Back to Front Page

ትግራይና አማራዊት ኢትዮጵያ

ትግራይና አማራዊት ኢትዮጵያ

 

ኻልኣዩ ኣብርሃ

12-1-21

 

መርጦ መብላትና እያዩ መዝለል፣

ያድናል ከቁርጠት ከመግባት ገደል።

ከዚህ ተሰባስቦ ከዛም ተጠራርቶ ሲጨፈጭፍ ትግራይ፣

ነበር ሲገለፍጥ መንጋጋው እስኪታይ።

ጅራት የነብሩን ጋማ ያንበሳውን ቀንድም የወይፈኑን፣

ካላበዱ በቀር ወደው ሞታቸውን፣

አይነኩም ነበረ ቢያማክሩ ሰውን።

የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ የተባለው ተረት፣

Videos From Around The World

የደርግ የተፈሪ የሚኒሊክ ድፍረት፣

ያዋጣ መስሏቸው ወሮ ገድሎ መቅረት፣

ትውልዱን ሳያውቁት ሳይገነዘቡት፣

ገቡ ከአዘቅቱ፣ ገቡ ከረግረጉ ከማይወጣበት።

ድሮ ነበረንጂ መጥኖ መደቆስ፣

አሁን ምን ይረባል ድስት ጥዶ ማልቀስ።

ይሄን ያበው ምክር በእብሪት ተጥሶ፣

በጉራ ፉከራ በጩኸት በስድብ ቅመም ተለውሶ፣

ለያዥ አልተመቸ ለገራዥ አልሆነ ገባ እሳት ጎርሶ።

 

ከእብድ ከመጋፈጥ ከንክ ከመፋጠጥ መሸሽ የመረጠው የወይኑ አውራ፣

ከሲቺዌሽን ሩም አጉል ተሳቀበት ውጊያ እንደፈራ።

በቀላል ድል ሰክሮ ትግራይን ሲያወድም፣

ሲማስ ነበር ቀብሩ እስከ ዘለአለም ይቺን እንዳይደግም።

ህልም ነው እውን ነው ዘመቻ አሉላ?

የአምላክ መአት ነው የሚሻ ምህላ?

ዱቄት ብረት ይዞ ቢያለብሰው ጦሩን፣

ረገፈ እንደቅጠል፣ አነሳ እጁን፣

እውነትም መአት ነው የሚዘገንን።

እናት እልል አለች የተገሰሰችው፣

ነፍሱ እፎይ አለች ገደል የገባው፣

ታሪኩ ታደሰ ውሃ የበላው።

ፃድቃናት ዘመሩ ለፈረሱት ደብሮች፣

ገበሬው ተፅናና ለታረዱት በሮች።

ሰብሉም ጎመራ እሳት ያቃጠለው፣

ሞፈሩም ጠገነ የተሰበረው።

ወፍጮና ምጣዱ የኑሯቸው ዋልታ፣

አለን አለን አሉ ምንም ብንመታ፣

ማሺን ይተካናል ትውልድ ሲበረታ።

ከግዛት ሞት ይሻል ቢራብም ቢጠማ፣

ጠላት ጥሎ መውደቅ ለፅኑ አላማ።

ክሊኒክ፣ ስኳላው፣ ፋብሪካው እንደሆን፣

በእጥፍ ይመለሳል እድሜ ለምሁራን።

 

ይብላኝ እንጂ ለሱ ለወራሪ መንጋ፣

ጨልሞበት ምድሩ መቸውም ላይነጋ።

በፈፀመው ድርጊት አዝኖ ከመፀፀት፣

ማሩኝ እንደማለት ላወደመው ንብረት፣

እየየ እንደማለት ላደረገው ድፍረት።

ላረከሰው ታቦት፣ ላፈረሰው ደብር፣

ያክሱም ተዋህዶ እንባዋን አፍስሳ ላምላክ ስትነግር፣

ንስሃ እንደመግባት መቆም በባዶ እግር፣

ሊያመልጥ ይፈልጋል እንዲያው በግርግር እንዲያው በክርክር።

ሰይጣን ይሻለናል ከአክሱም ፅዩን ሰው፣

ብለው ሲያበቁ ሃይማኖት አርክሰው፣

በስማም ብለህ ጀምር አሉት ለሚተኩሰው።

እናት አለም ትግራይ ጉድ ነው የገጠማት፣

ተበድላ እያለ አጥፊ ነሽ የሚላት።

ራሷን ላድን ብላ ታጥቃ ብትነሳ፣

አገር አፍራሽ ብሎ አሳያት አበሳ።

ያገዛትን ሁሉ በሰብአዊ ስሜት፣

ወንጀል አደረገው ላፍሪካ ነፃነት።

ወይ ነገር ማክበድ መቆለል መከመር፣

ከትንሽ ኩይሳ ተራራ እንደመፍጠር።

ህዝቡ በተራበ መንገድ በተዘጋ፣ ርስቱን በተቀማ፣

አለም ተጣላበት በኒዩርክ ከተማ።

 

አንዱ እረፍ ይላል ሌላው ተመለስ፣

ያስጠነቅቀዋል ሸገር እንዳይደርስ።

ወይ እነሱ አይቀጡ ወይ አይፈቀድለት፣

እንዲሁ አቁም ነው የተፈረደበት።

ህዝብን ለመቀስቀስ ለመላክ ዘመቻ፣

ስልጣን ላይ ቂብ ያለው ያገር አራሙቻ፣

አገር አፍራሽ አለው የትግራይን ህዝብ፣

የውጭ መንገድ መሪ የባንዳ ስብስብ።

ሳቀ ሞሶሎኒ፣ ከት ከት አለ ድርቡሽ፣ ገረመው ግብፃዊ፣

ትግራይን ባንዳ ነህ ሲለው ኢትዮጵያዊ።

ባይኖራት አሉላ፣ ባይኖራት ዮሃንስ፣ ባይኖራት ሓየት፣

ትሆን አልነበረ ምስራቃዊት ሱዳን፣ አፍሪካዊት ጣልያን፣ ደቡብ ግብፃዊት።

ኢትዮጵያን ለትውልድ አኑሮ ያቆየው፣

ማነው የተጎዳው ማነው የረገፈው?

ማነው የደኸየው ማነው ፍዳ ያየው?

መሃል አገር ሰፍሮ በምቾት በድሎት፣

ሳይገድሉ ጎፈሬ ቃላት ጀብድ መስሎት፣

አድዋ አድዋ ይላል የብቻው ድል መስሎት።

አሉላ መንገሻ ያጋመሱት ድል፣

ለቆየው ሚኒሊክ ከፈተለት እድል፣

ይወራል ዝንታለም እንዳማራ ገድል።

በተምቤን በማይጨው በጉራዕ በመተማ ምድር፣

በዶጋሊ ጉንደት እንዳልሰራ ታምር።

ትግራይ ባንዳ አለችው ውለታ ቢስ አገር።

ሰላሳ አመት ሙሉ ሲስላት ሲኩላት፣

ከአዘቅት አንስቶ በሰማይ ቢያኖራት፣

ሰላሟን አስፍኖ ባለም ቢያሳውቃት፣

ሞቷ ተቀንሶ ህዝቧን ቢያበዛላት፣

ጤናና ትምህርቷ ጉዞዋ ቢደላት፣

እጁን ነከሰችው፣ የሰውነት ባህርይ ይሉኝታ የሌላት።

 

መካድ አንድ ነገር፣ ማለት አልበደልኩም፣

አምላክ እንደማያይ የሆነው ሁሉንም።

ዞሮ ጣት መቀሰር በተበዳዩ ላይ፣

እንደ ግፍ ፈፃሚ መቁጠር እንደገዳይ።

አማራን ጨፍጫፊ የቡሃቃ ሌባ፣

የህዝብ ንብረት አጥፊ በወረረው አምባ።

እያሉ ሲቀሙት ስቃዩን ጩኸቱን፣

የገደል ማሚቶ ሲያስተጋቡት ድምፁን።

አለም ደካማ ነው ቀላሉን ይመርጣል፣

ተጎጂውን ትቶ ለጎጂው ይቆማል፣

የእውነት ድምፅን ሳይሆን ማሚቶን ይሰማል።

ይህ አልበቃ ብሎ ውንጀላው ክህደቱ፣

እንደ ባእድ መቁጠር ከጥንት መሰረቱ፣

አፉን በከፈተ ጊዜ ባጀገነው በማይባል አንቱ።

ትግራይ መዘለፏ የክብሯ መነካት የታሪክ መዘረፍ፣

ያነሰ ይመስል ያላዋቂው ስድብ የልጋጉ ጎርፍ፣

አንስቷል በጭፍን የዘረኛ ሰይፍ።

ባመጣው ጠብመንጃ ባመጣው እርሳስ፣

ተፈጠመ ጣልያን ካበሻ ሳይደርስ።

ብሎ የቋጠረው የድሮ ገጣሚ፣

እየነገረን ነው ከተገኘ ሰሚ።

ማን እንደሚጠፋ በደገሰው ድግስ፣

ስለት እንደሚቀድ መኖሪያውን ድጉስ።

አረም ነው ንቀለው ካንሰር ነው ቁረጠው፣

ሰይጣን ነው አማትበው ጅብ ነው አትጠጋው፣

ጁንታ ነው ግደለው እሰር አንገላታው፣

አርገው ማስፈራሪያ ክጭንቅላት አጥፋው፣

በከፋ ጥላቻ በጭካኔ ስሜት ከምድረገፅ ክላው።

ወይ ንዴት ወይ እብደት በመላ ኢትዮጵያ፣

የዘረኝነት ፅንፍ የሚዘልቅ ለወዲያ።

ሂትለር ይገርመዋል፣ ሂምለር ይደመማል፣

አፅሙ ከመቃብር ይገለባበጣል።

የአለምን ሬኮርድ ይዘን ስንመካ፣

እጅግ የሚበልጠን አበሻ ነው ለካ።

በማለት አዘኑ እጅጉን ተቆጩ ነገሩ አመማቸው፣

የኖቤል ሽልማት ባለማግኘታቸው።


Back to Front Page