የኤርትራ መንግስት የሰሙኑ ዝምታ: ስልታዊ ማፈግፈግ ወይስ ድክመቱን መደበቅ?

Articles

የኤርትራ መንግስት የሰሙኑ ዝምታ: ስልታዊ ማፈግፈግ ወይስ ድክመቱን መደበቅ?መረሳ ፀሃየ ፤ መቀለ ዩኒቨርሲቲ-3/25/2012- ባለፈው ለካቲቲ ወር የኤርትራ ዜና ሚኒሰቴር ባቀረቦዉ ሀተታዊ መግለጫ “እስከ ዛሬ በተለምዶ የኢትዮጵያ ቀኝ ኣገዛዝ ስባል የነበረ የተሳሳተ በመሆኑ መታረም ኣለበት” ይላል። እንደሚክንያት የተቀመጠ ደግሞ “ኢትዮጵያዊያን ቀኝ ገዝዎች ልሆኑ ቀርቶ ኣስቸጋሪ ተገዝዎችም መሆን ኣልቻሉም” በማለት የሃፀይ ሀይልስላሴ ወደ ለንደን፤ መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ዝምባባዌ መሸሽ እንደምክንያት ያቀርባል። በመሆኑም “የኤርትራ የ40 ዓመታት ቀኝ ኣገዛዝ የኣመሪካ የእጃዙር ኣገዛዝ ነበረ።የኢትዮጵያዉያን ገዝዎች ግን ኤርትራን የመግዛት ብቃት ኣልነበራቸዉም”…፤ “ወያነም እድሁ ተላላኪነዉ”በማለት ያጠቃልላል። እዚህ ላይ የኤርትራ መርዎች ራስቸዉ ለኣመታት ህዝባችዉ ኣንቀሳቅሶዉ ስታገሉ የነበሩለት ታርክ በዜና መልክ ስሹሩት በኣንድ በኩል የኤርትራ ቢሄርተኝነት መሰረቱ(Ethiopian colonialism) በመናድ ለህዝባቸዉ ስያታግሉበት የነበረ ምክንያት በታርካዊ ትነታኔ ሳይሆን በዜና ማልክ ስነግሩት ህዝባቸዉ ምንያክል እንደሚኑቁ የሚያመላክት ስሆን፤በሌላ በኩል ግን ኣሁን ለገጠማቸዉና የስረኣቱ ዉጤት የሆነ የኤርትራ ኣገራዊ ድህንነት ችግር ከተሰፋመቁረጥ የመነጨ የንቀት ፕሮፓጋነዳ በመስበክ ህዝቡ ኣመርካን ዳግም ለማሸነፍ በምል ፈሊጥ ፀረ ኢትዮጵያ ለማነሳሳት እንደሆነ ለመገመት ኣያሰቸግርም።

 


ላይ የተገለፀዉ ኣባባል ኢምክኒያታዊ መሆኑን የሚያሳዮው ደግሞ የሰሙኑን የኤርትራ ዉጭጉዳይ ሚኒስተር “ግብረመልስ ኣንሰጥም፣ ብንወረርም ጥይት ኣንተኩስም” የሚል መግለጫነዉ።የሚገርሞዉ ደግሞ ከዚ በፊት የኤርትራ ህዝብ ባለ በሌለ ምክንያት መሬትህን በ ወያነ ተወረዋል ስሉት ዮነሩት ኣሁን ግን ኢትዮጵያ ኦፊሻለዊ በሆነ መልኩ በኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ የኣሽባርዎች ማሰልጠኛ ካምፖች ጥቃት መፈፀምዋ ስታሳዉቅ የኤርትራ መንግስት ከኣጭር የዉጭጉዳይሚኒስተር መግለጫ በስተቀር ለመድበቅ መመኮሩ ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ እነደሚክኒያት ስሆነኝ፤ ሊነሱ የሚገባቸዉ ጥያቄዎች ድግሞ የሻዕቢያ የተለመድ ስለታዊ ማፈግናግ(በሻዕብያ ኣነጋገር “ምዝላቅ”)? ጥቃት ኣልተፈፀመቢኝም ብሎ ሽንፈትን ለመደበቅ? የኢትዮጵያ መንግስት ጥቃት የመፈፀም ኣቅም የለዉም ለማለት? ሻዕቢያ ህዝብን ለማንቀሳቀሰ ኣለመቻሉና ግብረመልስ ለመስጠት ኣለመድፈሩ? ኢትዮጵያ በኤርትራ የሚሰለጡኑናየሚደገፉ ኣሸባርዎች ማጥቃትዋ እዉቅና ላለመስጠት ወይም የተመቱት ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች ናችዉ በመሆኑም የኤርትራን ቢሄራዊ ድህንነት መነካት ኣያመላክትም ለማለት? የምሽግ ቁፎራ ዝግጅት ያልተጠናቀቀ በመሆኑ? ወይም በተደጋጋሚ እንደሚሉት ኢትዮጵያዊያን የሚያከሂዱት ራስን የመከላከል ጥቃት የኣመሪካ ተልእኮ ጦርኖት በመሆኑ ኢትዮጵያን ኣጥቅቶ ኣመሪካን ከማበስጨትኣመሪካን በኮርደር ዲፕሎማሲ ለመለመን በመወሰናችው የተደረገ ዝምታ? ወዘተ ጥያቄዎች ልነሱ ይችላሉ።ዋናዉ ነገር ግን የሻዕብያ ያልተለመደ ዝመታ እንዴት ኣሁን ያለዉ ደረጃ ልደርስ ቻለ?

የታርክ ድርሳነት እነደሚያመለክቱት የኣሁኑ ኤርትራ የሚባል ኣጠራር ወደ ፖለቲካ ድርሳናት የገባ ከ ኣፀይ ዮሃንስ ሞት በኅላ በ1890(እ.ኢ.ኣ) በጣልያን የተሰጠ ስም ነዉ።ይህን ስም ያገኘቹ ደግሞ “ባህረ ነጋሽ/ምድር” ወይም “መረብ ሰገር” የሚባል ኣገረ በቀል ስም በመተካት ስሆን፤ቀጥሎም የኤርትራ ነፃ ኣዉጭ ግንባሮች የኤርትራን ህዝብ ትግል መሰረት ኣድርጎ የወሰዱት “ፀረ ቀኝኣገዛዝ(colonial thesis)ትግል” እንደታርካዊ መሰረት በመጠቀም ኣሁን ያለቹ “ሃገረ ኤርትራ” መፍጠር ችሎዋል። በኤርትራ የትግል ታርክ ሁለት ተቀናቃኝ ግንባሮች ተፈጥሮ የነበሩ ስሁኑ፤ የመጅመረያ “ፀረ ቀኝኣገዛዝ (colonial thesis)ትግል” በ ጀብሃ የተጀመረ ብሆንም እስላማዊ ቢሄርተኝነት (Sectarian nationalism)መሰረት ያደረገ ትግልና “Islamic state of Eritrea” ለመፍጠር ኣልሞ የነበረ ሲሆን፤ ቡዙ ልጋዝ ባለመቻሉና በዋናነት ድግሞ ክርስቲያን ኣማኒ ኤርትራዊያን በ ድምክርሲያዊ መንገድ ባለ ማካተቱ በኤርትራዊያን መካካል ለ እርስባእስ ጦሩነቶች እንዳሰከተለና ጀብሃም ከ ኤርትራ የትጥቅ ትግል ሜዳ ዉጭ ኣንደሆነ የግንባሮቹ የታርክ መፃህፍት ይናገራሉ።

ከጀብሃ ተገንጥሎ የወጣ ሻዕብያ ግን የጣልያን ግዛት መሰረት ያደረገ ብሄርተኝነት(territorial nationalism) በመከተል ለነፃነት ቢደርስም፤ የነፃነት ቱግሉ ግን ደሞክረሲያዊ ሁሉምኣቀፍነት የጎደሎዉ፤ኤርትራ ከኣንድ ፖለቲካዊ ድርጅት በላይ መሽከም ኣትችልም በምል ሁሉም ድርጅቶች በኣዋጅ የከለከለ፤ ኣገር ግንባታዉም ከዚህ በፊት ሻዕብያ ራሱ ፀረኢትዮጵያ ስዋጋለት የነበረ ቡዝህነት የማቅልጥ(melting-diversity)ደግሞ በኤርትራ ህዝብ በመጫኑ፤ወዘተ እንደምክነያት የሚቀርቡ ብሆኑም “የኤርትራ ብሄርተኝነት ታርካዊ ኣፈጣጠር” ግን በዋናነት ለኣሁኑ የኣገራዊ ድህንነት ችግር እንደመሰረታዊ ምክንያት መዉሰደ ይቻላል።የታርክ ፅህፎች እንደሚያመላክቱት የኤርትራ ቢሄርተኝነትበጣልያን ቀኝኣገዛዝ ግዜ መሰረታዊ ቅርፁን ኣንዳልያዘ ነዉ። ቀጥሎ የመጣ የኢንግሊዝ “ሞጉዚት ኣስተዳድር” በፈቀደዉ የነፃ ፕሬስ የመጠቀም፤ፖሊቲካ ኣደራጃጅት መፈቀድ ምክንያት የተፈጠሩ የፖሊቲካ ድረጅቶች ማህበረ-ሃይማኖታዊ ና ጅኦግራፊያዊ(ቆላነናደጋ፤ሞስሊምና ክርስቲያን) ቅርፅ በመያዛችው የጣልያን ቀኝኣገዛዝ መሰረት ያደረገ ኣንድ ወጥ የሆነ ኤርትራዉንት መፍጠር ባለመቻላችወዉ ለዉጭ ጣልቃ ገብነት ስዳረጉ፤ኣንደዉጤቱም በሁሉም ኣካለት ያልተፈለገ “ፈደረሽን” (በ ተ.መ.ድ. የተረቀቀ ኤርትራዊ ያልሆኔ መፈቲሄ)በላያቸዉ እንደተጫናቸዉና ለተራዘመ “ኤርትራዉነት በትጥቅ ትግል” የመፈለግ ጉዞ መዳረጋቸዉ ነዉ። በነገራች ኤርትራ በዘመናዊ የኣፍርካ ታርክ ለመጀመርያ ግዜ ደሞክራሲያዊ የተፃፈ ህገመንግስት በፈደረሽን የተቀበለች ብቸኛ ኣገር ነበረች። ህገመንግስቱም የኤርትራ ህዝብ ማህበራዊ፤ጆኦፖሊቲካዊ ናሃይማኖታዊ እንዲሁም የቃንቃ እኩልነቶች የተቀበለ ነበረ። በኣሁን ግዜ ግን ከሶማሊያ ቀጥላ ህገመንግስት የሌላት ኣገር ናት።

ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ በመጀመርያ ደረጃ ኤርትራዊያን ሁሉም ኣቀፍ ኤርትራዊ መፍቲሄ ባለማቅረባችው ተከትሎ የመጡ ለኢትዮጵያ መንግስታት ና ለተለያዩ የኤርትራ ድርጅቶች የሚደግፉ የዉጭ ጣልቃ ገብነቶች ኣሁን ላለው የኤርትራ መንግስት “ዉጭንኣለም መጥላት መሰረት ያደረገ ራስንመቻል(“self-reliance”)ፖሊሲ” እንደ ታርካዊ ምክንያት ይወሰዳል። ይህንን ደግሞ ኤርትራዉነት በዋናነት በራሳቸው ኤርትራዉያን ከዉስጥ የሚገለፅ ሳይሆን በዉጭ ሃይላት(external relevant othering) አንደ ኢትዮጵያ፤ሱዳን፤ኣመርካ ና ሌሎች ሃያላን ኣገሮች በመጥቀስ የኤረትራ ህዝብ የዉስጡንለኣገራዊ ኣንድነትና ድህንነት ምሰሶ የሆኑ የኣገረ ግንባታ መርሆችእንዳያተኩር ከማድረጋቸው በላይ ትንሽዋ ሃገረ ኤርትራ ለሃያላን ኣገሮች ኣሸነፈች በማለት ኤርትራ ካለት ነባራዊ ኣቅም በለይ በመለጠጥ ንቀትናግጭት(arrogant and conflictual) መሰረት ያደረገ የዉጭ ግንኝነት እንድትከትል ዳርጋታል። በተጨማሪ ሻዕቢያ ኣንደሚሎዉ የኤርትራ ብሄርተኝነት በትጥቅ ትግል የተፈጠረ ከሆነ ደግሞ ኣድስ ጦርነት መሰረት ያደረገ ብሄርተኝነት(war based nationalism) ከመሆኑ የተነሳ ወደ ስላማዊ ኣገር ግንባታ(Peace time nation-building) ለማሸጋገር የሚከብድ ቢሆንም የትጥቅ ትግል መርሆች በሰላማዊ የኣገረ ግንባታ በግዴታ መከተል ደግሞ የባሰ ችግሩን እንዳወሳሰቦዉ እንመለካታልን።

በመሆኑም የሻዕቢያ መንግስት በ “ደህረ ነፃነት” የተከተሎው ፖሊሲ ዳገም የኣሽናፊነት ዙፋን ለማጥለቅ በሚል መርህ ከትናናሽ እስከ ትላልቅ የጎሮቤት ኣገሮች ጦርነቶች ብያካሂድም ዉጤቱ ግን ኤርትራ በሉላዊ ኣለማዊነት በዝግ (enclave state) የምተኖር ኣገር ኣድርግዋታል።

ስለዚ የሰሙኑ የሻዕቢያ ዝምታ በኣንድ በኩል የሻዕቢያ ኤርትራ ጦርነት መጀመር እንጂ ማሸነፍ እንደማትችል “የተገነዘበ” ይመስላል። በሌላ በኩል ትንሽዋ ኤረትራ እንዳሽነፈቹ ሲነገረን የነበረ የኣለም ማህበረሰብና ጎረቤት ኣገሮች ጥንቻዎች ካሻዕቢያ ምናባዊ ሃያልነት የሚበልጡ መሆናችው ለማሳየት መመኮራቸው፤ ኣንደሁም የኤርትራ ህዝብ ሲነገሮው የነበረ ዴምክራሲያዊ ቡዝህነትና ነባርያዊ የኤርትራ ሃቅነት( ማህበረ-ሃይማኖታዊ ና ጅኦግራፊያዊ) የማይቀበል “ኣንድ ህዝብ ኣንደ ልብ” ከኣለም አቀፋዊ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ የማይሄድ መሆኑ በመገንዘቡ ከዚህ በፊት እንድ ቀኝገዚ(ኢትዮጵያ)ናእስላማዊ በታኝ(ሱዳን) ሲመለከታቸዉ ና ሲንቃችዉ የነበሩት ጎረቤት ኣገሮች ከየሻዕብያ ኤርትራ የተሻሉ በመሆናችዉ ና የኤርትራ ወጣት በሰላም ለመቀበለ በመወሰናችው ሻዕብያ ለጠላትነት የሚያንቀሳቅሶው ወጣት ማጣቱ ልሆን ይችላል። በመሆኑም ከዝህ በፍት በተደጋጋሚ የማይረቡ(“የደሰከሉ”) ብሎ የሚጠራቸዉና ሲሸነፍ ግን በለሊት ከእንቅልፋቸ ቀስቅሶ ኣዱኑኝ የሚላቸዉ እንደነ ኣፍርካ ህብረት ና ተ.መ.ድ. ኣሁንም የኢትዮፕያ መከላከያ ጥቃት ሲሰነዝር ለተ.መ.ድ. “ተላለኪ (ላቄባ)” ለሚሎው የኢትዮጵያ መንግስት(ወያነ) እንዲቀጣለት ሲጠይቅ፤ የሚያማላክቶው እዉነታ ካለ ሻዕብያ እንካን ድሞክራሲያዊ የኣገራውነት ዳግመ ቅየሳ ልያካህድ ቀረቶ ስከተሎው የነበረ የ “ኣንድ ህዝብ ኣንደ ልብ” መፈክር በቅጡ ለመምራት ኣለመቻሉ ነው።

የሻዕብያ ኣቅመ ደካማነት የሚያጠናክሮው ደግሞ የ “ዋርሳይ ይካኣሎ” ሞራለዊ ኣቅሙ መዳከም፤ ተዋግቶ ኣለመሽነፉ ና ለስድት መሸፈቱ ነው። በኤርትራ ሁለት ትውልዶች ይገኛሉ። የመጀመርያ ትዉልድ “ ይካኣሎ(ይቻሎው)” የሚባል ስሆን የ”ናቅፋ” ትዉልድ ይወክላል። ይካኣሎ የኤረትራ ግዛታዊ ነፃነት ያረጋገጠ፥ተዋገቶ ሃያላንን (ኢትዮጵያ ብቻ ሳይ ሆን ኣመርካና ራሻ) ያሸነፈ ና በኣፍርካ ቀንድ ብቸኛ ሃያል ትዉልድ ተደርጎ ይገለፃል። የድህረ ነፃነት ትዉልድ ድግሞ “ዋርሳይ(የሚወርስ)” ተብሎየሙጠራ ስሆን የ “ሳዋ” ትውልደን ይወክላል። ኣላማው ደግሞ ኤርትራን ሲንጋፖር የማድረግ ነበረ። በመሁኑም ሳዋ የሁለቱም ትዉዶች (“ዋርሳይ ይካኣሎ”) ሁሉም ኣቀፍ የማወራረሰ ሃላፈት የተጣለባት ብትሆንም ቅሉ ግን “ዋርሳይ” በይካኣሎ ኣሰተማሪነት ና በፕረዚደንት ኢሳያስ ትእዛዝ እንድወርስ የተፈቀደለት ጎሮቤት ኣገሮች በመዉረር ወታደራዊ ሃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ኣቅም መለወጥ፥የኣፍርካ ቀንድ መሪነት መንጠቅ፥ ዋርሳይም እንደ ይካኣሎ የኢትዮጵያ መንግስት ዳግም ማሸነፍ፥ የኣለም ህግጋትን ማሰቀየር፥ወዘተ፥ወዘተ ብሆንም የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ መንግስት መካላከያ ላይደግሞዉ መሸነፉ ፕረዚደንት ኢሳያስ በኣዲሱ ትዉልድ (ዋረሳይ)ተስፋ እንዳይጥሉ የዳረጋቸው ይመስላል። በመሆኑም የሰሙኑ ዝምታ ከ ቻይናዉ “Long march” የወረሱት “ምዝላቅ”(ማፈግፈግ) ሰይሆን ላይ የተገለፁ መሰረታዊ ድክመቶች ኣቀፎ በቤተ መንግስት መሰንበት ይሻለል ያሉ ይመስላል።

Meressa Tsehaye

Lecturer at bMekelle university, College of Law and governance


Videos From Around The World

 


 
Tigrai Telethon July 28, 2019
Armed with a slogan "Tigrai bi Tsifrina!" organizers were expecting to raise around 250 million but Tigrai Telethon has surpassed 600 million and still counting!!! The Diaspora Community is yet to be counted but the plan is in the works to raise more funds from North America in the coming months! Congratulations!!


 Mark Your Calendar


Atlanta for Tigrai 2019 Event

 


To All Northern California Tigreans!!

August 25, 2019

 Ashenda Boston 2019 Event

 Victoria Australia for Tigrai 2019 Event

 Ashenda Philadelphia 2019 Event

 Ashenda Dallas 2019 Event

 Ashenda San Diego 2019 Event

 Ashenda London 2019 Event(updated!)

 Ashenda Portland 2019 Event

 Ashenda Houston 2019 Event

 Seattle Ethiopian New Year Event

 


Opinions and Views published on this site are those of the authors only! Aigaforum does not necessarily endorse them. © 2002-2018 Aigaforum.com All rights reserved.