Back to Front Page

ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ገቢ የሚያደርግ ኃይል ሌላ ምንም ሳይሆን ወያኔ ትግራይ ነው

ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን

ገቢ የሚያደርግ ኃይል ሌላ ምንም ሳይሆን ወያኔ ትግራይ ነው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 04-30-21

 

መንደርደሪያ፥ እ.አ.አ ከ1991ዓ/ም ማለትም ከሶቬት ህብረት መደርመስና መበታተን ጀምሮ የዓለማችን አሰላልፍ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከተለወጠ በኋላም ቢሆን ርእሰ ኃያላኑ ላለፉት ሣላሳ ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ኢትዮጵያን እንደ መሳሪያ (proxy) በመጠቀም በቀጠናው የሚኖራቸው ጥቅም በማስጠብቅ ረገድ ከሞላ ጎደል ስኬታማ ነበር ቢባልም፥ ርእሰ ኃያላኑ ኢትዮጵያ በአጋርነት ለማሰለፍ የተቻላቸው ያህል ግን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ገብተው እንዳሻቸው የሚፈተፍቱበት፣ ኢትዮጵያ ራስዋን የሚመዘብሩበት አቅም ግን ፈጽሞ አልነበራቸውም። ርእሰ ኃያላኑ ቀጠናው በሚፈልጉት መልክና ቀርጽ ለማስያዝና ለማበጃጀት ያስችላቸው ዘንድ ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊት አገር በመቀበልና በማክበር በአጋርነት ማጨትና ማሰለፍ ማለትና አገሪቱ ራስዋ የርእሰ ኃያላኑ ህቡእ አጀንዳ ሰለባ መሆንና ማድረግን ሁለት ጽንፍ ናቸው።

 

ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊት አገር በመቀበልና በማክበር በአጋርነት ማጨት፣ ማሰለፍና በቀጠናው ለጋራ ጥቅም (የተጠቃሚነት መጠን ቢለያይም) አብሮ መስራት ማለት በሁለቱም አገራት መካከል የሚኖሮው መልካም ግኝኑነት መሰረት ያደረገ ሰጥቶ መቀበልን የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛውና ሌላኛው ግንኙነት ግን፥ የአንዲት አገር ውድቀትንና ኪሳራን ተከትሎ የሚፈጠር ወዶ ገብነትና የተመጽዋጭነት ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ ነው። ይህ ሁለተኛ መደብ ቀለል ባለ አማርኛና በምሳሌ የተመለከትነው እንደሆነ፥ ባልበሰለ ሰው በዐቢይ አህመድ ዓሊ እየበሰለች የምትገኘው፣ ህልውናዋ ግድግዳ ላይ በሚንጠለጠል የወረቀት ካርታ ያለፈ እንደ አገር ህልውና የሌላትና ያበቃላት፣ በሁሉም አገራዊ መስኮች መቀመቅ ውስጥ የገባችው፣ በነጋ በጠባ ቁጥር የዜጎችዋን ሞትና እልቂት በሰበር ዜና ማብሰር የተለመደ የስራ ጸባይ የሆነባት የደም መሬት ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በገሃድ የሚተርክ ነው። ከሊፋ ቢን ዛይድ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ሲመላለስ ካላየሁ የሚል በእንቅልፍ ልቡ የሚመላለስ ሰው ካልሆነ በቀር፣ አንድም፥ ማፈሪያ ማለትም መመኪያ ማለት አይደለምና ኢትዮጵያ ሲባል የጥቁሮች መመኪያ የሚለው የአዝማሪዎች ትርክርት እንደ እናትህ ጡት እርሳው። አድዮስ ኢትዮጵያ!

Videos From Around The World

 

ከምዕራቡ ዓለም እጅ ይልቅ የወያነ ትግራይ እጅ ትከብዳለች

 

በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ስለ ሰብአዊ መብት በጠበቅና መከበር ግድ ይለናል በማለት በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ ስለ ፍትህ፣ ስለ ዲሞክራሲና ስለ ነጻነት ተናግረውና አውርተው የማይጠግቡ የሚታወቁ በኢኮኖሚያዊ ቁጠባቸው የበለጸጉና በወታደራዊ አቅማቸው ፈርጣማ የሆኑ መንግስታትና አገር አዝጋሚ አሰራርና የኤሊ አካሄድ ዓላማ በሚገባ ልንረዳውና ሊገባን ይገባል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የውስጥም የውጭም አገራትና መንግስታት አሰልፎ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የኃያላኑ መንግስታትና አገራት የግብር ይውጣ አሰራር፤ አንድም፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሂቃን በዓለም ማኅበረሰብ ዘንድ ርጉም ከመ ሰይጣን ውጉዝ ከመ አርዮስ! ተብሎ ፈጽሞ የተለየና የተወገዘ የሰው መጨረሻ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የኃያላኑ መንግስታትና አገራት ይህን የመሰለ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም የወንጀሎች ሁሉ አውራ የሆነ ወንጀል በአስቸኳይ መጨረሻ እንዲኖረውና የዐቢይ አህመድ ዓሊና የኢሳይያስ አፈወርቂን አሳዳጊ የበደላቸው እጆች በብረት ሰንሰለት ጠፍረው ፍርድንና ፍትህን ለማድረግ የሚያስችላቸው የመረጃና የማስረጃ እጥረት ስለገጠማቸውና ስላላቸው ሳይሆን አገራቱ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የተዘጋባቸው በር ማለትም በኢትዮጵያ ጥቅማቸውን ለማስከበር አገሪቱ አሁን የምትገኝበት የተመሰቃቀለና የለየለት ቀውስ የተሻለ ሁኔታ/አጋጣሚ ሊፈጠር አይችልምና በትግራይ መሬት ላይ እየተፈጸመ ያለ ወንጀል የዘር ማጽዳት ወንጀል መሆኑን በይፋ የታመነበት የትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ለራሳቸው ጥቅም መጠበቅ መጠቀሚያ እያደረጉትና እየተደራደሩበት ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ግን ሳይማር መጠሪያው ያሳመረና ሳይቀባ የተሾመ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሆነ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ከፍትህ ያመልጣሉ ማለት አይደለም።

 

v  መስዋዕትነት መጎናጸፊያው ያደረገ፣

v  ጽናትና ቁርጠኝነት ምልክቱ የሆነው፣

v  ሲታገል ለመጣል የሚታገል፣

v  በቁጥር ጥቂት ሆኖ ሳለ በፈረሰኛ ብዛት የሚመኩትን በማጥመልመልና በማሽመድመድ የታወቀ፣

v  ክፉ ቀን እንደ መቀነት የሚታጠቅ፣

v  ትጥቁና ስንቁን ከጠላት የሚቀበል፣

v  ለክብሩና ለህልውናው በታንክና በቡዝቃ ሳይሆን በህዝባዊ መስመር የሚታመን ወያነ ትግራይ ቼክ-ሜት! (Checkmate) በማለት ያለ ግብዣ በራሱ ጊዜ ተጠራርቶ የትግራይ መሬት የገባ ወራሪ ኃይል ሁሉ የትግራይ መሬት መቀበሪያቸው ሲያደርገው ሰውዬው (ዐቢይ አህመድ ዓሊን) የወደቀና የተጣለ ሆኖ ሳለ ደጋግፈው ያቆሙትን፣ በትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት የራሳቸው ጥቅም ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው! በማለት እየተረባረቡ የሚገኙ ርዕሰ ኃያላኑ ወደው ሳይሆን ተገደው ገቢ ያደርጉታል። የወያነ ትግራይ እጅ በጠላቶቹ ላይ ስትከብድ፣ የትግራይ ህዝብ በልጆቹ የህይወት መስዋዕነት በድል ማማ ላይ ሲቀመጥ እንደ ኤሊ እየተራመዱ ያሉትን ኃያላን አገራትና መንግስታት ሁሉ እንደ ጥንቸል ይፈጥናሉ።

ከዚህ ቀደም ቅድሳት መጻህፍትን በማጣቀስ በተደጋጋሚ እንዳሳሰብኩት የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከእንግዲህ ወዲህ ኢሳይያስ አፈወርቂን ውጣልኝ ብሎ ሊያስጣው ቀርቶ ነገሩን በሃሳብ ደረጃ ለማንሳት የሚያስችለው ሞራልም ሆነ ሐሙቱ የለውም። መጽሐፍ ሲናገር እውነት ነው፣ መጽሐፍ ሲመሰክር ትክክል ነው፣ መጽሐፍ ሲያስተምር ግልጽ ነው! እስራኤልን ለመውረርና ለማጥቃት የሶሪያን ንጉሥ ወልደ አዴር ስፍር ቁጥር በሌለው ወርቅና ብር ገዝቶ ባኦስ የወረረና የመታ ስለ የይሁዳ ንጉሥ ስለ አሳ የሶሪያ ንጉሥ ጭፍራ ከእጅህ አምልጦአል እንዲል ዐቢይ አህመድ ዓሊ በሰሜን በኩል ትግራይን ይወርና ያወድም የትግራይንም ህዝብ ይገድልና ይጨፈጭፍ ዘንድ መክሮና ገዝቶ ያስገባው፤ ከገባ ጀምሮ እስከ ዛሬው ዕለትም የትግራይ ህዝብ እየጨፈጨፈና ሀብትና ንብረቱን እየዘረፈና እያወደመ ያለ የሰው ፍጥረት የሌለው የኤርትራ ሠራዊት በተመለከተ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የእምዬም ሆነ የአዬ ታቦት ተሸክሞም ቢሆን ውጣልኝ! ብሎ የሚያወጣው ኃይል አይደለም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ገዝቶ ያስገባው የሰው ፍጥረት የሌለው ሌባና ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ የኤርትራ ሠራዊት በአንድም በሌላም መንገድ ውጣልኝ ብሎ ሊያስወጣው አይችልም። በትግራይ ከተሞች የመሸገው የኤርትራ ሠራዊት አለቦታው ከተቀመጠ ከዐቢይ አህመድ ዓሊ አቅምና ቁጥጥር ውጭ ነው። ታድያ፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ የትግራይን ህዝብ እንዲገድል ሀብትና ንብረቱን እንዲያወድምና እንዲዘርፍ ያሰማራው ሠራዊቱ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች ቀለብ ሲሆን ወዶ ሳይሆን ተገዶ ይወጣል። እንደጀመሩት እንጨርሰዋለን!

 

በተረፈ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ በቅሌት፣ በውርደትና በኪሳራ የሚጠናቀቀው ቆይታው ወደ ፍጻሜ ከመምጣቱ በፊት ያልጎበኘው መናፈሻና ፓርክ ያለ እንደሆነ እነሱን በመጎብኘትና በማስጎብኘት አሳፋሪ ፍጻሜው ከመጠባበቅና በአሁን ሰዓት በትግራይ ህዝብ እየፈጸመው ያለ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል እስኪማር ድረስ ከመቀጠል ውጭ ሌላ እዚህ ግባ የሚባል የረባ ድርሻ የለውም። ከተራ የሦስተኛ ዓለም ወታደር ቤት ወጥቶ በመተት ይሁን በምትሃት ቤተ መንግሥት ውስጥ የተገኘው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሲመዘን ቀሎ በመገኘቱ ሳይገባው መኖሪያው ይሆን ዘንድ የተፈቀደለት የቤተ መንግሥት ቆይታው አብቅቷል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com


Back to Front Page