Update on Dr Eyassu Health Situation
Dr
Eyassu deeply appreciates all the people who helped during his critical health
problem. Specially he thanks all the people from the Ethiopian pal talk like Ethio
Tigray Selam Deki Addey and Viva Tigray members who contribute
around 69,500.00 /Sixty nine thousands and five hundred birr. He has a great
appreciation for Journalist Tamerat Yeman (producer of Betegna/memunay
radio program) who is
supporting him every day while he is being treated in Addis Ababa.
He also said thanks Dr. Eisubalw, Dr. Solomon and St. Michael clinic society
generally.
Dr. Eyassu is in a very good health condition with normal sugar level. He is free from Anti-Petident drug dependency and all infections. He is ready to start bone treatment outside Ethiopia which he badly needs. This kind of medication needs around $20,000 dollars which he couldn’t afford. Let us help this scholar and the reward will go to young Ethiopian students who are in need of Dr. Eyassu’s knowledge.
For more information inside country tel. +251913852143 Outside Country +004917619422106 or +251911237409
ዶክተር እያሱ ያዘው በሞት አፋፍ ላይ ደርሶ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አድኑኝ የሚል ጥሪውን ሰምተው ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው ምስጋናውን ይገልፃል ፡፡ በተለያዩ በኢንተርኔት የፅሁፍና የድምፅ መገናኛ ቤቶች / paltalk groups / በተለይ Ethio Tigray Selam Deki Addey & Viva Tigray / የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ለዶክተር እያሱ ያዘው ለህክምናው 69000 ስድሳ ዘጠኝ ሺህ ብር ባደርጋችሁት እገዛ ልትኮሩ ይገባል ፡፡
ዶክተር እያሱ በአሁኑ ወቅት የነበሩት ኢንፌክሽኖች ድነውለት የስኳር መጠኑ ተስተካክሎ በጥሩ ጤንነት ላይ ስለሚገኝ በዚህ ድጋፍ ለተሳተፋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡ የድካማችሁ ውጤት ፍሬ አስገኝታል ፡፡ዶክተር እያሱም ለሁሉም የፓልቶክ አባላት ምስጋናውን ይገልፃል ፡፡ በአገር ቤት በአዲስ አበባ ለዶክተር እያሱ ከፍተኛ ውጣ ውረድ የተሞላበት የህክምና ክትትል እንዲያደርግ በማስታመም ፡በመንከባከብ ለዚህ ላደረሰው የቤተኛ ፕሮግራም (በትግርኛ ቋንቋ የመእሙነይ አዘጋጅ ) የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት የማነ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ፡፡
እንዲሁም የአዲሱ ሚካኤል ከፍተኛ ክሊኒክ የጤና ባለሙያዎች ለዶ/ር ሰለሞንና ለዶ/ር እሱባለው እንዲሁም የክሊኒኩ ማህበረሰብ በሙሉ የእናንተ ልፋትና ውጤትም የላቀ ስለነበር ምስጋናው ይድረሳችሁ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዶ/ር እያሱ ከስቃይ ማስታገሻ ቁርኝት /Anti Petident Dependency/ ተላቆ የአጥንት ህክምናው በደህና ሁኔታ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል ፡፡ ወደ ውጭ ሃገር ሄዶ ለመታከም እስከ ሃያ ሺ /20,000 / ዶላር ያስፈልገዋል ተብሎ በሃኪሙ ተወስኑዋል ፡፡ ስለዚህ ውድ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር እያሱን ማዳን የቡዙ ተማሪዎች የትምህርት ሂወት ማለምለም ስለሆነ ከዚህ በታች ባለው የሂሳብ ቁጥር የተቻላችሁን አግዙን ፡፡
ለበለጠ መረጃ የአገር ቤት 00251913852143 ለውጭ አገር 004917619422106 00251911237409
አስተባባሪ (King of Raya) Solomon Assefa