ከጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች እንደተፈናቀሉ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው

NEWS

ከጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች እንደተፈናቀሉ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነውአዲስ አበባ, ሚያዝያ 1 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) -ከደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተደርጎ በቅርቡ የተናፈሰው ወሬ መሰረተ-ቢስ መሆኑን የክልሉ ርእስ መስተዳድር አስታወቁ።

ርዕስ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለመገናኛ ብዘሃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በቤንች ማጂ ዞን በሚገኙ አስር ወረዳዎች ውስጥ ከ30 ዓመታት በላይ የኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አሁንም ሰላማዊ ኑሯቸውን እየመሩ ነው።

በዞኑ በ2000 ዓ.ም በተካሄደ ጥናት በጉራፌርዳ ወረዳ 22 ሺህ 46፣ በሜኒ ሻሻ 1ሺህ 484 በሜኒት ጎልደያ ደግሞ 1ሺህ 520 የአማራ ክልል ተወላጆች እንዳሉ ተረጋግጧል ብለዋል።

እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ እነዚህ የአማራ ክልል ተወላጆች በወረዳዎቹ አሁንም ህይወታቸውን በሰላማዊ መንገድ እየመሩ ናቸው።

የክልሉ መንግሥት በ2001ዓ.ም አንድ ሰፋሪ ሁለት ሄክታር የእርሻ መሬትና 1ሺህ ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኝ መመሪያ ማውጣቱን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በወቅቱ በተካሄደው የመሬት ልኬት በጉራፌርዳ ወረዳ ከ2-12 ሄክታር፣ በሜኒትጎልደያ ከ3-60 ሄክታር መሬት ይዞታ የነበራቸው ሰዎች እንደነበሩ አስረድተዋል።

በጉራ ፌርዳ፣ በሜኒ ሻሻና በሜኒት ጎልደያ ወረዳዎች የሚገኙ ሰፋሪዎችም በዚሁ መመሪያ መሰረት እንዲስናገዱ እንደተደረገም አብራርተዋል።

የክልሉ መንግሥት በ2001ዓ.ም ባወጣው መመሪያ ከነሐሴ 30 ቀን 1999 ድረስ ወደ ዞኑ የገቡ ሰዎች ባሉበት ኑሯቸውን እንዲመሩ ሲደረግ ከነሐሴ 30 ቀን 1999 በኋላ ወደ ዞኑ የገቡት ደግሞ ወደቀያቸው እንዲመለሱ መወሰኑን አስታውሰዋል።

በዚሁ መሰረት በጉራፌርዳ ከሚኖሩት 22 ሺህ 46 የአማራ ክልል ተወላጆች መካከል መመሪያው ከወጣ በኋላ የገቡ 800 ሰዎች በወቅቱ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉንም አቶ ሽፈራው አስታውቀዋል።

ርዕስ መስተዳድሩ እንዳሉት የክልሉ መንግሥት እነዚህን ሰዎች በራሱ ትራንስፖርት ባህርዳር ከተማ ድረስ ወስዶ ለአማራ ክልል መንግሥት ማስረከቡን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል መንግሥትም እነዚህን ሰዎች በምእራብ አማራ እንዳሰፈራቸውና አስፈላጊውን ድጋፊ ሲያደርግላቸው እንደነበረ በቂ መረጃ እንዳላቸው ርዕስ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

እንደ ርዕስ መስተዳድሩ መግለጫ በወቅቱ እነዚህን ሰዎች ወደቀዬአቸው ለመለለስ ጥረት ሲደረግ የሁለቱ ክልል መንግሥትታት መወያየታቸውና የፌዴራል መንግሥትም ጉዳዮ መስመር እንዲይዝ ተሳትፎ አድርጓል።

በአንጻሩ ቀደም ሲል በወረዳው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ያመጧቸው 35 ሰዎች በአካባቢው ያለውን ጥብቅ የተፈጥሮ ደን በመመንጠር ጉዳት በማድረሳቸው የወረዳው አስተዳደር በህግ ለመጠየቅ እንቅስቃሴ ባደረገበት ወቅት ተባረናል ብለው አዲስ አበባ መሄዳቸውን ጠቁመዋል።

የእነዚህ ሰዎች ጉዳይ በሚጣራበት ጊዜም ከሁለቱ ሰዎች በስተቀር 33ቱ ህጋዊ ባለመሆናቸው ከነቤተሰቦቻቸው ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መደረጉን አስታውቀዋል።

በመሆኑም ከቤንች ማጂ ዞን ጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ እንደሆነና ከወረዳው የተፈናቀለ ሰው እንደሌለ አቶ ሽፈራው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


Videos From Around The World

 


 We started Aigaforum some 20 years ago right around the end of the Shaibya-Ethiopia war. One of the earlier songs we have on our page for a long time was "ክነዛርቦምኢና". As if our talented brother was reading our brain he has updated his old song. What a coincidence! We are entering a new chapter to defeat Derge 2.0. Enjoy ክነዛርቦምኢና 2.0. Thank You, Berhane Haile.
ሸጥ መዓንጣ!!

  


Mark Your Calendar

Follow US on Facebook
Custom Search