በመቀሌ የመድረኩ ስብሰባ ቦታ እስኪጠብ ድረስ በሺሆች የሚቆጠሩ ተገኙ -ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነገሮች ከእጁ እያመለጡበት ነዉ !
«እኛ ሁላችን አንድ ነን። ኢትዮጵያዉያን ነን»
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
«የትግራይ ሕዝብ እምቢተኝነት ዉስጥ ገብቷል»
አቶ ስዬ አብርሃ
«የትግራይ ሕዝብ ሁለት ጊዜ አምጿል። አሁን ሶስተኛዉ ተጀምሯል።
ዶር ነጋሶ ጊዳዳ
«ቅንጅት ያኔም፣ አሁን ደግሞ አንድነት ከሥርዓቱ ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር ጠብ የለዉም»
ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ
አቡጊዳ - መጋቢት 4 ቀን 2002 ዓ.ም
እሁድ መጋብት 4 ቀን 2002 ዓ.ም መድረኩ በመቀሌ ያደረገዉ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ከአምስት ሺሆች በላይ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት፣ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ገለጸ።
የተዘጋጀዉ አዳራሽ ከመሙላቱ የተነሳ ቆሞ ለማዳመጥ አዳራሹ በመጥበቡ፣ ከአድራሹ ዉጭ በግቢዉ ዉስጥ ስፒከር ተዘጋጅቶ ሕዝቡ ስብሰባዉን ይከታተል የነበረ ሲሆን በስብሰባዉ የነበረዉ ስሜትና የፖለቲካ ግለት እጅግ ከፍተኛ እንደነበረም ለማወቅ ችለናል።
የክልሉ የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በቀጥታ ከአዲስ አበባ በደረሳቸዉ መመሪያ መሰረት ስብሰባዉን ለማደናቀፍና ለመረበሽ የተለያዩ ሙከራዎችን ያደረጉ ሲሆን፣ በተለይም ሕዝቡን ለማስፈራራት ያደረጉት እንቅስቃሴ የትም እንደማይደርስ በመገንዘባቸዉ፣ ከጥቅም ጋር የተገናኙ የተለያዩ አራት ዝግጅቶችን፣ መድረኩ ስብስባ በጠራበት ቀን አዘጋጀትዉ እንደነበረ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ።
በተለይም ትምህርት በሌለበት በሰንበት ቀን፣ የትም ብታ ያልተደረገ፣ የወላጆችና የአስተማሪዎች ስብሰባ እንዲደረግ ባለሥልጣናቱ ማድረጋቸዉ፣ ምን ያህል የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ትንሽ እንደሆነ ማሰባቸዉንና ምን ያህል የሚያደርጉትን እንደማያውቁ የሚያሳይ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
በወላጆችና በአስተማሪዎች መካከል እንዲደረግ ከተጠራዉ ስብሰባ በተጨማሪ፣ የነጋዴዎች ስብሰባ፣ ወጣቶች በትናንሽ ኢንዱስትሪ ዉስጥ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ለማድረግ የሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ለመወያየት የተጠራ ስብሰባ እንዲሁም በመቀሌ ከተማም የብስኪሊት ዉድድር ተዘግጅቶ እንደነበረ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ሕዝቡ እነዚህ በሕወሃት የተዘጋጁ ዝግጅቶችን ወደ ጎን አድርጎ በነቂስ የመድረኩን ስብሰባ ለመካፈል መምጣቱ፣ የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባላትን ሁሉ ያስደነቀ ሲሆን፣ የመድረክ አመራር አባላት ከስብሰባዉ በኋላ፣ በመቀሌ ከተማ በነጻነት በእግር በተመላለሱበት ጊዜም እንዲፈርሙላቸዉ የጠየቋቸዉ «አይዟቹህ እኛ ከናንተ ጋር ነን» እያሉ የሳሟቸዉ እጅግ በጣም በርካታ እንደነበሩም ለማወቅ ችለናል።
በስብሰባዉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ ዶር ኃይሉ አርአያ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አሥራትና ወ/ሮ አረጋሽ በየነ የተገኙ መሆናቸዉን የገለጹልን ዘጋቢዎቻችን፣ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይን ምድር የረገጡት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ «ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን። ሁላችንም አንድ ነን» ባሉበት ጊዜ ሕዝቡ በጋለ ስሜት፣ በጭብጨባ፣ በፉጨትና በሆታ አዎንታዊ ምላሽ እንደሰጣቸዉ ገልጸዋል።
በስብሰባዉ ንግግር ያደረጉት ሌላዉ የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባል፣ ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እንደሆኑ በመግልጽ የፓርቲዉ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በቃሊት እሥር ቤት፣ ለሕዝቡ ነጻነትና መብት ስትል ፣ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መታሰሯን በማሳሰብ፣ ሕዝቡ ይችን ታላቅ የሕዝብ መሪ እንዲሁም በርካታ የሕሊና እሥረኞችን ለማስፈታት ከፍተኛ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።
«እዚህ የቀረብኩት ምክትል ሆኜ ነዉ። ይህ የማስተላልፍዉ መልእክት በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ስም ነዉ» ያሉት እንጂነር ግዛቸዉ፣ አሁን በሥልጣን ላይ ያለዉ አገዛዝ ቅንጅት የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንደሆነ ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ ሲረጭ እንደነበረ አስታወሰዉ፣ ነገር ግን ቅንጅት ያኔ ጠቡ ከሥርዓቱ ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር እንዳልነበረ በግልጽ አስረድተዋል። «ቅንጅት ያኔ የሕዝብ ጠላት አልነበረዉም። አሁንም የቅንጅት ወራሽ የሆነዉ አንድነት የሕዝብ ጠላት የለዉም» በማለት ገዢዉ ፓርቲ የሚጫወተዉን የዘር መከፋፈል ጨዋታ አጋልጠዋል።
ዶር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸዉ የትግራይ ሕዝብ ሁለት ጊዜ ግፍን እምቢ ብሎ ያመጸ ሕዝብ እንደሆነ አስታወሰዉ «ሶስተኛዉ አመጽ ይኸዉ አሁን ተጅምሯል» ሲሉ ሕዝቡ አፈናንና ማስፈራራትን እስርንና መገደልን ሳይፈራ ለመብቱና ለነጻነቱ መነሳቱን ገልጸዋል። ወያኔ በሚል በደቡብ ትግራይ በአጼዉ ዘመን ግብር በዛብን ብለዉ ለመጀምሪያ ጊዜ አምጸዉ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ለሁለተናም ጊዜ በተለይ በደቡብ ትግራይ ተቀባይነት ለማግኘት ታሪካዊና ተወዳጅ የሆነዉን «ወያኔ» የሚል ቃል ሕወሃት በመያዝ በደርግ ላይ አምጾ የደርግን ሥርዓት ለማስወገድ መብቃቱም ይታወቃል።
ከስብሰባዉ በኋላ ስብሰባዉን በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የቀድሞ የኢሕአዴግ መከላከያ ሚኒስቴርና የአሁኑ ከፍተኛ የአንድነት አመራር አባል አቶ ስዬ አብርሃ «የመቀሌ ሕዝብ ፍርሃትን ሰብሮ እምቢተኝነት (ዲፋይንስ ) ዉስጥ ገብቷል በማለት ትግሉ ወሳኝ ምእራፍ ዉስጥ እንደገባ አስረድተዋል።
በተያያዘ ዜና በመቀሌ የአንድነት ጽ/ቤት በተደረገዉ የክልሉ አመራሮችና አደራጆች ስብሰባ አንድነትና አረና ወደ መዋሃድ የሚያመሩ ስለሆነ ሥራዎች በቅንጅት ከታች እስከ ላይ እንዲሰሩ፣ የአረናና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባላት መመሪያ የሰጡ ሲሆን የመቀሌዉን ስብሰባ ተከትሎ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ወ/ት አረጋሽ አዳነ፣ አቶ ገብሩ አሥራትና አምባሳደር አዋሎም ወልዱ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በሽሬ እንዲሁም በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ከሕዝቡ ጋር እንደሚነጋገሩ፣ በርካታ ህዝባዊ ስብሰባዎችም እንደሚደረጉ የደረሰን ዜና ያመለክታል።



It is grteat!
This was a great event that broke Woyane propoaganda that all other Ethiopians are enemy of Tigreans. We all Ethiopians are brother and sister and want to see strong, democratic and peaceful Ethiopia.
It is clear message for Meles Zenawi no more to hide your hidden agenda by the name of Tigray people.
ትግራይ የኢትዮጵያ ነች!ኢትዮጵያም የትግራይ ነች!በዘር አንለያይም!መለስ አይከፋፍለንም!መለስ ትግራይን ከናት ሀገርዋ ከኢትዮጵያ አይለያትም!መለስ ትግራይን አይወክልም!መለስ በትግራይ ስም መነገዱን ያቁም!መለስ ኢትዮጵያን አይወክልም!ህልመ ቢስ:ጠባብ አሳቢ:አለያይ:ተንኮለኛ:ኣቂመኛ:አድርባይና የሙስና መሪ መለስ ኢትዮጵያን አይወክልም!የመለስ ክፉ አገዛዝ ያብቃ!ይሕ የተከፋፈልንበት የተለያየንበት የተዋረድንበት የተዘለፍንበት የሞትንበት የተጨቆንበት ይበልጡን ደሃ የሆንንበት የተሰደድንበት የተከፋንበት ያዘንንበት የመለስ ክፉ አገዛዝ ያብቃ!በትግራይ ንቃት ለመላ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ይሁን!ደግ ቀን ይውጣ!እንደሌሎች አገሮች አገር ሆነን እንልማ!የአፍሪቃ ጃፓን ህልማችን ይታደስ!በኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪቃ ዳግም ትወለድ!በኢትዮጵያ ትንሳኤ ለቅርጫ የተዘጋጀችው አፍሪቃ የአድዋን ልብ የአድዋን ክንድ ታግኝ!ገናናውና ሃያሉ አምላካችን ይርዳን!
What a good news and a wonderful development of peacfull stragle.
You see what EPRDF is doing? using its authority to stop the peacfull gatherings of oppositions.
That was a lowless and full of complexcity.
Shame for TPLF/EPRDF.Enough is enough, time to leave the chaire and return to privete life.
Ethiopian will Unite onece and for all.
One Ethiopianism will win.
God bless Ethiopia and Ethiopians.
Glory to God for this day !
Glory to God for this day !
Glory to God for this day !
የተከበርክ ጀግና የትግራይ ህዝባችን! ከደም ሲል የነበሩት ሁለት ስርአቶች ማለት የሃይለ ስላሰና የደርግ ስርአቶች በተባበረ ክንድህ ደምሥስሃቸዋል;የሃይለስላስ ስርአት የንግሊዞችን ርኩስ ምክር በመስማት መብራት ውሃ መንገድና እለክትሪክ የመሳሰሉት የልማት አውታሮች በትግራይ እንዳይስፋፉ በማድረግ ዲምትስ በለለው መሳርያ አስካይቶሀል; ፋስስቱ ደርግም ያለፈው የተፈስመብህ በደል ሳይበካ ባንተና በንብረትህ ከፍተና በደል አድርሰዋል;ይባስ ብሎም አስቸካይ የተከለከለ ወታደራዊ ከተና ብሎ በማወጅ አንተም ልጆችህም ከብቶችህም ከቦታ ቦታ እንዳትንከሳክሱ በማድረግ ከፍተና በደል አድርሶብሃል.. ሆኖም ለሰላም;ለፍትህና ዲሞክራሲ ሥትል ራስህም ሆነ ልጆችህን ከጎንህ በማሰልፍ በተባበረ ኪንድህ ደምሥሰህዋል. ሆኖም ምንም እንካ አረመነው የደረግ ስርአት ቢደመሰስም ይመሩናል ያልካቸው ካንተው መስለው የወቱ አስመሳዮች የምኒልክን በተ መንግስት ክያዙ በሃላ ይክር ሰላም; ፍትህና ዲሞክራሲ ሊያመቱ ለዘመናት ሰንቶ የኮየው ያገሪትዋ ዳርድንበር ሊያስተብኩ አልቻሉም, በምትኩ ውዲቱ አገርህ እኢትዮፕያ ወደብ አልባ በማድረግ, ህዝብዋም በብህር በክዋንክዋ በመከፋፈል አገሪትዋ ልትወታው ከማትችልበት አዘክት ውስት ከተዋታል,ያ አንተና ልጆችህ የከፈላችሁት መስዋእትነት ሁሉ ከኩብም አልኮተሩትም;ይልኩንስ ባንተ መስዋእትነት ያገኑት ስልታን ለነርሱና ለበተዘመዶቻቸው መበልሰጊያ ሆነዋል,በአገር ውስትም ሆነ ውች የትላልክ ህንሳዎች በአዝማድ ዘመዳቸው ስም ባለበቶች ሆነዋል,ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ባንተ ስም ነው;በንግድም ይሁን በተለያዩ ዘረፋዎች የሚያገኑት ሀብት የሚያስከምቱት በውች ባንኮች ነው,ለላው እኩይ ተግባራቸው ደግሞ አንተን ከለላው አኢትዮፒያዊ ወገንህ ህብረት እንዳትፈትር የተላያዩ ውስብስብ ተንኮሎችን ባንተ ላይ ይፈስማሉ;አንዳደም በለሎች ብሀረስብ ወገኖችህ እንድትተላም ያደርጋሉ;የአባቶችህ እትዮፒያውያን ታሪክና እናት አገርህ እኢትዮፒያን እንዳታውክ በታሪክ የለለ ለነርሱ መሰሪ አላማ የሚስማማ ታሪክን ያስተምሩሃል;እናት አገርህ እኢትዮፒያ እንካን ልጆችዋ ለሎችን መከለብ የምትችል ታላክ አገር ነች;በአገርህ መልክአ ምድር በፈለከው ጊዘና ቦታ ሰርተህ መኖር እንዳትችል ግዛቶችዋን ሁሉ በክልል ከፋፍለው ከክልልህ እንዳትወታ አድርገውሃል;እነዚህ በታት የሚኮተሩ ከአድዋና አካባቢው የፈለኩ ሰዎች ባንተም ሆነ በእኢትዮፒና ህዝብዋ እስከመቸ ባንተ ላይ ተንተላትለው እየከለዱ ይኖራሉ;ባሁኑ ጊዘ በተከረው የአኢትዮፒያ መረት ምንም የህዝብ ድጋፍ ካቱ አመታት ተኮትረዋል;በተለይ ከምርቻ ‘97 በሃላ! እነርሱም ተደናግተዋል;ለዚህም ማረጋገቻችን አምባገነኑ መለስ በየካቲት 11 በመከለ ከተማ ያደረገው አስከያሚ ንግግር ነው;እንደውነቱ ከሆነ በአሉ በዛች ከውቲ ጊዘ ለሰላም;ለፍትህና ዲሞክራሲ ሲሉ መተኪያ የለላት ሂወታቸውን ለገበሩ የህዝብ ታጋዮች መታሰቢያ መሆን ሲገባው ያ ሁሉ የተከፈለው መስዋእትነት ዋጋ የሚያሳታ መሆኑ በታም ያሳዝናል;ስለዚህ ላንተ ተኮርካሪ መስሎህ በትክሳህ እስከ አሁን ተሰክመከው የኮየህ ወያነ-አኢሃዲግ ከወገኖችህ ጋር በማበር እምቢ አልገዛም የምትልበት ጊዘ አሁን ነው!የብዙ ወገኖች ስብስብ የሆነው መድረክ ወደ ክልልህ ዘልኮ በመግባት እኢትዮፒያ አገሩንና እኢትዮፒያውያንን ከአምባገነኑ የወያነ-እኢሃዲግ አገዛዝ ለመታደግ ከፍተና መስዋእትነት በመክፈል ላይ ይገናል;እስከአሁንም ባደረገው እንክስካሰ አባሉና የፓርላማ ተወዳዳሪ የነበረውን አረጋዊ ገብረዮሃንስ ለኮራትና ክኑ አላማ ተሰውተዋል; የወንድማችን አረጋዊ ክቡር መስዋእትነት ከደም ሲል ደርግን ሲፋለሙ ክተሰውት ጀግኖች የሰማእታት መዝገብ ጋር ይመዘገባል;ስለዚህ ሰፊው ህዝባችን የሊጅህን የወታት አረጋዊ ገብረዮሃንስን አራእያ በመከተል እንደወገኖችህ እኢትዮፒያውያን መድረክን ተከላከል;
)))))))…..ከእጁ እያመለጡበት ነው::((((((
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘረኝነት እና ከጠባብ ጎሰኝነት ቀንበር በትግሉ ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል ሁሉ ወያኔ-ባንዳዎች “ሕዝቡ ከእጃችን ሊያመልጥ”ነው እያሉ ሰቆቃውን ለማራዘም በአደባባይ እያሾፉበት ነው::ይህ በሕዝብ ደም የማሾፍ ከንቱነት በቅርቡ እንደታየው ወደ ግድያ እያመራ አንዳንድ ኑሮአቸው ሞት ያስመረጣቸውን በእጅ-አዙር የቅጥር ገዳይነት እና አጥፍቶ ጠፊዎችን በአሥራ አምስት ቀናት የሰው ሰራሽ ዳኝነት ውሳኔ ደመ-ከልብ ለማድረግ ተያይዘውታል::”ረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት”ነውና የግንቦት ሰባት አለኝታ ዋጋው
ቀላል አይደለም;ይሁን እንጂ እንቅስቃሴው በከረረ የትግል ወቅት መጨመር ሲገባው የደፈጣ አዝማሚያው በጉልሕ ይታይበታል::ምነው እነዚህ ሰዎች አገር ቤት በትንንቅ ላይ ሳሉ ግንቦት ሰባት አጋርነቱን ነፈጋቸው::ምንም እንኳን በመሰረታዊ ጉዳይ ለይ:”በእንሳተፍ አንሳተፍ”ልዩነት ቢኖርም አሕዛዊ መረጃዎችን በመፈንቀል እና የዝርፊያውን ቅሌት በማጋለጥ”ባራባሶ ጫማ”አድርጋ አዲስ አበባ የገባችው አዜብ ዛሬ ሚሊዮርነር እንደሆነች:የመለስ ወንድም ከመዝገብ ቤት ሥራ ወጥቶ ዛሬ የለየለት ቱጃር ተብሎ ዶላር መመንዘሩን:በየውጭ አገሩ ድርጅት ከፍተው እንደውኃ ቀጂ አዲስ አበባ እየተመላለሱ መረጃ የሚያቀባብሉትንስ መቼ ነው ይፋ አድርጎ የከረረ ትግሉን የሚጀምረው????
የኢትዮጵያ አምላክ ለድካማችን እድሜና ጤና ይስጠን!!!
ይህ የ2002 ታላቅ ድርጊት ተብሎ መመዝገብ ያለበት ጉዳይ ነው:: የትግራይ ሕዝብ የነመለስ ልብ ሲደነድን ማስፈራሪያ: ሲበረግጉ ደግሞ መደበቂያ ዋሻ መሆኑ ያበቃባት እለት ሆና በታሪክ የመትመዘገብ ይህች ቀን ነች!
የትግራይ ወንድም እህቶቻችን በርቱ!
በተወሰነ ደረጃ ስዮ አና የቀደሞ የሀውህት ታጋዮች ራሳቸውን አስትካክልዋል
Bravo Medrek,
it’s very good that the tigreans did also join the struggle against the weyane tyranny, as this is a great start it should continue through out the country to bring democracy over weyane once and for all in Ethiopia.
Let everyone say no more dicatorshiop in Ethiopia!
ኣኢትዮጵያ በጀግኖች5 ምንጊዜም ትኮራለች”
ኣእሁንም ከተባበርን ያሉብንን ችግሮች ሁሉ ለመወጣት ስለምንችል ህብረትን ኣናጠንክር
What is good for Ethiopia is better for Tigraye,yes it is.Neither a sharp knife nor lieing mouth can split the unity between Ethiopians.
In simple terms,it was synergy in unity;indeed,victory is in the hand of Ethiopians,whereas defeat is Zinawi’s family fate.Amen.
የትግራይ ህዝብ መችየም ቢሆን ….ደሙ ላገሩ ያፈሳል እንጂ ተጠቃሚ ሆኖ አያውቅም!!
ትግሬዎችን የሚጠላ የሃየሎም ደም አጥንት ሁኖ ይውጋው እላሎህ!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ትግራይ አላገባም ብየ ነበር ! አሁን ግን ፍክር ልይዘን ነው>
This is the kind of struggle we were looking for.
Enough is enough, Ethiopians who lived together for thousands of years can not be fooled by Meles. Our struggle was not meant to enrich Meles and his group but for democracy and Ethiopian Unity. We know this Mafia group during the time of our struggle as well as in power, we don’t need them, they must go for good.
Yifter huluf i dont have any problem your appeal for tegrean
Ethiopians what i disagree with you is during the time of
Hailesellasie there was no special mistreatment for tegreans
other than the rest Ethiopians which is not tegray origin
having said that dont forget that Ethiopia is a very poor
country to fulfil the wish of every province,the only time
where the money starts flowing to Ethiopia is zemene woyanne
which sums 97 times than that of the king and derg together
and as i think it was because of the precondition that woyanne
agrees to disintigrate Ethiopia. this is the only time where
you can blame the administration being not capable of contributing
un balanced development and putting the money in its own account
that prefers to build many buildings rather than health and education
and childs care and only depends on donors than creating a healthy
and creative young generation for the future Ethiopia