Back to Front Page

የቆመውን ማስኬድ የሚሄደውን ማስቆም አይቻልም

የቆመውን ማስኬድ የሚሄደውን ማስቆም አይቻልም

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል  07-02-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ ሰው አንድም ሳይገባው ገብቶትም ነገሩ የእሱ ፍላጎት ስለማያሟላና መስማት የማይፈልገው መራራ እውነት ሆኖ ሲገኘው በተጨባጭ የሆነውን ነገር አልሆነም፣ አይሆንም! ብሎ ነገሩን መሸምጠጥና መካድ ብሎም ይህን ተከትሎ ለሚደርስበት የሞራል መላሸቅና የልብ ስብራት ሜክአፕ በመቀባባት ለጥቂት ቀናትና ወራት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማስመሰል መመላለስ ይችል ይሆናል። ጥጉ፥ ሰው በሐሰትና በልበ ወለድ ድርሰት ቀናት መግዛትና ጥቂቶችን ማወናበድ ተቻለው ማለት ግን የህይወት ተፈጥሮአዊ ህግ ተላልፎ የቆመውን ማስኬድ የሚሄደውንም ማስቆም ይችላል ማለት አይደለም። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ይህን ሐቅ ለማስገንዘብና ሰሚ ጆሮ ላለው ዜጋ ሁሉም ለማስጠንቀቅ ተጻፈ።

 

ሐተታ፥ በትሪ ወያነ ትግራይ በአሁን ሰዓት ያልናጠውና ያልሸረሸረው ጨጓሮ፣ ያላናጋው ቤትና ያላንቀጠቀጠው የጠላት አዳራሽ ተፈልጎ አይገኝም። ምቱ ባረፈበት ስፍራና ባሳረፈበት ሠራዊት ላይ ሁሉ ከፍተኛ መደናገጥ፣ የስነ ልቦና መቃወስና የህሊና መዛባት በገሃድ ታይቷል። ከዚህ የተነሳም፥ ሰዎቹ በሆነው ነገር ከመደናገጣቸው ጋር በተያያዘ የገጠማቸው ሽንፈትና ኪሳራ ለማስተባበል ሰሚ ጆሮ በሳቅ ጦሽ አድርጎ ለበሽታና ለሞት ሊዳርግ የሚችል የፈጠራ ማስተባበያዎች እየተሰሙ ነው። ለጥቆም፥ መሪው ብቻ ሳይሆን አንድ ሦስተኛውን የአገሩን ግዛት ለሱዳን አስረክቦኢትዮጵያዊነት አትንኩኝ ባይነት ነውእያለ ሲዘፈን የሚውል ትምክተኛና ቅሌታም ዜጋ ሁሉ የመድረክ ቀልደኛ ሆኗል። ሰዎቹ ውስጣቸው እርር ኩምትር ብለው፣ ሳንባቸው ደም እያንጠባጠበና እየተፋ አፋቸውን ከፍተው የሚናገሩት ሐሰተኛና የፈጠራ ወሬ የሚያመላክተው ታድያ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ውሸትን በመፈብረክና በመዝራት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውን የዋለው ውለታ ምስክርነት ነው። መልካም ዜናው፥ ሰዎች የደረሰባቸው ሽንፈትና ኪሳራ ለማድበስበስ አስበው የሚፈበርኩት ትርክትና የሚያሰራጩት ሐሰተኛ ዜና መሬት ላይ አንዴ ፈጽሞ የሆነውን ነገር ሊደመስስ ቀርቶ ሊቀይርና ሊቀለብስ አለመቻሉ ነው።

 

አንድ ምሳሌ ላንሳ፥ ኦፕሬሽን ራእሲ አሉላ አባ ነጋ ተከትሎ ወያነ ትግራይ በጥላቶቹ ላይ የተቀዳጀው ድል ሁላችን እናውቃለን። ኦፕሬሽኑን ተከትሎ መቶና አምስት መቶ ሳይሆኑ በሺህ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነፍሳቸውን ለማትረፍ ለትግራይ መከላከያ ሠራዊት (TDF) እጅ መስጠታቸውን ድፍን ዓለም ተመልክቶታል። ወያነ ትግራይ እንደ መብረቅ እየተገለጠ ለምርኮ የሰበሰባቸው ዕለት አስመልክተው ሙርከኞቹ በከፊል ትውስታቸውን አጋርተዋል። ስማቸው፣ ማዕረጋቸው፣ የመጡበት አከባቢና የተማረኩበት ቀን ጨምሮ እጅ የሰጡበት ሁኔታ በተመለከተ ተንተን አድርገው ገልጸዋል። የተማረኩት ድንጋይ ሰር ተኝቼ፣ በለስ ውስጥ ተደብቄ ወዘተ ሳለሁ ነበር፤ የተማረኩበት ወር ሰኔ ነበር እያሉ ሲመሰክሩ የሰሙ ጦቢያውያን ታድያ የሰሙት መራራ ሐቅ መስማት ስለማይፈልጉ፤ ነጩን አጥቁረው ማሩን አምርረው ማቅረብ ደግሞ ደማቸው ውስጥ ነውና በፈጠራ ወሬና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ራሳቸውን ለማጽናናት ተማምለው ወጡ። አዲስ አበባና ዋሽንግተን ጎንደርና ለንደን መሽገውምአይ ሙርኮኞቹ ህዳርና ታህሳስ ለማለት ፈልገው ነው፣ የቴክኒክ ችግር ነውበማለት እኛን በሳቅ ጦሽ አድርገው ሲያዝናኑን በአንጻሩ በወገኖቻቸው ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ በገዛ ወገናቸው ላይ ድራማን መስራት ገፍተውበታል። በእውነቱ ነገር፥ በአካለ ስጋ ከምውታን በላይ በህሊና ከህያዋን በታችና የምውታን እኩያ ካልሆነ በቀር ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ይህን ዓይነቱ ቀልድ ይገዛል ተብሎ አይታመንም። በርግጥ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የዋለላቸው ውለታ በጥቅሉ ስንመለከተው ይህ ነው። ይህ ግለሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው፣ የተማርኩትና ያጠናሁት ከዚህ ቀደም በቅርበት በገሃዱ ዓለም ያላየሁት አደገኛ የሰው ባህሪ መገለጫ ከመሆኑ በላይ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የውሸት፣ የምዋርትና የምቀኝነት ባህል በሰማያዊ ተአምራትና ፈውስ ካልሆነ በቀር ለሚቀጥለው አንድ ሺህ ዘመን ወደ ማይቀለበስበት ላቅ ያለ ደረጃ ከፍ ያደረገ ሰውም ነው። እግዚኦ ማለት ታድያ አሁን።

 

Videos From Around The World

በነገራችን ላይ፥ ሰው በባህሪው በተለይ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ያልበስለ ቅሌታም ግለሰብ ዕይታው እንደ አህያ ከሁለት ሜትር በላይ መሄድ ስለማይችል ሲሸነፍ አዎ ተሸንፋለሁ! ብሎ ሽንፈቱን አምኖ ይቀበላል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ካለ የዋህ ነው። እንደዚህ ዓይነት ከትምህርትም ከአእምሮም አጉል የቀረ የታይታና የብልጭልጭ ሰው ዙምባቤም ገብቶ አልተሸነፍኩም ማለት የተለመደ ነው። ጠላት መሸነፉን የሚገባንና ድል ማድረጋችንን የምናውቅ እኛ ድል አድራጊዎችና የድሉ ባለቤቶች ብቻ ነን። የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ የፍዬል ዓይን ቀቅሎ የበላ ኃፍረት የማያውቀው ሰነፍ መሸነፉ የሚገልጽበት መንገድ ታድያ ቃል በቃል አዎ ተሸንፊአለሁ በማለት ሳይሆን አልተሸንፍኩም በማለት ለሽንፈቱ ምክንያት በመደርደር ነው። ባይሸነፍ ኖሮ መጀመሪያውኑ አልተሸነፍኩም በማለት ምክንያት መደርደር ባልተገደደና ባላስፈለገው ነበር። ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኸለች

 

መነጸርህን አስተካክል

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት በወያነ ትግራይ ከደረሰበት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሽንፈት ተከትሎ የገባበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ፣ ከዚህ የተነሳም በውጭ ዓለም እየተከናነበው ያለ አገሪቱ በታሪክዋ ገጥሟት የማያውቀው ዲፕሎማሲያዊ ውርደትና ኪሳራ ተጨምሮበት እልም ያለ ቅዠት ውስጥ የተዘፈቀው የአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ነዋሪ ሲጨንቀው ስራ እየሰራ ነው ተብሎ ዜና እንዲሰራለት፣ እንደ መንግሥት አለሁ ለማለትና ለመታየት ዐረቡም ቻይናም ብቻ የተገኘ የውጭ መንግሥት ለግርፋትም ቢሆን ወደ አገራቸው ጠርተው በጥፊ እንዲያጮሉት እየተማጸነ ያለ ግለስብ ነው። መነጸርህን አስተካክል፥ ከአሁን በኋላ እንደ የሎጥ ሚስት የጨው ሓወልት ሆኖ ቆሞ የቀረው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ገፍተህና ተሸክመህ የትም አታደረሰውም። የዚህ ሰው ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ ፋይሉ በናስ ብረት ተቆልፏል። ታድያ፥ እየሆነ ባለና በቀኑ መጨረሻም መሆኑ የማይቀርለት ነገር ከውዲሁ እንቅልፍ አሳጥቶህ ሐቁ በፈቃደኝነት ላለመቀበል ብትፍጨረጨር እንኳ የትም ላትደርስ መላላጥ ነው የሚሆንብህ። ብትገፋውም ብትሸከመውም የትም ልታደሰው ሳይሆን በድኑ ወደሚያርፍበት መቃብር ስፍራ ብቻ ነው ልታደርሰው የምትችለው።

 

እስራኤል በግብጽ ምድር ላይ የነበራቸው የባርነት ዘመን ለአንዴና ለመጨረሻ መቋጫ አግኝቶ ወደ ርስታቸው የሚመለሱበት ወቅት በደረሰ ጊዜ ጓዛቸው እንዲጠቀልሉና ህዝቡን ለጉዞ እንዲዘጋጁ የሚያስተባብሩ ሙሴና አሮን የተባሉ ሁለት ዕብራውያን መሪዎች በፈርዖን ፊት እንደቀረቡ፤ የመጡበት ጉዳይ በተመለክተም ለግብጹ አገረ ገዢ ለፈርዖን ባስረዱበት ወቅት ጉዞአቸው በድንቅና በታምራት የታጀበ ቢሆንም ፈርዖን የመልክተኞቹ መልዕክት ፈጽሞ እንደማይቀበልና በእስራኤል ላይ የወደደውን ለማድረግ የሚሳነው ነገር እንደሌለው ለማሳየት በዙሪያው የሰበሰባቸው ቀለብ እየተሰፈረላቸው የሚጠነቁልና ምዋርተኞችና አስማተኞች ጠርቶ ሙሴና አሮን ለማሳጣት ብዙ ርቀት እንደተጓዘ ቅድሳት መጻህፍት ይመሰክሩልናል። ታድያ በቀኑ መጨረሻ የፈርዖን ድርጊት መፍጨርጨር ከመሆን አላለፈም። ጠንቋዮችም ፈርዖንን ሊታደጉት አልተቻላቸውም እንደውም ይህችስ የእግዚአብሔር ጣት ናት በማለት ኬላው ማለፍ እንደተሳናቸውና እንዳቃታቸው እንዲሁ ይህን እወቅ፥  

 

v ከወደ ሰሜን የተነሳ ፍትህ ያጣና የተጓደለበት፣ የተገፋና ያመረረ ብርቱ አውሎ ነፋስ ላይቆም ተነስቷል።

 

v ይህ ነፋስ፥ መበተን፣ መጠረግ፣ መፍረስ፣ መነቀል፣ መቅጣትና መቁረጥ ያለበትና የሚገባው ቆሻሻና መናኛ ነፋቂ ሳይበትን፣ ሳይጠርግ፣ ሳያፈርስ፣ ሳይነቅል፣ ሳይቀጣና ሳይቆርጥ እንዲሁ በቀላሉ የሚመለስና የሚቆም ነፋስ አይደለም።  

 

v ይህ ነፋስ፥ የተለመደ፣ ከዚህ ቀደም ያየነውና የምናውቀው ዓይነት ነፋስ ሳይሆን ሲመጣም ሲሄድም የማይታይ፣ በዚህ አለ እየባለ በዚያኛ እየተገለጠ መሰበሰብ የማይገባውን እንደ ዱቄት የሚበትን፣ የቆመ የሚመስል የሚገለብጥ፣ ደንበራውንና አጀበኛውን የእጁን ለመስጠት በስራ የሚገለጥ ነፋስ ነው።   

 

v ይህ ነፋስ፥ ናቕፋና ወለጋ የሰፈረው በታላቅ ዋይታና ሐዘን የሚገኝ ህዝብ ለማሳረፍ አስመራና አዲስ አበባ መግባት ሳያስፈልገው ወላፈኑ ብቻውን በእስራት ያሉትን ህዝቦች ነጻ የሚያወጣ፣ ጉልላቱን መትቶ መሰረቱን የሚያናጋ፣ የራሽያና የቻይና የጦር መሳሪያ የማያስቆሞው የቁጣ ነፈስ ነው።

 

v ይህ ከሰሜን ተራሮች የተነሳ የተቆጣ ነፋስ ዓላማና መዳረሻው፥ በቀጠናው የተንሰራፋው የተዝረከረከ፣ ግብዝነትና ሴሰኝነት የሞላበት የውሸትና የቅጥፈት የሴራና የአሻጥር ፖለቲካዊና ማህበራዊ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ለማጽዳትና መልክ ለማስያዝ የተነሳ የሰው ጉልበትና ብርታት የማያስቆመው፣ ብዙዎችን የሚያሳርፍ ኃያልና ብርቱ ነፋስ ነው። ከቻልክ አሰላለፍን አሳምር፣ ካልቻል ዘወር በል፣ እምቢ ብትል ግን የትል ሲሳይ ለመሆን በራስህ ላይ እንደፈረድክ እወቅ። ደግሞም፥ አዲስ አበባና ኬንያ፣ ለንደንና ዋሽንግተን መሽገህ፥ ዘራፍ ራያ፣ ወልቃይት! እያልክ ከምታጓራና የሳይበር አርበኛ በመሆን እንደ ውሻ ምላስህን ከምታላቅቅ በር ዘግተህ መቀደድ ይቅርብህና እንደ ወንድ ሱሪ ታጠቀህ ራያና ወልቃይት ላይ ቁመህ ጠብቀን። ውይ፥ ለካ ኢምሬት የለችም፤ ጀርባቸው ላይ ተፈናጥጠህ የመጣህበት የወገቡ ጅማት የተፈታ የዐቢይ አህመድ ዓሊ የኤርትራና የሶማሊያ ሰራዊት የለም፤ ለካ ለሰማይ አሞራና ለምድር አራዊት ሲሳይ ሆኖ የቀረው የሶማሌ፣ የአፋርና የኦሮሞ ሌግዮን በስፍራው የለም። እያውራህ ትቀበራለህ።

 

ሌላው፥ ብታምንም ባታምንም፣ ቢገባህም ባይገባህም፣ ብትቀበልም ባትቀበልም፥ ዓለም አጨብጭባ የተቀበለችው ጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የቤተ መንግስት ቆይታ በትሪ ወያነ ለሚያዩና ለሚሰሙ ለሚገባቸውም በሎህሳስና በሲግናል መቋጫ አበጃጅቶለታል። በማታቀው ዓለም እየኖርክ ዳሩ ግን ስትለፈልፍ እንደ አዋቂ ራስህን በማታለልና በወሬ ለተጠመድከው ዜጋ ታድያ መልዕክት አለኝ፤ ይኸውም፥ ነገ እውን ሆኖ የምታየው የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሽኝት እንዲሁ ሳይሆን በምህረት እንደሆነ እንድታውቅ እወዳለሁ። ዐቢይ አህመድ ዓሊ አሁን የተሰጠው በህይወት የመኖር ዕድል በአግባቡ ከተጠቀመበት ጋዳፊና ሙባረክ በሄዱበት መንገድ ከመሄድ ይተርፋል። ሽኝቱም፥ እሱ ራሱ አለሁ አለሁ እያለ፤ በውሸት ልክፍ የተነከረው ደጋፊም አለ አለ እያለ በሎህሳስ ይሆናል። በዚህ መንገድ እንደሚሰናበትም አምናለሁ፤ ተስፋም አደጋለሁ።

 

መቼ ይህ ብቻ መጪው ዘመን፥ ገና ለገና የሚይዘውና የሚጨብጠው አጥቶ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ እየወጣ ዘራፍ! እያለና ቢጫ ወባ እንደያዘው ነገር እየቀላቀለ ያለ፤ ከባህርዳር እስከ ለንደን፣ ከጎንደር እስከ ዋሽንግተው የተሰለፈው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰላም ነስቶ አገር እያተረማመሰ የሚገኝ፤ በአስተሳሰባቸው የሰው መጨረሻና አተላ ሆኖው ሳሉ በምላሳቸው ከደመና በላይ የሚመላለሱ ዘመኑን የማይመጥኑ ጠባቦችና ትምክህተኞች፤ ጉራን መንፋት፣ መሳደብ፣ መራገምና በሰው ላይ ማሟረት እንደ ጀግንነት የሚቆጥሩ፤ የምቀኝነትና የምዋርት ፖለቲካ ባለቤትና የምላስ አርበኛ የአማራ ልሒቃን ለዘመናት የዘለቀ የቀረርቶና የሽለላ ሐሰተኛ ኑሮም ፈጽሞ ላይመለስ ደልዳላ ሜዳ የሚሆነበትና የሚቀበርበት፣ ልኩን አውቆ በሥርዓት የሚኖርበት ዘመን ከፊታችን ነው። ይህ ስለ ፍጻሜው ተናገርኩ እንጅ ነገሩ እውን ከሆነ ውሎ አድሯል። ቀጥሎም፥ የኤርትራና የሻዕቢያ ቡድን ኢትዮጵያን በማተረማመስ፣ ትግራይና የትግራይ ህዝብ አብርሶና አጥፍቶ ማንኪያና ሹካ፣ ብሎኬትና አሸዋ፣ አህያና እንቁላል ሳይቀር ትግራዋይ የደም ላብ አውጥቶ ያፈራው ሀብትና ንብረት ዘርፎ ሊገነባት ያሰባት፣ ዓለም የረሳትና የበከተች፣ የሌቦችና የዘራፊዎች አገር ከኢሳያይስ አፈወርቂ ጋር አብሮ የሚቀበርበትና ህልም ብቻ ሆኖ የሚቀርበት ዘመን ነው። አሁን የቀረው፥ የተራሮቹ ባለባት ወያነ ትግራይ አራትና አምስት መንግስታት ላሽ አድርጎ እንደገና የሚፈጥረውና የሚያበጃጀው አዲስ የምስራቅ አፍሪካ አሰላለፍ እውን መሆን ብቻ ይሆናል። ይህ ዛሬ ላይ ሆነው ሲሰሙትና ሲያነቡት ለማመን የሚከብድ፣ በትግራይ ልጆች የህይወት መስዋዕትነት እውን የሚሆነው፣ ትግራዋይ ከጀግንነቱ የተነሳ በማንነቱ ተከብሮ የሚኖርበት አዲስ ታሪካዊ ክስተት ለማየት ታድያ ከእውነት ጎን መቆምና መሰለፍ ይጠይቃል። ለምን? ተቀላቅለህ አንድም በእናትህ ቀሚስና ጥላ ውስጥ ተደብቀህ የምታልፈው የሰላም ኬላ አይኖርምና።      

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page