Back to Front Page

ለምን ኢትዮዺያ፣የትግራይን ህዝብ ማጥፋት ፈለገች ? ክፍል ፩

ለምን ኢትዮዺያ፣የትግራይን ህዝብ ማጥፋት ፈለገች ? ክፍል

 

ሙሉጌታ በሪሁን 05-12-21

 

ኢትዮዺያዊነት እንደየ አረዳዳችንና ፍላጎታችን፡ልንገልጸው የምንችል የዜግነት መለያችን ሲሆን፡ ከእግዚአብሄር የተሰጠ የማይደፈር የማይገሰስ ማንነት ነው የሚል ካለ፣ ችግሩ እዛ ላይ መሆኑን እንወቅ። እንደው እስኪ ራሳችን እንጠይቅና እንዴት? ከየት ? መቼ ? መጣን ወይንም ይህ ኢትዮዺያ የሚለው መጠርያስ ለማንና ? በነማን ? ተሰጠን የሚለውንም እንጠይቅ። እርግጥ ነው ኢትዮዺያ ረዘም ያለ ታሪክና፣ አኲሪ ታሪክ አላት ይባላል። የዚህ አባባል ሚስጢሩ ደግሞ፣ታሪክ እንዳበጁት ይበጃልበሚለው ምናባዊ አባባል ሳይሆን፣ መሬት ላይ ባሉ ተጨባጭ ማስረጃዎች እያመሳከርን ማቅረብ ስንችል፣ተቀባይነትና፡ተአማኒነትን እናገኛለን።

 

ካልሆነ (ውሸት ሲደጋገም፣እውነት ይሆናል) በሚለው መሰረተ ቢስ ትርክት መቀጠል አይቻልም። ለምሳሌ የአክሱም ሃወልት 3 ዘመናት በላይ ያስቆጠረ ትናንት የነበረ፣ ዛሬም ያለ ታሪካዊ ቅርሳችን ሲሆን፣ የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያኖች 12ኛው ክፍለ ዘመን፣ በንጉስ ላሊበላ የተሰሩ ታሪካዊ የኢትዮዺያ ቅርሶች ናቸው። ከዚህ በመነሳት እንዴት ? ወዴት ? የሚልን ጥያቄ ለመመለስ በአይን የሚታየውን ጭብጥ ማስረጃ መሰረት በማድረግ፣ ላሊበላ ከአክሱም ስልጣኔ በኃላ 1200ኛው /ዘመን የተሰራ፣ የአክሱም ስልጣኔ ተቀጥላ ስለሆነ፣የአክሱምን ስልጣኔ ገሸሽ እያደረጉ፣ስለ ላሊበላ መደስኮር ግብዝነትን ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮዺያዊነት ጭምብል የሚደረገው ደባን በግልጽ የሚያሳይ የተዛባ ትርክት ማሳያም ጭምር ነው። ከመቼ እስከ መቼ ? በነማን ? የተሰራ የሚለውንም ከአንዳንድ የታሪክ መፃህፍትና፣ ሰነዳዊ ጭብጦችን፣ ማቅረብና ማገናዘብንም ይጠቅማል።

 

የኢትዮዺያ ታሪክ በተለይ፡ እነዚህ አንድ ህዝብ፣ አንድ ቋንቋና፣ አንድ ሃይማኖት እየሰበኩ በራሳቸው ፍላጎት፣ 700መቶ አመት በላይ በሃይማኖት ብረዛ የተጀመረ ሲሆን፣ ከንጉስ ዘርአ ያእቆብ ጊዜ ጀምሮ በሃይማኖት ሽፋን ወደ ግልፅ የሆነ ጉልበተኝነትና፣ እንዴት እንናቃለን ?ተደፈርን የሚል የግብዞች አስተሳሰብ እየተስፋፋ በመምጣቱ፣እንዲሁም ካለ መታደል ይመስለኛል፣ያለፉት የኢትዮዺያ ደራሲያን፣ከያንያንና፣ሃያሲያን የሚጽፉዋቸው ታሪኮችና ድርሰቶች ይዘታቸው ያሉትን የገዢ መደብ አባላት ታሪክና ስብእና እየቀባቡ ለነሱ የሚያሞካሹ ተደረገው የተፃፉ፣ የአድር ባይነት ገፅታና ይዞታ የተላበሱ ስለሆኑ፣የሃገሪቱን እውነተኛ ታሪክ ማሳየት አልቻሉም። ለዚህም ነው ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል, አይነት የተዛባ ታሪክ ይዘን አሁን ለምንገኝበት የውድቀትና፣የዝቅጠት ደረጃ የደረስነ ብዬ አምናለሁኝ።  ግፉ የተጀመረው ከነ ደቂቀ እስጢፋኖስና፣ በራሱ በአባ እስጢፋኖስ፣ ሲሆን ለምን ? ለንጉስ ዘርአ ያእቆብ አትሰግዱም ? ለምንስ አንገታቹህ አትደፉም ? ለመሆኑ እናንተ ማን ስለሆናቹህ ነው? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፣ በሰጡት ሃይማኖታዊ ምላሽ፣ ንጉስ ሆይ እኛ ላንተ እንፀልይልሃለን። ለአምላካችን ደግሞ እንሰግዳለን፤ በሚል የሞራል ልዕልናና፣ ለእምነት መኖርን እስከ መስዋእት የሚያስከፍል አቋማቸው በማሳየታቸው፣ በፍርደ ገምድሉ ንጉስ ሂወታቸውን ያጡት። እዚህ ላይ ታሪክ ስለሆነ የንጉስ ዘርአ ያቆብ ድርጊትና፣የካህናቱ የአቋም ጽናትን ታሪካዊ ይዘት ትግራዋይነት ይባላል። ንጉስ ዘርአያእቆብ፣ አባ እስጢፋኖስን ለምን አንተ እያልክ ትጠራኛለህ ? ብሎ ሲጠይቀው፣ እንኳን አንተን፣ ለአምላካችንምኮ አምላካችን፣ በደላችንን ይቅር በለን፣ከክፉ ስነምግባር ጠብቀን፣ እያልን ነው ፈጣሪያችንን የምንለምነው፣ አንተ ነው የምንለው። ቅር ሊልህ አይገባም ነበር ያለው። አባ እስጢፋኖስ የተወለደው፣በትግራይ፣ ተምቤን ውስጥ ሲሆን፣ 3 ግዜ በንጉስ ዘርአያቆብ ተከሶ፣ በመጨረሻ እሱና ተከታዮቹ ለንጉሱ አያጎነብሱም፣ አይሰግዱም፣ ተብለው ለእስር የተዳረጉ ናቸው።ከዛም አባ ዘርአያቆብ፣ በታሰረ 7ወር በኃላ ሂወቱ አልፏል። እዚህ ላይ ውድ አንባቢያን፣አላማና ፅናት፣ ስለ ተመኘከው የምታገኘው ሳይሆን፣ ማንነት ነው። አምባሳደር ስዩም መስፍን፣ ተጋዳላይ አባይ ጽሃየ፣ ተጋዳላይ አስመላሽ /ስላሴ(አባ ነብሶ) ተጋዳላይ ጌታቸው ሴኮቱሬን፣ አንምበረከክም፣ መስዋእት ከሆነም ለህዝባችን የሚከፈል የክብር መስዋእትነት ስለሆነ እንቀበለዋለን። ለማናምንበት አላማ ከመሰለፍ፣የክብር መስዋእትነት ለመቀበል ዝግጁ ነን በማለት፣ የክብር መስዋእት ከፍለው አልፏል። ይህ ትግራዋይነት ይባላል።

Videos From Around The World

 

የኢትዮዺያ ታሪክ በግርድፋ ለመነካካት ያህል ጠቃቅሼ ወደ ዋናው የዛሬ ነጥቤ ለማለፍ ያክል በተለይ የአማራው የበላይነት ለማስፈን በተደረገው የሸፍጥ ሂደት፣ ብዙ የሰው ሂወት፣ብዙ የአገር ሃብት፣ወደር የሌለው ኃላ ቀርነት፣እንዲሁም መድረስ ይገባን ከነበረው ከፍታ ሳንደርስ፣ የኃሊት ጉዞ በመጏዝ፣ የጎንደር ዘመነ መንግስት የነፋሲለ ደስ፣ የኢትዮዺያ መበታተን የዘመነ መሳፍንት፣ከዛም በኃላ የኢትዮዺያ ሃገረ ምስረታ የነ አጼ ቴዎድሮስና፣ የአጼ ዮውሃንስን ጊዜ ተሻግረን፣አረመኔውን የንጉስ ሚኒሊክ ዘመን ደረስን፣ ኢትዮዺያም በየ ጊዜው የውጭና የውስጥ ጠላቶች አንዳንዴ ተመሳጥረው፣አንዳንዴ እየተፈራረቁ ፣በአለም የጊነስ ሬከርድየድህነትና የችጋርተምሳሌት ሆና እንድትታወቅ የአማራ ልሂቃን፣ ሃይማኖተኞች፣ ሙሁራን መሰል ማሃይሞች ሲጫወቱባት እስከ ደርግ ዘመነ መንግስት ደረስን። እዚህ ላይ ከታሪክ በጭልፋ ለመጥቀስ ያህል፣በርግጥ የኢትዮዺያ ቅርፅ በዘመነ ሚሊሊክ አሁን የያዘችውን ቅርፅ ባይኖራትም፣እንደ ሃገር ወዳድ ዜጋ፣አንዱንና ዋናውን ሸጠህና አከራይተህ፣ሌላውን መጠቅለል ግራ ያጋባል። ለምሳሌ ወላይታዎች ንጉሳቸው ንጉስ ጦናበሚሊሊክ ተማርኮ ግዛቱንና ስልጣኑ ሲነጠቅ፣ ኤርትራ ባለ ባህርዋ ለጣልያን ስትሸጥ፣ ጅቡቲ ደግሞ ለ፩፻ አመት ለፈረንሳይ በኪራይ ተሰጥታለች። የኢትዮዺያ ህልውና በተለይ የትግራይን ሕዝብ ደግሞ፣ ክፋይ አብራኩ የሆነው ወንድሙን የኤርትራ ሕዝብ በያኔው አጠራር(ባህረ፣ነጋሽ) ለባዕድ ተሰጠበት ለምን ? ቢባል፣በወቅቱ የነበረው የጣልያን የጦር አዛዥ ለሚሊሊክ ያለው፣ አንተ ግዛትህ ወደ ደቡብ አስፋፋ፣ ባህር ቢኖርህ፣ ባይኖርህ መጀመርያ ተጠቃሚዎቹ ተጋሩ እንጂ አንተ አይደለህም። ባህር ለተጋሩ መስጠት ማለት፣ በስልጣኔ አንተን ጥለውህ እንዲሄዱ እድል መስጠት ማለት ነው። ስለዚህ ከመረብ ምላሽ ያለውን ትግራዋይና፣ ከመረብ ወዲያ ያለውን ትግራዋይ ረግጦ ለመግዛት፣ ያለው አንድ አማራጭ ከፋፍሎ መግዛት ብቻ ነው። ይህን መንገድ ተግባራዊ ካደረክ ያንተን ስልጣንና ግዛት እያስፋፋህ ሃይልህን ማደራጀት ትችላለህ፣ኢትዮዺያንም አንተ በምትፈልጋት መንገድ መቅረጽ ትችላለህ የሚል ምክር ተሰጠው፣ሚሊሊክም ወዲያውኑ መሬት ላይ ተገበረው ።ግዛቱም አሰፋ፣ኦሮሞ፣ሶማሌ፣ጋምቤላ፣ወላይታ ወዘተ የመሳሰሉትን ግዛታዊ ይዞታውን አስፋፋ።በዛን ጊዜ ሚሊሊክ ከሱዳን ጋርም 1902/ ውል ተፈራርሞ ሲያበቃ ፣አሁኑ 2021 ሱዳን መሬቴ ነው ብላ ወራ የያዘችው።እና ሱዳንና ኢትዮዺያ ተፋጠው ይገኛሉ።

 

ሚሊሊክም እንደተባለውም አደረገው፣ አማራይቱ የሚሊሊክ ኢትዮዺያም ትግራይን እስከ 1983/ ቀጥቅጦና ረግጦ አንድ አገር፣ አንድ ሕዝብ፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት በማለት፣ የኢትዮዺያ ገበሬ ጥሩ ትምህርት፣ ህክምና ሳይኖረው፣ እነ ንጉስ ሃይለስላሴ፣ በቤተመንግስታቸው፣ የወርቅ ማንኪያ፣ የወርቅ ስሃንና፣ 200 በላይ ቅንጡ የቤት መኪኖች፣ የግል የባቡር ፍርጎ፣ እየተቀናጡ ረግጠው ገዝተዉታል።

 

የወሎ፣የትግራይና፣ የአፋር ህዝብ, 1966,67 “በወሎ ድርቅየሚታወቀው የርሃብ ቸነፈር,ተከስቶ ህዝቡ ሲረግፍ ነበር፣ንጉስ ሃይለ ስላሴ ግን በህዝብ ሃብት ያላግጡ እንደነበር፣ አብይ አህመድ ለኢትዮዺያ ህዝብ በቴሌቭዥን አሳይቶናል። ላለፉት 25 አመታት የትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ኢትዮዺያን አፈራርሰው በሌላ

መንገድ ሊሰሯት የፈለጉበትን ዋና መንገድና፣ የሃገሪቱ ገጽታ ግምባታ ምን መምሰል አለበት? ለሚለው ጥያቄ፣ ለሃገሪቱ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን ይችላል በማለት በህ... የፖለቲካ መሪነት፣ኢትዮዺያ የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች አገር እንደመሆኗ መጠን፣ ለሃገሪቱ ችግር መፍትሄ ያሉትን ሕገ መንግስት በማርቀቅ ፣፣ሃገሪቱን ከምትታወቅበት የርሃብተኝነትየጊነስሪከርድ መዝገበ ቃላት በማላቀቅ፣ ከአፍሪቃ ቀዳሚ፣ በአለም ከህንድ ቀጥላ እስከ ማደግ የደረሰችን ሃገር ገምብተዋል፣ መርተዋል፣ ለኢትዮዺያ ሕዝብ የሰላም፣ የእድገት የጉዞ ፋና ጀምረው በተግባር አሳይተዋል።

 

ያም ሆኖ እስከነ ስህተታቸውና ድክመቶቻቸው በሚዛናዊነት መፈረድ ሲገባቸው፣የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅእንዲሉ፣ጭራሽ በውሸትና በፈጠራ ውንጀላ ለዘመናት አባቶቻቸው፣ አያቶቻቸው ከፈፀሙት ክህደትና ሸፍጥ በላይ፣በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በሃይማኖት፣ በመሬት ይዞታ ፣በቅርስ ሌብነት፣በታሪክ ብረዛ እነሱ ባገኙት ስልጣንና፣ በተቆጣጠሩት ሚዲያ ዘመቻው አጠናክረው ተያይዘዉታል። ። ኢትዮዺያ በሰላም፣ በኢኮኖሚና፣ በዲፕሎማሲ፣ ለጥቃም በወታደራዊ አቅሟ፣

ከአፍሪካ 4ተኝነት እስከ 2018 ተከብራና ታፍራ እንድትሄድ ከማድረግ ባሻገር፣ የምስራቅ አፍሪቃ አገራትን አስተባብራኢጋድንበመመስረት የመሪነት ሚናዋም ተወጥታለች። እንደው እደዛሬ አያድርገውና። ሌላውየብሉናይል” 10 አገራትን መርታና አደራጅታ ካጠናቀቀች በኃላም የማይደፈረውን የኢትዮዺያዊያኖች የዘመናት ህልም፣ እውን እንዲሆን በክቡር/ መለስ ዜናዊየመሪነት ብቃትና፣ ቆራጥ ብልህ አመራር፣ የአባይን ግድብ ጀምራ ... ስልጣኑን በሰላም እስካስረከበበት ጊዜ 68% ገምብታለች። እዚህ ላይ አማራ፣ ወያኔ ተባረረ ብለው፣ እነሱ እንዳባረሩት ለመዘላበድም ይዳዳቸዋል፣ባንክና ታንክየያዘን ሰራዊት በባዶ ቂጥህ ልታባርረው አትችልም። በፍላጎታቸው እነሱ ...ቶቹ በመሰረቱት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ተገዝተው አስረክበዋል፣ ኢትዮዺያ ውስጥ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽጝግር ተደረገዋል። ሃቁ ይሄው ነው። እርግጥ ነው በተጋሩና፣በአማራ በሚደረገው የስልጣንና፣ የበላይነት ፍቲጊያ ሃገሪቱ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገረች ስለሆነች፣ በበኩሌ መባል ያለበትን ሁሉ፣ ታሪክና ጭብጥን መሰረት አድርጌ ለማቅረብ እሞክራለሁኝ። ከዛ በፊት ግን የኢትዮዺያ ችግር በተለይ ደግሞ የሁለት ተቃራኒ ማንነቶች ችግር ነው ብዬ ስለማምን፣ እነዚህን ሁለት ማንነቶች ትግራዋይነትና፣አማራነት ልዩነታቸውና ታሪካዊ እውነታው፣ ከሌሎች የታሪክ ተመራማሪዎች ያቀረቡትን ጥናት ላቅርብ።

የትግራይ ሕዝብ ማን ነውለሚለው ጥያቄ እስኪ ምንም የዘር፣የሃይማኖት፣ቁርኝነት የሌላቸው የታሪክ ተመራማሪዎች ከሚያቀርቡት ጥናታዊ ምርምር ከፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ጋር የተደረጉ ሰነዳዊ ማስረጃ እያጣቀስኩኝ ላቅርብ ታሪክ ምንድን ነው? በሚለው ልጀምር፤ ፕሮፌሰር፦ በእውነት ለአክብሮታቹ ኦጅግ አመሰግናለው፤….ታሪክ ማለት ከብዙ ዘመናት በፊት እስከ አሁኗ ሰከንድ ድረስ የተከናወኑና፣ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ስራዎችን ከእውነተኛ መረጃ በመነሳት ስለ አንድ ሀገር ህዝብና መንግስት፣ የስራ የባህል፣የቋንቋ ፣የወግና ስርዓት የመሳሰሉትን የምናጠናበትና የምንማርበት መሳርያ ነው። በጠቅላላ ታሪክ እውነትን መፈለግ ማለት ነው።

 

ይላሉ ጠያቂ መልካም፤ አጠር ባለ መልኩ ዛሬ የምንነጋረው በኢትዮጲያ ህዝቦች ዙርያ ይሆናል፣ ከሰሜን ልጀመርና ትግሬዎች ማናቸው፤ ከየትስ መጡ፣ ምንስ ለዚች ሀገር አበረከቱ?

ፐሮፌሰር እሺምን መሰለህ በመጀመሪያ ለትግራይ ህዝብ ልዩ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለው፣ ኢትዮጲያን የታሪክ ማማ ላይ እንድትቀመጥ ያስቻለ እኮ ይሄ ታላቅ ህዝብ ነው፡፡ ከጥንቱ የኢትዮጲያን ግድግዳ ያቆመ፣ ጣራውን ያጸና፣ የራስዋ ትውፊት እና ባህል እንዲኖራት ያረገ፤ ሀገራችን የዘመናት ዑደት ስፍር ቀምራ የራሷን ፊደል ቀርጻ፣ ቁጥር መቁጠሪያ አኀዝ ይዛ፣ በነጻነት ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ያደላደለ ህዝብ፣ አስደናቂ ጠቢባን ነገስታት እና ተወዳዳሪ የሌላቸው እልፍ አእላፍ ጀግኖች ማፍለቂያ፣ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን፣ ዘጠኙ ቅዱሳንን እና እስልምና ሀይማኖት በክብር ተቀብሎ በስነስርአት ያስተናገደና ያኖረ ህዝብ ነው። ስንቱን ልንገርህ የኩራታችን ምንጭ፣ መነሻን ነው ብልህ ምንም ክፋት አይኖረውም፡፡ ለዚህም ነው ልጄን በራስ አሉላ ስም የሰየምኩት። ልጄ አሉላ ፓንክረስት (alula Pankhurst) ይባላል፡፡ ይሄ ህዝብ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው፡ ሀገሩን የሚወድ፣ እጅግ ሃይለኛ ጦርነት ገጥሞ የማያፈገፍግ ምርጥ ተዋጊ፣ ቸር ተባባሪ እና እንግዳ አክባሪ ነው። የትግራይ ሕዝብ ከዓድዋ ጦርነት በፊት የአውሮፓ ወራሪዎችን ድባቅ መትቶ ያባረረና ያሸነፈ ነው።

 

ለምሳሌ ከአድዋ ጦርነት በፊት የትግራይ ሕዝብ ብቻውን ኢጣሊያን፡ ቱርክን ግብጽን ለሶስት ጊዜ ያህል፡ የግብጽ፡የአሜሪካና የእንግሊዝ የተቀናጀ ጦርን፡... በጉራዕ ፣በጉንደት፣ በኩፊት ፣ በሰሐጢ ፡ በዶግዓሊ፣ በተድዓሊ፡ በምጽዋ ላይ አሸንፏል። ይህም በተለያዩ የኢትዮጵያና የውጭ የታሪክ ሙሁራን ተጽፏል። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ ወይም ሆን ብለው የነጭ ወራሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈው በዓድዋ ላይ እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል ይህ ግን ስህተት ነው።

 

እንደሚታወቀው በዓድዋ ጦርነት ወቅት ከፍተኛውን ተጋድሎ የፈጸመው የትግራይ ሕዝብ ቢሆንም የሌሎች ብሔረሰቦች ተሳትፎም ነበር። የትግራይ ሕዝብ በወቅቱ የጣሊያንን ጦር ጠንክሮ ባይመክተውና ባያስቆመው ኖሮ የኢትዮጵያ ሰራዊት ያን ሁሉ ኪሎ ሜትር በኋላ ቀር መጓጓዣ ተጉዞ ዓድዋ እስኪደርስ ድረስ ጣሊያን መላዋን ኢትዮጵያ ይቆጣጠራት ነበር። ጠያቂ የመጀመርያ ትግሬዎች መኖረያቸው የት ነበር? ፐሮፌሰር፦ ትግራውያን የኢትዮጵያያ ጥንተ ነዋሪዎች ከሚባሉት ውስጥ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ዋናው ቁም ነገር ቀድሞ መኖርያቸው የት ነበር የሚለው ነው። እንግዲህ ታሪኩ እጅግ ረጅምና ውስብስብ ቢሆንም አጠር ባለ መልኩ የነበሩ ዋና ዋና ሁነቶችን ለመናገር እሞክራለው፡፡ እንደሚታወቀው እግዚአቢሔር ሰዎች በሰሩት ሀጥያት የተነሳ፣ ጻድቅ ከሆነው ኖህና ቤተሰቡ ውጪ ዓለምን ሁሉ በጥፋት ውሀ ደመሰሰ፡፡ እግዚአቤሔርም ለኖህና ቤተሰቡ ዳግመኛ ዓለምን በጥፋት ውሀ እንደማያጠፋት በሰማይ ላይ ቀስተ ደመናውን በማኖር ቃል ኪዳን ገባለት። በዚህም መሬት በኖህ ቤተሰቦች ማለትም በነገደ ሴም፣ በነገደ ያፌትና በነገደ ካም ከጥፋት ውሀ ጀምሮ መቶው አመት እስኪ ፈፀም ድረስ ያለ ልክ ቁጥራቸው በዛ። አዲሷ ምድርም እንደገና በሰው ተሞላች፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ወደ መርከብ ከገቡት በቀር የጥፋት ውሀ መጥቶ ሰውንና እንስሳን ሁሉ እንዳጠፋ ይተርኩላቸው ስለ ነበር በጥፋት ውሀ የሆነውን ሁሉ የሚያስታውሱ ወይም ወሬውን የሰሙ ሁሉ የሰው ክፋት ያንኑ የመሰለ ቅጣት እንደገና መልሶ ያመጣብናል እያሉ ይሰጉ ነበር፡፡ ሰዎች በሚሰሩት ሀጥያት የተነሳ እግዚአቢሔር አለምን በድጋሜ በጥፋት ውሀ ያጠፋታልና ከነዚህ ሰዎች መለየት አለብን በማለት እንዲሁም ለእኛ ራሱ ወደ ሰማይ የሚያደርስ ግንብን እንስራ በምደርም ላይ ሳንበታተን ስማችንን እናስጠራ በማለት ()ግሪስኤፍራጢስአካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ራሳቸውን ለመለየት ታላቅ ግንብ ለመስራትተማከሩ፡፡ ከነዚህ ህዝቦች መካከል የትግራውያን ቀደምት ዘሮች ዋነኛ ተሳታፊና ባለቤት ነበሩ፡፡ የሰው ልጅ ታላቅ ስልጣኔና ጽሁፍ የተጀመረውም በነዚህ ወንዞች ኣካባቢ ነው፡፡ ትግራይ-ትግሮት- የሚለው ስምም የዚህ ህዝብ ቀድሞ መኖርያ ከሆነው ጢግሪስ (ቲግሪስ) –tigris-ከሚባለው የስልጣኔ ማእከል ከሆነው ባቢሎን ሞሶፖታሚያ አካባቢ ከሚገኘው ታላቅ ወንዝ ስም የተገኘ ነው ብለው የሚከራከሩ ብዙ የታሪክ ሰዎች አሉ፡፡ ስለ ስሙ በኋላ እመለስበታለው። በእንዲህ ትግራውያን እና ሌሎች አያሌ ነገዶች(ህዝቦች) በህብረት ታላቁን የባብል ሰናኦር ግንብ በኢፍራጠስ ወንዝ ዳርቻ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ሲገነቡ ቋንቋቸው 2247 .. ስለተደበላለቀ ወደ ተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ተበታተኑ፡፡

 

 ትግራውንም አንጸባራቂ የሆነውን ስለጣኔያቸውን እና የጽሁፍ ጥበባቸውን ይዘው በ2000 ዓመተ ዓለም አካባቢ በሰሜን(ላይኛው) ቀይ ባህር በኩል አርገው በመሻገር ወደ አፍሪካ ምድር በመግባት ወደ ግብጽ(ምስር) አመሩ። ከብዙ ዘመናት ጉዞና እልህ አስጨራሽ የማያባራ ጦርነት በኋላ በኃይል የግብጽን በትረ መንግስት በመዳፋቸው ስር በማስገባት፣ በአፍሪካ መሬት የመጀመሪያ መቀመጫቸውን በዚያ ምድር አደረጉ። ሀገሪቷንም ወረሷት። ለብዙ ምእተ አመታትም ግብጽን በብልሃት በጥበብና በማስተዋል መርተዋል። የሚገርመው ነገር ደግሞ ተቀዛቅዞ የነበረውን የፒራሚድ ስራ እንደገና ነፍስ የዘራበት ይሄ ህዝብ ነው። እነዚህ ፒራሚዶች ፍጹም የግንበኝነት ጥበብ እና ልዩ የሂሳብ

ቀመር የሚሹ ናቸው። ትግራውያንም ለዚህ በጣም የሚመጥኑ ነበሩ። እንዴት ብትለኝ ከምስራቅ ይዘውት የመጡት ስልጣኔያቸውን እዛው ከቆያቸው ጥበብ ጋር በማጣመር ቀድሞ ከነበሩት አያሌ ፒራሚዶች የተሻሉ ፒራሚዶችን ማነጽ መቻላቸው ነው። ጠንካራ የአእምሮ እና የጉልበት ሰራተኞችም ናቸው። ብዙ የታሪክ መጻህፍትምየግብጽን ፒራሚዶች የገነቧቸው ኢትዮጵያውን ናቸው ሲሉ ትግራውያንን እየገለጹ መሆኑን መዘንጋት የለብህም።

 

ተጋሩ ፒራሚዶቹን የሰሩት ምትሃት መሰሎቹን አስደናቂ የአክሱም ሓወልቶች ከመትከላቸው ብዙ ዓመታት አስቀድሞ ነው፡፡ ጠያቂ፦ የተከበሩ ፕሮፌሰር እንዴት ትግራውያን አሁን ወደ አሉበት ቦታ ሊመጡ ቻሉ ፕሮፌሰር፦ ትግራዉያን እንደ ሌሎቹ ስርወ መንግስታት የራሳቸውን ፒራሚዶች በግብጽ ምድር ከሰሩ በሁዋላ ሃይላቸውና አንድነታቸው እየላላ መጥቶ በሌሎች ሃይሎች ተጽእኖና ስር ወደቁ በዚህም ግብጽን በመተው መሰደድ ግድ ሆነባቸው። እነሱም ከጠላቶቻቸዉ ጋራ አንገት ለአንገት እየተናነቁ

ጥቂት ጎሳወች ወደ ምድረ እስራኤል አካባቢ፤ አብዛኞቹ ግን የግብጽን ደቡባዊ በረሃ በመሰንጠቅ አሁን ሰሜን ሱዳን፤ ቀይ ባህር ሰሜን ኢትዮጲያ እና ኤርትራ አካባቢ ተሰባስበው መኖር ጀመሩ፡፡.መለያየታቸው ያደረሰባቸውን መአትና ፍዳ በመረዳትም እንደገና ሃይላቸውን በማጠንከር ማንሰራራት ጀመሩ። ለንግድ እና ለተለያዩ ተግባራት በሚያመች መልኩ ወደ ባህሩ በመጠጋት የደአማት መንግሥታቸውን መሠረቱ። በመቀጠልም የአክሱም መንግስትን መሠረቱ። የግዛት ወሰናቸውም እጅግ

ሰፊ የሆነ ሲሆን ከሰሜን ቀይ ባሕር እስከ በናዲር (የአሁኑ ሞቃዲሾ ) የእነሱ ግዛት እንደነበር የታወቀ ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን የዛን ጊዜ ኢትዮጲያ ድንበሯ በሰሜን እስከ ግብጽና ሊቢያ ፤ በምዕራብ እስከ ቻድና ምዕራባዊ አፍሪካ በደቡብ እስከ ዩጋነዳ ነጭ ኣባይ በምስራቅ እስከ ሰሜን የመን ፤ ሲናሞሞፎሩስ ህንድ ውቅያኖስ መዳረሻ ድረስ የተለጠጠ ነበር፡፡

 

የተጋሩ ጎሳዎች እርስ በእርሳቸው እየተባበሩ አንድ እንድ ጊዜም እየተለያዩ ብቻ ለብቻ እስከ አምስት የሚደርሱ ንገስታት ነበሯቸው። ነገስታቱም መዲናቸውን አሁን ሱዳን ውስጥ በሚገኘው መርዌ እና ትግራይ ውስጥ በምትገኘው አክሱም እየተመላለሱ ሰፊውን ግዛት ያስተዳድሩ ነበር። የታሪክ መጻህፈት እንዲህ ይላሉ አክሱምንም ከሠሩ በኋላ መርዌንም ሠሩ።…..ያን ሰፊ ግዛት በጥሩ ሁኔታ ለማስተዳደር ሲሉ አንዱ አክሱም ላይ አንዱ መርዌ ሱዳን ላይ ነገሡ። ይህም 1000 ዓም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነበር ። ስለ ታሪኩ ካወሳን ዘንድ፥ ይሄ ዛሬ ሱዳን የተባለው ምድር ሁሉ በዓረቦች ወረራ ስር ከመውደቁ በፊት ቢያንስ 2500 ዓመታት ያህል የተጋሩ ግዛት ነበር። ጥንት የሚታወቀው ኑብያ ተብሎ ነበር። መናገሻውም መርዌ ነበር። የዛሬ 2900 ዓመት ግን ሱዳን ይባል ጀመር። ይህ ስም የወረደው ከአፄ አክሱማይት እናት ከንግሥት ሳዶንያ ነው። እሱ በህፃንነቱ የግብጽ ፈርኦን ሆኖ እስከሚያድግ ድረስ እስዋ በትግራውያን ሰራዊት ጠብቆት ስር ሆና ዙፋኑን እየጠበቀች በሱ ስም ቻድን ፣ግብፅን፣ ሊብያን የዛሬውን ሱዳን ታስተዳድር ነበር። በዚህ ምክንያት፥ ከሳሃራ በርሀ በታች ያለው ምድር በሙላ ሳዶንያ ተባለ። ቀስ በቀስ ተለውጦ ሱዳን ሆነ።

 

እንዲያውም ኑብያ ውስጥ የነበረው መርዌ ለዛ አካባቢ እንደ ዋና መናገሻ ከተማ ሆኖ ያገለግል ነበር። ቢያንስ 14 የኢትዮጵያዊ ትግራውያን ሴቶች ህንደኬ በሚል ማእረግ በንግሥትነት በተከታታይ ዛሬ ሱዳን ግብፅና ሊብያ የሚባሉትን ሃገሮች 1000 ዓመት ያህል ገዝተዋል። ትግራውያንም በዚ ዘመን ብዙ አስገራሚ ተጋድሎዎችን አድርገዋል። ፋርሶችን ደመስሰዋል ግሪኮችንም ድባቅ መትተው ስለ አስደናቂ ተጋደሏቸው ‹‹tigri-ትግሪ›› ነብሮች ተብለው በታላቁ እስክንድር ተሰይመዋል። ትግራዋይ ለሚለው ስምም መነሻው ይህ ነው፡፡

 

ጠያቂ፦ ትግሬ ስለሚለው ስም እዚህ ጋር ላቁሞትና እስኪ ብዙ ሰዎች አክሱም የሚለው ቃል ትርጉሙን አያቁትምና ምን ማለት እንደ ሆነ ይነግሩናል? ፕሮፌሰር፦ ጥሩ ጥያቄ ነው። አክሱም የሃገራችን ስልጣኔ ጫፍ ማሳያ ናት። አንዳንድ ጸኃፊያን አክሱም የሚለው መጠርያ ከአፄ አክሱማይት የመጣ ነው የሚሉ አሉ። የቅርብ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩን ግን ታሪኩ ወዲህ ነው። አክሱም የነገስታት የበአላትና የብሄራዊ ስርአቶች መከወኛ መንበር እንደ መሆኗ መጠን ዘላለምየንግስናና የድግስ ስርዓቶችየሚፈጸሙባት መንደር ነበረችኩስሚመንደር! ኩስሚማለት በትግርኛድግስግብዣታላቅ ግብርማለት ነው! ስለዚህ አኩስም”(አክሱም) ማለት ስርወ-ቃሉኩስሚየሚለው ሲሆንአኩስም(አክሱም) ማለት ደግሞ ደግስግብዣ አድርግግብር አብላማለት ነው። ለምሳሌ :-“መብልብሎአብላ” “ትምህርትብሎአስተምርሲል ኩስሚብሎአኩስምይላል ማለት ነው!-ስለዚህአኩስም”(አክሱም) የቃላት ቅንብር ሳይሆን ከግዕዝ-ትግርኛ ማህጸን ቀጥ ብሎ ወጥቶ ከአንዲት ቃል የተፈጠረ ስያሜ ነው። የአክሱም መሪዎችም ነጋሲ ንጉስ በሚል ይጠሩ ነበር፡፡ንጉሱቹ በዚህ ስም መጠራት የጀመሩት ክርስቶስ ሊወለድ

500 ዓመት ሲቀረው ነው። የትግራይ ስርወ መንግሰት አክሱም ላይ ለብዙ ግዜ መናገሻ ከተማውን አጽንቶ መኖሩ ግልጽ ነው። እክሱምም ለብዙ ግዜ ገናና ህዝብ ሆኖ ቆይቷል::

 

 ጠያቂ፦ ትግሬ የሚለው ቃልስ ከየት መጣ ፕሮፌሰር፦ ስም በቁሙ ከግብር የሚወጣ ቦታነትና አካልነት ህላዌና ህይወት ያለው ማናቸውም ሁሉ በየክፍሉና በየአካሉ በየራስ ቅሉ፣ በየዓይነቱና በየመልኩ በየነገዱ፤በየዘሩና በየዘመዱ ተለይቶ የሚጠራበት የሚታወቅበት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የተጠራባቸው በዙ ስሞች አሉት።

 

እነዚህም፦ ‹‹ሒክሶስ፤ ደብዓ፤ ሐመድ፤ አግዓዚ ፣ሳባ፣ ሐበሻ፤ በደው፣ ነጋዴ፣ ትግሬ›› የሚሉ ቃላት የጥንት ትግራውያን የግል መጠሪያ ስሞችናቸው። ከነዘህም መካከል አንዱ አግዓዚ ሲሆን ትርጉሙም መገዛት የማይወድ ነጻ የሆነ ህዝብ ማለት ነው፡፡ በጥንት ጊዜ የህንድ ንጉስ ራማ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ንጉስ ጲኦሪን ወግቶ አሸንፎ መንግስቱን በመቀማት ህዝቡን በጭቆና ይገዛ ጀመር፡፡ በዚህን ጊዜ የንጉስ ራማን(ብራህማ) ግፍ ያዩት ትግራውያን ሃይላቸውን በማሰባሰብ ራማን በመውጋት ራሳቸውንና ብዙ ሌሎች ነገዶችን ነጻ አውጥተው እንደገና ኢትዮጲያን በአዲስ መልክ መምራት ጀመሩ፡፡ በዚህም የተነሳ አግአዚያን ተባሉ፡፡ አግአዚ ማለት በግዕዝ አግዓዘ ማለት ሲሆን ትርጉሙም ነፃ አወጣ ማለት ነው። አግአዚያን ማለት ደግሞ ነፃ የሚያወጡ፣ መገዛት የማይወዱ አርበኞች ማለት ነው፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ በብዙ ህብረተሰብ ዘንድ የሚታወቀው ትግሬ ወደ ሚለው መጠርያ ስም ስመጣልህ ደግሞ ቅድም እንደነገርኩህ ትግራይ-ትግሮት-ትግራዎት የሚለው ስም የዚህ ህዝብ ቀድሞ መኖርያ ከሆነው ጢግሪስ (ቲግሪስ) –tigris-ከሚባለው የስልጣኔ ማእከል ከሆነው ባቢሎን ሞሶፖታሚያ አካባቢ ከሚገኘው ታላቅ ወንዝ የተገኘ ስም ነው ብለው የሚከራከሩ ብዙ የታሪክ ሰዎች አሉ፡፡ ሌላኛው ትንታኔ ደግሞ ትግሬ ከበርቴ ነጋዴ ማለት ነው የሚሉ ኣንዳንድ የአረብ ጽሁፎች አሉ። ለዚህ መነሻ ምክንያቱ ጥንታዊያን ትግሬዎች ዝሆን እየጋለቡ፤ ግመልና ፈረስ እየጫኑ፤ ውቅያኖሱን ልዩና ምትሃታውያን በሚመስሉ ባለክንፍ መርከቦቻቸው አየሰነጠቁ የሚገበያዩ በባህር እና በየበስ የተወጣላቸው ነጋዴዎች ስለነበሩ ነው። ነገር ግን በሃገራችን ባሉ የግዕዝ ድርሳናት ላይ ትግሬ የሚለው ግስ ስርወ ቃሉ እና አመጣጥ ታሪኩ ግልጽ በሆነ መልኩ ተሰንዶ ተቀምጧል፡፡

 

ታሪኩም‹‹እስክንድር በጥንት ዘመን የአክሱም ባሕረ ነጋሽን ሕዝቦች ሊያስገበር በዘመተበት ወቅት፣ለጀግንነታቸውና ለኣስደናቂ ተጋድሏቸው ኣግዓዝያንንትግሪስእንዳላቸው ያስረዳናል፡፡ በንግስት ኒኮላህ ህንደኬ 3 ጊዜ እንዴት በታላቁ የዓለም ንጉስ ትግሬተብለው እነደተሰየሙ ስታይ በጣም የሚገርም ታሪክ ነው፡፡ የአማልክት ግማሽ ልጅ የሚባለው ሄርኩለስ እንኳን ሊደፍረው አይችልም የተበላውን የግሪክና የመቄዶንያ ንጉስ የነበረውን ታላቁ እስክንድር የአጋዝያንን መብረቃዊ ጥቃት ፍጹም ሊቋቋመው አልቻለም ነበር። በውጊያው የሽንፈት ጽዋውን ሲጎነጭም እንዲህ አለ፦አፍቶ ሰኢነ ትግሪ-ተጋሩ ..!” (ከነዚህ ተወርዋሪ የነብር

-ነብሮች ጋር መዋጋት ከባድ ነው!) “ትግሪ(tigri)=ነብር ; …(በግሪክ) “ተጋሩ=ነብሮች); …(በግሪክ)…..ከዚያ ጊዜ ጀምሮአግአዚያንየነበረው ስማቸው ቀስ በቀስ እየተረሳ ሄዶ ትግራውያንየሚለው ስም ደግሞ ይበልጥ እየገነነ ሄደ….!ይሄ ሁሉ የሆነውም 5160 .ዓ፣ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 340 ዓመት(332 BCE) ወይም የዛሬ 2248 ዓመት ገደማ ነበር። እንግዲህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ትግራውያን የሚለው ስም በይፋ መጠቀም የተጀመረው። ትግሬ የሚለው ሰም 100 ዓመት በፊት የመጣ ሳይሆን ከጥንቱ ከጥዋቱ ጀምሮ የነበረ ነው። ምሳሌ ይሆንሀ ዘንድ መረጃ ላቅርብልህ ፣ ከ650ዓመት በፊት ለሶሎሞናዊው ንጉስ ዓምደ ፅየን በተሰባበረ የአማርኛና ግእዝ ግጥም ላይ ትግሬ የሚለው ስም በደማቁ ተጽፎ ይገኛል፡፡እንዲህም ይላል ‹‹ሓርበኛ ዓምደጽየን መላላሽ የወሰን፣ ወኸ እንደ መሰን መላላሽ የወሰን፤ ከገንዝ ጠጣን ምን ቀረህ በመሰን፣ ከባሌ አሊን ከደውሮ ኄደራን፣ ከአገው አቤት አዠርን፣ ከትግሬ ነገደ ክርስቶስ ይውረድ፤ ከጎጃም ጃን ክምርን ከጋፋት አወላሞን፣ በዳሞት ሞት ለሚን ማን ቀረህ በወሰን፤ ሓርበኛ አምደ ጽዮን መላላሽ የወሰን፡፡››፤፤፤፤፤ልጨምርልሀ 560 ዓመት በፊት ለንጉስ ዘርአያቆብ በቀረበ መወድስ ትግሬ የሚለው ስም እንደገና ታገኘዋለህ፤እንዲህም ይላል ‹‹….የለመደው በግዳይ፤ ዣን ዘርዓያእቆብ በድል ጸሀይ፣ ቀለበው እንደ እንቧይ፤፤ አፈረጸው እንደሎሚ አላዋልቶ ዋጋ ይታይ፣ በትግሬ በነገደ ዘእየወሰ ጋይ፣ ግብጽ የመጻ ፈርዘነይ የከመሩት ድንጋይ፣ ሰማ ዘርአያቆብ እንደይቤይ……፡፡ ፠፠፠፠፠፠፠ ፠፠፠፠፠ ፠፠፠፠፠ አማራስ ማን ነው?.....

 

ጠያቂ፦ እሺ አማራ የሚባለው ህዝብስ ማነው አንድ እውነት ልንገርህ አሁን አማራ ነን የሚሉ ሰዎች ትክክለኛ ስማቸው አማራ ሳይሆን የትግራይ ነገስታት የሰጧቸው ‹‹አምሓራ›› የሚለው ቃል ነው፡፡ ኣማራ አንድ ነጠላ ነገድ ሳይሆን በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ፤ ከተለያዩ ጎሳዎች፤ ነገዶች፤ ዘሮች፤ ቋንቋዎች ፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት የፈጠሩት ድብልቅ ማንነነት ነው፡፡ የአማራ ታሪክ፣ ቋንቋና ባህል ለመጻፍ የሚሞክሩ ተመራማሪዎች ሁሉ የጥናታቸው ማጠንጠኛ እየተንሸራተተ ሄዶ አማርኛ በትግሬዎች እና በአገዎች (በተጨማሪም ሌሎች ህዝቦች) ላይ የተመሰረተ ማንነት ከመሆን አላዳኑትም፡፡ በተለይ ከዛግዌ መንግስት መውደቅ በኋላ 13ኛው ክፍለ ዘመን አስክ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀይማኖት፣ በአስተዳደር ምክንያት የተፈጠረና የተገነባ የድብለቆሽ ማህበረሰብ እንጂ እንደ አነድ ነጠላ ነገድ እንደ አሮሞዎች፣ አገዎች፣ ትግሬዎች፣ አፋሮች፣ ሱማሌዎች ወዘተ... ዘሩ ከኖህ ልጆች የሰው ዘር የትውልድ ቅርንጫፎች ሴም ካም ፡ እና ያፌት በቀጥታ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አይደለም፡፡ አማራ ነን የሚሉ ሰዎች ወደ ኋላ ዘር ማንዘራቸውን ሲቆጥሩ ከዚህ በፊት የነበረው ማንነት ራሳቸው ሲያንቋሽሹት የነበረው ህበረተስብ ይሆንበቸወል፡፡ ማለትም አሁን አማራ የሆኑት የቀደሞ የዳሞት፣ አገው ሕዝቦች (ቅማንት፣ዋግኽምራ፣አዊ) ፈላሻ፣ ወይጦ፣ ሽናሻ፣ ኩንፈል፣ ካይላ፣ኦሮሞ፣ አርጎባ፣ ጋፋት ህዝቦች ወዘተ ነበሩ፡፡ ጠያቂ የሚገርም ነው። ፕሮፌሰር እና አሁን አማራዎች ከየት የመጡ ናቸው ፕሮፌሰር ይህ እውነት በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንቶ የተደረሰበት ነው። ባይገርምህ አማራ የሚባለው ጎሳ ሥያሜው እነዴት እንደ መጣ እና ትርጉሙም ምን እንደ ሆነ ብዙ ሊቃውንቶች ይቸገሩበታል፡፡

 

አንዳንዶቹ ለስሙ ትርጉም ለመስጠት የልብ ወለድ ታሪክ ለመናገር የሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ አማራ ማለት‹‹‹‹ምህረት የጠየቀ›››እንደ ማለት ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በጥንት ዘመን ዓባይ ወንዝ ዳር ይመለክበት የነበረ የጣኦት ስም የተገኘ ነው ይላሉ፡፡ ትግሬዎች ኣማሮችን ወደ ደቡበ የሄዱ ትግሬዎች ናቸው እሰከ ማለትም ደርሰዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ሰሃራ ውሃ የሌለበት ሲሆን አምሐራ ውሃ ያለበት ለምለም ቦታ ማለት ነው ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአገውን ታሪክ የሚመረምሩ የአማራ ጎሳ ምንጩ

አገው ነው ይላሉ፡፡ በወሎ አማራ ሳይንት የሚባል የሀገር ስም እንዳለ ይታወቃል፡፡ እንደውም አሁን ወሎ የሚባለው ግዛት አማራ ይባል ነበር፡፡ ህዝቡም ሃይማኖቱ ክርስትያን ስለነበር በግራኝ ጦርነት ጊዜ ሃይማኖቱን ሳይለውጥ የቀረውን ሁሉ አማራ ማለት ተጀመረ የሚሉም አሉ፡፡›››››እንግዲህ ታሪኩ ወዲህ ነው በግዕዝ የተጻፉ የታሪክ መዛግበት እንደሚነግሩን ከሆነ በመካከለኛው ዘመን አማራ ማለት ያልተማረ(ጨዋ) ወታደር ፤ሰልፉ ስርአት የሌለው ዘማች፤ የንጉስ አሽከር ሞግዚት፤ የትግሬ እና የአገው አገልጋይ የነበረ፣ ምራተኛ፣ ‹‹‹‹ስለ አገልግሎቱ ብዛት በባለገር ላይ የተሰራ በቀን ብዛት ባላባት የሆነ ››.››፤ምህረት የጠየቀ ፣ከብዙ ግዞት በኋላ ከባርነት ነጻ የሆነ ህዝብ ማለት ነው፡፡ ጠያቂ፦….ይቀጥሉ

 

ፕሮፌሰር፡-…በጥንት ዘመን ታላቁ የአክሱም መንግስት ኢትዮጲያን በሚያስተዳደርበት ጊዜ በጦርነት የተማረኩ እንዲሁም በግዢ የተገኙ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ባርያዎች ነበሩት። የጥንት የትግራይ ነገሥታት አክሱም ላይ ሆነው ጠንካራ ንግድ ከግብጾች ከፋርሶች፤ከህንዶች እና ከጥንት ቻይናዎች ጋር መሠረቱ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ሃብት ተፈጠረ በአካባቢው ለሚሰሩ ግንባታዎች ፣ ለቀን ሠራተኝነት ፣እና የቤት ውስጥ ታዛዥ እና አገልጋይ ለመሆን ከተለያዩ ሐገራት ሰዎች ይመጡ ነበር። ዋናው መምጫቸው ደግሞ ከምእራብ ደቡብ አፍሪካና ከሰሜንና ደቡብ የመን ነበር፣እንዲሁም አክሱማውያን ጦርነት ሲያሸንፉ የተማረኩትን አገልጋይ ያረጓቸው ነበር። እነዚህ ባርያዎች በእድሜ እና በስራ ሲደክሙ አሊያም ከነዚህ ባርያዎች ልጆች ሲወለዱ ፤አሜሪካኖች ጥቁሮቹን እምጥተው ላይቤሪያ እንዳሰፈሯቸው የአክሱም ነገስታትም የደከሙትን ባሪያዎች ከትግራይ በስተደቡብ ወደ ሚገኝ ቦታ አሁን wello ቦረና ሳይንት በሚባለው አካባቢ እንዲሰፈሩ ፈቅደዋል፡፡

 

እነዚ አገልጋዮች ስርአቱን በታመኝነት ስላገለገሉ ማንም መስፍን፤ወይም የጦር መኮንን ጦርነት እንዳይከፍትባቸው ፤ከባርያነት ህይወትም የተላቀቁ ነጻ ህዝቦች ናቸውና አምሐራ ተብለው እንዲኖሩ ነገስታቱ አድርገዋል፡፡ ቦታውም ቤተ-አምሐራ ተባለ፣ የአማራዎች መኖርያ የተከለለ የተለየ ስፍራ እንደማለት ነው፤በግዕዝ-ትግርኛ(አም-ህዝብ፣ሐራ-ነጻ)፣ ከባርያነት የተላቀቀ ነጻ የወጣ ህዝብ ማለት ነው፤(አም-ሓራ,ነጻ ህዝብ-ከፍዳ የተላቀቀ) በዚ ትክክለኛ ስማቸው የሚጠሯቸው ደግሞ ስም ሰጪዎቹ ትግሬዎች ብቻ ናቸው፡፡ ያን ጊዜ አምሐራ የብሔር ስም ሳይሆን፤አገልጋይ ወይም ከባርያነት የተላቀቀ ማንኛውም ህዝብ ማለት ነበር። አሁንም ድረስ ትግሬዎች አማራዎችን ‹‹ኣምሓራ-ለምድሩ፣አምሓራይ-ለወንድ፣ አምሓረይቲ-ለሴት.አምሓሩ-ለብዙ ቁጥር ››ብለው ይጠሯቸዋል ፡፡ የእነዚህ ህዝቦች ቋንቋም አማርኛ ተባለ።ለትግራይ ቅርብ ስለሆኑ እንዲሁም ትግራዮች ክርስትና ሃይማኖትን እንዲቀበሉ ስላደረጓቸው በዚህ ምክንያት ቋንቋቸው ከግዕዝ(ትግርኛ) ብዙ ቃላትን መውረስ ችሏል። ይህ ቋንቋም ባለው የተስፋፊነት ጸባይ ከወሎ ተነስቶ ሸዋና ጎጃምን ተሻግሮ በአካባቢው የነበሩትን የዳሞት፣አሮሞ፣ወይጦ፣ሽናሻ፣ኩንፈል፣ አገው፣ አዊ ጋፋት ልሳንን ውጦ አማርኛ አላብሷቸዋል፡፡ በዚህም አልተገደበም ሰለሞናዊው መንግስት በኦሮሞች ታላቁ ፍልሰት እና በግራኝ ጦርነት ምክንያት መናገሻ ከተማውን ከሸዋ ወደ በጌምድር ጎንደር በቀየረ ጊዜ እዛ ወዳሉ ነባር ማህበረሰቦች ለመጀመርያ ጊዜ 380 ዓመት በፊት አማርኛ ተዋውቋል፡፡

 

ቤጃዎች 4ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታላቁ የአክሱም ንጉስ ኢዛና ጊዜ ተማርከው ለአገለግሎት የመጡ ባሪያዎች ናቸው። የሰፈሩበት ቦታም በስማቸው ቤገ ምድር (ቤጃምድር) ተባለ። ጎንደር የሰሎመናዊው መንግስት ቋሚ መኖሪያ ከተማ ሆና 17ኛው ምዕት አመት መጀመርያ ላይ መቆርቆሯ በአካባቢው ለአማርኛ ቋንቋ መስፋፋት ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ቤጃዎች ብቻ ሳይሆኑ እዛ አካባቢ የነበሩት ብዙ ቁጥር ያለቸው ፈላሻዎች ካይላዎች ቅማንቶች አና አገዎች ቋንቋቸው ከሰሞ አማረኛን ተቀብለዋል። እስከ ቅርብ ጊዜ እንኳን አንድ ቅማነት ወይም ፈላሻ ወደ ክርስትና ሲቀየር አማራ ሆነ ነበር የሚባለው፡፡ እንዲህ እየሰፋ አሁን ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጰያ ህዝብ ይሄን ቋንቋ ይናገረዋል። እናም 1900 አካባቢ ሰዋሰው ተቀርጾለት የግዕዝ-ትግርኛ ፊደላትን በመጠቀም ወደ ጽሑፍ ደረጃነት ተሸጋግሮ አሁን መልካም የሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ብዙ የትግራይ ባህሎችንም እነኚህ ማህበረሰቦች ወደ ተጋዙበት በታ ይዘው ሄደዋል፡፡

 

ጠያቂ፦ ምን ምን

ፕሮፌሰር፦ አረ ብዙ ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን

1.የጸጉር አሰራር(በተለይ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ጎነደር ያሉ)

2.የሀበሻ(የተጋሩ) ባህላዊ ልብስና አለባበስ፤

3.አስተዳደር ስርዓት፤

4.የጤፍ እንጀራ፤አምባሻ

5.የከብት እርባታን የእርሻ ስራንና ንግድ

6.ሃይማኖት(አይሁድ እምነት፤ክርስትና እስልምና…)

7.  .ፊደል፤ቁጥር፤ካላንደር፤ስእል፣ቅርጻ ቅርጽ፣ዜማ፤የህንጻ አሰራር ጥበብወዘተ ከትግራውያን የተወረሱ የተጋሩ ፍሬዎች ናቸው። ባይገርምህ 19ኛው ክፍለዘመን እንኳ አንድ የትግራይ የሰፈር ባላባት የሚሰራው ቤት ‹‹ህድሞ ሰቀላ››(በድንጋይ የታነጸ ፎቅ ቤት ማለት ነው) አንኮበር ከሚገኘው የሚኒሊክ ሳር ቤተመንግሰት በብዙ እጥፍ ይበልጥ ነበር፡፡

8.  በዓላትና አያሌ ባህላዊ፤መንፈሳዊ ማህበራዊ እሴቶችናአንዳንዴ ከተጋሩ በተለየ መልኩ አማራዎች የአህዛብን ልማድ ይከተላሉ ለምሳሌ ያህል በክርስትና እምነት ክልክል የሆነውን ጥሬ ስጋ መመገብ

9.ዘፈን፣ጭፈራና ጨዋታ….ትግሬዎች መጀመርያ እየተሸከረከሩ መጨረሻ ላይ እስክስታን ይመታሉ፣አማራዎችም ትግሬዎች የሚሽከረከሯትን በመተው እስከስታውን ብቻ በመውሰድ እየተጠቀሙበት ይገኛል። እነዚህ ….ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

 

ጠያቂ፦ ብዙ የማላቀውን ነገር እየነገሩኝ ነው ፕሮፌሰር። አማራዎች ልቦለዳዊ የተፋለሰ ታሪክ ድርሰቶችን ይጽፋሉ የሚባለውን ነገርስ እንዴት ያዩታል? ፕሮፌሰር፦ ፈገግ ብለው እያሰቡ….በኢትዮጵያ ታሪክ ከአፈታሪክ ውጪ እስከዚህች ሰአት ድረስ በአርኪኦሎጂ ቁፋሮም ሆነ በብራና ላይ ጽሁፎች ስለ አማራዎች ስልጣኔ የሚጠቁም ቅንጣት ታህል መረጃ እንኳ አልተገኘም፡፡ አንዳንዴ ከዛግዌ መንግስት በኋላ 700 ዓመት በፊት የተመሰረተው ሰለሞናዊው መንግሰት በድፍረት የኛ ነው ሲሉ ስሰማ እጅግ ይገርመኛል። ደግሞ እውነት ከመናገር አላፈገፍግም። የአክሱምን መንግስት መዳከም ተከትሎ ብዙ ተጋሩ ወደ ተለያዩ የዓለም ምድሮች ተበትነዋል። ወደ ምእራብ አፍሪካ የሄዱ axime የሚባል መንግስት ገንብተው ነበር። ወደ ደቡብ ኢትዮጲያም በመሄድ ከነባር ህዝቦች ጋር በመጣመር የሀረር፤ጉራጌ፤ሸዋ፣ከፋ፣ወላይታ ትግሬ መንግስታትን መስራት ችለዋል።

 

በትግራይና በአሁኗ ኤርትራ ያሉ ትግሬዎች ግን የደርግ መንግሰት እስኪመጣ ድረስ ከራሳቸው አብራክበወጡ ሰለሞናዊ የነገስታት ዘር ሉኡሎች ነው ሲተዳደሩ የነበሩት። ከትግራይ የሐ እና አክሱም ተነስተው መንበረ ንግሳቸውን በሸዋ አገር ያደረጉት ግማሾቹ፣ የትግራይ ሰለሞናውያን ነገስታትና ኣማካሪዎቻቸው ከላይ ሆነው የሚገስጽዋቸው የትግራይ መሳፍነት ሲሆኑ ከስር ሆነው በውትድርና ሲያገለጉሏቸው የነበሩት ግን የዛው ኣካባቢ አማራዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይሄ ከቤተ መንግሰት አገልጋይ እናት የተወለደው ዳግማዊ ሚኒሊክ ወደ ስልጣን ሲመጣ ትንሽ ማሸሻያ ነገር ኣድርጎበታል። ወደድንም ጠላንም በቅርብ 100 ዓመታት አማራ በሰራተኛነትና አንድን አሮጌ ጠመንጃ ተሸክሞ

ሹማሙንቶችን ከኋላ ከኃላ እየተከተለ ለብዙ ዓመታት ሲያገለግል ቆይቷል፣ይሄንንም እውቅና ልንሰጥ ይገባናል፡፡ ለማንኛውም አማራዎች እንዴት በውህደት እንደተገኙ የታሪክ መጻህፍት ይነግሩናል። ለዚህ እኮ ነው የታሪክ ጸሃፍያን አማርኛ የሚባል ቋንቋ እንጂ አማራ የሚባል ብሄር የለም የሚሉት፡፡ ምክንያቱም አማራ አንድ ወጥ ማህበረስብ ሳይሆን በድብልቆሽ የተፈጠረ ማንነት ነውና፡፡ ጠያቂ፦ ማጠቃለያ ካሎት ፕሮፌሰር፣- ኢትዮጲያውያን በተለይ ተጋሩ ከሰሩት ተኣምር እስካሁን አለም በምርምር ያወቀው 3% ብቻ እንኳን አይሞላም። በሰው ልጅ መሰራታቸውን ለመረዳት እንኳን የሚያስጨንቁ ሚስጢራውያን ሀወልቶች ኢትዮጲያ ከርሰምድር ውስጥ ተደብቀው ፒራሚዶች፣ከአክሱም እስከ ኤርትራ ይደርሳል የሚባለውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጨምሮ ገና ምንም ያልተጠናውን የጥበብና የተክኖሎጂ ስራዎች ፈጽሞ ሊፈተሹ ይገባል። ባህሉም ጭምር፤ለመሆኑ በአክሱም ጊዜ በእንፋሎት ሃይል የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችና ማሽኖች እነደነበሩ ታቃለህ፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ የትግራይ ህብረተሰብ በአልባሳትም ይሁን በቋንቋው፣ በምግቡ በሙዚቃው በአኗኗር ዘይቤው ሁሉ ከድሮው ጋር ተመሳሳይ ነው። እንዲያውም ባህሉን አለባበሱን አመጋገቡን ወዘተ... ስታይ እስከ ዛሬዋ ኢራቅ

ህንድ ኢራን ድረስ ተወራራሽነት ይታይበታል። ያም የሆነው ትግራውያን የዚያ ቀደምት ኗሪ መሆናቸው እና እስከ እዚያ ድረስ በግዛት ማስፈፋት አሻራ ያስቀመጡ መሆናቸውን አስረጅ ነው። የትግራውያን ታሪክ፤ትውፊት” “ክህሎትጥበብ ያለው ከላይ ባቢሎን እስከዛሬው የትግራይ ክልል ዝርው በሆነ መንገድ ተበትኖ ያለ ነው። ባህላቸውን እና ስልጣኔያቸውን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ይገልፃሉ፣እሴቶቻቸውንም በተግባር ኖሮባቸዋል፣ታላቅነታቸውንም ትግራውያን የስልጣኔዎቻችን ማሳያበሆኑቱን ሃወልቶች ፣ቤተ መንግስታት ኣብያተ ክርስትያናት እና መስጊድ ሲያንጹ፣ዜማ፤ፊደሉን ካላንደሩን እየቀመሩ በሌላ በኩል ድግሞ ከሃገር ሀገር እየተወነጨፉ ከባህር ባህር እየተዟዟሩ ጠላታቸውን ሲቀጡ፣ባእዳውያን ወራሪዎችን ሲያሳፍሩ እና ሲያስገብሩ የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል። ለሃገራቸው ካላቸው ክብር የተነሳ በትግራይ የነበረው የመሓላ ባህል በሀገር ስም ነበር። ካልሆነ አብሮት በሚያወራው ሰው ስም(ሰጋህን፤ስጋሽን) እያሉ መማል ነበር፡፡ ሌላው ነገር በዘመናዊት ኢትዮጲያ ግንባታ አሁን ትግራዋይ ተብሎ የሚጠራው ብሄር ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

 

አሁንም ቢሆን ከዚ አልቦዘኑም ሀገራቸው ከነበረችበት ኋላ ቀርነት ጭቆና እና ስር የሰደደ ድህነት ወደ ነበረችበት ታላቅነትዋ እንድትመለስ ትልቅ ጥረት እያደረጉ ያሉ እና ለኢትዮጵያ ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት አድገው የሰጡ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን በእነዚህ ህዘቦች በአዲስ መልክ ተሞሽራ በእውነተኞች ልጆችዋ እየተመነደገች ነው።

 

 ጠያቂ ታዲያ ለምን እውነቱን አታስተምሩንም

 

ፕሮፌሰር የዝምታው ምክንያት ሌሎች የኢተዮጲያ ምሁራን ናቸው ዝምብለዉ ሰላም ያደፈርሳል ይላሉ። ይህ ግን እውነተኛ ታሪክ ነው በሐሰት የሚፈጠር ሰላም ዘላቂ አይደለም ጠያቂ አመሰግናለሁ ፕሮፌሰር ። እንግዲህ ይህንን ምስክርነት የሰጡት እንግሊዛዊው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ሲሆኑ የተለያዩ የታሪክ ተመራማሪዎችና፣ደራሲያንም ስለ ኢትዮዺያ ጽፈዋል። ለመጥቀስ ያክልም፣ እነ (ጀምስ ብሩስየአባይ ማመንጫ”) (ሄረድተዝ ደግሞፐርሻን ሲቪላይዜሽን”) በሚለ መጽሃፉ ሰለ ኢትዮዺያ ከክርስቶስ ልደት በፊት ስለነበሩት የአክሱም ነገስታት፣ምስክርነት ይሰጣል። እንዲሁም እስራኤላዊው ደራሲ (ሃጋይ ኤርልችአሉላ ና ለአፍሪካ ቅርምት”) የሚለውን መጽሃፍ፣በተለይ የተጋሩ ማንነት በንጉሰ ነገስት፣ሃጸይ ዮውሃንስ ፬ተኛ ኢትዮዺያ የገጠሟት ወራሪዎች፣ ተጋሩ በራስ አሉላ አባነጋ የጦር መሪነት፣ የተመዘገቡ ድሎችን ታሪካዊ አፈፃጸማቸው ያስረዳል። ማገላበጡ መሬት ላይ ያለውን የተጋሩ የታሪክ እውነተኝነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።

 

አማራና፣የአማራ ደራሲያን፣ ሃይማኖተኞች፣ ጋዜጠኞች በአጠቃላይ ሙሁራነን ባዮች ለምን በትግራይ ሕዝብ ላይ ይህንን የመሰለ ክህደት መፈጸም ፈለጉ ? ለሚለ ጥያቄ በርግጥ አንድን ሰው ወይም (ህዝብ እንደ ህዝብ) የምትጠላበት የተለያዩ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ በመሰረታዊነት ጠቅለልና፡ አጠር ባለ አገላለፅ ግን፣ በሃሳብና

በፍላጎት ካንተ/ካንቺ ሳይስማማና ሳይግባባ ሲቀር፣ አንተ/አንቺ ከዛ ሰው ወይም(ህዝብ፣ወይም ማሕበረሰብ)የምትፈልገው/የምትፈልጊው፣ የምትመኘው/የምትመኚው ፍፁም የሆነ፣ ወደ ራስህ/ራስሽ ማዛወር የምትፈልገው/የምትፈልጊው ጠቃሚ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። እንግዲህ ከላይ እንደጠቀስኩት፣ የአባትና ልጅ፡ምሳሌ፣የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የኖረ፣ በለ አኲሪ ታሪክና ገድል ህዝብ ነው። ለምሳሌ፣ እርግጥ ነው ሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት ለገጠማት ችግር ግምባር ቀደም ተጠያቂው ህዝቡ ቢሆንም፣ በሃገሪቱ ውስጥ አንድም ክፍል የቆጠረ ሰው እንዳሌሏት በሚያስመስል መልኩ፣ የሙሁር መካን የሆነች ሃገር ለማየት ችለናል። ለስሙ ግን የፕሮፌሰርና የዶክተሮቿ ቁጥር ኢትዮዺያ ከአለም ግምባር ቀደምም ሳትሆን አትቀርም ብዬ እገምታለሁኝ። እኔ የሚገርመኝ ግን ? የሰው ልጅ ከእንሰሳ የሚለየው ስለሚያስብ ነው ይባላል፣ አንድ ሰው ተምሯል የሚባለው፣ ከተራው ማህበረሰብ ላቅ ያለ አስተሳሰብና ሞራላዊ ብቃት ሲኖረው አይደልን ? ሌባን በስሙ ሌባ ማለትን ስለምወድ ከዚህ በኃላ፡ የማሽሞነምነው ስም አይኖረኝም።  መማር ማለት ምንድነው ? ኢትዮጲያን እየገደሏት ያሉት ከገበሬው የማይሻሉ ሃገራቸውን ከውጭ ጠላት ጋር አብረው ትናንት ሲያደሟት የነበሩ፣ እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ከኢህአፖ፣ ኢህአዴግ፣ ቅንጅት፣ ግንቦት ፯፣ አርበኞች ግንቦት፯ እስከ ኢዜማ ስም እየቀያየረ፣አንዴ ከግብፅ ፣ለጥቆ ከኤርትራ፣ አሁን ደግሞ ከአረቦች ጋር እየተቧደነ በስልጣን ጥም፣ እየተንገዋለለ፣ ባለ ሰው ፖለቲካዊ እቅድ ሰለተመራች። እነ ፕሮፌስ ዳኛቸው ስለ ትልቋ ኢትዮዺያ ሲዘምሩና ሲሰብኩ ከርመው፣ መጨረሻቸው በራያና፣ ወልቃይት የሚቋጩ ሙሁራን ተብየዎች፣ የሙሁራን ሃሳብ ሰለተበረዘች፣ እነ ዳኒኤል ክብረት በሃይማኖት ውስጥ ተደብቀው፣ ለዘመናት የኢትዮዺያ ዋልታና ማገር የሆነችውን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ሲገዘግዙና ሲያፈርሱ የነበሩ ደብተራዎች የአማካሪነት ቦታ ስለተያዘ፣ ያገኟትን እድል ተጠቅመው ለዘመናት ሲማሩትና ሲሰሙት ያደጉትን የዘርአያቆብ ምኞትን ለማሳካት አላማ የያዙ። እንደነ አዝማሪ ታማኝ በየነ ሳይቀር የኢትዮዺያ ህዝብ በብሄራዊ ቲያትር ውስጥ አስገብቶ እንደሚያዝናናው ህዝብ ቆጥሮት፣ ሲያሰኘው ለጌዶ፣ ሲያሰኘው ለመተከል፣ ሲያሰኘው ለትግራይ የመለመኛ ገፀ በረከት ሆነውለት ማየት፣ ቢገርምም የኢትዮዺያ የቁልቁለት ጉዞውን ግን እያፋጠነው እያየን ነው። እንግዲህ ውድ አንባቢያን ጽሁፌ ይቀጥላል ለምን የትግራይ ሕዝብ ማጥፋት ተፈለገ ? የትግራይ ሕዝብስ በነ ጉግ ማንጉግ እውነት የሚጠፋ ሕዝብ ነውን ? የሚለውን ደግሞ

በሚቀጥለው ጽሁፌ እናየዋለን።

 

 ሙሉጌታ በሪሁን

mba1277@gmail.com


Back to Front Page