላው ዜጋ የደም ላብ ተዘለው የመኖር ቅጀታቸውን እውን የምታደርግ ኢትዮጵያ መልሰው መምጣት ነው።

 

በርግጥ ሰዎቹ የሚሰማቸው አጡ እንጅ የአማራ ልሒቃን ማለት፥ ኢትዮጵያዊነት ወደ መንግስተ ሰማያት የምንገባበት ብቸኛ መታወቂያ እንደሆነ ሲነግሩንና ሲሰብኩን ሰውና እግዚአብሔር ምን ይለናል?! የማይሉ ኃፍረት የማያውቃቸው የሰው አውሬዎች ናቸው። እውነት ነው፥ ከእነሱ በላይ የኢትዮጵያ አምላክ እያለ የአዞ እንባ እያነባ መሬት ለመሬት የሚንከባለል አስመሳይ፣ ከእነሱ በላይ የፈጣሪ ስም የሚጠራና የሚመጻደቅ ሰው የለም። ሐቁ ግን፥ መጽሐፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር፥ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል እንዲል እንደ የአማራ ልሒቃን ያለ እግዚአብሔር አምላክ ነፍሱ እጅግ አድርጋ የምጽየፈው፥ ሌብነት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ምዋርት፣ የሰውን እምነት ማጉደል፣ ሴረኝነት፣ እኔነት፣ ሐሰተኛ መልስ፣ አሉባልታ፣ መተት፣ የክህደትና የምቀኝነት ህይወት ውስጥ የተዘፈቀ ዜጋ በዓለም በእግርና በፈረስ ቀርቶ በኩራዝ ተፈልጎ አይገኝም። አሁን ቀደም ሲል ወዳነሳሁት የአማራ ልሒቃን የአማራ ክልል ተወላጆች እንደ ከብት እያጋደሙ የሚያርዱበት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች በአጭሩ ላስቀምጥ። ይኸውም፥

 

1.   ቀደም ሲል በኦሮሚያ በሱማሌና በጋምቤላ ቀስ በቀስ የጀመሩት በህወሓት መሪዎች ላይ ሲያሳብቡት የከረሙት ህቡእ ኦፕሬሽን አድጎ ዛሬ ደግሞ በመተከልና በአፋር ደሙን እንደ ውሻ ደም በከንቱ እንዲፈስ እያደረጉት ያለው የአማራ ህዝብ፥ ልሒቃኑ የአማራ ህዝብ ቀድመው ወዳዘጋጁት ወጥመድ ዘው ብሎ እንዲገባላቸው (ከጎናቸው እንዲቆም) ያለመ ነው። በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሚዘውሯቸውና በሚደጉሟቸው መገናኛ ብዙሓን እንዲሁም ልዩ ልዩ የሶሻል ሚድያ መድረኮች በመጠቀምም በክስተቱ ዙሪያ ቀድሞ የተዘጋጀ ጥብስ የሆነ ዜና በመስራትና በማሰራጨት፤ የንጹሐን ዜጎች ሞትና እልቂት በሰበር ዜና ከሚገባ በላይ በማራገብ፣ በመቸርቸር፣ በማሰራጨት አማራ ነኝ! ብሎ የሚያምን ሁሉ ይህን ሁሉ ግፍና በደል ሲያይና ሲሰማ ሆ! ብሎ በቁጣ እንዲነሳና እንዲያምጽ፤ የተቀረው ህዝብ ደግሞ ድንጋጤ ውስጥ በመክተት የሚፈልጉትን ለማግኘት (የፌዴራል ስርዓቱን በመናድ አሃዳዊ ስርዓት መትከል) የገዛ ራሳቸው ወገን የሆነው የአማራ ህዝብ ያለ ምንም ርህራሄ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፍ፣ እንደ ከብት እያጋደሙ ማረድና እንደ ቡቃያ አንድ ጉድጓድ ውስጥ መጨመር፣ በሰው ፊት ደግሞ አዛኝ መስለህ ማልቀስና ምሾ ማውረድ የተፈተነና አዋጪ ስትራቴጂ ነው! ብለው ስለሚያምኑ፤

 

2.   ሁለት፥ በአማራ ልሒቃን ስውር እጅ በተለያዩ ቦታዎች እየተፈጸመ ያለው ንጹሐን ዜጎች የመመንጠር ዘመቻ የዓለም ማህበረሰብ ቀልብ እንዲስብ በማድረግ ለዚህ ሁሉ እልቂትና ደም መፋሰስ ቀንደኛ ምክንያት ፈዴራላዊ መንግስታዊ ስርዓቱ የሚለው ሐሰተኛ የውንጀላ ትርክታቸው ድጋፍ እንዲያገኙ በማስተጋባት የፌዴራል ስርዓቱን በመናድ የሚያልሟት አሃዳዊት ኢትዮጵያ ለመመለስ ያለመ ነው። ጥያቄው፥ ለተራው የአማራ ህዝብ ከሌላው ህዝብ በተለየ መልኩ ተጠቃሚ የማያደርግ ዳሩ ግን በአማራ ህዝብ ስም ንግዳቸውን ማጧጧፍ የተካኑ የብሔሩ ልሒቃን ቅዠት ለማሟላት ሲባል ስንት ንጹሐን ዜጎች አለ አግባብ መቀጣት አለባቸው ተብሎ ነው የሚታመነው?

 

ሌላው፥ አቢይ አህመድ ዓሊ ጨምሮ ነፈዘቹ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ ታዬ ደንድአና፣ ወ/ሮ ታከለች፤ የአማራ ልሒቃን የደገሱላቸው ድግስ የሚገባቸው የተቀመጡበት ዙፋን በላይ ላያቸው ከተደፋ በኋላ መሆኑን ስገልጽ በአክብሮት ነው። በተረፈ፥ የንጹሐን ዜጎች ሞትና እልቂት በመንግስት የመገናኛ ብዙሐን ከፍተኛ ሽፋን አግኝቶ በሰበር ዜና ሲዘገብና ሲሰራጭና እያየንና እየሰማን የጉዳዩ ባለቤት የመንግስት ባለስልጣናት ለመሆናቸው የሚጠራጠር ባለአእምሮ ዜጋ ካለ ባይወለድ ይሻለው ነበር።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com


Back to Front Page