Back to Front Page

መፍትሔው ትግራዋይ ብሔርተኝነት ነው

 

መፍትሔው ትግራዋይ ብሔርተኝነት ነው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል (ስትራቴጂስት) 01-30-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ ዓለትን እየሰነጠቀ የምንጭ ውኃ፣ ሰማያትን እየከፈተ መናን አውርዶ እስራኤልን የመገበና ያጠጣ አምላክ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ምህረት ካለወረደና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፥ ከእንግዲህ ወዲህ ትግራዋይ ብሎ ኢትዮጵያዊ የለም። ለፍትህና ለእኩልነት ታግሎ ያታገለ ትግራዋይ፥ የነፍሰ-ገዳይ ባህሪ ከተላበሰች ከዳተኛይቱ ኢትዮጵያና አምልኮተ ጣዖት ከሆነው ኢትዮጵያዊነት ምንም ዓይነት ሕብረት ሆነ ክፍል የለውም። ትግራዋይነት ብቻውን፥ የነበረና አሁንም ያለ እውን ማንነትና ጽኑ መንግስትነት ነው። በመሆኑም፥ መጽሐፍ በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ እንዲል ማንኛውም ትግራዋይ፥ ትግራዋይነት አንድም ትግራዋይ ብሔርተኝነት እውነት ነው፤ ትክክል ነው! ሲል በአደባባይ ለሚያራምደው ግልጽ የሆነ እምነትና አቋም ጋር በተያያዘ ከማንኛውም ወገን ለሚነሳ ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ምክንያታዊነት ለማቅረብ ያለመ ነው።

 

መንደርደሪያ፥ በአንድ ወቅት ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ሴረኞች ተሰበሱና ወደ ኢየሱስ ይመጣሉ። እንዲም አሉት፥ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ? ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ ይሉታል። ልብ ይበሉ፥ ምን ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ? እንዲል ሰዎቹ ቻይነቱን የሚፈታተን ብቻ ሳይሆን ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ እያሉ የብሉይ ኪዳን መጻህፍት አጣቅሰው ኢየሱስን ሲሞግቱ፤ ሰዎቹ እውነት ስላላቸውና በእውነቱ ነገር ለሰሚ ጆሮ እንደሚመስልም ኢየሱስ ጥያቄቸውን ተቀብሎ ከሰማይ መና አውርዶ ቢያሳቸው፥ በርግጥ አንተ ስግደትና አምልኮ የሚገባ አምላክ ነህ! ብለው አምላክነቱ አምነው እንደሚቀበሉ ሳይሆን የሰዎቹ አባባልና አቀራረብ በምክንያት ሆዳቸውን የሚሞሉበት ሴራ ማሴራቸው ነው። በእነሱ ቤት መጻህፍትን ማጣቀሳቸው ኢየሱስን ማታለላቸው ነው። እስቲ እውነተኛ ከሆንክ እንደ ሙሴ መና አውርድና እንይህ ሲሉት፤ ኢየሱስ በሴራቸው ተጠልፎ መና እንዲያወድና እንዲበሉ እየበሉም እንዲያሾፉበት እንጅ ኢየሱስ መና በማውረዱ እንዲያምኑት አምነውም እንዲቀበሉትና እንዲከተሉት አይደለም። የሰዎቹ ክፋትና ሴራ ይበል! የሚያሰኝ ቢሆንም ኢየሱስን የሚያልፍ ግን አልነበረም። ሰዎቹ መርፌ ሆነው እየወጉ ቢመጡም ኢየሱስ ግን እያጣበቀ የሚሄድ የማይበጠስ ክር ነበር።

Videos From Around The World

 

ጎበዝ፥ እነዚህ በአንደበታቸው ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት እያሉ ባንዴራን እንደ ልብስ አሰፍተው፣ እናት አገሬ እያሉ ፊታቸው እየቧጨሩና ጸጉራቸውን እየነጩ መሬት ለመሬት ሲንከባለሉ የምናውቃቸው ግብዞችና አስመሳይ አረመኔዎች ቅድሳት መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት፥ አፉቸው ከቅቤ ይልቅ የለዘበ፥ ቃላቸውም ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው። ስራቸውም የሚሰሩ በተንኮልና በሴራ ነው። ሴረኛና ተንኮለኛ ሰው ሲገድልህም ሲቀብርህም ጦርና ጋሻ ይዞ ሳይሆን እኔ ነኝ ያለ ድግስ ደግሶ ነው። ክፉና ምዋርተኛ ሰው ባለንጀራውን የሚያጠፋ እጥፍ ዝርግት እያለና እየተሽሞነሞነ ነው። ኮሓልቲ መሲለን መንቆርቲ እንደሚባለው። ታድያ፥ ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሲባል እውነት መስሎህ በተከፈለ ልብ የቆምክ እንደሆነ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ትቆርጥ ዘንድ ቁርጥ ያለ መልዕክት እጽፍልህ ዘንድ ወደድኹ። ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት ወዘተ በሚል ዲስኩራቸው የሚታወቁ አስመሳይ ግለሰቦችና ቡድኖች፤ በእውነቱ ነገር ሰዎቹ፥ በፍቅር፣ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስለሚያምኑ ሳይሆን ሰሚ ጆሮ የሚያጠምዱበት ወጥመድ ነው።

 

አንድነት ሆነ ፍቅር የሚጠላ ዜጋ የለም፤ ሊኖርም አይችልም። የአንድነትና የፍቅር ውጤት የሆነው ኢትዮጵያዊነትም እንዲሁ በተመሳሳይ መልካም ነገር ነው። ዳሩ ግን ይህ ሁሉ ውሸት ነው፤ እውነትነት የለውም። ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት! ወዘተ እየተባለ የሚዘፈነው ዘፈንና የሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ሁሉ ዜጎችን እንደ ከብት ለእርድና ለሞት የሚያዘጋጅ የአሞሌ ጨው ነው። ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት የሚሉ የተለመዱ የአማርኛ ቋንቋ አባባሎች በጥሩ ዕቃ የተዘጋጁ መርዛማ አበባዎች ናቸው። እውነት መስሎት የገባ ያለ እንደሆነም ይሰምጣል እንጅ አይተርፍም። የተረፈና የሚተርፈው ይህን ሰይጣናዊ ስራቸው የነቃባቸው፣ ነቅቶም መሰሪ ገበናቸው ሲያጋልጥባቸውና ሲያራቁታቸው፥ ብሔርተኛ፣ ጸረ ማሪያም፣ ገንጣይ አስገንጣይ ወዘተ የሚሉ ጥራዝ ነጠቅ ታፔላዎች እየለጠፉ የሚያሳድዱትና የሚገድሉት ዜጋ ብቻ ነው።

 

ትግራዋይ ብሔርተኝነት የትምክህት በሽታ ፍቱን መድሃኒት ነው

 

በአንድነትና በኢትዮጵያ ስም፥ ክብርህን ገፎ፣ ማንነትህን አጥፍቶ፣ ታሪክህንና ስልጣኔህን ፍቆ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብትህን አዋርዶና አራክሶ፣ ከሰው ተርታ አውጥቶና አውርዶ፥ በገዛ አገርህ በኃይልና በጉልበት ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የሚቋምጠውን አስመሳይና አታላይ ኃይል እምቢ ማለት፣ በልጦ መገኘትና ማሸነፍ እንዴት ነው ብሔርተኛ የሚያስብለው? ሐቅን ይዞ እምቢ ያለ፣ የሰውን አልፈልግም የራሴንም አሳልፊ አልሰጥም ብሎ ፍትሓዊነትን የሰበከና ያነገሰ፣ የከረመውን ችግር ከምንጩ ለማድረቅ ብሎም ሰላምና ፍቅር የነገሰባት አገርና ህዝብ ለመገንባት የተሻለውን አስታራቂ መንገድ የያዘ ሰውና ማኅበረሰብ ብሔርተኛ ከተባለ፤ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ሆኖ ሳለ ዳሩ ግን፥ ባንዴራ እያውለበለበ፣ የአዞ እንባ እያነባም እምዬ እናት አገሬ ልደፋልሽ! እያለ የንጹሐን ዜጎች ደም የሚደፋ፣ አልፎም ተርፎ የእግዚአብሔር ስም እየጠራ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም ህጻናትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ንጹሐን ዜጎችን እንደ ከብት አጋድሞ የሚያርድ፣ ደም የተጠማ የዛር መንፈስ የነገሰባቸው ሴሰኞች፣ ሌቦችና ነፍሰ-ገዳዮች ሆነው ሳሉም ጻድቅ መስለው የሚመጻደቁ አስመሳዮችና ሐሰተኞች ምን ሊባል ነው? ለመሆኑ፥ ብሔርተኛ ማን ነው? ብሔርተኛ ማለትስ ምን ማለት ነው? ብሔርተኝነት እንደ ነውርና የስድብ ቃል በመጠቀም ሌላውን በማሳጣት ስራ ላይ የተጠመዱ ተሳዳቢዎች ራሳቸው ምንድን ናቸው? እነሱን የማይመስልና ተቀበል ሲሉት አሻፈረኝ የሚላቸውን የነቃና የበራለት ጭምት ዜጋ ለማሳጣት በሚያመች መልኩ ብሔርተኝነት ማለት እንዲህና እንዲያ ነው እያሉ ኃይለ ቃሉ የጭራቅ መልክ ሰጥተው እንዲተረጉምት ሥልጣኑ የሰጣቸው ማን ነው? ብሎ ጥያቄ ማንሳቱ አስፈላጊ ነው።

 

በነገራችን ላይ፥ የብሔርተኝነት እውነተኛ ትርጓሜና ዓላማ፥ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ስም አረንጓዴ ቢጫ ቀር ባንዴራ እያውለበለ የዜጎች ተፈጥሮአዊ ክብርና ማንነት የሚገፍና የሚያጠፋ አስመሳይ ኃይል እንደሚለውና እንደሚነዛው ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ብሔርተኝነት ዲሞክራሲያዊ ፍትሓዊነት ነው። ብሔርተኝት የስድብ ቃል አንድም ሊያሸማቅቀን የሚገባ አሉታዊ ኃይለ ቃል ሳይሆን በአንጻሩ፥ ኢትዮጵያ እንደ አገር ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ አብሯት ለመጣው የአማራ ልሒቃን ርካሽ የእኔነት አስተሳስብ ፍቱን መድሃኒት ነው። ብሔርተኝነት የአንድ የነቃ ግለሰብ/ማኅበረሰብ ልዩ መታወቂያ ነው። ብሔርተኝነት አያሳፍርም፤ የሚያሳፍረው፣ ወጊድ ተብሎ ሊወገዝም የሚገባው በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለማሳጣት የሚሰራ ክፉ ተንኮልና ሴራ ነው። ብሔርተኝነት አደጋ ነው ከተባለ እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያዊነት ስም የሚያቀነቅኑት እንወክለዋለን የሚሉት የአማራ ገበሬን እንኳ የማይወክል ብሔርተኝነት ነው።

 

የአማራ ልሒቃን ሐሙቱ ስለሌላቸው የእኛ የሚሉት የአንድ ብሔር የበላይነት ለማንገስ አማራ የሚል ቋንቋ እያስተጋቡ ፊት ለፊት አይመጡም። ታድያ መርዛቸውን የሚረጩ፥ ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት ወዘተ በሚሉ ለአፍ የሚጣፍጡና ሰሚ ጆሮ የሚሰልቡ የውሸት ቃላቶች መርጠውና ፈብርከው ነው። እነዚህ ሰዎች ስልጣን ላይ ቢወጡም ችግር፤ ቢገፈተሩም ችግር ፈጣሪዎች ናቸው። በርግጥ አንዳንዶች፥ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ እንደ አገር የገባችበት አዘቅት የኦሮሞ ልሒቃን የፖለቲካ ብቃትና ብስለት ማነስ፤ ብሎም የአስተዳደር ችሎታና ክህሎት ማጣት እንደሆነ አድርገው የሚሞግቱ አሉ። ይህ አባባል ሙሉ ለሙሉ መሰረት የለውም ተብሎ የሚነፈግ አባባል ባይሆነም የኦሮሞ ልሒቃን ችግር ተብሎ የተጠቀሰው ምክንያት ግን በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ እንደ አገር ለገባችበት ድቅድቅ ጨለማ ዋና ምክንያት ሆኖ ሊያገለግል አይችልም። የዚህ ሁሉ እልቂትና ደም መፍሰስ ዋና አቀነባባሪ የኦሮሞ ልሒቃን የእርስበርስ መናከስና መጠፋፋት እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም ሾልኮ የገባ የአማራ ልሒቃን የፖለቲካ ሴራ ነው። ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም፣ ኢትዮጵያን ለመምራት አልበቃም፤ የሚል ትርክትም የአማራ ልሒቃን በጨለማ የሚጋግሩት ፕሮፓጋንዳ ነው። በርግጥም የእነዚህ ሰዎች የተቃወሰ ሥነ ልቦና ፈጽሞ ካልደቀቀና ካልተፈወሰ የምታርፍ አገር ሆነች የሚፈወስ ህዝብ አይኖርም።

 

የጠላቶቻችን ፍርሃትና ስጋት የወለደው ቅናትና ምቀኝነት

ወደ ጥላቻ አድጎ ያመጣብንን እንመልከት

 

የሆነብንን ቆም ብለን እናስብ። ይህ ሁሉ እልቂትና ውድመት ከሰማይ አልወረደም፤ አንድም፥ የአንዲት ሌሊት ጽብና ኩርፊያ ውጤትም አይደለም። ይህ ሁሉ እልቂትና ውድመት መንስኤ አለው። የአማራ ልሒቃን ኢትዮጵያን እንደ ፈለጉት አድርገው ለመግዛት እንዳይችሉ ሽባ አድርጎ ያስቀመጣቸው ትግራዋይ እንደሆነ ያምናሉ። ከትግራይ ህዝብ በቀር የሚፈሩት ህዝብ እንደሌላቸውም ይመድራሉ። በቁጥር አነስተኛ ነው ተብሎ የሚታወቀው ከትግራዋይ በቀር ሌላውን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬም እንደ ከብት ሊነዱት እንደሚችሉ ደረታቸውን ገልብጠው ይናገራሉ። የአማራ ልሒቃን በትግራዋይ ፊት የሚያወጣውጧት ነገር ብትኖር የማትሞት ያልተጠመቀች ምላሳቸው ብቻ ናት። የሚያሰሙት የተካኑበት ሽለላና ቀረርቶም ራሳቸውን ለማጽናንት የሚያሰሙት ባዶ ጩኸት ከመሆኑ አልፎ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። የአማራ ልሒቃን አይደለም በውናቸው በህልማቸውም ቢሆን ከትግራዋይ ጋር ገጥመው ታግለው እንደማይጥሉትም አሳምረው ያውቃሉ። አይሞክሯትም፤ አዳልጧቸው በተደጋጋሚ በተደረጉ ጦርነቶችም ሽንፈትን እንጅ ድልን እንደማያውቁ እነሱ ራሳቸው አይክዱትም፤ ትግሬ ገደይ! እንኳ ይሉ የለ!? (ይህ እግሬ አውጪኝ ብለው ሲፈረጥጡ የሚያሰሙት ድምጽ ነው)። ታሪክ በደማቅ ቀለም ጽፎት ያለፈው ሐቅም ይህ ነው። ታድያ ኢትዮጵያዊነት በማለት የሚታወቁ እውነትን መሸጥ እንጅ መግዛትን የማያውቁ፤ የትግራይ ህዝብ ስም ሲነሳና ትግራዋይ ሲባል የሚጥላቸውና አራፋ የሚያስደፍቃቸው የአማራ ልሒቃን ዘወትር የትግራይ ህዝብና ግዛት የሚያጠቁበት ብቸኛ መንገድ ከባዕድ ኃይሎች ጋር በመተባበርና በማሴር ነው።

 

በሰሜን በኩል የተቀመጠው የኤርትራ መንግስትም ቢሆን በተመሳሳይ፥ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያን በመዳፉ አስገብቶ በሪሞት ኮንትሮል ለመቆጣጠር ሆነ በኢትዮጵያ ትክሻ ላይ ተቀምጦ ከኢትዮጵያ ማግኘት የሚፈልገው ነገር ሁሉ በወደደው ሰዓትና ጊዜ ያሻውን እንዳያገኝ ያደረገው ሊንደው የማይችል አለት የሆነበት ትግራዋይ የሚባል ዘር እንደሆነ ያምናል። የኢትዮጵያ መለኮታዊ ጠበቃ ነኝ ብሎ የሚያምን አማራን ጨምሮ ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጠው መንገድ ከመንገዱ ሊጠርገው እንደሚችል ያምናል ሲሉም ያክሉበታል። ይህ አባባል የእኔ የግል አስተሳሰብ ሳይሆን የአከባቢው ፖለቲካዊ የአየር ጸባይ የሚቆጠሩ በቀጠናው የተሰማሩ የምዕራባውያን የደህንነት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት የሚሉትና የሚያቀርቡት ክላሲፋይድ ያልሆነ ሪፖርት ነው።

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ ያሰማራው ሠራዊትና ዐቢይ አህመድ ዓሊ መራሹ የአማራ ልሒቃን ሴራ የተነሳ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ መንስኤ ቀደም ሲል ካነሳሁት ነጥብ አንጻር በመጠኑም ቢሆን ግልጽ ያደርገዋል የሚል እምነት አለኝ። ሻዕቢያም ሆነ አማራ የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጭፉ፣ ህጻናትንና ሽማግሌዎቻችን ሲረሽኑ፣ ካህኖቶቻችን ሲያርዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት በታንክ ሲደረምሱ፣ አንስት እህቶቻችንና እናቶቻችን ሲያስነውሩ፣ ሹካና ማንኪያ ድስትና መጥረጊያ ሲዘርፉ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ እንዲሁም የንጹሐን ዜጎች በላባቸው ያፈሩትን ሀብት ሲያወድሙ፣ ከተሞቻንን በእሳት ሲያነዱ፣ ህዝባችንን በርሃብ እንደ ቅጠል ሲያረግፉ መነሻው ቀደም ሲል የተጠቀሱ ሁለት ምክንያቶች የወለደው ፍርሃት (ትግራይ-ፎቢያ) ያመጣው ቅናት ምቀኝነት ወደ ጥላቻ በማደጉ ነው።

 

እንግዲህ፥ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቀው ምስራቃዊት የአፍሪካ አገር ከተቆረቆረች ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ የሚታየው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ዋና ዘር ወይም ቫይረስ ኢትዮጵያን የመምራት መለኮታዊ ስልጣን ያለን እኛ ብቻ ነን በማለት የሚዳክሩት፣ ሰውን እንደ ሰው መቀበል ያቃታቸውና እውነትን መሸጥ የለመዱ የአማራ ልሒቃን ለመሆናቸው የሚጠራጠር ዜጋ ሊኖር አይገባም። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ እየጎተተ ያለው የአማራ ልሒቃን ዘመኑን የማይመጥን ልሃጫም እምነትና አስተሳሰብ የሚል ድምዳሜ የታመነ ነው። ኢትዮጵያን እያመሰና እያተረማመሰ ያለው የእነዚህ ሰዎች የበከተ አእምሮ የወለደው አመለካከት ነውና። ህወሓት፣ ኦነግ፣ ኦብነግ ወዘተ አንቲቦዲ (antibody) ናቸው። በመሆኑም፥ እንደ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ለገጠመው ችግር መፍትሔው ትግራዋይ ብሔርተኝነት ነው። ለምን? ትግራዋይ ብሔርተኝነት ከምንም በላይ ምክንያታዊነት ነውና።

 

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ፍትሓዊነት ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት አዱላዊነትን መቃወም ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ለፍትህና እኩልነት መቆም ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ሰው በሰውነቱ መቀበል ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ባለ እንጀራህን እንደ ራስህ መውደድ ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም መዝረፍና መግደል የለመዱ እጆች መቁረጥ ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት የአጥማቂና ተጠማቂ ስርዓት ዘርግተው ሌላውን ረግጠው የመግዛት ህልም ያላቸው ሰላቢዎች ማሳጣት ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ተኩላ ሳለ የበግ ለምድ ለብሶ በበጎች መካከል የሚርመሰመሰውን በላተኛ አውሬ መግለጥና ማራቆት ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያን የመግዛት መለኮታዊ ስልጣን ያለን እኛ ብቻ ነን ብሎ የሚያምን ትምክህተኛ ኃይል መና ማስቀረትና ማንሳፈፍ ብሎም እጅና እግሩ ሰብሶ እንዲቀምጥ ማድረግ ነው፤

v ለጥቆም ትግራዋይ ብሔርተኝነት ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣንና መብት ማረጋገጥ ነው፤

v ትግራዋይ ብሔርተኝነት ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸውና ሌሎች ነጥቦች እውን ለማድረግ የማንም ይሁንታ እውቅና አለመሻት መሆኑን አውቀን የጀመርነው የህልውና ትግል አጠናክረን ልንቀጥልበት ይገባል።

 

አቢይ አህመድ ዓሊ ገና አፈር ይለብሳል፤ ገና ይደበቃል። ዘመኑን በሚጠይቀው የትግል ስልት ራሳችንን እያስተካከልንና እያመቻቸን የዐቢይ አህመድ ዓሊ የዙፋኑ መቀመጫ ገና ይሽመደመዳል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page