Back to Front Page

እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አይድረስ! ማለት አሁን ነው

እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አይድረስ! ማለት አሁን ነው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

10-15-21

 

ትርጓሜ፥ ልሃጫም ምንሊካዊ አስተሳሰብና እምነት ማለት ለዚህ ትውልድ የማይመጠን፣ የድህነትና የድንቁርና የጦርነትና የእልቂት የሞትና የደም መፋሰስ የኋላቀርነትና የተመፅዋችነት የሁከትና የግርግር መዝገብ የሆነ፥ ዘመኑ ያለፈበት፣ የበከተ፣ መናኛ፣ አብሮነትና እኩልነት መከባበርና መጠባበቅን የሚፀየፍ፣ በህዝቦች በተሳትፎ የማያምን፥ ፀረ-እኩልነት፣ ፀረ-ፍትህ፣ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አመለካከትና አስተሳሰብ የሆነ ጨፍላቂ የአፈናና የግፍ አሰራር/አገዛዝ ለማለት ነው።

 

ወያነ ትግራይ፥ እንዴት እዚህ ውስጥ ልንገባ ቻልን? መውጫው ምንድ ነው? አንድም፥ እንደዚህ ያለ ነገር ላይደገም ምን መደረግ አለበት? ቀጣይ ጉዞአችንስ ምን ይሁን? ተብለው ለሚነሱ ጥያቄዎች በጥሞና አስቦበት ዘመን ተሻጋሪ የመፍትሔ ሃሳብ ወይም ምላሽ መስጠት ከቻለ ዳርጋ ዘይሞትና!

 

ሐተታ፥ ስለ ጦርነት አስከፊነትና አውዳሚነት አንስተን/እያነሳን፥ መጡብን እንጅ አልሆንባቸውም፣ ተኮሱብን እንጅ አልቶኮስንባቸውም፣ ጦርነቱን የጀመሩት እነሱ እንጅ እኛ አልጀመርነውም ወዘተ እያልን ንጽህናችን ለማሳየት፣ ለማሳወቅና ለመግለጥ ብዙና ጥቂት የምንልበት ሰዓት አልፏል። ጦርነት የሰው ህይወትና ንብረት እንደሚበላ፣ ጦርነቱ እኛ እንዳልጀመርነውና ወራሪ ኃይሎች አማራጭ አሳጥተውን ህልውናችንና ድህንነታችን ለመጠበቅና ለመከላከል ተገደን የገባንበት ለመሆኑ እኛም እናውቃለን - ከዚህም ከዚያም ተሰባስበው መጥተው በዓላማና በዕቅድ ወረራ የፈጸሙብን ህዝቦችና አገራትም ጠንቅቀው ያውቃሉ። የጦርነት አውዳሚነት በተመለከተም አመል ያልበት ካልሆነ በቀር ለትግራይ ህዝብ ስለ ጦርነት አስከፊነት አፉን ሞልቶ መናገር የሚደፍር ቢኖር በእውነቱ ነገር ጦርነትን የማያወቅ ዜጋ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ቢሞክርም ለኳየሩ መስበክ በመሆኑ እዚህ ላይ የምናጠፋው ጊዜ አይኖርምና በቀጥታ ወደ ፍሬ ነገራችን እንግባ።

 

1.      እንዴት እዚህ ውስጥ ልንገባ ቻልን?

 

እአአ 1991 ዓ/ም የተመታ አመለካከት እንዴት አንሰራራ? የሚለው ጥያቄ ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ተንሰራርቶ የፈጀን አስተሳሰብና አመለካከት ላቶክር። ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊና ልሃጫሞቹ የአማራ ልሒቃን፥ ትግራይን ከካርታ የትግራይን ህዝብ ስመ ታሪኩ መታሰቢያ ላይኖረው ለመደምሰስና ለመፋቅና፥ ከሱዳን መንግሥት ጋር መክረውና ዘክረው፥ ከምዕራቡም ከምስራቁም ርዕሰ ኃያላን አገራትና መንግሥታት ይሁንታና ፈቃድ አግኝተው፣ የሶማሊያና የኢምሬትስ ድሮንና የሰው ኃይል (ሠራዊት) አስከትለው ትግራይን በአራት አቅጣጭ በመክበብና በመነጠል የፈጸሙት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም፣ የጦርና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማናችንም ልናስበው በማንችለው ሁኔታ እውን ሆኖ አይተናል። ጥያቄው፥ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን ሊደረግ ቀርቶ ፈጽሞ የማይታሰብ ግፍና በደል ትፈጽምብን ዘንድ ጉልበት የሰጣት ነገር ምንድ ነው? የፈጸመችብን አረማዊና ሰይጣናዊ ግፍና በደል በጠራራ ጸሐይ እንድትፈጽምብን እንዴት አቅም ልታገኝ ቻለች? የሰምንት ዓመት ህጻን ልጅ የሚደፍር፣ የሰማኒያ ዓመት የዕድሜ ባለ ጸጋ የሚያስነወር፣ ዘመናቸው በሙሉ እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ቤት ከማገልገል ውጭ ሌላ ዓለም የማያውቁ መነኮሳት የሚጋሰስ፣ አንዴት ሴት ለአስራ አምስትና ለሃያ እየተፈራረቁ የሚማግጡ፣ አባት ከሴት ልጁ ጋር እንዲተኛ ብረት የሚደቅኑ፣ ሰውን እንደ ጠቦት በገመድ አስረው የሚያርዱ፣ ሰው ገድለው በእሳት የሚያነዱ፣ ወደ ገደልና ወደ ወንዝ የሚወረውሩ ወታደሮች እንዴት ልትፈጥር ቻለች? ይህን ሁሉ ግፍና በደል እያየ በደስታ የሚዘልና ዊስኪ የሚራጭ ህዝብስ እንዴት ልታፈራ ተቻላት? የሚል ነው።

 

Videos From Around The World

እአአ ግንቦት 2020 ዓ/ም በአሜሪካን አገር ለህተመት የበቃ አዲዮስ ኢትዮጵያ የተሰኘ መጽሐፌ ላይ እንዳሰፈርኩት፥ በትግራይ ላይ የተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋ፣ ያየነው እልቂትና ውድመት ሁሉ ከሰማይ የወረደ ቁጣ እንዳልሆነና የአንዲት ሌሊት ፀብና ኩርፊያ ውጤት እንዳይደለምም አትቼ ነበር። ይልቁንም፥ እነዚህ የጥፋትና የትምክህት ሃይሎች የትግራይ ህዝብ በዚህ ደረጃ ሲጨፈጭፉ፣ ህጻናትና ሽማግሌዎቻችን ወጣቶችና ጎልማሶቻችን ሲረሽኑ፣ ዲያቆናትና ካህናቶቻችን ሲያርዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት በታንክ ሲያፈራርሱ፣ ሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን እንደ ሰዶምና ጎመራ ሲያራክሱና ሲያስነውሩ፣ ፋብሪካዎቻችን ሲያጋዩ፣ ሹካና ማንኪያ ድስትና መጥረጊያ ሲዘርፉ፣ የህዝብና የመንግስት ንብረት ሲያወድሙ፣ ከተሞቻንን በእሳት ሲያነዱ፣ ከጥይት ያመለጠ ህዝባችን በምግብና በመድኃኒት እጦት እንደ ቅጠል ሲያረግፉ እንዲሁ ከመሬት ተነስተው ሳይሆን፥ ትምክህተኛና ልሃጫም ምንሊካዊ አስተሳሰብ የጸነሰው ቅናትና ምቀኝነት ያዋለደው ትግራይ ጠል የጥላቻ ፖለቲካ ነው። ቀለል ባለ አማርኛ፥ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ለደረሰበት የዘር ጭፍጨፋና እልቂት ዋና ተጠያቂና ምንጭ በዋናነት የትግራይ ህዝብ ህልውና እንደ ኮሶ መድኃኒት የሚመረራቸው፣ ኢትዮጵያን የመግዛት መለኮታዊ ስልጣን ተሰጥቶኛል፣ ስዩማነ እግዚአብሔር ነን፣ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋላና ሻንቅላ እያልኩ እንዳልገዛቸው እንቅፋት ሆኖብኛል፣ ትግራይና ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ሳናጠፋ የትግራይ ሀብት ሀብታችንና ገንዘባችን ማድረግ ሆነ የአባታችን የምንሊክ ህልም ልናሳካ አንችልም ብለው የሚያምኑ የአማራ ልሂቃን የትምክህት፣ የምቀኝነትና የምዋርተኝነት የበከተ ፖለቲካ (አስተሳሰብ) ነው። መፍትሔው? ንባቡን ይቀጥሉ

 

2.     እንደዚህ ያለ ነገር ላይደገም ምን መደረግ አለበት?

 

ለጥያቄው መልስ ከመስጠቴ በፊት ግን የንባባችን መንፈስና ዓውድ በጠበቀ መልኩ የአማራ ልሒቃን ማንነት በተመለከተ አጠር ያለ ሃሳብ ላስፍር። ይኸውም፥ የአማራ ልሒቃንና ቢራቢሮ አንድ ናቸው፤ ሲለቀቁ ምድርን ይሞላሉ ሲያዙ እፉኝ የማይሞሉ አቅመ ቢሶችና የሃሳብ ድሆችና ናቸው። ሰዎቹ የሃሳብ ድሆች ከሆኑ፥ እንዴት ይህን ዘመን ዘለቁ? ተብሎ ሊነሳ ለሚችል ጥያቄ መልሱ አጭር ነው። እነዚህ ሰዎች ብዙሐኑ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያሳጡት፣ የሰለቡትና ያኮላሹት በሃይማኖት ስምና ሽፋን በሚሰበኩ ልበ ወለድ ድርሰቶችና ተረቶች ሲሆን በዋናነት ግን በቀረርቶና በሽለላ፣ ዘራፍ ብሎም በማይደክመው ተሳዳቢ፣ ተራጋሚና ምዋርተኛ መርዛም በምላሳቸው ህዝቡን ማሸማቀቅ ስለ ተቻላቸው ነው። ቀደም ሲል ጋላ ሻንቅላ ወላሞ እያሉ አሁን ደግሞ መብቱን የጠየቀ ሁሉ ጸረ አንድነት፣ ጸረ ማሪያም፣ ጸረ ኢትዮጵያዊነት የሚሉ ልዩ ልዩ ታፔላዎች በመለጠፍና በማሸማቀቅ ነው። ሐቁ፥ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚደግፋቸው፣ የሚያጽናናቸው፣ የሚያባብላቸውና ሞራል የሚሰጣቸው፥ የደቡብና የሶማሌ የአፋርና የኦሮሞ የጋምቤላና የሐርሬ ሰው ካላገኙ በቀር የአማራ ልሒቃን ራሳቸው ችለው መቆም የማይችሉ ደካሞች ናቸው። ሰዎቹ፥ በማንነት ቀውስ የሚሰቃይ፣ የበታችነት ስሜት ያበሰለው፣ ራሱን ጥሎ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚልላቸው እንደ ኦባንግና እንደ ሙስጠፌ እንደ ታድዮስ ታንቱና እንደ አወል አርባ እንደ አረጋዊ በርሀና እንደ አብርሃም በላይ፥ የደቡና የጋምቤላ የሶማሌና የአፋር አንድ ሰው ሲያገኙ፥ አንዴ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ሌላ ጊዜ የቁርጥ ቀን ልጅ እያሉ የሌላ ብሔር ተወላጅ ሲሸልሙና ሲያቆለጳጵሱ የሚውሉበት ምክንያት ታድያ ምን ይመስሎታል? ሰዎቹ ሲፈጥራቸው እንደ ባዶ ቆፎ ክፉኛ የተቦረቦረና የተመታ ሥነ ልቦና ባለቤቶች ስለሆኑ ነው። ጩኸት የሚያበዙበት ምክንያትም ይህን ባዶ ማንነታቸው ለመሸፈንና ለማደባበስ ነው። ምን አለፋዎት፥ በኤርትራ፣ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሚሊሻዎች፣ ታጣቂዎችና ልዩ ሃይል ታዝለው መጥተው ያሸነፉ መስሎ በታያቸውና በተሰማቸው ወቅት አማራ ታሪክ ሰራ! ድልን የሚሸከም ትክሻ ስጡን ብላችሁ ጸልዩ እያሉ በአደባባይ ሲመጻደቁ የከረሙ ሰዎች ዛሬ ያነደዱት እሳት በላያቸው ላይ ሲደፋባቸው ደግሞ፥ ይግባኝ ለክርስቶስ እያሉ ማለቃቀስና ማላዘን የሙሉ ጊዜ ስራቸው ሆኗል።

 

አሁን ወደ ጥያቄው ለመለስ። ለጥያቄው ያለኝ ግልጽና ቀጥተኛ ምላሽ፥ ትምክህተኛና ልሃጫም ሰይጣናዊ እምነትና አስተሳሰብ ፍጻሜ እንዲኖረው ላያዳግም መስበርና መቅበር ነው። ወያነ ትግራይ እንዳትሳሳት፥ ሰላም የሚወርደውና የሚፈጠረው ስለ ሰላም ተብሎ ፍትሕና ፍርድ ከማድረግ ወደኋላ በማለትና በማመቻመች ሳይሆን ሰላም የሚወርደውና የሚፈጠረው ፍትሕና ፍርድ በማድረግ ብቻ ነው። ህዝብና አገር የሚያርፈው፥ ሥልጣኑን ለማደላደል፣ ለመጠበቅና ለማስቀጠል በህዝብና በአገር ላይ ወንጀል የፈጸመ ባለሥልጣን ሁሉ በህግ ፊት ቀርቦ ተጣያቂ እንዲሆን በማድረግ ነው። ህግና ስርዓት አቅምና ጉልበት ኖሯቸው መንግስትነት ሊያጸኑ የሚችሉ፥ ህዝባዊና አገራዊ ስልጣኑን ተገን አድርጎ ህዝብና አገር ያደማና የበደለ - ህዝብና አ&##4872;ር ሰላማቸውና ደህንነታቸው ለማስጠበቅ ተማምነውና ተስማምተው ባጸደቁት ህግ ሲዳኝ ብቻ ነው። አገር ወደ ነባራዊ ሁኔታ ለመመለስ ሆነ የትግራይ ህዝብ ለመደበስ የሚቻለው ወያነ ትግራይ ዓይኑን ሳያሽ የህግ የበላይነት በተጨባጭ እንዲረጋገጥ የደረገ እንደሆነ ብቻ ነው። መማር ያለበትና የሚገባው ህግ ካላስተማረው ስለ ማይማር የህግ የበላይነት እንዲከበር ከማድረግ ውጭ የሚኬድ ማንኛውም መንገድ ታድያ ፓናዶላና አስፕሬን የመዋጥ ያህል ነው የሚሆነው።

 

የትግራይ ህዝብ በማንነቱ ለደረሰበት ግፍና በደልና ለከፈለው የህይወት መስዋዕትነት በክንቱ እንዳይቀር ጥንቃቄ ይሻል። የዚህ ሁሉ እልቂትና ደም መፋሰስ አውራ ምንጭና ተጠያቂ ቀደም ሲል እንደ ተመለከትነው የእነዚህ ልሃጫሞች ያረጀ ያፈጀ ሰይጣናዊ አስተሳሰብና የበከተ ምንሊካዊ አስተሳሰብ የወለደው ለመሆኑ አስታዋሽ ባያስፈልገንም መዘንጋት ግን የለብንም። በመሆኑም፥ጦርነቱ ፍጻሜ ከምንም በትግራይ ላይ እጆቻቸው ያነሱ፣ በትግራይ ሰማያት ላይ ጥቁር መጋረጃ የጣሉ፣ በህዝባችን ላይ ሐዘን የጨመሩ፣ ህዝባችን ለስደትና ለሰቆቋ ለስብራትም የዳረጉ የኢትዮጵያ አውራ ቂሶች ሁሉም አንዳቸውም ማምለጥ ሳይቻላቸው፣ ልሃጫሞቹና አስተሳሰባቸው በመስበርና በመቅበር ሊጠናቀቅ ይገባል። ጦርነቱ የአማራ ልሒቃን ልሃጫም ምንሊካዊ እምነትና አስተሳሰብ በመቅበር ማጠናቀቅ እንደሚገባ ለእኛ ለተጋሩ የምርጫ ጉዳይም አይደለም ይህን በማድረግም የትግራይ ህዝብ መስዋዕትነት በከንቱ እንዳይደለ ለዓለም ማሳየታችን ብቻ ሳይሆን የአማራ ጭቁን ገበሬ ጨምሮ መላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማሳረፍ ይገባል። ወያነ ትግራይ አዲስ አበባ ደጃፍ ሲደርስ እሺ እንደራደራለን ተብሎ የሚሰራ ቀልድና ድራማ ሳይዘናጋ በከንቱ ለፈሰሰ የንጹሐን ደም ምክንያት የሆነው ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ላያንሰራራ በመቅበር ይጠበቅበታል። ጦርነቱ ልሃጫሞቹ የአማራ ልሂቃን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ያታለሉበት፣ ያጭበረበሩበት፣ ያወናበዱበትና ያደናገሩበት ማስክመቀንጠጥና በማራቆት ሊጠናቀቅ ይገባል።

 

እዚህ ላይ ጠላትም ወዳጅም ሊያውቀው የሚገባ ሐቅ ቢኖር፥ ወያነ ትግራይ ሆነ የትግራይ ህዝብ የሰው ጠላት የለውም። በሰውነቱ ጠላቴ ነው የምንለውና ክፉ እንዲገጥመው የምንመኝለት ግለሰብ ሆነ ቡድን የለም። የእኛ ጠላት የሰው ያይደለ ፀረ-ሰው የሆነ፣ ህልውናችን የማይቀበልና የማይዋጥለት፣ ተፈጥሯዊ መብቶቻችንና ክብሮቻችን ገፎ ባሪያ ሊያደርገን የሚቋምጥ ክፉ አመለካከትና አስተሳሰብ ነው። መማረክ ብቻ አይደለም፤ በኢትዮጵያዊነት ስም በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍና በደል ያደረሰና የፈጸመ ሲቪልና ወታደራዊ ባለ ሥልጣን ሁሉ ኃጢአቱና በደሉን ከተናዘዘ ንዛዜዉን ተቀበልን እንቀበላለዋለን። እነሱ ገድለው ስላቃጠሉን፣ ወደ ገደልና ወደ ወንዝ ስለ ወረወሩን ተመሳሳይ ግፍና በደል የምንፈጽምበት አንድ ሰው አይኖርም። ትግራዋይ እንዲያህ አስነዋሪና ኢ ሰብአዊ የሆነ ድርጊት ይፈጽም ዘንድ ባህላችን ሆነ እምነታችን አይፈቅድልንም። ይህ ማለት ግን፥ ወንጀለኛ በነጻ ምሳ ይበላል፣ ፍትሕና ፍርድን አናደርግም ማለት አይደለም። በህግ መዳኘት ያለበትና የሚገባው ሁሉ ህግ ፊት ቀርቦ በፈጸመው ወንጀል ይጠየቃል። እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አይድረስ! ማለት አሁን ነው።

 

3.     ቀጣይ ጉዞአችንስ ምን ይሁን?

 

ይህን ጥያቄ መመለስ የሚችለው የህዝብ ውክልና ኖሮት ግልጽ ዓላማ ያለው አካል ብቻ ነው። የእኔ ሃሳብ የግለሰብ ሃሳብ ነው። የድሮ ነገር አንስተን፥ የትግራይ ጨምሮ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ነው ያልን እንደሆነ ግን ለተነሳ ጥያቄ መልስ ሊሆን የሚችለው፥ የህዝብ ጥያቄ እንደ ከዚህ ቀደሙ ያማረ ህገ መንግስት ጽፈህ ስታበቃ ዕቃ ዕቃ መጫወትና መሸዋወድ ሳይሆን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በትክክል መመለሰ፣ ህገ መንግስቱም በተግባር ማለትም በስራ የሚገለጥ ገዢ ህግ እንዲሆን በመፍቀድ (መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎ)፣ አመራሩ ውስጣዊ ዲሞክራሲ እንዲኖረው ራሱን በማስተካከልና ተቋማዊ አስተሳሰብና አሰራር እንዲሰፍን በማድርግ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር ይቻላል በተረፈ፥ ተቀምጠን ማፈስ ባይሰለቸንም ቁመን ማፍሰስ ግን ሊሰለቸን ይገባል እያልኩ ጽሑፌ እዚህ ልቋጭ።

 

E-mail: mahbereseyta@gmail.com

 

Back to Front Page