Back to Front Page

የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው የሚለው የአማራ ጩኸት ሲያምረው ይቀራል እንጅ አማራ ደምነትን ተክሏል

የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው የሚለው የአማራ ጩኸት

ሲያምረው ይቀራል እንጅ አማራ ደምነትን ተክሏል

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 04-26-21

 

እናቴ የኢትዮጵያ 7ኛ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኛለች የሚለው፣ በሐሰተኛና የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ መጠሪያ ስሙ ያሳመረ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሚመራው የኦሮሞ ልሒቃን ኦሮሚያዊት ኢትዮጵያ ለመፍጠር፥ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፣ ስንኖር ኢትዮጵያውያን ስንሞት ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ወዘተ እያሉ ሐሰተኛ መፈክር በማሰማትና በማስተጋባት ኢትዮጵያዊነት አማራነት ነው ብለው የሚያምኑ ትምክህተኞች የአማራ ልሒቃን በማማለል፥ ኢምሬት፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሱማሌ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሶማል አሰልፈው በትግራይ ህዝብ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ፤ አይደለም የሀገር ሉዓላዊት ሌላ የሚሸጥና የሚለወጥ ነገር ካለም ያለንን ሁሉ ሸጠንና ለውጠን ትግራዋይ የሚባል ህዝብና ትግራይ የምትባል አገር ማጥፋትና ማብረስ ከተቻለን ቀሪውን እናውቅበታለን! ብለው የሚያምኑ የአማራ ልሒቃን ደግሞ በፊናቸው ምንሊካዊት ኢትዮጵያ ለመፍጠር ቀደም ሲል የተዘረዘሩ የውጭና የውስጥ ኃይሎች ትክሻ ላይ ተፈናጥጠው በመምጣት በምዕራብና በደቡብ ትግራይ ወረራን መፈጸማቸው፣ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ትግራይዋይ ደም ያለው ሁሉ በአሰቃቂ ሁኔታ በሰይፍና በጥይት መጨፍጨፋቸውንና መግደላቸውን፣ የትግራይ ህዝብ ሀብትና ንብረት መዝረፋቸውንና ማውደማቸውን፣ የትግራይ ከተሞች ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን በእሳት ማጋየታቸውን ይታወቃል።

 

በሌላ አገላለጽ፥ የኦሮሞ ልሒቃን የተገኘውንና ማሰለፍ የቻልነውን የውስጥም የውጭ ኃይል ሁሉ ይዘን የትግራይ ህዝብ ማዳከም ከቻልንና ከተሳካልን አማራ የማያጠግብ ቁርስ ነው! ሲሉ፤ የአማራ ልሒቃን በፊናቸው፥ በተባበሩት ክንዶች ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ከደመሰስነው ኦሮሞ የእኛ ችግር አይሆንም! ሲሉ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈቱት ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከሥድስት ወራት በኋላም ቢሆን ሁሉም ወራሪ ኃይሎች እንዳሰቡትና ተስፋ እንዳደረጉት ሊሳካላቸው ቀርቶ በር ዘግተው የመከሩትን ምክር በአደባባይ በላያቸው ላይ ተደፍቶባቸው ወያነ ትግራይ እንደ እሳት እያገለባበጠ እየጠበሳቸው፣ እያነደዳቸውና እየፈጃቸው ይገኛል። ሁለቱም ወራሪ ኃይሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር የኤርትራና የሱማሌ ሠራዊት በሰሜን በኩል ትግራይን እንዲወር፣ በሰውና በንብረት ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ውድመት እንዲፈጽመውና እንዲያደርሱም ከፍተኛ ክፍያ ፈጽመው ካስገቧቸው በኋላ የትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት ምንሊካዊት ኢትዮጵያ ይወልዳል! ብሎ ሲቋምጥ የነበረ የአማራ ልሒቅ ተስፋው ሲጨላልምበት የራሱን ህዝብ እየገደለና እያስገደለ የአማራ ህዝብ ክዶናል አታሎናል በሚሉት በዐቢይ አህመድ ዓሊ ላይ እንደ እንቁራሪት ቢያንጫጩትም ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ የመጣንበት መንገድ ነው፣ አይደንቀኝም፣ አቧራ ነው! የሚል ምላሽ ሸልሟቸዋል።

 

Videos From Around The World

የሚደንቀው፥ ስድስት ወር የያዘው በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተው ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዋዜማ ላይ ጀምሮ በለው ግደለው! እያለ ዘራፍ ሲል፣ ሲሸልልና ቀረርቶ ሲያሰማ የነበረ ህዝብ ዛሬ ተገልብጦ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሰሜን ፖለቲካ ጠላት ነው፣ በትግራይ የተከፈተው ጦርነት ጸረ የትግራይ ህዝብ ነው፣ የኦሮሞ ልሒቃን ትግራይንና አማራን የማጥፋት ዕቅድ ነው ያላቸው፣ የትግራይና የአማራ ህዝብ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው! እያሉ ማለቃቀስና መጮህ መጀመራቸውን ነው። እዚህ ላይ ወዳጅም ጠላትም ግልጽ በሆነ አማርኛ ሊያውቀው የሚገባ ሐቅ ቢኖር፥ ወንድም ማለት ነፍሰ ገዳይ፣ ወራሪ፣ ሌባ፣ ዘራፊ፣ ከሃዲ፣ ነውራም፣ ህሊና ቢስ ማለት ካልሆነ በቀር የአማራ ልሒቃን የትግራይ ህዝብ ወንድም፥ አንድም ወዳጅ ሊሆኑ አይችሉም። ምቀኛና ምዋርተኛ ባህሪያቸው የሰው ሆነ የአገር እውነተኛ ወዳጆችና አፍቃሪዎች ይሆኑ ዘንድ አይፈቅድላቸውም።

v  የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው ብሎ መጮህና ደጅ መጽናት ዛፍ ያጣ ኩሬዛ ከሆንክ በኋላ አይደለም።

 

v  ትግራዋይ ወንድሜ ነው ማለት የትግራዋይ ስመ ዝክር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ዕድልህ ከሞከርክ፣ ከከሸፈብህና ከተበላህ በኋላ አይደለም።

 

v  የትግራይና የአማራ ህዝቦች ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ማለት ከውስጥም ከውጭም የሰውና የጦር መሳሪያ ዓይነት ሁሉ አሰባስበህና አሰልፈህ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ካጠፋህ በኋላ ልትፈጥራት ያሰብካትን አገር የውኃ ሽታ ከሆነችብህ በኋላ አይደለም።

 

v  ትግራይና አማራ አንድነት ሊፈጥሩ ይገባል በማለት ማላዘንና ደጅ መጽናት በገዛ እጅህ ባነደድከው እሳት መውጫ መግቢያ አጥተህ ተቅበዥባዥ ለመሆን በተገደድክበት ሰዓትና ዕለት አይደለም።

 

v  ይደርስልህና ያድንህ ዘንድ፥ ኧረ የትግራዋይ ያለህ! ብሎ ጩኸት የራስህ ያልሆነና ላንተ ያልተገባ ለመስረቅ ተስማምተህ ስታበቃ ስትካፈል ከተጣላህ በኋላ አይደለም።

 

ሐቁ፥ የሰው አእምሮ የሚያልፍ፣ ኹነትን እንዳለፈ ወንዝ የሚያሳልፍና የሚያስረሳ፣ ፈጽሞ የሚፈውስ ሰማያዊ ተአምር ከሰማይ ካልወረደ በቀር አማራ የትግራይ ህዝብ በታሪኩ የማይረሳው ደምነትን ተክሏል። አማራ ገዳያችን ነው። ከጠላት መንግስትና አገር ሠራዊት ግንባር ፈጥሮ ሀብት ንብረታችን የዘረፈ፣ ከተሞቻችን ያወደመ፣ የሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን ከብረ ንጽህና የደፈረና ያጎደፈ፣ ህጻናቶቻችንና ሽማግሌዎቻችን የገደለ፣ ካህናቶቻችን ያረደ፣ አብያተ ክርስቲያኖቻችንና ቅድሳት መጻህፍቶቻችንን ያቃጠለ፥ ምቀኞቹና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ያሰማሩት ዘራፊ፣ ሌባ፣ ህሊና ቢስና ኃይማኖት የለሽ የአማራ ሠራዊት ነው።

 

የትግራይ ህዝብ ለሣላሳ ዓመታት ጥሮ ግሮ በላቡ ያፈራውን ሀብትና ንብረት፣ ያቆማቸውና የገነባቸው ከተሞቹን እንዳልነበረ መውደሙንና መፈራረሳቸውን እንርሳው ቢባል እንኳ ከጥይት የተረፈውን በረሃብ፣ ከርሃብ ያመለጠውን በመድሃኒት እጦት በአሰቃቂ ሁኔታ የሞት ሲሳይ እንዲሆን የተፈረደበት ትግራዋይ ሞትና እልቂት አይቶና ሰምቶ የሰላም እንቅልፍ ተኝቶ የሚያድር፣ የወገኑን ሞት የሚረሳ ትግራዋይ የለም፤ አይኖሮምም። ከእንግዲህ ወዲህ በግምት የሚወለድና እንዲሁ በዘልማድ የሚያድግ ትግራዋይ አይኖርም። ይልቁንም፥ የተወለደ ትግራዋይ ሁሉ ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ የወገኖችን ሞትና ደም የሚፋረድና የሚመልስ ይሆናል እንጅ። በቅድሳት መጻህፍት በመጽሐፈ ነገሥት ላይ እንደ ተጻፈ፥ የእስራኤል ልጆች አዶኒቤዜቅን አሳድደው ይዘው የእጁንና የእግሩንም አውራ ጣት ከቈረጡ በኋላ የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣት የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበር፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ ሲል እንደተናገረ እንደ ባልቴት ሐሰተኛ ወሬ በመፈብረክ፣ ሐሜትንና አሉባልታን በማሰራጨት የማይታሙ የምላስ አርበኞች ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን እንዲሁ ምስክርነታቸው ሳይሰጡ ከትግራይ ህዝብ ጋር አንድ መዓድ የሚቀመጡበትና የሚካፈሉበት በህልማቸው ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።

 

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

 


Back to Front Page