Back to Front Page

የ"ከተሜው" እና የ"ኦሮ-ማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች ልዩነታቸው እና አንድነታቸው፣

"ከተሜው" እና "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች ልዩነታቸው እና አንድነታቸው፣ ኤርሚያስ ለገሠ እና ሀብታሙ አያሌው እንደ ማሳያ

 

==========================================

 

ታሪኩ ተዘራ 08-31-21

 

 

 

 

እስካሁን በድፍኑ ነበር አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎችን የምመለከታቸው፣ "ኦሮ-ማራ" ጨፍላቂ ኃይሎች በማለት፤ ሆኖም ግን ኤርምያስ ለገሠ እና ሀብታሙ አያሌው አስር ወር (የትግራይ ጦርነት ከተነሳ አንስቶ) ያላቸውን "ትልቅ" የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት በደምብ በማጥናት፣ "ከተሜው/ አዲስ አበቤው" እና "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች አንድ እንዳልሆኑ ተመልክቻለሁ። ሕብረ-ብሔራውያን ፌደራሊስት ኃይሎች ለሚያደርጉት ትግል ይጠቅም እንደሆነ ይህችን አጠር ያለች ጽሑፍ ማካፈል ፈለግኩ።

Graphical user interface

Description automatically generated

"ከተሜው" ("አዲስ አበቤው" ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ወዘተ) አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች [ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሠ] "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች ፍላጎት የተለየ ነው፤ ሕብረብሔራዊው ፌደራሊስት ኃይሎች በብዙ ነገራቸው የቀረቡ ናቸው፤ "መሠረታቸው" [አያት ቅድመ አያታቸው] ሕብረ ብሔራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች ስለሆኑ።

"ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች ሕብረ-ብሔራዊው ፌደራሊዝም የሚቃወሙት በዋነኝነት ከአማርኛ ውጭ የሚያውቁት ቋንቋ ስለሌላቸው [በኢትዮጵያ ከሚነገሩት ቋንቋዎች ማለቴ ነው](አማራ ግን አይደሉም!) ስለሆነም "አፍ መፍቻ ቋንቋቸው" ሊተዳደሩ ስለሚፈልጉ፣ እና በሚኖሩበት ከተማ በግዝያዊነት ሳይሆን፣ "የከተማው ባለቤት" መሆን ስለሚፈልጉ ብቻ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነሱ ቦታ ሆኖ ቢመለከተው፣ ትክክል ናቸውም ደግሞ። አዲስ አበባ ተወልደህ አድገህ "በሕግ/ሕገመንግሥት" "የአዲስ አበባ ባለቤት አይደለህም!" ስትባል ያበሳጫል፤ ቆሽትን ያስርራል፤ ሕገ-መንግሥቱን ለመቅደድ ያነሳሳል።

"ኦሮ-ማራ" ጨፍላቂ ኃይል ግን (ለምሳሌ ሀብታሙ አያሌው) ኢትዮጵያ "-ማራ" ወይም "ኦሮ-" ማድረግ ነው የሚፈልጉት፣ ስለሆነም "ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይሎች ብዙም አይግባቡም። የ"ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል በትንሹ የሚግባባው "ኦሮ-ማራ" ሳይሆን "ኦሮ-ማራ" አንደኛው ክንፍ፣ ማለትም "-ማራ" (አብን መራሹ) አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል ነው፤ ከሱ ጋርም የሚስማሙት በቋንቋ ብቻ ነው! አማርኛ ብቸኛ የአገሪቱ የፌደራል የስራ ቋንቋ ሆኖ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። ከዚህ በተረፈ "ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል፣ "-ማራ"/"አብን" ጨፍላቂ ኃይል ብዙም አይስማሙም። አማርኛ ቋንቋ ብቸኛ የአገሪቱ የፌደራል የስራ ቋንቋ ሆኖ እንዲቀጥል ከሚፈልግ ውጪ፣ "ከተሜው/አዲስ አበቤው" ሕብረ-ብሔራዊ ኃይል [ለምሳሌ የድሮው ኢሕአዴግ ዓይነት] "አብን" የተሻለ ኃይል እንደሆነ ይገነዘባሉ።

ለዚህ ነው አሁን "-ማራ"/"አብኑ" ሀብታሙ አያሌው እና "ከተሜው / አዲስ አበቤው" ኤርሚያስ ለገሠ ያለው የፖለቲካ ልዩነት በዚህ አስር ወር ግልጥልጥ እያለ እየወጣ ያለው።

"ከተሜው / አዲስ አበቤው" ኤርሚያስ ለገሠ የጦርነት አስከፊነት በደምብ ይገነዘባል፣ ጦሩነቱ ሕብረ-ብሔራዊው ኃይል ብያሸንፍ፣ ወይም ደግሞ "ኦሮ-ማራ"/ ፒፒ አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል ብያሸንፍ፣ "አዲስ አበቤው/ከተሜው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል ብዙም ለውጥ እንደሌለው ጠንቅቆ ይገነዘባል፤ እንዲያውም "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊው ጨፍላቂ ኃይል ከተሳካለት እና "ኦሮ-ማራ" ደግሞ "ኦሮ-" ከገነገነ ትልቅ ኪሳራ እንደሚገጥመው ጠንቅቆ ይገነዘባል፤ አማርኛ ቋንቋ ስለሚዳከም እና የአዲስ አበባ ባለቤትነት ሕልሙን እንደማይሳካለት ስለሚገነዘብ።

ስለሆነም "ከተሜው / አዲስ አበቤው" ኤርሚያስ ለገሠ ሁሉም የጦርነት ተፋላሚዎች እኩል ይኮንናል፤ የድሮውን ኢሕአደግ "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል የተሻለ እንደሆነ በደምብ ይገነዘባል፤ የድሮ ኢሕአዴግ የሚመስል ፌደራሊስት ኃይል ብያገኝ አብሮ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ይገነዘባል። ባጭሩ፣ "ከተሜው / አዲስ አበቤው" "ኦሮ-ማራ" አሓዳዊው ጨፍላቂ ኃይል የሶስት ዓመት የቁልቁለት ጉዞ ተስፋ ቆርጦአል፤ ፒፒ/"ኦሮማራ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል በሥልጣን እንዲቀጥል አይፈልግም።

በተቃራኒው ደግሞ፣ የ"-ማራ"/"አብኑ" [ለምሳሌ የሀብታሙ አያሌው] አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል፣ ፒፒ/"ኦሮ-ማራ" እንዲፈርስ ሳይሆን የሚፈልገው፣ "-ማራ" የሚዘውረው ፒፒ/"ኦሮ-ማራ" እንዲሆን ነው ፍላጎቱ። ሆኖም ግን ይኸ ምኞት እንጂ የአሁኑ ጦርነት እንደ ዕድል እንኳ ፒፒ/"ኦሮ-ማራ" ቢያሸንፍ (ይኸ የመሆን ዕድሉ ወደ ዜሮ የተጠጋ ነው) "-ማራ"/"አብን" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል "ቀዳማዊ/መራሽ" ኃይል የመሆን ዕድሉ ዜሮ እንደሆነ ያልገባው የደናቁርት ስብስብ ነው ይኸ አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል። [ሒሳብ በደምብ የሚገነዘበው አዲስ አበቤው አሓዳዊው ጨፍላቂው ኤርሚያስ ለገሠ (የሒሳብ መምህር ነበርኩ ሲል የሰማሁት መሰለኝ) ይኸንን የሁለት ወደ ዜሮ የተጠጉ ቢሆኖች (probability) ውጤቱ ያው ወደ ዜሮ በእጁ የተጠጋ እንደሆነ ጠንቅቆ ይገነዘባል፤ ሀብታሙ አያሌው እና መሰሎቹ ግን ይኸንን የሚገነዘቡ አይመስሉም።] ስለሆነም፣ "-ማራ"/"አብኑ" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል፣ ጦርነት እንዲቆም ሳይሆን ቀን እና ሌሊት የሚወተውተው፣ አንድ ፍሬ ጥይት እና አንድ ወታደር እስኪቀረው DC/ዲሲ ተቀምጦ ዕድሉን ለመሞከር ጦርነቱ ያጋግላል፤ ውጤቱ ወደ ዜሮ ለተጠጋ ጦርነት ሕዝብን ያስፈጃል። ከዚህ ዓይነት ድንቁርና ይሰውራችሁ ነው የሚባለው።

ለማጠቃለል፣ "ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል ለሕብረ-ብሔራዊው ፌደራሊስት ኃይል የቀረበ ነው፤ ስለሆነም፣ "ሓቀኛ" ፌደራሊስት ኃይሎች "ከተሜው / አዲስ አበቤው" አሓዳዊ ጨፍላቂ ኃይል ሊወክል የሚችል "ለዘብተኛ (ጨፍላቂ ያልሆነ) አሓዳዊ ኃይል" በውስጣችሁ እንዲኖር ብትሰሩ ይመከራል፤ ለምሳሌ "ኅብር" ይኸንን ካላደረጋችሁ ግን፣ "ከተሜው" ሆድ እና ጀርባ መሆናችሁ ይቀጥላል፤ ስለሆነም፣ በጦር ሜዳ የምታገኙትን ድላችሁ ዘላቂነት ላይኖረው ይችላል።

 

 

Back to Front Page