Checking Fact Checkers!
(Esayas Hailemariam 09-14-20)
የፕሮፌሰር ትሬንቮል መልእክት እና የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተዛባ ዘገባ (disinformation).
Journalist Elias Meseret has misconstrued Norwegian Professor Kjetil Tronvoll's recent message.
ትናንት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተይዘው የተለቀቁት የኖርዌይ ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ ትሬንቮል/ Kjetil Tronvoll በእንግሊዝኛ ያስተላለፉትን መልእክት ተርጉሞ ያቀረበው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት መልዕክቱን የተረዳበት መንገድ (በክፋት ላይሆን ይችላል) እና ፕሮፌሰሩ በርግጥ የፃፉት ፈፅሞ ለየቅል ነው።
ለ አንዳዶቻችን እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋችን ስላልሆነ መሳሳት ያለ ቢሆንም፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተከታዮች ያሉት፣ የሃሰት ዜና (fake news) መንጣሪ፣ የተሳሳተ መረጃ (mis/disinformation) የሚያርም እውቅ ጋዜጠኛ ይሄን መሰረታዊ የእንግሊዝኛ ስዋሶ (basic grammar) አለመረዳቱን ግን ማለፍ አልፈለኩም።
አስተያዬቴ፣ የተፈጠረውን ስህተት በማረም (ጉዳዩ ትኩረት የሳበ ስለሆነም) በሺ የሚቆጠሩ አንባቢዎቹ ትክክለኛውን መልእክት እንዲረዱ ከማድረግ ውጭ ሌላ አላማ የለውም።
በ ወንጀል ፍትህ (criminal justice) አንድ የተለመደ አባባል አለ፥ “police the police”- በፖሊሶችም ላይ ፖሊስ ያስፈልጋል እንደማለት ነው። በመሆኑም፣ የሃሰት ዜና (fake news) መንጣሪ፣ የተሳሳተ መረጃ (dis/misinformation) አራሚ ጋዜጠኛም መረጃ ሲያዛባ (በማወቅም ይሁን ባለማወቅ) የሚያስተካክል/የሚያርም ያስፈልገዋል ለማለት ነው።
ከታች እንደምትመለከቱት፣ ፕሮፌሰሩ የተመረጡ ቃላትን በነጠላ ትእምርተ ጥቅስ (single quotation) ውስጥ አስቀምጧል። የፕሮፌሰሩ ንግግር በሶስተኛ ሰው የተነገረ (reported speech) በመሆኑ በድርብ ትእምርተ ጥቅስ ከማስቀመጥ ውጭ፣ በነጠላ ትእምርተ-ጥቅስስ የተቀመጡት ሰባት /7/ ቃላት በኤሊያስ የአማርኛ ትርጉም ላይ አልተንፀባረቁም (ምናልባት፣ አልገባውም፣ አላስትውዋለውም፣ ወይም ደግሞ እርሱ የሚፈልገውን አይነት መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ይሆናል)።
ይህ የላቀ የእንግሊዝኛ ስዋሶ ክህሎት (advanced grammar skill) የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም። በመረታዊ የእንግሊዝኛ ስዋሶ ደንብ አንድ ቃል በነጠላ ትእምርተ ጥቅስ ውስጥ የሚቀመጠው፣ ከሞላ ጎደል፥ (1) አርእስቶችን (headlines) ስንጠቅስ፤ (2) ፀሃፊው/ዋ ቀደም ብሎ የተናገረ[ች]ውን ወይም ከዚህ ቀደም የተገለፀን ሃሳብ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ሲ[ስት]ጠቅስ፣ ወይም (3) በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ሌላ በትእምርተ ጥቅስ የሚገባ ቃል/ቃላት ስንጠቅስ (a quotation within a quotation) ሲሆን፣ ፕሮፈሰሩ የተጠቀማቸው ትእምርተ ጥቅሶች ከላይ የተዘረዘሩት የስዋሶ ድንቦች ስር አይውድቁም (መዘርዘር ይቻላል)።
👉(4) የጥርጣሬ ትእምርተ ጥቅስ (scare quote):
በተለይ በ እንግሊዛውያው እንግሊዝኛ (British English)፣ ቃል ወይም ቃላትን በነጠላ ትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ማስቀመጥ የጥርጣሬ ትእምርተ ጥቅስ (scare quote) ይባላል። የጥርጣሬ ትእምርተ ጥቅስ ማለት፣ በትእምርተ ጥቅስ የተጠቀሰውን ቃል የፃፈው ሰው ምጸት (irony)፣ ጥርጣሬ (doubt)፣ አሽሙር (indirect affront) መልእክት በማስተላለፍ፣ ጉዳዩ ጭራሽ ከተባለው ተቃራኒ መሆኑን ወይም እንደሚጠራጠረው፣ ብሎም ቃሉ ልዩ ትኩረት እንዲደረግበት ለመጠቆም ነው። በዚህ መሰረት፥ ፕሮፌሰሩ “parted as ‘brothers'” ሲል በወንድማዊነት መለያየታቸውን በጥርጣሬ፣ ምፀት፣ ብሎም ወንድማዊ በማይመስል (unfriendly/not brotherly) ሁኔታ መለያዬታቸውን ለመግለፅ ሲሆን፣ ባጠቃላይ በፕሮፌሰሩ መልክእክት ውስጥ ሰባት /7/ ያክል በነጠላ ትእምርተ ጥቅስ የተቀመጡት ቃላት ኤሊያስ ከገለፀው ወይም ከመሰለው ተቃራኒ ትርጉም ነው ያላቸው። የፅሁፉ መልእክት በመዛባቱ አንባቢዎች ትክክለኛው መልእክት ደርሷቸዋል ማለት አይቻልም። ![]() ![]()
Professor's original Facebook post/can prove Elias read both FB & Tweeter posts:
“After interr[o]gation by immigration officials for some time, and later a 1.5 hr intense, interesting, and at times heated, ‘discussion’ on Ethiopian politics with NISS head at Bole, we found some common ground I belive, and parted as ‘brothers.’ "
"በ ኢሚግሬሽን ሃላፊዎች ለተወሰነ ጊዜ ምርመራ ከተደረገብኝና ከዛም ለ አንድ ሰዐት ተኩል ከባድ፣ የሚገርም፣ አንዳንዴም የከረረ ‘ውይይት’ [‘ውይይት ትእምርተ ጥቅስ ውስጥ መሆኑን ልብ ይሏል]” የሚለውን ኤልያስ:
“በመስማሚያ ነጥብ ላይ ደርሰው ወዳገራቸው እንዳቀኑ”
በማለት፣ ፕሮፌሰሩ “ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት [NISS] ሃላፊ ጋር ስለ ኢትዮጵያ ፖሊቲካ ለአንድ ሰዐት ተኹል ከባድና የከረረ ውይይት አደረኩ” ያሉትን በመዝለል፣ የፕሮፌሰሩን ንግግር ሲጠቅስ:-
“አክለውም 'ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ከፀጥታ አካላት ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ይኼኛው ዕጥሩ እና አስደሳች የሚባልዕ ነው’ ብለው ፅፈዋል…” በማለት ጭራሽ በእንግሊዝኛ ያላሉትን ወይም ያሉትን ቅርፁን ቀየር አድርጎ ሌላ ትርጉም ሰጥቶታል።
ፕሮፌሰሩ እዚህ ጋ ያነፃፀሩት፣ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት፣ ያውም በጦርነትና አስቸጋሪ የፖለቲካ አለመረጋጋት ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያው ውስጥ ምርምር ሲያካሂዱ ይህን የመሰለ ክስተት አጋጥሞኣቸው እንደማያውቅ አፅንኦት ለመስጠት እንጂ (based on the context)፣ ለረጅም ሰኣታት በደህንነት ሃላፊ ከበድ ያለ ምርመራና የጋለ ውይይት ማድረጋቸው፣ ኤሊያስ እንዳለው፣ “ይኼኛው ጥሩ እና አስደሳች የሚባል ነበር” ለማለት አይደለም (የአረፍተ ነገሩ አገባብ/context/ራሱ ትርጉም አይሰጥም)።
The word "interesting" is a relatively low-impact adjective [ባለ ዝቅተኛ ተፅእኖ ቅጽል], it doesn't inherently imply a positive or negative connotation.” Interesting” አወንታዊም (positive) አሉታዊም (negative) ሊሆን ይችላል። ምናልባት ኤልያስ "Interesting" የሚለውን ቃል የሚረዳው አስደሳች፣ ጥሩ በሚል አገባብ (context) ብቻ ይሆናል።
ባጠቃላይ፣ ፕሮፌሰር ትሬንቮል ያስተላለፈውን ሃሳብ ኤልያስ በአማርኛ ሲያቀርበው ቅርፁን ቀይሮ ሌላ አይነት አንድምታ እንዲሰጥ አድርጎታል። ፕሮፌስሩ ከኢሚግሬሽን እና ደህነት ሃላፊዎች ጋር ለሰኣታት ያሳለፈውን ምርመራ፣ የጋለ የፖሊቲካ ክርክር ሳያነሳ፣ በተቃራኒው፣ ላለፈው ሰላሳ አመት ኤርፖርት አካባቢ ፕሮፌሰሩ ካጋጠሙት ክስተቶች ይሄኛው በጣም የሚያስደስት እንደነበረ፣ ምንም ቅር ሳይሰኝ ወደ ሃገሩ እንደተጓዘ በማስመሰሉ አንባቢዎች እንደሚደናገሩ ግልፅ ነው)።
በመጨረሻ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለወደፊት የመማር ማስተማር ነፃነት (academic freedom) ላይ ጣልቃ እንደማይገባ በመመኝትና ተስፋ በማድረግ፣ አሁን የተደረገባቸው ወከባ የመማር ማስተማር/ምርምር ነፃነትን እንደሚጋፋ ቀጭን መልእክት አስተላልፈዋል (ኦርጂናሉን ተመልከቱ)።
አድን ሰው ያላለውን ከተናገርን፣ በምእራባውያን ባህል “you put a word in my mouth” ይላሉ:: "የራስህን ቃል አፌ ውስጥ ከተትከው" ወይም "ያልተናገርኩትን አንተ አልክ" እንደማለት ነው።
Let's fight disinformation.
Back to Front Page |