አገሪቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ ንግድና ከሐዋላ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

NEWS

አገሪቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ ንግድና ከሐዋላ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች 

አገሪቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ ንግድና ከሐዋላ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች አዲስ አበባ መስከረም 23/2005

የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ባለፈው የበጀት ዓመት ከውጭ ንግድና ከሐዋላ ከሚገኝ ገቢ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ገለፀ። የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ገብሬ ኤርቃሎ ዛሬ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ አገሪቱ ከውጭ ንግድ በሦስቱ የመንግሥት ባንኮች ከሰባት ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል። የውጭ ምንዛሪ ግኝቱ በኢትዮጵያ ንግድ ፣ በኢትዮጵያ ልማትና በኮንስትራክሽን ቢዝነስ ባንኮች መገኘቱን አስታውቀዋል።

ገቢው በዋነኛነት የተገኘው ከእርሻ ፕሮጀክቶች የውጭ ንግድ፣ የማዕድን ሃብት የውጭ ንግድና የሐዋላ አገልግሎት መሆኑን አቶ ገብሬ አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ በዕቅዱ ከተያዘው 6ነጥብ24 ቢሊዮን ዶላር በመብለጥ የ112ነጥብ59 በመቶ ድርሻ መያዙንም ገልጸዋል። በኤጀንሲው የሚተዳደሩት የአራቱ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች የትርፍ አቋም ከታክስ በፊት 8ነጥብ62 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸው፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር 78ነጥብ10 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ኃላፊው ተናግረዋል። ለትርፉ ዕድገት ከተመዘገቡት ምክንያቶች በዋነኝነት ከዋስትና፣ ከሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ከገንዘብ ማስተላላፍ፣ የኮሚሽን መጨመርና ከአገልገሎት ክፍያዎች እንዲሁም ከምንዛሪ መዋዠቅና ከቋሚ ዕቃዎች ሽያጭ ከመሳሰሉት የተገኙት ገቢዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ድርጅቶቹ መሠረታዊ የአሠራር ሂደት ለውጥ በመተግበር ላይ እንደሚገኙም ኃላፊው መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Opinions and Views published on this site are those of the authors only! Aigaforum does not necessarily endorse them. � 2002-2019 Aigaforum.com All rights reserved.