Back to Front Page

ትግራዋይ፥ የወስላቶች አገር ከሆነችው አመንዝራይቱ ኢትዮጵያ ክፍል የለውም

ትግራዋይ፥ የወስላቶች አገር ከሆነችው አመንዝራይቱ ኢትዮጵያ ክፍል የለውም

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 02-15-21

 

መሪ ቃል፥ “ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፥ ወደ ቤጥ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን አሉት። ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ አላቸው። ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት። ሴቲቱም ማለዳ መጣች፥ ጌታዋም ባለበት በሰውዮው ቤት ደጅ ወድቃ እስኪነጋ ድረስ በዚያ ቀረች። ጌታዋም ማለዳ ተነሣ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፥ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፤ እነሆም ቁባቲቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ወድቃ፥ እጅዋም በመድረክ ላይ ነበረ። እርሱም፥ ተነሺ እንሂድ አላት፤ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፤ በዚያን ጊዜ በአህያው ላይ ጫናት፥ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ሄደ። ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ። ያየም ሁሉ፥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም፥ አልታየምም፤ አስቡት፥ በዚህም ተመካከሩ፥ ተነጋገሩም ይባባል ነበር። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፥ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም አገር ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ። ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ የሆኑ የሕዝብ ሁሉ አለቆች ሰይፍ በሚመዝዙ በቍጥርም አራት መቶ ሺህ እግረኞች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ቆሙ” ይላል። (መጽሐፈ መሣፍንት 19)።  

 

Videos From Around The World

ቅምሻ፥ “ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው!” የሚል ኃይለ ቃል ያልሰማ ዜጋ ቢኖር ገና ከእናቱ ማህጸን ያልወጣ “ሰው” ብቻ ነው። ይህ ቃል፥ ራሳቸውን ችለው መቆም የማይችሉ፣ በዘመናት መካከል ልዩ ልዩ ማስክ እያጠለቁ ካልሆነ በቀር ፊት ለፊት የመምጣት ድፍረቱ የሌላቸው፣ በሴራና በክፉ ተንኮል የበሰበሱ፣ ጉልበታቸው እንደ እባብ ምላሳቸው ላይ የሆኑና አፍዝ አደንግዛቸውን በመርጨት የሚታወቁ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ለዘመናት ንግዳቸውን ያጧጧፉበት ሐሰተኛ መፈክር ከመሆኑ በላይ በጥሩ ዕቃ የተዘጋጀ መርዝም ነው። በመሆኑም፥ “ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው፣ ኢትዮጵያዊነት አንድነት ነው፣ ኢትዮጵያዊነት ፈሪሓ እግዚብሔር ነው…” ወዘተ በማለት የሚታወቁ ተመጻዳቂዎች ህይወት ምን ያህል ከእውነት የራቀና ግብዞች እንደሆኑ ለማሳየት፥ እንደ ባንዴራ የሚያውለበልቡትን የክርስትና እምነት ለፖለቲካዊ ፍጆታቸው ከመጠቀም ያለፈ በህይወታቸው ላይ ቦታ እንደሌለውና እንደማይሰጡትም በተጨባጭ ለማሳየትና አመጸኛ ድርጊታቸውን ለመመስከር መጽሐፍ ቅዱስ መነሻ ያደረጉ ጽሑፎች ማዘጋጀት ግድ ብሏል። 

 

ኢትዮጵያ ግፍ ፈጽማብናለች

 

የወስላቶቹ አገር አመንዝራይቱ ኢትዮጵያ በትግራይ ህዝብ ላይ በአደባባይ የፈጸመችውና እየፈጸመችው ያለ ግፍና በደል የማይገልጸው ሰቆቃ ይሄው የትግራይ ህዝብ ታሪክ አካል ሆኖ በታሪክ ተከትቧል። ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩት፥ ወስላቶች፥ ጠማማዎችና አመዝራዎች፤ መንገዳቸውም ሸካራ ሲሆን በምኞታቸው ተጠምደው የሚጠፉም ናቸው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ልታገለግላችሁ የምትፈልጉ ከሆነና የምትፈልጉትን ሁሉ ያለ አንዳች ከልካይ ከኢትዮጵያ ማግኘት የምትችሉ፥ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ከካርታ መፋቅ ሲቻል ነው! በማለት ኃያላኑን ደጅ በመጽናት፤ ከእነሱ ባገኘው ፈቃድና ይሁንታ መሰረትም ከኤርትራና ከሱማሌ እንዲሁም ከኤምሬትስ መንግስታት ጋር ግንባር በመፍጠር፤ “ተጠቃሁ” የሚል ሐሰተኛ ወሬ በመንዛትም፥ የአማራ፣ የሱማል፣ የአፋርና የኦሮሞ በጥቅሉ ግማሽ ሚልዮን የሚያህል ሠራዊት አሰልፎ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመውና እየፈጸመው ያለ ትልቁም ትንሹም የትግራይ ተወላጅ የማረድና የመግደል፣ ከተሞቹን በእሳት የማቃጠል፣ ሀብት ንብረቱን የመዝረፍና የማውደም፤ በአጠቃላይ ትግራይ የሚባለውን ግዛት ዳግም ላያንሰራራ ሙሉ በሙሉ ውድማ የማድረግና የትግራይ ህዝብ ለማጽዳት እየተደረገ ያለ ሁለገብ የሆነ የጥፋት ዘመቻ በቃላት ተጽፎ የሚገለጽ አይደለም።

 

ያለ በደላቸውና ኃጢአታቸው ሰለባ ያደረጋቸው የዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ የኢሳይያስ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የሶማል፣ የአፋርና የኦሮሞ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት ነፍሳቸውን ለማትረፍ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ገብተው የተጠለሉ ህጻናትና ሽማግሌዎችን ሳይቀሩ በግፍ በጅምላ መረሸኑና መጨፍጨፉ ሳይበቃቸው በገቡበት ከተማ ሁሉ በሴቶች እናቶቻችንና እህቶቻችን ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት የሚገኝ ለሰሚ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ወሲባዊ ጥቃት ጨምሮ ህዝብን የማሸበር ወንጀል ዓለምን አስደምሟል። በሌሊት በጨለማ በርሃውን እያቆራረጡ ረጅም የእግር ጉዞ  ተጉዞው ድንበር አቋርጠው ሱዳን ከገቡ ስልሳ ሺዎች ወገኖቻችን መካከል የኢትዮጵያና የኤርትራ ሠራዊት አመንዝራ ባህሪይ ሰለባ የሆኑ የመቶዎቹ የእህቶቻችንና የእናቶቻችን አሰቃቂ ምስክርነት እንደተጠበቀ ሆኖ፥ ከሳምንታት በፊት በልዩ ልዩ ማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ይፋ የሆነው አንድ ቪድዮ እንደተመለከትነው፥ አንድ የአጉላዕ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አባት የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሠራዊት ተወካዮች በተገኙበት ስብሰባ ባደረጉት ልብ የሚሰብር ንግግር መካከል በዓይናቸው ያዩት፥ በከተማቸው የተፈጸመ አስነዋሪ ድርጊት ሲሆን ይኸውም፥ የካህን ሚስት በኢትዮጵያ ሠራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ መደፈርዋንና እንዳመነዘሩበትም የሰጡት ልብ የሚሰብር ምስክርነት ነው።

 

ቢ.ቢ.ሲ በትናንት ዕለት “Ethiopia's Tigray crisis: 'I lost my hand when a soldier tried to rape me'” ሲል ይዞት በወጣ አጭር ዘገባ፤ በኢትዮጵያ ሠራዊት ከደረሰባት አሰቃቂ ግፍ የተነሳ ከሁለት ወር በላይ በህክምና ስትረዳ የቆየችው በአሁን ሰዓትም ህክምና ላይ የምትገኝ በተንቤን የዓቢይ ዓዲ ከተማ ነዋሪ ከሆነችው አንዲት የአስራ ስምንት ዓመት ሴት ልጅ ትግራዋወይቲ ምስክርነት የሚያስነብብ ነው። እንደ ቢቢሲ ዘገባ፥ ታህሳስ 3 የኢትዮጵያ ሠራዊት መለዮ የለበሰ ወታደር ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንደገባና የትግራይ ታጋዮች የት እንዳሉና እንደሚገኙ እንዲነግሩት ከጠየቃቸው በኋላ፤ ቤቱንም አገላብጦ ፈትሾ ምንም ሳያገኝ ሲቀር የቤተሰቡ አባላት አልጋ ላይ እንዲተኙ እንዳዘዛቸው፤ በያዘው መሳሪያ ቤቱን ዙሪያ መለሽ ሞንፊት እንዳደረገውና ሽማግሌ አያትዋን የመዋች ልጃቸው ልጅ ከሆነችው ከልጅ ልጃቸው እንዲተኙ እንዳዘዛቸው፤ አያትዋም ወታደሩ የሰጣቸው ትዕዛዝ እምቢ በማለታቸውና ትዕዛዙን ሳይቀበሉት በመቅረታቸው ወታደሩ ሽማግሌውን ወደ ውጭ በማስወጣት ትክሻቸውና እግራቸው ላይ ደጋግሞ እንደተኮሰባቸው፤ ወደ ቤት ተመልሶ በመምጣትም አያትዋን እንደገደለውና ማንም የሚታደጋት እንደሌለ በመግለጽ ልብስዋን እንድታወልቅ ሲያዛት አበክራ ብትለምነውም ልመናዋን ከቁብ ሳይቆጥር ምኞቱን ለማርካት ደጋግሞ እንደመታት፤ ድብደባው እየበረታባት ከመምጣቱ የተነሳ ብትዳከምም ለደቂቃዎች እንደታገለችውና በመጨረሻም ተናዶ አፈ ሙዙን አዙሮ ቀኝ እጅዋን ሦስት ጊዜ እግርዋንም በተመሳሳይ ሦስት ጊዜ ተኮሶ በጥይት እንደደበደባትና ከውጭ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ጥሏት እንደሄደ የሚያስነብብ ነው።

 

ይህን ዜና ያነበቡ የውጭ አገር ዜጎች የስራ ባለደረቦቼ ስሜታቸው ክፉኛ ከተነካና ከተጎዳ፤ ከትግራይ ውጭ የሚኖር ትግራዋይ ይህን አሰቃቂ ድርጊት በተደጋጋሚ ሲሰማማ ምንኛ ቁጣው ሊነድበት እንደሚችል ለመገመት ኣስትሮፊዚስት መሆን አይጠይቅም። የወስላቶቹ አገር አመንዝራዊቱ ኢትዮጵያ የውጭ አገራትና መንግስታት ሠራዊት አስገብታ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመችው ወረራና እየፈጸመችው ስላለ ወንጀል በሚገባ ሂሳብ የምንወራረድበት ሰዓት እሩቅ አይደለም። የትግራይ ህዝብ የህይወት መስዋዕነት ከፍሎ ያፈራው ሀብትና ንብረት አውድማና ወርሳ፤ ከጥይት የተረፈው የትግራይ ህዝብ በርሃብ እንዲያልቅ የእርሻ መሬቱንና እህሉን በእሳት አቃጥላ፤ ትግራዋይ እንደ ቅጠል ረግፎ ለማየት ምግብና መድኃኒት ከልክላ፤ ከተሞቹን አውድማ፤ በደል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው እያፈናቀለች ወደ ግዞት አውርዳ፤ የትግራይ እናቶች ሽልማት፣ ብርና ወርቅ ዘርፋ፣ እህቶቻችን አስነውራና አራክሳ ስታበቃ፥ ኢትዮጵያ የሰላም እንቅልፍ ተኝታ ታድራለች ብሎ የሚያስብ ዜጋ ካለ ሲበዛ የዋህ ነው። መጽሐፍ “ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ” እንዲል የግፈኞች ፍጻሜ እሩቅ አይደለም።

 

በርግጥ፥ መጽሐፍ “ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው። የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፤ የማንም ዓይን አያየኝም ይላል ፊቱንም ይሸፍናል” እንዲል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ የኢሳይያስና የአማራ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለው ግፍና በደል አላየሁም አልሰማሁም! በማለት በአንጻሩ ሲሳለቁብን የሰማንና ያየን እንደሆነ በእውነቱ ነገር ሊደንቀንና ግራ ልንጋባ አይገባም። አመንዝራ ህዝብ፥ በንጹሐን ሰዎች ላይ ግፍ ሲፈጸም እያየና እየሰማ አላየሁም አልሰማሁም! ማለት የባህሪው ነው። ትግራይ ህዝብ ደግሞ እንዲህ ካለ አስነዋሪ የአመንዝሮች ባህሪይ ሆነ ስራ ምንም ዓይነት ህብረት የለውም።    

 

አመንዝራይቱ ኢትዮጵያ ግራ ቀኛቸው የማያውቁ ህጻናት ሳይቀር የትግራይ ተወላጆች በሆኑ ዜጎች ላይ ሁሉ በጅምላ እየፈጸመችው ያለ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት አሰቃቂ ግፍና ወንጀል ለመቃወም በቅድሳት መጻህፍት ላይ በግልጽ እንደተገለጠ፥ እውነተኛ አማኝ መሆን ብቻ ነው የሚጠይቀው። በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ግፍና በደል ለመቃወምና ለማውገዝ ትግራዋይ መሆንን አይጠይቅም። በሰው ላይ የሚደርሰው ግፍና በደልን ለመቃወም ህሊና ቢሶችን የሚጸየፍ አእምሮ ያለው ሰው መሆን ብቻ ነው የሚጠይቀው።

 

ክፉ ድርጊትና አመጸኝነትን ለመቃወም፥ አመጻን የሚቃወም፤ እውነትና ጻድቅን ፍትሓዊነትና መልካምነትን በማድረግ ደስ የሚለው፤ ከአድሏዊነት የጸዳ፤ ሩክሰትንና አመንዝራነትን የሚጸየፍ፤ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር እግዚአብሔር አምላክ የሚያውቅ፣ የሚፈራና የሚያመልክ፤ በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ህይወቱን በጽድቅ የሚመራ ሰው መሆን ብቻ ነው የሚጠይቀው። አንድ ህሊና ያለው ባለ አእምሮ ሰው ዓቢይ አህመድ ዓሊ፥ “አስተዳድረዋልሁ፣ ግዛቴ ነው!” የሚልውን ህዝብና መሬት የሌሎች አገራትና መንግሥታት ሠራዊት አስገብቶ ሲጨፈጭፈውና ሲያስጨፈጭፈው እያየና እየሰማ ቆሞ አይመለከትም። ዳሩ ግን፥ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም! ብለው ስለሚያምኑ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ከኤርትራ፣ ከሱማሌና ከኤምሬትስ ጋር ግንባር ፈጥሮ ሲወጋን፤ ለወራት፥ ውሃ፣ መብራት፣ ትራስፖርት በጣጥሶ፤ ባንክ፣ ምግብና መድሃኒት ከልክሎ፤ ከድሮን ድብደባ የተረፈ ህዝብ በርሃብ ሲቀጣ፥ ኢትዮጵያውያን ደስተኞች ናቸው። ይህ የምለው፥ ታሪክ በታሪክነቱ ለማስፈርና ለመከተብ ያህል እንጅ በዚህ ጉዳይ በተመለከተ ኢትዮጵያውያን ሊኖራቸው የሚችል አቋምና እምነት ከጠቀመም ለራሳቸው ለኢትዮጵያውያን ብቻ ነው ሊጠቅም የሚችለው። ኢትዮጵያውያን ሊኖራቸው በሚችል ማንኛውም ዓይነት አቋም የተነሳ የሚበርደው ሆነ የሚሞቀው ትግራዋይ የለም። ለምን? እስከ ዛሬ ድረስ የመጣንበትን መንገድ ስህተት ነበር ባይባልም ትግራይ ከአሁን በኋላ የምትጓዝበት ጎዳና ተመሳሳይ ስህተት የሚፈጠርበት ዕድል አይኖርምና።

 

ትግራዋይ፥ ከአታላይቱና ከዳተኛይቱ ኢትዮጵያን ጋር ምንም ክፍል የለውም

 

v  ምዋርተኛ ማንነታቸውን እያወቅን ስናስጠጋቸው ከሚያርቁን፤

v  ከነእድፋቸው በርህራሄ ዓይን አይተን ስንቀበላቸው ከሚያገሉን፤

v  በችግራቸው ላይ ደርሰን የእርዳታ እጃችን ስንዘረጋላቸው ከሚያሴሩብን፤

v  ሰላማችንና ዕድገታችን ከማይፈልጉ፤

v  ታሪካችን፣ ባህላችንና ሥልጣኔያችን ደም ከሚያስቀምጣቸው፤  

v  ደርሰንባቸው ሳይሆን እንዲሁ ትግራዋይ ማንነታችን ከሚያስከፋቸው፤

v  ሽለላና ቀርርቶ፣ ፉከራና ድንፋታ በማሰማት የሚታወቁ፤

v  ምላሳቸው ከዘንዶ ምላስ ይልቅ የከፋ፤

v  ከመሳደብ፣ ከመራገምና ከማጉረምረም ውጪ ቁምነገር ከማይገኝባቸው፤ ምቀኞችና ምዋርተኞች ጋር ትግራዋይ ምንም ክፍል የለውም።

 

እውነት ነው መጽሐፍ፥ “የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ” እንዲል ይህን ሁሉ ከማድረግ አንቦዝንም። የሚረግሙንን መመረቅና ስለሚያሳድዱን መጸለይ አንተውም። በሃይማኖት ስም፣ በፍቅር ስም፣ በአንድነት ስም፣ ወዘተ ሊገድሉንና ሊያጠፉን ሲመጡ ግን በራችን ከፍተን አንጠብቃቸውም። መርዝ ያበሉንና ያጠጡን ዘንድም ክፉ ከሚያስቡልን ሰዎች ጋር አንድ መዓድ ላይ አንካፈልንም፤ አንቀመጠምም። በልባቸው ሞት እየተመኙልን በአፋቸው ከሚሸነግሉን ግብዞች ጋር ህብረት አንፈጥርም። ኢትዮጵያ፥ የአገሪቱ ዘር የሆነው የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋትና ለማመናመን ያልቆፈረችው ጉድጓድ ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም። ኢትዮጵያ፥ በአንድነት፣ በፍቅር፣ በኢትዮጵያዊነት፣ ስም የንጹሐን ዜጎች ደም ማፍሰስ የለመደች የደም መሬት ሌላ ሁሉም ነገር አልቆባት፥ መንዳቢዎችን መጋቢዎች እያለች ነፍሰ ገዳዮችን መስቀል አስይዛ በመላክ የንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ የምታደርግ መተትና ምዋርት የሰለጠነባት የመቃብር ስፍራ ናት። ጥጉ፥ ትግራዋይ ከዚች በንጹሐን ዜጎች የጨቀየችው፥

 

v ህጻናትና ካህናትን እንደ ከብት አጋድማ የምታርድ፤

v ነፍሰ-ጹር እናቶችን የምታሳድድ፤

v ሠራዊትዋን ልካ፥ የአንስት መነኮሳትና ደናግል ክብረ ንጽህና በአደባባይ የምታራክስና የምትደፍር፤

v ዕድል ፈንታዬ፣ ርስቴና መሸሸጊያ እግዚአብሔር ነው! ብሎ ሰውና እግዚአብሔር በማገልገል የሚታወቅ የካህን ሚስት የምታስነውር፤

v በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት የሰው ልጅን በርሃብ የምትቀጣ፤

v አብያተ ክርስቲያናትና ቅዱሳት መጻህፍትን በታንክና በመትረየስ የምታፈራርስና የምታቃጥል፤

v በሐሰተኛ ወሬ የንጹሐን ደም የምታፈስ፤  

v ንጹሐን ዜጎች እንደ ጎመን የምትመነጥር፤

v ሰዎች በደል ተገኝቶባቸው ሳይሆን በትግራዋይነታቸው ወደ ውህኒ የምትወረውር፤

v የተጋሩ ህብትና ንብረት የምትዘርፍ፤

v የደከሙትን ሽማግሌዎች በጉልበታቸው የምታስኬድ፤

v ጅብ ከሚበላኝ ጅብ በልቼ ልቀደስ! ባዮች የኃይማኖት መሪዎች በመላክ የተገፋውን ህዝብ በድጋሜ የምትገፋ፤

v ፈሪሃ እግዚአብሔር የራቀባትና የሌላት፤ የግፈኞች፣ የምዋርተኞችና የነፈሰ ገዳዮች አገር ጋር ጉዳይ የለውም። መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ! ካልሆነ በቀርም፥ ኢትዮጵያ፥ በቅድሳት መጻህፍት ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በማፍሰስ የምትታወቅ የኤልዛቤል መናገሻ ዙፋን ናት።   

 

ኢትዮጵያ፥ የንጹሐን ዜጎች ደም ጠጥታ የማትጠግብ የመቃብር ስፍራ ናት። ኢትዮጵያ፥ የአመጸኞችና የአመዝሮች አገር ናት። መጽሐፍም አለ፥ “የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና” እንዲል። ኃጢአት፥ አታድርግ የተባልከውን መድረግ ብቻ ሳይሆን፤ አድርግ የተባልከውን አለማድረግን ጭምር ነውና ትግራዋይ፥ የውስላቶቹ አገር አመንዝራይቱ ኢትዮጵያ አስነዋሪ ተግባር በመቃወም ከእውነት ጋር ይቆማል እንጅ የግብዞች ማንነት ተላብሶ ራሱን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ አይጠራም።

 

እየሸራረፍን ጉልበታቸው እስኪዝል ድረስ እናብረከርካቸዋለን እንጅ አንበረከክም!

 

የትግራይ ህዝብ፥ ኢትዮጵያ የሚትባለው የመቃብር ስፍራ ከመፈጠርዋ በፊት የራሱ የሆነ፥ ታሪክ፣ ባህል፣ ሥልጣኔ፣ የስነ ልቦና ውቅር፣ ወግና ልማድ ያለው በዘመናት መካከል ለማንም ሳይንበረከክ፤ የሠራዊት ብዛት የማያስደነግጠው፤ ኃያላንን ወጊድ! ማለትን የሚያውቅ፤ ለህልውናውና ለማንነቱ ልጆቹን እየገበረና የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ፣ በደሙ ታሪክ እየጻፈ፥ ዛሬ ላይ የደረሰ የተፈተነ ህዝብና መንግስት ነው። የዐቢይ አህመድ ዓሊ ህገ-ወጥ መንግሥት በአንጻሩ እንደ ጣሊያን ፋሽሽታዊ መንግሥት፥ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም የመጣ ወራሪ ኃይል ነው። በተጨማሪም፥ ትግራይ፥ የሚገድልም የሚያድንም አንድ አምላክ ብቻ ነው! ብላ የምታምን አገር እንጅ፤ በፈጣሪ ቦታ ራሱን ያስቀመጠ ያልበሰለ አምባገነን የምትቀበል አገር አይደለችም። መሽረፈት የተባለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ (መሽረፈት ወስላታ ማለት ነው)፥ በትግራይ ምድር ላይ አምልኮና ውዳሴ የሚቀበልበት የመሰውያ ስፍራ ሊሰራ ቀርቶ (መንግስትነት ሊያቆም ቀርቶ) ለመቃብር የሚሆን ስፍራ የለውም።

 

የትግራይ ህዝብ፥ እየተራበና እየተጠማ፣ እየደማና እየቆሰለ፣ እየተሰደደና እየሞተ፥ ክብሩና ሉዓላዊነት ያስከብራል እንጅ ኢተጌ ተጣሩ ብሎ አቤት የሚል ህዝብ አይደለም። የወሰደውን ጊዜ ይውሰድ፣ የተከፈለውን የህይወት መስዋዕትነት ይከፈል፣ ታሪካዊት ሀገረ ትግራይ ለማልማት የተከፈለው የህይወት መስዋዕትነት አሰር በመከተል፥ ዛሬም ዘመኑ በሚጠይቀው የትግል ስልት ሁሉ ራሳችንን በማስታጠቅ የጣላቶቻችን ጉልበት እያሽመደመደና እያጥመለለመልን ታሪካዊ ስፍራችንን እንጠብቃለን። እዚህ ላይ፥ የውስጥም የውጭም ጠላት ሊያውቀውና ልናስታውሰው የምንፈለገው ሐቅ ቢኖር፥ ትግራይን በኃይል ለመግዛት የተነሳ ማንኛውም ወራሪ ኃይል ሁሉ፥ እየሸራረፍን ጉልበቱ እስኪዝል ድረስ እናብረከርከዋልን እንጅ፥ የኤለክትሪክ፣ የትራንስፖርት፣ የባንክ፣ የስልክ፣ የውሃና የኢንተርኔት አገልግለቶች በማጥፋትና በመቆራረጥ፤ ምግብና መድኃኒትም በመከልከል፣ በድሮንና በጀት፣ በታንክና በቡዝቃ በመደብደብና በመጨፍጨፍ እንደማያብረከርከን ግልጽ ሊሆን ይገባል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page