Back to Front Page

ርዕሰ ኃያላኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይህን ያህል ያስጨነቃቸው ምክንያት ምንድ ነው?

ርዕሰ ኃያላኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይህን ያህል ያስጨነቃቸው ምክንያት ምንድ ነው?

 

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

09-24-21

 

መንደርደሪያ፥ በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ነው አሉ አንድ በስራ ምክንያት ወደ አውሮፓ የተጓዘ አሜሪካዊ አንድ ካፍቴሪያ ውስጥ ሳለ ከአንድ ራሽያዊ ጋር ይተዋወቃል። ሰላምታ በመለዋወጥ የተጀመረ ትውውቅ ሞቅ ወዳለ ጨዋታ ያመራል። በዚህ ማኸል አሜሪካዊው ራሽያዊውን እኛኮ ሙሉ ነጻነት ያለን ህዝቦች ነን፤ ከፈለግንም ዋይት ሃውስ ደጃፍ በር ቁመን ሬገን ይውደም! ማለት እንችላለን ይለዋል። በአሜሪካዊው አባባል እምብዛም የተደነቀ የማይመስለው ራሽያዊው ተቀበለና፥ ታድያ ይህ ምን ችግር አለበት እኛም እኮ ከርመሊን (የራሽያ ቤተ መንግስት) በር ድረስ ተገኝተን ሬገን ይውደም! ማለት እንችላለን ሲል መለሰለት ይባላል። የአማራ ልሒቃን በሌብነትና እያስመሰሉ በሚሰሩትና በቅጂ የሰበሰቡትና ያካበቱት ካልሆነ በቀር በታሪክ አፋቸው ሞልተው ይህ የእኛ ነው የሚሉት የራሳቸው የሆነ ታሪክም ቅርስም የሌላቸው እንደ እባብ መርዛምና ተናዳፊ የሆነ ምላሳቸው እያወጣወጡ በሽላና በቀረርቶ ተደብቀው ዛሬ ላይ የደረሱ ትምክህተኞች ለመሆናቸው ዝርዝር ሐተታ ውስጥ መግባት ለዘመናት የዚህ ያበቃለት የትምክህት ኃይል ባዶ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖ ለኖረው ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች የመርዳት ያህል ነው። የአማራ ልሒቃንና ከበሮ መቺዎቻቸው ፈር የሌለው መቀደድና የትምክህት ጥግ ግን እንዲሁ የሚታለፍ ሳይሆን ለትውልድ መመስከር ስለሚገባ ከሰሙኑ ጋር በተያየዘ ከብዙ በጥቂቱ አንድ ለማለት እወዳለሁ።

 

የአማራ ልሒቃን የሐሰት፣ የበሬ ወለደና የአሉባልታ ልክፍት ዛሬ ላይ የተከሰተ አዲስ ነገር ሳይሆን ከልሒቃኖቹ ማንነ ጋር አብሮ የቦቆለ ምቀኝነትና ምዋርተኝነት ሴሰኝነትና አመንዝራነት የወለደው ክፉ በሽታ የማይገልጸው የልሒቃኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ለመሆኑ ታሪክ ወደኋላ መለስ ብሎ መፈተሽ ያስፈልጋል። ይኸውም፥ የታቦተ ጽዮን በአክሱም ማረፍ/መኖር ትግራይ የዓለም የታሪክ ሊቃውንትና የቅርሳ ቅርስ ተመራመሪዎች ማዕከል ከማድረጉ በላይ ነገሩ የትግራይ ህዝብ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስልጣኔ ለዓለም የሚያስተዋውቅና የሚመሰክር ድንቅ አጋጣሚ በመሆኑ በአንጻሩ ደግሞ ታቦተ ጽዮን ተብሎ ትግራይ! ሲባል በሰሙ ቁጥር ደም የሚያስቀምጣቸው የአማራ ልሒቃን ምቀኝነት የወለደው በሽታ እየጸናባቸው በመሄዱ የእግዚአብሔር እጅ መጠምዘዝ እንደማይችሉ፣ በቅናትና በማጉረምረም የሚፈጥሩት ተአምር እንደሌለም አጥብቀው በተረዱ ጊዜ ግን ቅናት ያሰከረው ተቅበዥባዥ ማንነታቸው በሐሰተኛ ድርሰትና ትርክት ለማጽናናት፣ ጉብኚ ወደ ትግራይ በጎረፈ ቁጥር እኛንም አስቡን/አስታውሱን ለማለት፣ ብሎም በቅናትና በምቀኝነት የሚሰቃይ ማንነታቸው ከትግራዋይ ማንነት ጋር እኩል ለማስቀመጥና ለማስተካከል እንደለመዱት ታቦተ ጽዮንን በቅዢ እኛ ጋርም አለች አለን ማለት ስለማይችሉ ከታቦቱ ሊስተካከል ይችላል ብለው ያሰቡትን መስቀሉን ግማሹ እኛጋ ነው የሚል የሌለ ወሬ ፈጥረው ግሼን ደብረ ከርቤ የልጇ ግማደ መስቀል የከተመበት አምባ እያሉ ሐሰተኛ ድርሰት መጻፍና ማዜም የጀመሩ ሰዎች ናቸው። ታድያ፥ የአክሱም ሓወልት ሲባል ፈሲለደስ ህንጻ የሚሉትን ቀልድ ትተን (ላሊበራ የተጋሩ አሻራ ያረፈበት የአገር ነውና) የእግዚአብሔር በሆነ ሀብትና ንብረት መቆመር ያልተዉና የለመዱ ሰዎች ታንካቸው ከነ ታንከኛው AK-47 (ክላሽንኮፍ) በያዘ ትግራዋይ ሲማረክ የዓለም ዜጎች አይ ጀግንነት! እያሉ በሁለት ዓይናቸው በአግራሞት ሲመለከቱ እያዩና እየሰሙ የአማራ ልሒቃን የአባቶቻቸው ቅናትና ምቀኝነት የወለደው የምዋርትና የሴሰኝነት መጻህፍቶቻቸው በማገላበጥ ጀግናው በባዶ እጁ 15 ማርኮ 40ቹን ደመሰሰ እያሉ ቢዘፍኑብንና በላያችን ላይ ቢያነበንቡ ፈጽሞ ሊደንቀን አይገባም እያልኩ ወደ ዋና ሃሳቤ ላዝግም።

 

ሐተታ፥ ከ30 ዓመታት በፊት በርሃብና በጦርነት ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በይፋ ወደ ቀድሞ መታወቂያዋና የኪሳራ ታሪክዋ ተመልሳለች። ኢትዮጵያ፥ የዓለማችን መሪዎች እግራቸው በቆመባቸውና ለምክክር በተቀመጡበት ስፍራና አገር ሁሉ ለሰው ልጆች ሰላምና ደህንነት ጠንቅ የሆነች አገር ተብላ ከየመን፣ ከአፍጋኒስታን ከስሪያና ከሊብያ ቀድማ የምትጠራ የደም መሬት አገር ሆናለች። ከነተረቱ፥ ሞኝ የጨው ክምር ሲፈርስ አይቶ/እያየ ይስቃል እንደሚባለው ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያ የቁልቁሊት ጉዞ ጀብድነት ሆኖ የሚሰማቸውና ሐሰተኛ መፈክር አነግበው ሲሸልሉና ሲመጻደቁ ውለው የሚያድሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። መስከረም 6 ቀን 2021 ዓ/ም የኢትዮጵያዊነት ቀን ተብሎ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቷ አንተን መሰል አጨብጫቢ፣ ደንቆሮና ኋላቀር ሰዎች ተይዞ አገርና ትውልድ ማዳንም መለወጥም አይቻልምና ቋንቋህን አስተካከል! ሲሉ ምርኮኛው ባጫ ደበሌን በወስጠ ዘ የሚገባው ስፍራ ስያስቀምጡት፤ የሌለን እናዳለ በማስመሰል ሲራገብ የዋለው ኢትዮጵያውነት የሚለው የምዋርተኞች ፈሊጥ የከነከነው፣ በስብሰባው መገኘቱ በራሱ ያሸማቀቀውና ክፉኛ ያስከፋው የሚመስል፣ እውነተኛ ማንነቴን ጥዬ እየተነገረ ያለ ልብ-ወለድ ድርሰት የሆነ ሐሰተኛ ማንነት አልቀበልም በማለት ቤቱን ግር ያሰኘ አስተሳሰብ ያንጸባረቀ ፕሮፌሰር በተመሳሳይ ኢትዮጵያ አትፈርስም ኢትዮጵያ አልማዝ ናት እያለ ሽመት ፍለጋ ሲፎክርና ቤተ ጴንጠ ላይ የለመደው ሐሰተኛ ትምህርት የመዝራት አባዜው እንዲያቆም ፕሮፌሰሩ በጥበብና በዘዴ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል ሰው ከእኛ ከፖለቲከኞቹ በላይ ሆኖ ሲዋሽና ሲቀባጥር አይመቸኝምና ውሸትህን አቁም! ሲሉ በሎህሳስ መልዕክታቸው ባስተላለፉበት በዚህ ትንግርተኛ ውሎ በሰፊው ሲንጸባረቅ የተስተዋለው የዐቢይ አህመድ ዓሊ ጆክር የሆነችው ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚል ሐሰተኛ ፈሊጥ ነው።

 

Videos From Around The World

ኢትዮጵያ አትፈርስም እየተባለ እየተስተጋባ ያለ ሐሰተኛ ትርክት ታዲያ በይዘቱ ፖለቲካዊ መሆኑ ቀርቶ ጭራሽ ኃይማኖታዊና መለኮታዊ መልክና አንድምታ እንዲይዝና እንዲላበስ ለማድረግ ያልተደረገ ጥረት የለም። ፈጣሪ ዓለምን እየገዛ ያለ ኢትዮጵያ ላይ ተቀምጦ እንደሆነና ኢትዮጵያ የፈጣሪ የመንግስቱ መቀመጫ እንደሆነች አድርጎ የሚያስብ ከዚህ የተነሳም ኢትዮጵያ አትፈርስም ብሎ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ቁጥር ቤት ይቁጠረው። በርግጥ፥ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የዙፋኑ የሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንደሚነዙት ፕሮፓጋንዳና እንደሚያሰራጩት ሐሰተኛ በሬ ወለደ ዜና ሳይሆን ከራሱ ከዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ ከአማራ ልሒቃንና ከኢሳይያስ አፈወርቂ ውጭ ያለው ኃይል ሁሉ አሜሪካና አውሮፓ ጨምሮ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የማቅናትና ህዝቦቿም ከገቡበት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መቀመቅ የማውጣት ዓላማና ተልዕኮ እንጅ ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳ የላቸውም ኖሯቸውም አያወቅም። አሜሪካና አውሮፓ ኢትዮጵያ የማፍረስ ዓላማ የላቸውም ሲባል ግን፥

 

v ኢትዮጵያ የእመቤታችን የአስራት አገር ናት ብለው ስለሚያኑ፤

 

v ኢትዮጵያ ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ የባረከቻች አገር ናት ብለው ስለሚቀበሉ፤

 

v ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት የሚል ብዥታ ስላላቸው፤

 

v ኢትዮጵያ፥ የሰማይ መብረቅ ሻማና ጥዋፍ ሆኖ ከሰሜን ወደ ደቡብ በሚበርቅበት ኃይልና ፍጥነት መጻህፍት የሚያነቡ፣ የድንጋይ ቆብ አሰፍተው እስከ ምጽአት የማይሞቱ ገዳማውያን ያላት አገር ናት የሚለው ቅዠት ስለ ሚያምኑበት፤

 

v ኢትዮጵያ መቶ ኪሊ ሜትር ከመሬት ስር ተቆፍሮ በሚገኝ የከበረ የድንጋይ ማዕድን (ድያመንድ) የተሰራች የማትሸረፍ፣ የማትቆረስ አገር ናት የሚል አዲስ ተረት ተረት እውነት ነው ብለው ስለ ተቀበሉ፤

 

v አድራሻው የማይታወቅ የኢትዮጵያ አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃታል! የሚለው ቱሪናፋ ስለ ሚጋሩ ሳይሆን ርዕሰ ኃያላኑ ለእነሱ የቢዝነስ ፕላን የሚያዋጣቸው፣ ለራሳቸው ጥቅም ሲባል ብቻ በቀጠናው መኖር ያለበትና የሚገባው አገርና መንግስት የመወሰን ማለትም የማድረግና የመንፈግ ስልጣን ስላላቸው፣ .. መስከረም 06 ቀን 2013 ዓ/ም ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መባቻ ምክንያት በማድረግ ከአገር ውስጥ የዜና አውታሮችና መገናኛ ብዙሐን በትግርኛ ቋንቋ ባያደረጉት ረጅም ቃለ መጠይቅ ነባራዊ የኢትዮ-ኤርትራ በተመለከተ "የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ መጨረሻ ምንድ ነው? መፍትሔውስ?" ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢትዮጵያ 2ኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረች ሀገር ናት። ያም ሆነ ይህ ሌላ ሰው የፈልገው ሊል ይችላል ይህች ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር ግን 2ኛ የዓለም ጦርነት ተከትሎ የመጣ የዓለም ሥርዓት ሥርዓቱ ራሱ በሚመርጣቸው ገዢዎች ይጠቀምባት ዘንድ የፈጠራት ኃይል ናት እንዲል ያቺን ኢትዮጵያ የማስቀጠል መሻት ስላላቸው እንጅ ኢትዮጵያ የማትሸጥ የማትለወጥ ድያመንድ ስለሆነች አይደለም። አገሪቱ ከፈራረሰችና ከተበታተነች ቆይታለች በኪነ ጥበባቸው ደግፈው የያዝዋትና ያቆዩዋት ታድያ ሌላ ማንም ሳይሆን አውሮፓና አሜሪካ ናቸው።

 

ለመሆኑ፥ ዲያመንድ የማይሸረፍ የማይቆረስ የከበረ የድንጋይ ማዕድን ከሆነ ተሸራርፋና ተቆራርሳ ገና በቀጣይም የምትጋመሰው ኢትዮጵያ የማትሸረፍ የማትቆረስ ዲያመንድ የሆነች ከመቼ ወዲህ ነው? ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ አገር ከሆነች በኋላ? ዐቢይ አህመድ ዓሊ ባድመን ለኤርትራ እሰጣለሁ ካለ በኋላ? ወይስ በ2020 ዓ/ም ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ሰፊ የእርሻ መሬት ለሱዳን ካስረከበች በኋላ መሆኑ ነው? የሚደንቀው ኢትዮጵያ ድያመንድ ናት እያሉን ያሉ አፋቸው የሚከፍቱ ኃፍረት የሌላቸውና የማያውቃቸው ስልጣን ፈላጊ አፈጮሌዎች ኢትዮጵያን እንደ ዲያመንድ ሊጠብቋት ቀርቶ መቀመጫቸው መጠበቅ ተስኗቸው የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን አስረክበው የተቀመጡ ድኩማን መሆናቸው ትርክቱን ትንግርት ያደርጓል። ወገን፥ ይህ ሁሉ ቅዥትና መቀባጠር ክፉ ደብተራ ጠላ ጠግቦ የጻፈው የምዋርተኞቹና የአመንዝሮቹ የአማራ ልሒቃን ዘመን ያለፈበት ሐሰተኛ ድርሰት በዚህ ዘመን የሚገዛው ትውልድ ይኖር ተብሎ ባይገመትም፥ ርዕሰ ኃያላኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይህን ያህል ያስጨነቃቸው ምክንያት ግን የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሓፊ የሆኑት አንቶኔ ጉተሬዝ በቀርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ትግራይ በብረት የምታንበረክከው ህዝብ አይደለም ሲሉ ግልጽ በሆነ ቋንቋ እንዳስቀመጡት የምዕራባውያኑ ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ ምስጢሩ፥

v ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ቆፎን ያለ ንብ ማንጠልጠል ማለት እንደሆነ ስለሚያውቁ፤

 

v ትግራዋይ ያገለለች ኢትዮጵያ የሞትና የእልቂት መናገሻ ብሎም የመቃብር ስፍራ ማለት እንደሆነች ስላዩ፤

 

v ትግራዋይ የሌለባት ኢትዮጵያ እንደ አገር ልትቆምና ለሌሎች ምቹ የሆነች አገር ልትሆን ቀርቶ ለዜጎችዋ የማትሆን አገር መሆኗን ስለ ተረዱ፤

 

v በጥቅሉ፥ ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ካልመለሰች አሜሪካም አውሮፓም ራሽያም ቻይናም ቱርክም ኢምሬትም ሳውዲም ኢራንም የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አገር የሆነችው ኢትዮጵያን በመጠቀም ሆነ ከኢትዮጵያ ከራሷ ሊያገኙትና ሊስያጠብቁት የሚፈልጉትና የሚችሉት ማንኛውም ዓይነት ጥቅም ሁሉ ዓይናቸው እያየ ጆሮቸው እየሰማ ውሃ ስለ ሚበላው ነው። ይህ ከመሆኑ በፊት ታድያ ምዕራቡም ምስራቁም አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል። አሁንም ርዕሰ ኃያላኑ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ለማስጠበቅ የሚደርጉትና የሚሄዱት ርቀት የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስደሰትና ለመታደግ ታስቦ ሳይሆን አገራቱ የራሳቸው ጥቅም ለማስጠበቅና ለማስከበር የሚደርጉት ድርጊትና የሚሄዱት ጉዞ እንደሆነ በድጋሜ ላሰምርበት እወዳለሁ።

 

ርዕሰ ኃያላኑ በየራሳቸው መንገድ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ለማስጠበቅ እየሰሩት ያለ ስራ ኢትዮጵያ አገር እግዚአብሔር ስለሆነች አትፈርስም ብሎ የሚያምነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከነ እምነቱ ግምት ውስጥ የሚያስገባ አይደለም ከኢኮዥን ውጭ ነው። የነገሮች መገጣጠም ማለትም፥ የምዕራባውያን ኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነቷ ጠብቃ መቀጠል አለባት የሚለው መሻታቸውና ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው ኢትዮጵያ የማትፈርሰው አመቤቴ በኪደተ እግሯ ስለባረከቻት ነው የሚለው ደብተራ ወለድ የሆነ ድርሰት ከመገጣጠማቸው በላይ ትምክህተኞቹ አፋቸው ሞልተው እንዲናገሩና ሰገጣም አስተሳሰባቸውም መንፈሳዊ መስሎ ለመታየት ሐሰተኛ ካባ አላብሶታል። እዚህ ላይ አንድ መራራ እውነት ልጨምርሎት ይኸውም፥ እግዚአብሔር ከድንጋይና ከአፈር ከሽንጥሮና ከተራራ ጋር ጉዳይ የለውም። እግዚአብሔር የሚያውቃት አገር አለች ከተባለችም እግዚአብሔር በሰሜን በደቡብ በምዕራብና በምስራቅ የሚገኙ አዋሳኝ ደንበሮቿን ጠርቶ እንደ አገር የሚያውቃትና ስሟን የጠራት አንዲት እስራኤል ብቻ ናት። ከዚህ ውጭ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ባለው መጽሐፍ ቦርደርዋ የታወቀች አንድም አገር የለችም፤ አልተጣራችምም።

 

ለመሆኑ ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለ ኃይል ማን ነው?

 

አንዱ ለኢትዮጵያ እዘምታለሁ ሌላኛው ለኢትዮጵያ አንድነት እንታገላለን በሚል ሐሰተኛ መፈክር ተደብቀው ኢትዮጵያን የደም መሬት እያደረጉ ያሉና አገሪቱን እያፈራረሱ ያሉ ብቸኛ ጣምራ ጠላቶች ሌላ ማንም ሳይሆን፥ 1. የኤርትራ ዕድሜ ልክ ገዢ ኢሳይያስ አፈወርቂ 2. ያለቦታው በስህተት የተቀመጠ ጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊ 3. የምላስ አርበኞቹና አመንዝሮቹ የአማራ ልሒቃን ናቸው። ከኢትዮጵያውያን በላይ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር ሰው በመምሰልና የኢትዮጵያ አንድነት ያስጨንቀኛል እያለ በነጋ በጣባ ቁጥር በሚዘራው ፕሮፓጋንዳ የተነሳ በተለይ የልሃጫሞቹና የትምክህተኞቹ ልብ በማማለልና በመስለብ የተሳካለት፣ ኢትዮጵያን ለረጅም ዘመናት ሲገዘግዛትና ሲያሴርባት የኖረ፣ በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ከዚህ ቀደም ለንባብ በበቁ ጽሑፎቼ በስፋት እንዳሰፈርኩት የኢሳይያስ አፈወርቂ ቀዳሚ ዓላማና ተልእኮ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ደም መቃባትና ኢትዮጵያን የደም መሬት ማድረግ ነው።

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ የሚፈልጋት ኢትዮጵያ፥ የብሄር ብሔረሰቦች መብትና ስልጣን ጠብቃ ልማትዋና ዕድገትዋን የምታፋጥን የበለጸገች ሀገረ ሰላም የሆነች ኢትዮጵያ ሳትሆን በዋናነት ትግራይን ውጣ ስታበቃ የተቀረው ማህበረሰብ ደግሞ ጋላ ሻንቅላ እያለች ብሔር ብሔረሰቦች በማንነታቸው እያሸማቀቀች፣ እያረደችና እየገደለች የምትኖር ምንሊካዊት ኢትዮጵያ መፍጠር ነው። ምን ነው? ቢሉ፥ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብትና ስልጣን የምትጠብቅና የምታከበር ትግራዋይ የሚባል ህዝብ የፈጠራት የበለጸገች ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያ ለኤርትራ መቀጨጭና መክሰም ከፍተኛ ሚና የተጫወተችና ወደ ነበረችበት የጦርነት ዓውድማ የሆነች አሃዳዊት ኢትዮጵያ መመለስ አለባት ብሎ ስለሚያምንና፤ የድንቁርና፣ የችጋር፣ የእጦት፣ የድህነት፣ የጦርነት፣ የኋላቀርነት መገለጫ የሆነችው ምንሊካዊት ኢትዮጵያ በአንጻሩ፥ ኤርትራ የአፍሪካ ሲንጋፖር፣ ኢሳይያስ አፈወርቂ ራሱ ደግሞ የቀጠናው አያቶላህ (ንጉሥ) የመሆን ጨለምተኛ ህልሙ በቀላሉ ለማሳካት እንደምታስችለው አጥብቆ ስለሚያምን ነው። በመሆኑም፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያውያን ለአንገታቸው ክራባት ለሆዳቸው ጥይት እየተመኘ ሰተት ብሎ በመግባትም በሰው አገር መሬት ላይ ገብቶ የሰው አገር ዜጎች እየፈጀና እያስፈጀ የሚገኘው። ጠቅላል ባለ መልኩ፥ ሻዕቢያ ወልዲያና ጎንደር መሽጎ እየተዋጋ ያለ አድጊ ብሎ ለሚጠራው አማራ ስለሚቆረቆር ሳይሆን፥ የአማራ ልሒቃን በመጠቀም ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ የድህነትና የሞት አፈራም ክብሯ ለመመለስ ስለሚያስችለው ነው።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊና አመንዝሮቹ የአማራ ልሒቃን ኢትዮጵያን እየፈራረሱና እየበተኑ ያለስ በምን መንገድ ነው? እንል ይሆናል። ጥያቄ ትክክለኛ ተግቢ ጥያቄ ነው። የዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ኢትዮጵያን የማፈራረስ መንገድ በሚገባ ሊታየንና ልንረዳው የምንችለው አንድ ክፉኛ ቁማር የመጫወት ሱስ ያለበትና የያዘው ሰው ስነ-ልቦናና የዕለት ዕለት ተግባራት በትክክል የተረዳን እንደሆነ ብቻ ነው። አንድ የቁማር ሱስ ያለው ሰው የያዘውን ይዞ ወደ ቁማር ቤት ሲሄድ ሁል ጊዜ የሚያስበው እበላለሁ ነው። እየተበላም አሁን እበላለሁ ነው። የቁማር ሱስ የተጸናወተው ሰው፥ ተበልቶም እበላለሁ በሚል ስሌት ያገኘውን ይዞ በመሄድ በባዶ እጁ የሚመለስና የሚበላ ሰው ነው። የተበላውን አስመልሳለሁ እያለ ሲጫወት ገንዘቡን የጨረሰ ይህ ሰው አሁንም እበላለሁ ስለሚል ያለውን ሁሉ አስይዞ ባዶውን እስኪቀር ድረስ የመቆመር መጥፎ ባህሪ አለው።

 

ለአንድ ሰው ክብርና ትምክህት ናላቸው ላዞሮባቸው ኋላቀር የአማራ ልሒቃን ምኞችና ድሎት ሲባል አገርና ህዝብ እንደ የመስዋዕት በግ እየታረዱ ነው። መንገደኛው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በድንገት ወደ ሥልጣን የመጣ ሌላው ቢቀር የእድሜው ልክ ያህል ያልበሰለ ሰው እንደመሆኑ መጠን ቀዳሚና ተከታይ የሌለው ውስጣዊ ፍላጎትና ግብ ዋናውና አንዱ፥ ሰውዬው ትልቁ ሰገጣም ሆኖ ሳለ ዘመናዊ ሰው፣ በተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ የማይገባ ስም የያዘና የተሸከመ ሰው ሆኖ ሳለ አዋቂና የተማረ ሰው፣ ለመብሰል ገና የሁለት አህያ ጭነት የሚቀረው ጥሬ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ሙሴ ተብሎ ለመታወቅና ለመታየት ካለው ተራ የመንደር አተሳሰብ ያልተላቀቀ ሰው የሚያስከትለው ጉዳትና ኪሳራ የሚመነጭ ችግር ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ብቸኛ የኢትዮጵያ አዳኝ ተብሎ መታወቅና መጠራት ይፈልጋል፤ በአገሪቱ የሚሰራ ማንኛውም መልካም ስራ ሁሉ የእኔ ሃሳብ ነው ማለት ይፈልጋል፤ የአትክልተኛና የሹፌር ስራ መስራት ይፈልጋት፤ ህግና ስርዓት እኔ ነኝ ብሎ ያምናል፤ የኢትዮጵያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ሚድያዎች ሁሉ አለማቋረጥ የሚሰጡት ክብር ስምና ዝና አንሶት ህዝቦች በስሜ ታቦት ቀርጸው ለክብሬ ሊሰግዱ ይገባል የኢትዮጵያ ህዝብ ሊፈራኝ ይገባል ብሎም ይናገራል፥ ይህ ዓይነቱ ጋጠ ወጥ ሰው ወደ ስልጣን ሲመጣ ታድያ ሀገር በመቆርቆርና በመገንባትና የላቀ ታሪክና ተሞክሮ ያለው በህግና በስርዓት የሚያምን የትግራይ ህዝብ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ባበጃጀው ቦቴ አልፈስም በማለቱ ታህሳስ 4 ቀን 2020 ዓ/ም ሰውየው ከሱዳን ጋር በመምከር የኤርትራና የሶማሊያ ሰራዊት በመሸመት የኢምሬት ድሮንም በማሳተፍ ወረራ የፈጸመበት። ትግራዋይ ተብሎ ስሙ ሲጠራ ሲሰሙ ብርክ የሚይዛቸው የአማራ ልሒቃንም የዚህ ሁሉ ሰይጣዊ አጀንዳ አሳላጮች በመሆን በንጹሐን የትግራይ ተወላጆች ደም ተጨማልቋል። እንግዲህ፥ እነዚህ ሁለት የዘመናችን ሰገጣሞች የማይገባቸው ክብር ፍለጋ ያነደዱት እሳት ተመለሶ እነሱን በሚበላበት በዚህ ወቅት ታዲያ ሰዎቹ ልክ ቀደም ሲል በምሳሌነት የተመለከትነው ክፉኛ የቁማር ሲስ የጸናበት ሰው እንዲሁ ውሃ የበላው የቀድሞ ህልማቸው (ትግራይን ከካርታ የመፋቅና የትግራይ ህዝብ ስመ ዝክር የመደመሰስ ህልም) ተግባራዊ ለማድረግ በየዕለቱ እያደረጉት ያለና እየሸመቱት ያለ የመሳሪያ ዓይነት አገሪቱ በታሪኳ አይታው የማታወቀው የኢኮኖሚና ድቀትና ማህበራዊ ቀውስ እየከተቷት ይገኛሉ። ርሃብን እንደ የጦር መሳሪያ በመጠቀም እየቀሰፈው ያለ የትግራይ ህዝብ ይቅርና በአሁን ሰዓት ማኸል አዲስ አበባ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ የኑሮ ውድነት እየቆላው ያለ ህዝብ እንደ አሸን መፍጠርና መፈልፈል አገር ወዳድ መሪ የሚያስብል ከሆነ ቀልዱ ለኢትዮጵያውያን ትቸዋለሁ።

 

የቻይና ጩኸት እውነትም ከፍየሏ በላይ ነው

 

አሜሪካ በዐቢይ አህመድ ዓሊ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለመጣል እያኮበኮበት ባለችበት በዚህ ሰዓት ቻይና ከዚህ ቀደም ለወራት ስትዘፍነው የነበረ ዘፈን ይዛ መጥታ የኢትዮጵያ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ ነው እያለች የምትነጫነጭበትና የምትጮሁበት ያለ ምክንያት የቻይና መንግስት ስለ ኢትዮጵያውን ሰላምና ደህንነት ተጨንቆና ተጠቦ ሳይሆን የቻይና መንግስት ኢትዮጵያ ከነ ግድፈቷ በዓለም መድረክ እንደ አገር ተከብራ ትጠራበት በነበረችበት ዘመን አተርፋለሁ ሲል በኢትዮጵያ ላይ ያፈሰሰው ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ ዓይኑ እያለ እንደ ጨው ሲሟሟ እየታየው ስለሆነ ነው። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ልታደርገው እያሰበችው ያለ ማዕቀብ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሚያብረከርክ ቅጣት ብቻ ሳይሆን የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ያለው ኢንቨስትመን ሳይቀር በነፋስ ፊት እንደ ተቀመጠ እምቅ ድራሹን የሚያጠፋ አውሎ ነፈስ እንደ ሆነ ስለገባቸውና ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እንደሚያስከትልባቸው ስለተረዱ ነው። ለቅሶው ከፍየሏ በላይ ነው ያለ ማን ነበር?

 

የቻይና ጩኸት እውነትም ከፍየሏዋ በላይ ነው። ቻይና እየጮኸች ያለችው የዐቢይ አህመድ ዓሊ አጋር ወይም ደጋፊ ስለሆነች፣ የእመቤቴ የአስራት አገር እንዳትነካብኝ በማለት አንድም ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ ማለትዋ ሳይሆን ጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሳይቸግረው የማይነካ ነካክቶ በራሱና በአገሪቱ በአጠቃላይ ጥቅም ባላቸው ርዕሰ ኃያላን ላይ ያስነሳው ዓውሎ ነፍስ ቻይና ሀብት ሳይቀር ፉት አድርጎ የሚበላ በመሆኑ ነው። አሜሪካ አደርገዋለሁ እያለችው ያለ ማዕቀብ ተግባራዊ ያደረገችው እንደሆነ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ዙምባቤ ከዚያም በከፋ መቀመቅ ውስጥ ስለሚከታትና ቻይና ኢህአዴግን ተማምና በአገሪቱ ላይ ያፈሰሰችው 13.7 ቢልዮን ዶላር እንደ ጤዛ መብነኑ ስለማይቀርለት ቻይና እየሆነችው ያለ ለመሆን ተገዳለች። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉሃል እንግዲህ ይህ ነው! በልኩ መኖር ለተሳነውና ላቃተው ሰገጣም መሪ ልኩን እንዲያውቅ ማድረጋቸው ሲሆን፤ ጎን ለጎን ደግሞ ቻይናን ከአከባቢው ከጨዋታ ውጭ የሚያደርግ ሰይፍ ነው። ቻይናውያን ታድያ የዋዞች አይደሉም፥ ነገሩ ገፍቶ መምጣቱ የማይቀርለት መሆኑን ከተረዱ ከአሜሪካ ጋር ቁጭ ብለው ለመመካከርና ለመወያየት አያቅማሙም፤ አሜሪካም ጥቅምዋን ለማስጠበቅ ከቻይና ጋር በመስማማት ከጨዋታ ውጭ መሆን ያለበትና የሚገባው ሰው ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ አይቦዙኑም። አሜሪካ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ኩታራ ጋር ሰጣ ገባ የመግጠምና ፊት የመስጠት ባህል የላትም።

 

ሌላው ራሽያ ናት። የራሽያ መንግስት የክፉ ደላላ ምሳሌ ነው። ክፉ ደላላ እንጀራው የሚጋግርና የሚያበስል የቸገረው ሰው በማነፍነው እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። ክፉ ደላላ፥ ሰው ቸግሮት ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ የሚያዝንና የሚራራ ዓይነት ሰው ሳይሆን የሰው ችግር እንደ መሰላል የሚጠቀም አውሬ ፍጥረት ነው። አንድ ሰው ቸግሮት ሰዓቱን አውጥቶ ሲሸጥለት፥ የለበስካት ጃኬት ጥሩ ኮንድሽን ላይ ያለች ጃኬት ናት ብትሸጣት እንደውም ከሰዓቱ የተሻለ ዋጋ ታወጣለች ብሎ ጃኬት አውልቆ የሚወሰድ፤ ችግረኛው እሺ ብሎ ጃኬቱን ሲሰጥ ደግሞ እቤትህ ሌላ ቅያሬ ጫማ ካለህ ይህ የረገጥከው ጫማ ራሱ አፍ ቢኖረው ጮክ ብሎ የሚያወራ ሙድ ያለው ጫማ ነው እንደውም እዚህ እያለህ ልንገርህ ይህን ያህል ብር ልስጥህ በማለት ጫማ አውልቆ የሚወስድ፤ ከመንገድ ተነስቶ ይህን ያንንም እያለ ግዷ ድረስ ዘልቆ የሚገባ፣ ችግረኛውን የሚያራቁትና ባዶ የሚያስቀር ወመኔ ነው። ፕሬዝዳንት ፑቲንና አገራቸው ራሽያ የኢትዮጵያ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ ነው እያሉ ከመጋረጃ በስተጀርባ በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ላይ እየሰሩት ያለ ስራ እንዲሁ በተመሳሳይ የክፉ ደላላ ስራ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት በየትኛውም ዓለም በየትኛውም መድረክ ከወያነ ዱላ አትርፉኝ እንጅ ያሻችሁትን ውሰዱ፣ ጠይቁኝ ልፈርምላች፥ በማለት በጉልበቱ ወድቆ በልመና የሚያስፈጽመው ጉዳይ እንጅ እንደ አገርና እንደ መንግስት በእጁ ላይ ካርታ ይዞ የመጫወትና የመደራደር ስልጣን ያለው መንግስት አይደለም። ሲያምረው ይቀራል!

 

እንደነ ኢራን፣ ቱርክ፣ ሳውዲ፣ ኳታርና ኢምሬት የመሳሰሉ ከባቢያዊ ተቀናቃኞችና ፈርጣሞች አገራትና መንግስታት በአፍሪካ በዋናነት ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላቸው የጥቅም ፍላጎት የተመለከትን እንደሆነ፥ የተጠቀሱ አገራትና ሌሎች መንግስታት የሚከተሉት ፖሊሲ እንደየ ጎራቸው ከሚዘውሯቸው አንድም ጥብቅ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ቁርኝነት ካሏቸው ርዕሰ ኃያላን አገራትና መንግስታት አጀንዳ ጋር የሚጻረርና የሚቃረን አይደለም ሊሆንም አይችልም። ይህ ማለት ግን እነዚህ አገራትና መንግስታት ጉዳት የማድረስ አቅም የላቸውም ማለት ግን አይደለም። ኤምሬት፥ ኢሳይያስ አፈወርቂና ዐቢይ አህመድ ዓሊን በመደገፍ ዘመናዊ የድሮን መሳሪያ ይዘው በእኛ ላይ በመዝመታቸው ብቻ ያደረስቡን ጉዳት አይተናል። ኢራንና ቱርክ፥ መግነዙን የመፍታት ያህል ዐቢይ አህመድ ዓሊን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በማስታጠቅና ጦሩነቱን በማስቀጠል ረገድ እየሰሩት ያለ አውዳሚ ስራ እየተመለከትን ነው። ኢምሬትም ቱርኩም ቢሆኑም ግን የሰሩትና እየሰሩት ያለ አጥፊ ስራ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ሚያስቡና ስለ ሚጨነቁ ሳይሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንት ስም እያፈናቀለ የሰጣቸውና እየሰጣቸው ያለ ለም መሬት ለመጠበቅና የምግብና የንግድ ዋስትናቸው ለማረጋገጥ እየሰሩት ያለ ስራ ነው። ኢራን በተመሳሳይ በአፍሪካ ቀንድ የሳውዲዎች ተጽዕኖ ለማመናመንና ለማኮላሸት፤ ቀጥሎም፥ የኢራን መንግስት ጸረ እስራኤል መንግስትና ህዝብ በሚያደርጋቸው ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎችና ዓላማውንና ተልዕኮውን ለማስፈጸምው በሚሰራቸው ሴራዎች ኢትዮጵያ እንደ አጋር መጠቀሚያ የማድረግ ዝንባሌ ስላላት ነው።

 

በተረፈ፥ ኢትዮጵያ ታቦት ስለሆነች ሳይሆን እንደ ማንኛውም የፖለቲካና ማህበራዊ ውጤት የሆነች አገር እንደመሆኗ መትረፍ ካላባትና ከተረፈች ዛሬም የሚያተርፋትና የሚታደጋት በሰው አገር ሰራዊት ሳይቀር የተጨፈጨፈ ትግራዋይ ነው። የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በሌላ በማንም እጅ ሳይሆን የህልውናው ያህል የላቀ የጀግንነትና የስልጣኔ ታሪክና ባህል ያለው በትግራዋይ እጅ ነው። ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ተቀብላ የመለሰች እንደሆነ ትተርፋለች ካልሆነ ደግሞ ሶቬት ህብረትና ዩጎዝላቪያን ትቀላቀላለች። ይህ የሚሆንበት ምክንያትም በዋናነት የትግራይ ህዝብ ጥያቄ የመላ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጥያቄ ስለሆነ ነው።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page