Back to Front Page

በትግራይ ላይ ተግባራዊ የተደረገ የሶቬት ህብረት ጀኖሳይዳል ወታደራዊ ስትራቴጂ

በትግራይ ላይ ተግባራዊ የተደረገ

የሶቬት ህብረት ጀኖሳይዳል ወታደራዊ ስትራቴጂ

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 06-18-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ አሃዳዊት ሶቬት ህብረት አፍጋኒስታን በወረረችበት ዘመን በአፍጋን ህዝብ ላይ የፈጸመችው ግፍ በደል ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ጨምሮ ዓለም በአንድ ድምጽ ተቃውሞውን ማሰማቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያ፥ ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ማሊያ ከተባበሩት ዓረብ ኢምሬት ጋር በመምከርና በመዘከር በተጨማሪም በቀጣናው ጽኑ ፍላጎት ካላቸው ኃያላን መንግስታትና አገራት በተቸረላት ፍቃድ፥ የኤርትራ፣ የሱማሊያ፣ የተባበሩት ኢምሬት የሰውና የጦር መሳሪያ በማስተባበር በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈተችው የዘር ማጥፋት ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ህዝብ ላይ ያልተነገረ እንጅ ያልተፈጸመ ግፍ የለም የዚህ ጽሑፍ ዓላማ፥ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ፌክ የሆነ ስብእና የተጎናጸፈ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ከፊት ለፊት እየመራ ወደ ገደል እየጨመራት ያለችው የመቃብር ስፍራ ኢትዮጵያ እንደ ዳዊት እየደገመችውና እያነበነበችው ያለ መጽሐፍ ምንጭ ለማሳወቅ የወስላቶችና የአመንዝሮች አገር ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሰችውና እየፈጸመችው ያለ ሰቆቃ ልክ ለማሳወቅ ተጻፈ።

 

መንደርደሪያ፥ ትግራይ ህዝብ የደርግ ወታደራዊ መንግሥት፣ የጃንሆይ ዘውዳዊ አገዛዝ፣ የምኒሊክ ጠባብና ትምክተኛ አጺያዊ ሥርዓት፣ የግብጽ፣ የድርቡሽና የሌሎች የውጭና የውስጥ ወረራዎችና የጭቆና ስርዓት ያከሽፈና ያሽመደመደ ህዝብ ለመሆኑ ጠላቶቻችን ሊክዱት የማይችሉትና በሚገባ የሚያምኑበት ታሪክ በደማቅ ቀለም የጻፈው ሐቅ ነው። አፍጋኒስታን ህዝብ በተመሳሳይ አሰፍስፎ የመጣባት ልዕለ ኃያላን አገር ሁሉ እያስተናገደ፤ አንዳቸውም ያሰቡትን ሳያሳኩ በአንጻሩ፥ ውርደትና ኪሳራ እያከናነበ ሲሸኝ ዛሬ ላይ የተደረሰ ህዝብ ነው ራራማዋ አገር አፍጋኒስታን፥ በምሥራቅና በደቡብ በኩል ከፓኪስታን፣ በምዕራብ ከኢራን፣ በሰሜን ከቱርክሜኒስታን፣ ኡዝቤኪስታንና ታጂኪስታን፤ በሰሜን ምስራቅ ከቻይና የምትዋሰን ወደብ አልባ አገር ስትሆን ከደቡብ ምዕራብ በስተቀር አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በበረዶ በተሸፈኑ ተራራማ በጥልቅ ሸለቆዎች የተያያዘ አገር ናት አፍጋኒስታን ዕድሜ ጠገብ ተብለው ከሚታወቁ ትልቅ ታሪክ ካላቸው አገራት መካከል የምትበደብ አገር ስትሆን አፍጋኒስታንን ከወረሩ በወቅቱ ልዕለ ሃያላን የነበረች የሶቬት ህብረት አንዷ ናት። በጽሑፉ ዓላማ ከተገለጸው በተጨማሪ፥ በዚህ ጽሑፍ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ከኢምሬት፣ ከሶማሌና ከሱዳን ጋር መክረውና ዘክረው የሦስትዮሽ ግንባር ፈጥረው በትግራይ ላይ የፈጸሙት ወረራ ሶቬት ህብረት አፍጋኒስታንን ለመውረር ስታኮበኩብ ከጥንስሱ ለወረራው እንደ ምክንያት የተጠቀመችበት ስልትና ወረራውን ስትፈጽም በአፍጋኒስታናውያን ላይ የፈጸመችው ግፍና በደል ለመፈጸም ያስችላት ዘንድ ተግባራዊ ያደረገችው ወታደራዊ ስትራቴጂ በንጽጽር እንመለከታለን። ይህ ታሪካዊ ዕይታ ወራሪዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ በዕቅድ የፈጸሙት ግፍና በደል ግቡና መነሻ ዓላማው አጥርተን እንድንመለከት ስለሚረዳን ነው።

 

የእንግሊዝ ወረራ

 

19ኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዝ በቀኝ ግዛት የያዘቻት ከአፍጋኒስታን በስተደቡብ የምትገ ሕንድ በስጋት ዓይን ከምትመለከታት ራሽያ ወራራና ጥቃት ለመከላከል ስታስብ ያደረባት ስጋትና ፍርሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ለመቅረፍ በማሰብ አፍጋኒስታንን መውረር አለብኝ የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰችው እንግሊዝ አፍጋኒስታንን ለመውረር በሰማኒያ ዓመታት ውስጥ ሦስት ተደጋጋሚ ጦርነቶች ያደረገች ሲሆን በመጨረሻ .. 1919-1921 / በተካየደው ጦርነት ታላቅነትዋን፣ ኃይልዋንና የግዟትዋን ስፋት ለመግለጽ the empire on which the sun never sets! ተብሎ የተነገረላት እንግሊዝ በጦርነቱ ስትሸነፍ ዱላና ድንጋይ ይዞ የተሰለፈ የአፍጋን ህዝብ ድልን ተቀዳጀ፤ አፍጋኒስታን ነጻ አገር ለመሆን በቃች

 

 

የሶቬት ህብረት ወረራ

 

አፍጋኒስታንን የወረረች 2 ልዕለ ኃያላን አገር (በወቅቱ በነበረው አሰላለፍ) የዛሬይቱ ራሽያ የትናንቱ ሶቬት ህብረት ስትሆን ለጦርነቱ መንስኤ የነበረው በፕሬዝዳንት መሓመድ ከሃን የሚመራው ማዕከላዊ መንግሥት በኑር መሐመድ ታራኪ የሚመራው የግራ ዘመም አቀንቃኝ ወታደራዊ መኮንኖች መገልበጥ ተከትሎ የተዋቀረው አዲስ ኮሚኒስታዊ መንግስት ከሶቪዬት ህብረት ጋር የጠበቀ ወዳጅነት በመፍጠር ፍጹም አምባገነናዊ ባህሪይ በመላበስም በሪፎርም ስም ከአፍጋኒስታናውያን ባህል፣ ታሪክ፣ ወግና ልማድ ፈጽሞ የማይጣጣም የሶቪዬት ሶሻሊዝም ጥብቆ በህዝቡ ላይ በኃይል ለማጥለቅ ባደረገው ጥረት ከህዝቡ በገጠመው ከፍተኛ ተቃወም 1978 / መጨረሻ አከባቢ የተቀሰቀሰ ህዝባዊ ጦርነት ሲሆን ሶቬት ያስቀመጠችው መንግሥት ክፉኛ በመነቅነቁና በመነናጋቱ .. 1978 / የሶቪዬትና የአፍጋኒስታን የወዳጅነት ስምምነት ይደግፈኛ በሚል ምክንያትና ሰበብ አሻንጉሊትዋ ለመታደግ ታህሳስ 24 ቀን 1979 / አፍጋኒስታንን ለመውረር በቃች። ይህ በአፍጋኒስታውያንና ሶቬት መካከል የተካሄደው ጦርነት ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የመጀመሪያ የሶቪዬት ወታደራዊ ወረራ ሲሆን ታንኮችንና ልዩ ልዩ ዘመናዊ ከባድ መሳሪያዎች አስከትሎ የአፍጋኒስታን ሉዓላዊ ግዛት ጥሶ የገባው 100,000 ሺህ በላይ የሶቬት ሰራዊት ታድያ ፈና ዘና ብሎ በአፍጋኒስታን ምድር ላይ መመላለስ መርመስመስ የተቻለው ለሳምንታት ብቻ ነበር

 

መክበብ፣ መነጠልና መደምሰስ የሚል ጀኖሳይዳል ወታደራዊ ስልት ጽፎ ዘመቻውን የጀመረ የሶቬት ሰራዊት እንዳሰበውና እንዳቀደው ሳይሆን ወራሪ ኃይሎችን የአሰማ ስጋ ያህል የሚጸየውፍ የአፍጋን ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቻለውና በያዘው ሁሉ እምቢተኝነቱን በመግለጹ የአፍጋኒስታን ምድር የረገጠ የሶቬት ሠራዊት ሁሉ የተወለደበት ቀን ለመርገም ተገዷል። እንቢተኛው ሙጅሃዲን ቀን ቀን ይመለከተዋል፥ ሌሊት ሌሊት አጨዳ ላይ የተሰማራ ይመስል እንደ ቃጤማ ያነጥፏል። Ak-47 በቀር ሌላ እዚህ ግባ የሚባል ትጥቅ የሌለው የአፍጋን ታጋይ ዱላ መቋቋም ያቃተው እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀ የሶቬት ሠራዊት ሲጨንቀው ታድያ ትግሉን ያዳክምልኛል ብሎ ያመነውን ሌላ መንገድ መከተል ጀመረ። ይኸውም፥ ህጻ ሴት ሽማግሌ ሳይል ያልታጠቁ ንጹሐን ዜጎች በጅምላ መጨፍጨፍና ከቀያቸው ማፈናቀል እንደ አንድ ስታራቴጂ መከተል ጀመረ። ይህ አሰቃቂ የሶቬት ራዊት እርምጃ ሚሊዮኖችን ለስደት የዳረገ ቢሆንም ይህን የተመለከተ የአፍጋን ጎበዝ ግን በአንጻሩ ክፉኛ በመቆጣቱ የበለጠ እንዲቆርጥና ትግሉን እንዲቀላቀል ድርጎታል .. 1989 / የተጠናቀቀው ይህ ጦርነት አስራ አምስት ሺህ የሶቪዬት ወታደሮች ደም ደመ ከልብ ከማድረጉ በላይ ጦርነቱ የሶቬት ህብረት ቁጠባዊ ኢኮኖሚ ኩፉኛ እንደጎዳና በኋላም አገሪቱ መበታተንና መክሰም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ይነገርለታል።

 

 

የአሜሪካ ወረራ

 

Videos From Around The World

አፍጋኒስታን የወረረች 3 ልዕለ ኃያላን አገር አሜሪካ ስትሆን አሜሪካ አፍጋኒስታን የወረረችበት ምክንያት ተብሎ በሰፊው የሚነገረውና የሚታወቀው .. 2001 / ሦስት ሺህ ሰዎች ህይወት የቀጠፈና 25 ሺህ በላይ ቀላልና ከባድ ሚባል የአካል ጉዳት ያደረሰ በኒውዮርክ ከተማ ላይ የተንጣለሉ ሁለት ግዙፍ የንግድ ህንጻዎች ላይ የተፈጸመ የሽብር ጥቃት ተከትሎ ሲሆን ድርጊቱን በማቀናጀትና ተፈጻሚ በማድርግ ዋና ተጠያቂ ነው ብላ ያመነችበት የአልቃይዳ ሰው ኦሳማ ቢንላደን ለመያዝ ፍለጋ ነበር አሜሪካ አፍጋኒስታን የወረረችው አሜሪካ ከሞላ ጎደል በተጠና መልኩ የምታደርገው ግድያ ካልሆነ በቀር እንደ እንግሊዝ የሶቬት ገዳይ ሰራዊት የለየላት ነፍሰ ገዳይ ወራሪ ኃይል ባትሆንም ለአፍጋኒስታውያን ግን አሁንም ወራሪ ኃይልች ነበረች። መሬት ላይ የገጠማት ፈተናም በተመሳሳይ ለዘመናት ልምድ ያካባቱ የአፍጋን ታጋዮች ሰለባ ከመሆን አልተረፈችም። ታሊባንን ዋጋ ለማስከፈል አቧራ እያጨሰች የመጣችው አሜሪካ በአንጻሩ ነገሩ ተገለበጠና ታሊባን ያልተጠበቀ ዋጋ አስከፍሏታል። በአንድ ወቅት 100,000 ሺህ ሠራዊት (ይህ ቁጥር የኔቶ ሰራዊት ሳይጨምር ነው) ብታሰልፍም ድል ግን ሊቀናት አልቻለም።

 

አሜሪካ የተከተለችው ትራቴጂ ቀደም ሲል ከተመለከትናቸው አርመኔያዊ ስልቶችና ሴራዎች ሙሉ በሙሉ የተለየ፤ ከህዝቡ ጋር የመስራትና ህዝቡን በመሰረተ ልማት ዳግም የማቋቋምና የማስተማር ፕሮግራም ላይ አተኩራ ብትሰራም የአፍጋኒስታውያን ልብ ግን ማሸነፍ አልተቻላትም። የአፍጋኒስታውያን ፍላጎትና እምነት፥ ልማታችሁ ቀርቶብን አገራችን ለቃችሁ ውጡልን፤ ድልዲ፣ ህክምና፣ ትምህርት ቤት ወዘተ ስሩልን ብለን አልጠራናችሁም፤ አገራችን ሬት ላይ የተቀመጣችሁ ያለ እኛ ፈቃድ ነው፤ ስለዚህ እኛ የምፈልገው አገራችን ለቃችሁ እንድትወጡልን ብቻ ነው፤ እኛ ጋብዘን ካላመጣናችሁ ፊታችሁ ማየት አንፈልግም፤ መሬታችን ለቃችሁ እስካልወጣችሁ ድረስ ደግሞ እየሞትንም ቢሆን እንለቅማችሁኋለን፤ አፍጋኒስታን መሬት ላይ የጥይት ድምጽ ሳትሙ፣ ሳትቆስሉና ሳትሞቱ በሰላም መኖር የምትችሉ በእኛ መቃብር ላይ ነው! የሚል ድርቅ ያለ አቋማቸው ላይ በመጽናታቸው ይሄው ልዕለ ኃያልዋ አገር አሜሪካ ያስከፈላት የህይወትና የነዋይ ኪሳራ ሁሉ እንዳለፈ ወንዝ ወደኋላ ትታ ከሃያ ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው አሸባሪ ስትል ከፈረጀችው ከታሊባን ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ላይ ተወያይታ በተደረሰው ስምምነት መሰረት .. ግንቦት 1 ቀን 2021 / ጀምሮ አፍጋኒስታንን ለቃ ለመውጣት ተገዳለ

 

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን

በትግራይ ህዝብ ላይ ተግባራዊ ያደረጉት የሶቬት ሴራ

 

በምድር ታንክና መትረየስ በላይ በሰማይ ተዋጊ ጀቶችና ሄሊኮፕሮች እያንጃበቡ አፍጋኒስታን በከበባ ውስጥ አስገብተው የሚደመሰስ ደምስሰው የሚገደል ከገደሉ በኋላ የወደዱትን ለማድረግ ያቀዱ የሶቬት ወራሪ ኃይሎች በመቃወም እንቢ! ያለው የአፍጋን ህዝብ ትግል ለማዳከም ሶቬቶች ተግባራዊ ካደረጓቸው ጀኖሳይዳይ ወታደራዊ ስትራቴጂዎች መካከል ንዱ ዛሬ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙትና ያደረጉት አረመኔያዊ ወንጀል ነው። ይኸውም፥ ርሃብና በከባድ መሳሪያ የታገ በሰማይና በምድር የሚደረግ ድብደባ (starvation and bombing tactics) ይጠቀሳል በተለይ ገጠራማው የአፍጋን ህዝብ የእርሻ ሰብልና የእህል ክምችት ሙሉ በሙሉ እንዲወድም አንዲቃጠል ማድረጋቸው በተጨማሪ የቻሉትን ያህል በጅምላ ሲጨፈጭፉና ሲገድሉ የተቀረው በሚልየን የሚቆጠር ህዝብ ደግሞ ከቀየው በማፈናቀል ለስደትና ለእንግልት እንዲዳረግ ማድረጋቸው ታሪክ ይመሰክርልናል

 

የዚህ ተመሳሳይ ስልት ሌላኛው ዓላማ የተመለከትን እንደሆነ ወራሪው ኃይል የተቆጣጠሯቸው ከተሞች ላለመልቀቅ ሲሆን፥ የህዝቡን ሁለመናዊ እንዲቅስቃሴ መቆጣጠር ስች ዘንድ ታድያ የመጀመሪያ ስራው የመረጃ ተፋሰስ መቆጣጠር ነው ይህን ለማድረግ በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖርው ህዝብ ወደ ከተማ እንዲፈልስ በማድረግ የፈለሰውን ህዝብ በልዩ ልዩ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮችና ሴራዎች በመጠቀም በማስጨነቅ፣ በማሸማቀቅና በማሸበር በፍርሃት ውስጥ እንዲኖር በማድረግ የሚፈለገው አዲስ የአገዛዝ ሥርዓት ለመጫን ያስችለናል ብለው ስላመኑ ነው። በርግጥ፥ ሶቬቶች በወረራ የገቡባት የአፍጋን ምድር በዋሉ ባደሩ ቁጥር ተሸራርፈው ከማለቃቸው በተጨማሪ ከአስር ዓመታት በኋላም ቢሆን ከውርደትና ከኪሳራ በቀር አንዳች ነገር ሳያሳኩ ሽንፈት ተከናንበው የአፍጋኒስታን ምድር ለቀው ለመውጣት ተገደዋል።

 

ለአንዲት ቀንም ብትሆን በትምህርት ገባታ ላይ ሳይገኝ እንዲሁ በደብዳቤ የዶክትሬት ማዕረግ ባለቤት የሆነው የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸመውና ተግባራዊ እያደረገው ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ምንጭ ሌላ ንም ሳይሆን የዛሬይቱ ራሽያ የትናንቱ ሶቬት ህብረት የዛሬ 30 ዓመታት በአፍጋኒስታን ህዝብ ላይ ተግባራዊ ያደረገችውና የተባበሩት መንግስታት በሙሉ ድምጽ ያወገዘው በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው።

 

ልብ ይበሉ፥ የሶቬቶች የጭካኔ ልክ ሁሉም ስፍራ ላይ እኩል አልነበርም። ይኸውም፥ ትኩስና ቀዝቃዛ ስልት (hot and cold strategy) ይሉታል። ይህ ማለት አብዛኛውን ስፍራ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችና የደከሙ ሽምግሌዎች ሳይቀሩ ሰውና እንስሳ ሳይለዩ እንደ ችቦ ያነዱት ባሉበት ስፍራ ሁሉ በታንክና በከባድ መሳሪያ ሲጨፈጭፉት፣ አከባቢውም ሁሉ ውድማ ሲያደጉትና ሲያበርሱ በሌላ ስፍራ ደግሞ ሌላ ለዘብተኛ ሴራ በመጠቀም ነበር የአፍጋን ህዝብን ሲገዘግዙት ሲያበርሱት የነበሩት። ስድስት ወራት የደፈነው ወረራ ጋር በተያያዘ የዓለም ማኅበረሰብ በመቐለ ከተማ ከሚኖር ህዝብ ውጭ የተቀረው የትግራይ ከተሞችና ገጠሮች የሚኖ ተጋሩ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉና እንደሚገኙ ይሄ ነው የሚባል የተሟላ እውቀት የለውም።

 

በአንዳንድ የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች የዕርዳታ ሠራተኞች አማካኝነት ሸልኮው በሚወጡ መረጃዎች የሚሰማ የትግራይ ህዝ እያለፈበት ያለ ሰቆቋ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ለማመን የሚከብድ ነው። በምዕራብ ትግራይ ይኖር ከነበረው ህዝብ 1.2 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ እስከ አሁን የት እንደ ደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም። አጉላዕ፣ ዓዲ ግራት፣ ኢሮብ፣ ዕዳጋ ሓሙስ፣ ተንቤን ሀገረ ሰላም፣ ሳምረ፥ ጨምሮ በተለይ በአክሱምና በአድዋ ከተሞችና አቅራቢያ አከባቢዎች በምስል የተቀረጸው ጭፍጨፋ በጭልፋ መሆኑን ለመረዳት ተችለዋል። በውጭው ዓለም የሚኖረው ትግራዋይ ባደረጋቸውና ባሰማቸው የተቃውሞ ድምጾች እንዲሁም የዲፕሎማሲ ስራዎች የተነሳ የመቐለ ከተማ በከፊል ለዓለሙ ማህበረሰብ ክፍት ለማድረግ የተገደደው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት በመቐለ ከተማ ሳይቀር እንኳ ተፈጻሚ እያደረጋቸው የሚገኙ ሴራዎች መካከል አንዱ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ህልውና እንዳይኖረው የሚያደርግ ሶቬት ሰራሽ ሴራ ተግባራዊ ደረገ ነው።

ሌላው፥ የኢሳይያስ አፈወርቂ የዐቢይ አህመድ ዓሊና የምዋረተኞቹ የአማራ ልሒቃን ሰራዊትና ሚሊሻ፥ በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ጠላትነት የዕድሜና የጾታ ጉዳይ ሳይሆን ጠላትነታቸው ትግራ ከሚባል ደም ለመሆኑ የወረራው ሰለባ የሆኑትን የወራት ዕድሜ ያላቸው ህጻናት ጨምሮ በዕድሜ የገፉና የደከሙ አረጋውያን ሳይቀር እየተወሰደው ያለ እርምጃ መመልከት በቂ ነው አሁን ቀደም ሲል ወዳነሳነው በኢሳይያስ አፈወርቂ፣ በዐቢይ አህመድ ዓሊና ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን ፊታውራሪነት በትግራይ ህዝብ ላይ ተፈጻሚ እየተደረገ ስላለ ሶቬት ሰራሽ ዘር የማጥፋት ትራቴጂ በተመለከተ አራት አንኳር አንኳር ነጥቦችን አንስተን እንመልከት

 

1.      አስቀድሞ፥ የታመመ የሚፈወስበት የቆሰለ የሚታከምበት የጤና ኬላዎችና ሆስፒታሎች በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲሁም በአማራ ሚሊሻ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ሆነ ተብሎ እንዲወድሙና እንዲዘረፉ ከተደረገ በኋላ በመቀጠል ደግሞ ለሰው ልጆች ጤና አደገኛነቱ የተረጋገጠ አገልግሎቱ ያበቃለት የምግብና የዘይት ዓይነት በእርዳታ መልክ ወደ ህዝቡ እንዲደርስ በማድረግ በህዝቡ ላይ የጤና እክል በመፍጠር የትግራይ ህዝብ ሲስተማቲክ በሆነ መልኩ የማዳከም፣ የማብረስና የማንጻት ሴራ እየተሰራ ነው። ይህ ሁሉ፥ በጅምላ የተገደሉ መቶ ሺህዎች የሚሆኑ ንጹሐን ተጋሩ፣ ከአስር ሺህ በሚበልጡ 8 እስከ 90 የዕድሜ ባለጸጋ ተጋሩ ህጻናት ሴቶችና እናቶች ላይ በዓላማ የተፈጸመ ወሲባዊ ጥቃት ሌላ ወንጀል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ሰዎች ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ በመላ የአገሪቱ እስር ቤቶች ተይዘው በበሽታ እንዲያልቁ እየተደረገ ያለ አሰቃቂ ግፍና በደል ሳይጨምር ነው።

 

2.     ሌላው፥ የትግራይ ህዝብ ተምሮ የተሻለ ህይወት እንዳይኖር፤ እየደረሰበትና እየተፈጸመበት ካለ ውድመት አፈሩን አራግፎ ፈጥኖ እንዳይነሳ በድንቁርና ለማኖር ታስቦ እየተፈጸመ ያለ ወንጀል ሲሆን ይኸውም ትምህርት ቤቶቹ በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲሁም በአማራ ሚሊሻ ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙና እንዲዘረፉ መደረጋቸው ሳያንስ ከጥይት የተረፈውን ህዝብ ሆነ ተብሎ ቤት አልባ እንዲሆን ከተደረገ በኋላ የሚታጨቅባቸውና በረቀቀ ሴራ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ የሚመክንበት ስፍራዎች እንዲሆኑ መደረጋቸው ነው ከባቢያዊ ጸጥታ፣ ሀብት ማከማቸትና የኢንተርኔት አገልግሎት የሚባል ነገር ትተን፥ መሰረታዊ የሆነ የህክምና አገልግሎትና መድኃኒት ማግኘት፣ መማሩ ቀርቶ ስለ ትምህርት ማሰብ፣ የተመጣጠነና ገንቢ ምግብ መመገብ፣ ስራ መስራት የሚባል ነገር ለትግራይ ህዝብ በአሁን ሰዓት የቅንጦት መገለጫዎች ሆኗል። የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ እንዳሳወቀው 4.5 ሚሊዮን የሚሆን ትግራዋይ የዕለት ምግብ እንደ ሌለውና በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ታድያ በኢሳይያስ አፈወርቂ አስተባባሪነት የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሰራዊትና የአማራ ልሒቃን ሚሊሻ ቅንጅት በትግራይ ላይ የከፈቱት ጦርነት ምን ያህል በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነና የዘመቻው ዓላማ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ለማብረስ ታልሞ የተሰራ ስራ ለመሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ጭብጥ ነው።

 

3.     በአከባቢው የገንዘብና የፋይናንስ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በተጠና መልኩ ባንኮቹ በኢትዮጵያና በኤርትራ የሰራዊት አባላት እንዲዘረፉ ተደርጓል። በአሁን ሰዓት በመቐለ ከተማ ከሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ ባንኮች በቀር በመላ ትግራይ የሚገ ባንኮች ተመልሰው አገልግሎት ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ይገኛሉ። የዚህ ሴራ ዋና ዓላማ፥ የትግራይ ህዝብ ተሎ ወደ እንቅስቃሴ እንዳይገባ፣ በሚደረገው የንግድ ልውውጦች እንደገና እንዳያቆጠቁጥና እንዳያንሰራራ ለማድርግ ያለመ ሲሆን ለወደፊቱም ቢሆን ራሱን ችሎ እንዳይቆምና ተመጽዋች ሆኖ እንዲኖር ስለ ተፈለገ ነው። በተጨማሪም፥ የወደሙና የተዘረፉ ፋብሪካዎችና መሰረተ ልማቶች፣ የግልና የመንግስት ንብረቶች ልብ ይሏል።

 

4.    ሌላውና ዋነ ነጥብ ደግሞ የሰው ልጆች በህይወት የመኖር ዋስታ ምሰሶ የሆነው የምግብ ጉዳይ ነው። ሲጀመር የኢሳይያስ አፈወርቂ፣ የዐቢይ አህመድና የአማራ ልሒቃን አጀንዳ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ እንደ ህዝብ ማብረስና ማንጻት ነውና በተለይ ገጠራማው የትግራይ አከባቢዎች የሚገኝ የእርሻ ሰብልና የእህል ክምች የቻሉትን ያህል ዘርፈውታል የተረፈውን ደግሞ በእሳት በማያይዝ እንዲቃጣልና እንዲወድም አድርጓል። ይህ ንጽሐን በርሃብ የመቅጣት ዒላማ ያደረገ ሶቬት ሰራሽ ሴራ ቀደም ሲል እንደተገለጸው የትግራይ ህዝብ ትግል ለማዳከም ያለመ ነው። ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ ከማጣት የተነሳ ለበሽታና ለስቃይ ሲዳረጉ ወላጆች አርፈው ይቀመጣሉ፤ ሽማግሌዎች በርሃብ ሲያልቁ ልጆች ቁጭ ብለው ያለቅሳሉ፣ ቅስማቸው ይሰበራል! ነው ስሌቱ ታድያ ይህ ሁሉ ግፍና በደ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈጸም የዓለም ማህበረሰብ አያውቅምን?

 

የዓለም ማኅበረሰብ ወዴት አለ?

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ ሆነ ዐቢይ አህመድ ዓሊ እንዲሁም ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን የትግራይ ህዝብ ልብ ሊያሸንፉ እንደማይ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በመሆኑም፥ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ብለው አልሰሩም፤ እየሰሩትም አይደለም። አማራጭ ብለው የሚያምኑት እየሰሩት ያለ ስራ ህዝቡን በጥይት በርሃብና በበሽታ በመጨረስና በጨፍጨፍ የተረፈው ደግሞ በወገኑ ላይ እየተፈጸመ ያለ ግፍ እያየ ተሸማቆ እንዲኖር ልዩ ልዩ የሶቬት የሽብር ታክቲኮች ተግባራዊ በማድረግ ላይ ተጠምዷል በርግጥ፥ ኢሳይያ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን፥ የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ መግደል እንችላለን! ብለው የሚያምኑ ቂሎች ካልሆኑ በቀር የትግራይ ህዝብ ለማንበርከ ሲባል ተግባራዊ እያደረጉት ያለ ተውሶ የተገኘ ጸረ ሰው ሰይጣናዊ ስልቶችና ወጥመዶችም ቢሆን ወራሪው ኃይል የሚፈልገውን ያህል ውጤት ሊያስገኝለት እንደማይችል የታወቀ ነው። ለምን? ህዝባዊ ወያነና ሓፂርን መሪርን ዓወትና ናይ ግድን ! ብሎ የሚያምን የትግራይ ህዝብ ለክብሩና ለነጻነቱ ፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የቆረጠ ህዝብ ከመሆኑ በላይ እየሆነና እየተፈጸመበት ባለ ነገር ተደናግጦ ትግሉን ስለማያቆምም ነው።

 

ጥያቄው፥ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጨምሮ መላ የዓለም ማኅበረሰብ ቃል በቃል በትግራይ እየሆነ ስላለ ነገር በማስመልከት በሰጡት ምስክርነት በትግራይ እየተፈጸመ ያለ ድርጊት የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው! ሲሉ እውቅና ከሰጡ በኋላ 21ኛው ክፍለ ዘመን ይህ የመሰለ እጅግ አሰቃቂ የሆነ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድና ዓሊና የአማራ ልሂቃን ለማስቆም ወደ ፍትህ ለማቅረብ ያልቻለበት ምክንያት ለብዙዎ እንቆቅልሽ ቢሆንም ለእኛ ለተጋሩ ያለን ብቸኛ አማራጭና ተስፋ ምዕራባዊያን ሳይሆኑ አንድነታችን አጠናክረን የጀምርነውን ትግል ግቡ ማድረስ መቻል ለመሆኑ ትርጓሜ የማይሻው የተገለጠ ሐቅ ነው።

 

መፍትሔው

 

መጽሐፍ በቃኝ ባልክ ጊዜ ቀንበሩ ከጫንቃህ ላይ ትሰብራለህ እንዲል፥ የተከፈለ መስዋዕትነት ይከፈል፤ የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ፥ ለእኛ ለተጋሩ ያለን ብቸኛ አማራጭ ጠላቶቻችን ታግለን መጣል ነው።

 

v ትግራዋይነት ታግለህ መጣል ነው።

v ትግራዋይነት ለዓላማ መቆምና ለዓላማ መሞት ነው።

v ትግራዋይነት ለክብራችንና ለህልውናችን ሲባል የሚከፈለውና መከፈል የሚገባውን ማንኛውም ዋጋ መክፈል ነው።

v ትግራዋይነት ከእኔነት ያለፈ ቤዛነት ነው።

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሆነ ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን ዕድላቸውን ለመሞከር ያህል ከዓረቡም ከምኑም የሰውና የመሳሪያ ዓይነት አሰባስበው መጥተው ወረራ ፈጸብን እንጅ በተናጠል መጥተው ታግለው የትግራይን ህዝብ እንደማያሸንፉት አሳምረው ያውቃሉ። እሁን እያደረጉት ያለ ሽርጉድም ቢሆን የሚፈጥሩት አዲስ ነገር ኖሯቸው ሳይሆን የከሸፈባቸው ትግራይን ከካርታ የመፋቅ ዘመቻ ቀርቶባቸው ለድርድር የሚያበቃ ቁመና ይዘው ለመውጣት የሚያስችላቸው የህልውና ጥያቄ ነው የሚያሯርጣቸው ያለ።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ አማራን በጠራራ ፀሐይ ገድሎና ጨፍጭፎ ሲያበቃ ተመልሶ ደግሞ ዘራፍ እያለ ቀረርቶ ያሰማ ዘንድ አክሮባት ሲያሰራው እያየ ክት ብሎ መሳቅ ተችሎት ይሆናል። መብቱን የጠየቀ የኦሮሞ ህዝብ በጥይት እየቦደሰ ሲለቅመው የተሰበሰበ ህዝብ መበተን ተችሎት ይሆናል። በሱማሌ የሆነው እናንተ ላይም ይሆናል ብሎ ሲዝትባቸው ደቡቦች እኔ የለሁበትም እያሉ አንድ በአንድ እንዲሸሹ ማድረግ ተችሎት ይሆናል። ሰዎች የሚፈልጉትን በመስጠት ወጥመድ ውስጥ ማስገባት ይቻላል ብሎ ሚያነው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይህን ተፈጻሚ በማድረግ አፋርና ሱማሌ ማስመጥ ተችሎት ይሆናል። አሁን ታድያ የደረሰው ኬላው ላይ ነው። በሚገባ የሚፈተሽበት ስፍራ። እንከን የተገኘበት እንደሆነ የእጁን የሚያገኝበት ስፍራ።

 

v ትግራዋይ፥ ተመትቶ የሚያለቅስ፣ እየተለቀመም በባዶ የሚፎክርና የሚሸል ህዝብ አይደለም።

v ትግራዋይ፥ ኧረ ፌዴራል ፖሊስ እየመጣ ነው እያለ ገና ለገና ቤቱን ቆልፎ የሚቀመጥ ህዝብ አይደለም።

v ትግራዋይ፥ የጥይት ድምጽ ሲሰማ የሚበተን ህዝብ አይደለም።

v ትግራዋይ፥ ዘይትና ስንዴ ይዘህ ስትሄድ ሃሳቡን የሚቀይር ህዝብ አይደለም።

v ትግራዋይ፥ በዘመናት መካከል ራሱን ችሎ የቆመ፣ የራሱ ልዩ ታሪክ፣ የራሱ ባህልና የራሱ የፖለቲካ ስልጣኔ ያለው፣ በቁጥር ጥቂት ሳለ በቁጥር የሚመኩ ትምክህተኞች እያጥመለመለና እያሽመደመደ እጁን ያነሰበት ወራሪ ኃይል ሁሉም እየሰባበረ የመጣ የማይላስ የማይቀመስ እሳት ነው።

v ትግራዋይ ዘር ነው። በገደልከው ቁጥር ትግሉን የሚያፋፍምና ለወራሪ ኃይሎች የማይመች ረመጽ ህዝብ ነው።

 

ጥጉ፥ ትግራዋይ ለወራሪ ኃይሎች የሚንበረከክ ህዝብ ሳይሆን ምዋርተኞችና ነፍሰ በላ ቡዳዎች የዋጡትን የሚያስተፋ የቡዳ መድኃኒት ነው። መተተኞቹና ቡዳዎቹ ደግሞ ይህን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ከዚህም ከዚያም ወዝ የሌለው ሌግዮን (በቁጥር ብዙ የሆነ ሠራዊት) አሰባስበው የመጡብን። መፍትሔው? ክብርህንና ህልውናህን ጠብቀህ ታስጠብቅ ዘንድ ፈጣሪ በሰጠህ የትግራይ ተራሮች ከፍታ ላይ ተቀምጠህ በእግሩ የመጣውን ወራሪ ሬሳውን እንደ ኤልሳ ቆሎ እያሸግክ ወደመጣበት አገር መላክ ነው። የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ቅናትና ምቀኝነት የሰለጠነባቸው የአማራ ልሒቃን ከእንግዲህ ወዲህ ሰበር ዜና ብለው ለኢትዮጵያ የሚያወሩላት ወሬ አይኖርም። ካወሩም፥ መሸነፋቸውን አምነው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከወያነ ትግራይ ለድርድር መቀመጣቸው ብቻ ይሆናል።

 

ትግራዋይ ዘበለ ኹሉ ክገብሮ ዝኽእል ነገር እንተዳኣ ገይሩ ትግራይ ክትስዕር !

 

ይህ ጽሑፍ አድዮስ ኢትዮጵያ ከሚል አዲስ መጽሐፍ የተወሰደ ነው። መጽሐፉን ለመግኘት አማዞን የገበያ ድረ ገጽ በመግባት የመጽሐፉን ስም በመጻፍ ማግኘት ይቻላል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

 

Back to Front Page