Back to Front Page

ወደ 2014 ለደረሳቹ የዱሮዋ ኢትዮጵያ ህዝቦች ይድረስ ዘንድ!

ወደ 2014 ለደረሳቹ የዱሮዋ ኢትዮጵያ ህዝቦች ይድረስ ዘንድ!

 

..ኣ 09-10-21

እንዴት ናቹህ? እኔ ደህና ነኝ። ይህንን ኣጭር ጽሑፍ ስጽፍ፣በኣእምሮየ ሃዘንን፣ቁጭትን፣ብቀላንና ጀግንነትን እየተፈራረቅኝ ነው።

 

ሃዘኔን!

ባለንበት ዘመን፣ በዚች ኣለም ላይ ትልቅ ግፍ እይተደረገበት ያለ ህብረተሰብ፣ የትግራይ ህዝብ እንደሆነ ያልተገነዘበ ፍጡር ኣለ ብሎ ኣይታሰብም። ይህንን ህዝብ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ኣካል ሁኖ እያለ፣ ኣንድም ኢትዮጵያዊ ለምን ይህንን ግፍ ይወርድበታል ብሎ መጠየቅ ይቅርና፣ ቤተሰቦችህ እንዴት ናቸው ብሎ የሚጠይቅ ወገን ሲጠፋ፣ከምን ኣይነት ህብረተ-ሰብ ስኖር እንደነበርኩኝ ሳስብ በጣም ይዘገንነኝል፣ያሳዝነኛልም። ሰዎች ኣይቁም ይሆናል ብለህ፣ያለውን ሃቅ በማስረጃ ስታሳያቸው፣ ይህማ ውሸት ነው ብለው ሲመልሱልህ፣ምን ኣይነት ጨካኞችና ኣረመኔዎች መሆናቸውንም ስረዳ፣ይበልጥ በነሱ ኣረመኔነት ለነሱ ማዘን ስጀምርም፣ራሴን ያሳዝነኛል።

የኤርትራ ኣራዊት ሰራዊት-የሽንፈትንና የቅናት ቂም በቀል ካለው ሃይል፣ የኣማራው- ያልሰለጠነ ኋላ ቀር ምሁር ነኝ ባይ ዘራፊ ሃይል፣የUAE-የኣካባቢው ሃያል ልሁን የሚል ጠንካራውን ሃገር ወዳዱን የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ጥቅም የማይደራደረውን ለማጥፋት የመጣ ሃይል ሴራ፣ኣገሩን ኣንድ ማድረግ ያልቻለ የመቛድሾ ጥገኛ ሃይል፣ለግል ስልጣን ሲሉ ከውጭ ጠላቶች ያበሩ የኣብይ ኣህመድ የክህደት ፊተኣውራሪዎች ትብብር፣ የትግራይን ህዝብ ከዛች የጀግንነት መፈጠርያ የሆነችው ገጸ-መሬት ለማጥፋት በሚደረገው ወንጀል ዝምታህን የመርጥክና የተባበርክ የዛች ኢትዮጵያ ዜጋ ነኝ ባይ፣ የወንጀሉ ተባባሪ መሆንህን ሳቅ፣በጣም ኣዝኛሎህ።

Videos From Around The World

 

እስኪ ኣስበው/ቢው ኣንተ/ ጨካኝ ኣህዛብ! ኣእምሮ ካለህ/?

-ልጆችህ በፊትህ ሲገደሉ?

-ልጅህ ኣንተን ኣስረው ሲደፍሯት?

-ቤተሰቦችህ ገድለው ሲያበቁ፣ ሬሳ እንዳትቀብር ተከልክለህ፣ክቡር የሰው ሬሳ እንስሳ ሲበላው?

-ሚስትህን በባልዋና ብልጆችዋ ፊት ስትደፈር?

-እህትህ ኣንተነትህን እንዳትወልድ፣ ማህጸንዋን ምላጭና መስማርን መክተት?

-ወገኖችህን ተገድለው በወንዝ ተጥለው፣ ወደ ጎረቤት ኣገር ሲጎርፉ?

-ወገኖችህ ከቀያቸው ተፈናቅለው ሲሰደዱ?

-የተማርክባቸው ትምህርት ቤቶች ሲጋዩና ሲዘረፉ?

-ክሊኒኮችህንና ሆስፒታሎችህን ሲዘረፉና ሲጋዩ?

-ፋብሪካዎችህን ሲዘርፉና ሲጋዩ?

-ያመርትከውን ሰብልና ማሳ ሲጋይ?

-የምታርስበት መፎር፣ ቀንበር ሲቃጠልብህና በሬዎችህ ሲታረዱ?

-የገነባሀው መብራት ሃይል ተነፍገህ ስትጨልም?

-የገነባሀው ቴሌ ስትቛረጥ?

-ጥረህ ግረህ ያካበትከው ንብረትና ገንዘብ ስትዘረፍ?

-የባንክ ኣካውንትህ ሲዘጋ?

-በማንነትህ ብቻ ከቤትህና ከስራህ ስትባረር?

-እርዳታ እንዳታገኝ መንገድ ሲሰጋብህ

እረ ኣያልቅም ግፉ። ለመጻፉም የሚዘገንን።

 

ቑጭቴን!

"I will never regret the thing I did wrong. I only regret the good things I did for the wrong people"

በጣም ይቆጨኛል ከምላቸው ነገሮች ኣንዱ፣እንደ ኣንድ ኣዋቂ ሰው፣እንደዚህ ኣይነት ህብረተሰብ፥ ያልሰለጠነ፣ጨካኝ፣ከሃዲ የሞላባት ሰው ኣገር መሆንዋን ባለማወቄና ባለማስተማሪ ነው።ሌላውም ከሚቆጨኝ፣ሁሉንም ዜጋ እንደራሴ ያስባል በማለት ሳላዳላ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የነበረኝ በጎ ምኞትንና ልፋትን ነው። ለሁሉም እኩል የሆነች ኢትዮጵያ፥ያደገች፣የሰለጠነች እንትሆን ነበር እምመኘው።እንደ ኣንድ የትግራይ ሰው "ኢትዮጵያዊ" ቁጭቴን እንደ ስህተት በመቁጠር የተሻለ ስራ እንድሰራ መትጋት ነው። Mistakes are always forgivable, if one has the courage to admit them.

 

ብቀላን!

ብቀላን ሳስብ "Eye to Eye" እንዳይመስላችሁ። "The best revenge is success ".ትግራይንና የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት የሚሰራው ስራና ግፍ በሌላው የኣለም ህብረተሰብ እንዳይደገም፥መደረግ የሚገባቸውን ስራዎች በመስራት ነው። መሰራት የሚገባቸውን በዚሁ ጽሁፍ መጻፍ ኣስፈላጊ ነው ብዪ ኣላምንም። ግን፣ባጭሩ ህዝባችንን ለግፍ የፈረደ፣የደገፈ፣የተሳተፈ የትም ይሁን የትም ለህግ ለማቅረብ ለሚደረጉት ስራዎች በመተባበር እንደምበቀልና፣ ካዝውም በላይ የጠፋውን የትግራይ እድገት በበለጠ እንዲሰራና፣ ላንዴና ለመጨረሻ፣ ህዝባችን እንደዚሁ ኣይነት ችግር እንዳያገጥመው መሰረታዊ ስራዎችን በመስራት ለሚቀጥለው ትውልድ የሰለጠነችና የማትደፈር ትግራይን ማስረከብ የብቀላየን ጫፍ እንዲሆንልኝ እመኛሎህ።

 

ጀግንነት!

ከወላጆቼ፣ከታላቆቼና ከመጽሃፍ፣ የድሮ የተጋሩ ጀግንነትና ተጋድሎ ብምሰማበትና በማነብበት ግዜ፣ ይህንን ታሪክ ተጋኖ ይሆን? እል ነበር። ኣለማወቄ "it is my bad" ለካ ኣልተጋነነምም፣ ኣልተጻፈ ይሆን እንጂ።

በዚሁ ዘመን ያለ ኢትዮጵያዊ ይሁን ትግራዋይ፣ ይሁን የኣለም ዜጋ፣የተጋሩን ጀግንነትና ጽናትን በመመስከር ይገኛል።በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ህብረተስብ ወደ ተሻለ ህይወት በመቀየር የኣንበሳው ድርሻ ይነበረው የትግራዋይ ጭንቅላት እንደሆነ በህይወቴ በማየቴ ደስታና ጀግንነት ይሰማኛል።

 

ኢትዮጵያ 1983 በፊት ምን እንደነበረች ኣታስታውሱም እንጂ፣ ("Short Memory" ተብላቹ የለ) ከኣለም መጨረሻ ድሃ እንደነበረች ላስታውሳቹህ።

የኢኮኖሚ መሰረታዊ የሆኑ መዋቅሮች -መንገዶች፣ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች፣ዩንቨርስቲዎች፣የሃይል ማመንጫ ግድቦች፣ የትግራዋይ ልፋትና ኣመራር በመሆኑ ጀግንነት ይሰማኛል።

-የትግራይ ተጋድሎ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለኣሰርተ-ኣመታት ያህል 10% በላይ በኣመት GDP እድገት ኣምጥቷል።

 

ብፖለቲካው!

-የትግራዋይ ተጋድሎ፣ ህግና ስርኣትን በመቅረጽ፣ ሁሉን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቛንቓው እንዲዳኝና፣ ባህሉን እንዲከበር ኣድርጓል።

-ሁሉም ኢትዮጵያዊ የራሱን ተውካዮች በመምረጥ የህገ መንግስቱን ባለቤት እንዲሁን ኣድርጟል። ምንም እንኳን የዛሪዎቹ  የትግራዋይ "ኣሽከሮች" ነበርን ብለው ይዋሹ እንጂ።

-የትግራዋይ ተጋድሎ ለህዝቦች እኩለነትና እድገት የሰራና የተሰዋ መሆኑን ሳስብ ጀግነነትን ይሰማኛል።

-ይህንን ብቻ ኣይደለም፣ የኣገሪትዋን ኣቅም ገንብቶ፣ የተሻለ ፖለቲካ ኣስተሳሰብ የፈጠራል በማለት ስልጣኑን በስላም ኣስረክቦ ሲያበቃ፣የገነባውን የህዝብ ሃብትና ኢኮኖሚ ለመዝረፍ ሲባል፣ የውስጥና የውጭ ጥገኞች፣የውሽት ፕሮፖጋንዳና ጦርነት ኣውጀው ከምድረ ገጽ ሳያጠፉት ኣመድ ልሶ ሲመለስ በህይውት እያሎህ በማየቴንና የህዝቤን ጀግንነት በመቋደሴ ደስተኛ ነኝ።

 

ስናይ 2014!ሰው ለሆናቹ!

Back to Front Page