Back to Front Page

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከገቡበት መቀመቅ ለመገላገል ዐቢይ አህመድ ዓሊ መንግሎ መጣል ነው

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከገቡበት መቀመቅ ለመገላገል

ዐቢይ አህመድ ዓሊ መንግሎ መጣል ነው

 

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

11-17-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ በማቀደም የሽብር አለቃ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የዙፋኑ ተሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን ከሂትለር በተኮረጀ የጥፋት፣ የሞትና የእልቂት ዕቅዳቸው የራሳቸው ጥፋትና ሞት መንገድ እንዴት እያቀጠኑት እንዳለ እንመለከታለን። በመቀጠል፥ ነፍሰ ገዳዮቹ (ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን) በመላ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ በኢትዮጵያዊነት ስም ያጋቡት የጥላቻ፣ የጋጠ ወጥነት፣ የአመጽ፣ የዝርፍያ፣ የውስልትና፣ የሴሰኝነትና የነፈሰ ገዳይነት ክፉ መንፈስ በተለይ፥ ጊዜ ሰጠኝ ብሎ በኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ ንጹሐን የትግራይ ተወላጆች ላይ ግፍና መከራ እየጨመረባቸው ያለ፣ ሀብት ንብረታቸው በመዝረፍ ላይ የተጠመደ በጥላቻ የተሞኘና ያበደ ዜጋ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ካጋቡበት ደም የተጠማ አውሬ ምኒሊካዊ እምነትና አስተሳሰብ ያልነበረ ያህል ለአንዴና ለመጨረሻ እንዴት መፈወስና ማፈራረስ እንደሚቻል ለመጠቆም የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው።    

 

ቅምሻ፥ ለሃምሳ ዓመታት ያህል ያለ ማቋረጥ በዕለቱ ሎቶሪ እንዲወጣለት አጥብቆ የሚጸልይ አንድ ሰው ነበር ይባላል። ከዕለታት አንድ ቀንም፥ የእግዚአብሔር መልዓክ በእግዚአብሔር ፊት ይቀርብና ጌታ ሆይ፥ ይህ ሰው ለረጅም ጊዜ ሲጸልይ የኖረ ሰው እንደሆነ ታውቃለህና አባክህ ስለ ስምህ ስልጣን ስትል የዚህ ሰው ጸሎት መልስ ሲል ይጠይቃል። እግዚአብሔርም በፊቱ ለቆመ መልዓክ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ ደስ ይለኛል፤ ሎቶሪ እንዲደርሰው የእኔ መልካም ፈቃድ ነው፤ ግን አንድ ችግር አለ፥ ሰውዬው ሎቶሪ ቆርጦ አያውቅም! ሲል መለሰለት ይባላል። ስለ ትግራይ፣ ስለ ኦሮሞ፣ ስለ ደቡብ፣ ስለ ቤንሽንጉል አልፎም ተርፎ ስለ ኢትዮጵያ ግድ ይለናል! የሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ሁሉም “አገሬ” ለሚሏት አገርና “ህዝቤ” ለሚሉት ህዝብ ከችጋርና ከእጦት ወጥቶ እውን ሆኖ እንዲያዩት የሚመኙትና የሚስሉት መልካም ስዕል በቃልና በጽሑፍ የማንበልበትና የማስተጋባት ችግር የለባቸውም። ዳሩ ግን፥ ያሉና የነበሩ ሁሉም አታላዮችና አስመሳዮች ከመሆናቸው የተነሳ፥ በህዝብና በአገር ስም የሚገኝ ጥቅም፣ የሚሰበሰብ ያልተላበበት ሀብትና ንብረት ሰውተው አገርና ህዝብ የማትረፍና የመታደግ ፍላጎት ስላልነበራቸውና ስለሌላቸው በቃልና በጽሑፍ የሚያንበለብሉት ምኞት እውን ለማድረግ የሚያስችል ወሳኝ ስራ ለመስራት ፍላጎት ሳይኖራቸው ቀርቷል የላቸውም። ቀለል ባለ አማርኛ፥ “ህዝቤ! አገሬ!” የሚል የተለመደ የአዝማሪ ዘፈን በማቀንቀን የሚታወቁ፥ ከድሃ ተወልደው፣ በድህነት አድገው፣ ድህነታቸው ረስተው፣ በድሃ ላይ የሚበረቱ የአእምሮ ድህነት የተጸናወታቸው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ልሒቃን “ህዝቤ” የሚሉት ህዝብ ሆነ “አገሬ” የሚሏት አገር ለመለወጥ የሚያስችል አንዳችም ትክክለኛ ነገር አድርገው አያውቁም። ትክክለኛ ነገር እያደረግን ነው ለማለትና ተታለው ለማታለል ታድያ መልካም የሚመስል ነገር በማድረግ ሰፊው ህዝብ ማደናገርና ማወናበድ የተካኑ ናቸው። አሁን ታድያ የማይታለፍ ኬላና ፍጻሜ ላይ ተደርሷል።  

 

ሐተታ፥ በጽሑፉ ዓላማ ላይ በግርድፉ እንደተጠቀሰ በቀጥታ ወደ መፍትሔው ሃሳብ ከመዝለቄ በፊት ግን፥ ወይ መመሳሰል! ከማለት ያለፈ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ነፍሰ ገዳዮቹ የአማራ ልሒቃን ከውጭ ኃይሎች መንግስታትና አገራት ጋር በመምከርና በመዘከር ትግራይ ለወረርና የትግራይ ህዝብ ዘር ማንዘሩ ለማጥፋትና ለመጨፍጨፍ በራሳቸው ጊዜ ያነደዱት እሳት በላያቸው ላይ ሲደፋባቸው፣ ሞት የተረፈደበት ወያነ ትግራይ በሞት ጥላ ስር በፊቱ የቆመ የጠላት ሠራዊት ሁሉ እያራገፈ፣ እየፈጨና እየመነጠረ ወንጀለኞች ወደ መሸጉባቸው ከተሞች እየገሰገሰ የሚገኝ የትግራይ ሠራዊት ጠላት ያለ የሌለ አቅሙ አሰባስቦ መጥቶም ቢሆን ሊያስቆመው እንዳልተቻላቸው በተረዱ ጊዜ ቋንቋው ተገልብጦ፥ አንዴ “የህልውና ጦርነት” ሌላ ጊዜ “የሉአላዊነት የሚደረግ ጦርነት” ሲጨንቀቸው “ህዝባዊ ማዕበል” አሁን ደግሞ ጭራሽ “ያያዝከውን ይዘህ” የሚለው የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናትና ሽሟምንት የዕብደታቸው ጥግ ምንጭ የሆነ የናዚው አዶልፍ ሂትለር የተቀዳ የጦርነት መጽሐፍ እአአ ከ1943 - 1945 ዓ/ም ከሂትለር ዕብደት የተነሳ ጀርመን የገባችበት መቀመቅ አንስተን በዐቢይ አህመድ ዓሊ በጎ ፈቃድ ለዕርድ ተላልፋ የተሰጠች ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ የወስላቶችና የአመንዝሮች ጋለሞታ አገር አሁን በዚህ ሰዓት ያለችበትና የምትገኝበት ድቅድቅ የጨለማ ዘመን ለታሪክ በንጽጽር ለማሳየት እወዳለሁ።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከሂትለር በኮረጆው ስልት ተፈጻሚ ያደረጋቸው የናዚ አሥሩ ትዕዛዛት

 

1.      ከፍተኛ ቁጥር ያለው የናዚ ሠራዊት ልክ እንደ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች መጠነ ሰፊ የሰውና የንብረት ውድመትና ኪሳራ እያስተናገደ ነው። ወታደራዊ ትጥቅና ቁሳቁስ የሚያመርቱ የጀርመን ፋብሪካዎች ዘመኑ ያፈራው እጅግ ዘመናዊ ታዋጊ ጀቶችና አውሮፕላኖች፣ ታንኮችና ከባባድ መድፎች እንዲሁም አውቶማቲክ ብረቶች በገፍ እያመረቱ ሠራዊቱን ቢያስታጥቁትም “ሬድ አርሚ” ተብሎ የሚታወቀው የሶቬት ሠራዊት ፊት መቆም ግን አልተቻለውም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ቁርስ በልቶ እራት የማይበላ፣ ከመላ ጎደል አሰቃቂ በሆነ ድህነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ እየገዛ፣ የአገሪቱ ካዝና አራቁቶ ሚልዮን ዶላሮች ወጪ በማድረግ፥ ከራሽያ፣ ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከምዕራብ አውሮፓ አገራት ሳይቀር ዘመናዊ ሰው አልባ ድሮኖች፣ ታንኮች፣ ከባባድ መድፎችና አውቶማቲክ ክላሾች በመሸመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቢያሰልፍም የትግራይ ሠራዊት መቆቋም ተስኖት ጀኔራሎቹ ዘማሪዎችና አዝማሪዎች ሰብስበው፥ የትግራይ ሠራዊት ለማስቆም ይረዳን ዘንድ እባካችሁ ግጥምና ዜማ አዋጥሉን ለማለት ውሎ ማደራቸው በየሆቴሉ የሚገኙ አደራሾች እንዲሆኑ አድርጓል።

 

2.     ተኩስ በከፈተበት ግንባር ሁሉ እንደ እንክርዳድ እየታጨደ ስጋው ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እየሆነ የመጣ ስፍር ቁጥር የሌለው የሂትለር ሠራዊት፥ ያልቀናው ያለቀባሪ - የቀናው ደግሞ ቆስሎም ቢሆን ምሽጉን ጥሎ እግሬ አውጭኝ ወደኋላ በሮጠ ቁጥር የናዚ ሠራዊት ቁመና ክፉኛ መናጋቱ፣ መሸርሸሩ፣ መሽመድመዱና ክስተቱም የጀርመን ፀሐይ በሚገባ መጥለቅ፣ የአዶልፍ ሂትለር ዘመነ መንግስትነት ፍጻሜ መቃረብን ያበሰረ ሐቅ ቢሆንም የጥይት ድምጽ ከሚሰማበት ጦር ግንባር ርቀው በከተሞቹ የመሸገው የሂትለር የሐሰትና የፈጠራ ፕሮፓጋንዲስቶች አቅምና ጉልበት ግን ሠራዊቱ በተመታበት ሚዛን ልክ ገና አልተመቱምና በቀኑ ፍጻሜም ሂትለርና ባለሟሎቹ የማይቀርላቸው፣ መጎንጨት የሚገባቸው ጽዋ ሊያሳልፏት ባይችሉም በወቅቱ የነበረ እውነታ ከጀርመን ህዝብ ጆሮ መደበቅ መቻላቸው ሳያንስ ግን የጀርመን ህዝብ በፈጠራና በሐሰተኛ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማሞኘት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የጀርመን ዜጎች ነፍስ በከንቱ መቀጠፍ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከወራት በፊት መሆኑ ነው፥ የኤርትራ ሠራዊት ጨምሮ እንደ ፈርዖን ሰረገሎች ትግራይ መሬት ላይ ያለቁና የተቀበሩ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የትግራይ ህዝብ ለመጨፍጨፍ ያሰማራቸው ክፍለ ጦሮች ትተን ወያነ ትግራይ ስደትና ጥቃት ተሻግሮ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊትና የአማራ ልሒቃን ያሰማሩት ኢንተርሃምዌ ሚኒሻና ታጣቂ የገቡበት እየገባ ማሳደድና ማጥቃት ከጀመረ በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ማለትም ከቆቦ ጀምሮ የመጨረሻ ዘመቻ ተብሎ ብዙ የተዘፈነለት እስከ የደሴ ግንባር ያለቀ የኢትዮጵያ ሠራዊት፣ የአማራ ኢንተርሃምዌ ሚሻና ታጣቂ እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የአፋርና የሶማል ጨምሮ ከየ ክልሉ የመጣ ስፍር ቁጥር የሌለው ሚኒሻና ታጣቂ አጠቃላይ ድምር ኢትዮጵያ ለሩብ ክፍለ ዘመንና ከዚያም በላይ ወደኋላ ያስቀረ ጥፋትና ውድመት ነው ተብሎ ቢቀመጥ ቢያንስበት ነው። ለሰው ልጅ ህይወት ቅንጣት ታክል ክብር የሌለው ነፈሰ ገዳይ ዐቢይ አህመድ ዓሊና በአሽከርነት የተዋጣላቸው የአማራ ልሒቃን ቀለብ እየሰፈሩ የሚያስጮኸቸው፣ በሚሰጣቸው ክፍያና ጎርሻ ልክ አፋቸው የሚከፍቱና ላይሰፉ የሚቀደዱ፥ እንደ‘ነ ኢቢሲ፣ ፋና፣ ዋልታ የመሳሰሉ የባልቴት ወሬ ነጋሪዎችና አሉባልተኞች ታድያ አዲስ አበባ ተቀምጠው “ወያነ ሞተ አለቀ” እያሉ ትፋታቸው ሲያስታውኩ ማየትና መስማት የተለመደ ነው። በዚህ ድርጊታቸውም፥ እውነቱን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመሸፈንና ሰፊው ህዝብ በውሸትና በሐተኛ ፕሮፓጋንዳ ለማወናበድ ያላቸው ቁርጠኝነት መመልከታችን ብቻ ሳይሆን እነዚህ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ልሳኖች በሚነዙትና በሚያሰርጩት ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የተነሳ ተጭበርብሮ እየዘመተ ያለና በየበርሃው የጅብ ምግብ እየሆነ የሚገኝ የኢትዮጵያ ወጣት ቁጥር ስንመለከት አመራሩ ድንግጥ የማይል ደመ ቀዝቃዛ መሆኑ ነው። የእነዚህ ልሳናት ሠራተኞችም ቢሆኑ ለአንድ ሰው ስልጣን መጠበቅ ሲባል ዛሬ በገፍ ህይወቱ እያጣ ያለ የኢትዮጵያ ወጣት ነገ ዕዳ ለመሆኑ ሳያውቁ ቀርተው ሳይሆን ለዐቢይ አህመድ ዓሊ ህገ ወጥ ስልጣን መጠበቅ ሲባል የረገፈ ያህል ቢረግፍ ግድ ስለ ማይላቸውና ስለ ማይሰጣቸው ነው።  

 

Videos From Around The World

 

3.     በፍጥነት እየገሰገሰና በላያቸው ላይ እየጣ ያለ ውርደትና ኪሳራ በሚገባ የታያቸውና ሞታቸው ያረጋገጡ መዋቾች (ሂትለርና አሽከሮቹ) ታድያ በዚህ ሰዓት ብቻቸው ይሞቱ ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩም። ዐቢይ አህመድ ዓሊና የዙፋኑ ተሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን፥ የደቡብና የኦሮሞ ወጣት እንዲሁም የአማራ ሚኒሻና ታጣቂ ገበሬ ለማስጨረስና ለመፍጀት አልመው “ህዝባዊ ጦርነት” እያሉ እያንበለበሉት ያለ ባንዴራና እየደለቁት ያለ የእልቂት ከበሮ፥ እአአ የካቲት 18 ቀን 1943 ዓ/ም የናዚ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር የነበረና በጦርነቱ ማብቂያ ከመሬት ስር ተቆፍሮ በተዘጋጀ ማምለጫ ምሽግ ውስጥ ባለቤቱና ስድስት ህጻናት ልጆቹን ጨምሮ መርዝ ጠጥቶ እንደ ሞተ የሚነገርለት ጆሴፍ ጎብልስ፥ ጦርነቱ የሁለት ሺህ ዓመት የከበረ ባህል ያላት የተቀደሰች አገረ ጀርመን ለመጠበቅ የሚደረግ ጦርነት ነው ወይም total war! በማለት አጠቃላይ የአገሪቱ የሰው ሃይልና ሀብት ሁሉ ለጦርነት እንዲውል በማድረግ ጦርነቱ ለማሸነፍ የተደረገ ሙከራ የሚልዮኖች ጀርመናውያን (ንጹሐን ዜጎች) ደም ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር አድርገዋል። አይደለም ዐቢይ አህመድ ዓሊ እንደ ሸሚዝ የሚቀያይራቸው ሃይማኖትና ፖለቲካ ተቀላቅሎባቸው ሰገጣሞቹ የአማራ ልሒቃን በነጋ በጣባ ቁጥር፥ ክተት፣ ዝመት፣ አዋጅ! እያሉ የሚነፉት የጦርነት መለከት መቁጠር ቀርቶ አንዴ ከትት፣ ዝመት! ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ደግሞ ክተት፣ ዝመት ለኢትዮጵያ ህዝብ አይበጅም! የሚለው በሌላ በኩል ደግሞ “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፥ የትም፣ በምንም፣ መቼም” የሚል ጆሴፍ ጎብልስ ጀርመን ለማዳን ሁሉም መዝመት አለበት ሲል ካደረገው ታዋቂ ንግግር የተገበጠ መፍክር አስይዞ እሳት የሚያነድ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከትግራይ ጋር እየተደረገ ያለ ጦርነት “የሺህ ዘመናት ታሪክ ያላት ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ብሔራዊት አገረ ኢትዮጵያ የመታደግ ጦርነት ነው!” እያለ በውሸት የጻፈበትና “መንግስታዊ” መግለጫዎች የሰጠባቸው አገጣሚዎች መቁጠር በራሱ ከብዛቱ የተነሳ ስራ መፍታት ነው የሚሆነው። የሠራዊት አለቆቹ፣ ሙፍቲውና ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ባለ ሀብቱ፣ ትልቁም ትንሹም ሥልጣን የቀመሰ፣ ዘማሪና አዝማሪ፣ ምን አለፋዎት በአምልኮተ ዐቢይ ልቡ የጠፋበትና የተሰለበ ጭፍራ በሙሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድሃውን ማህበረሰብ ጥይት ማብረጃ ሆኖ እንዲያገለግል ወደ ግንባር ለመላክና ለመማገድ የጦርነቱ ዓላማ ለማስረዳት የሚናገሩትና የሚያሰራጩት ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ሁሉ እንደተጠበቀ ነው።   

 

4.    ሞትና እልቂት የጀርመን ሰማያት በጋረደበትና የናዚ ሠራዊት በከፍተኛ ሁኔታ ጉልበቱ እየተሽመደመደና እየተጥመለመለ በመጣ ቁጥር ሂትለርና አሽከሮቹ የሚያሰሙት በተቃራኒው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚያደምጠውና የሚያነበው ሬድዮና በጋዜጣ እንዲሁም በቴሌቪዝን መስኮት ብቅ እያሉ መሬት ላይ የሌለ ዲስኩርና ቀረርቶ ሲያሰሙ ታድያ ሰው በዚህ ደረጃ ይዋሻል? እግዚኦ! የሚያስብል ነው። በከፍተኛ ሁኔታ ሽንፈት እየተጎነጨ የመጣ የሂትለር አደጋ ጣይ ቡድን ጦርነቱ ለማሸነፍ ታድያ የማይቆፍረው ጉድጓድ አልነበረም። የናዚ ጀምበር ዓይን ያለው ሁሉ በሚያየው መልኩ እየጠለቀች ስትመጣም ናዚዎች መሬት ላይ የሌለ ሐሰተኛ ድል እያወጁና እያስነገሩ (ጥቅምት 18 ቀን 1944 ዓ/ም መሆኑ ነው) ሂትለር Volksterm ወይንም People-storm! በማለት ከ16 - 60 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም የጀርመን ዜጋ ሁሉ በእጁ ላይ የሚገኝ መሳሪያ ይዞ ወደ ግንባር እንዲዘምት ቀጭኝ ትዕዛዝ መስጠቱና አዋጅ ማስነገሩ ታሪክ በደማቅ ቀለም ጽፎ አስፍሮታል። ሂትለር ባለቀ ሰዓት ጦርነቱን ለማሸነፍ ያስችለኛል ሲል የወሰደው ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ በአማርኛ የተረጎምነው እንደሆነም፥ ቆሞ መዋጋት ቀርቶበት መድፍ ሲተኮስ ሰምቶ የሚበተን ዜጋ እየሰበሰቡ ምድሪቱ በደም እያጨቁ የሚገኙ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ፍርፋሬ ለቃሚዎች የአማራ ልሒቃን “ህዝባዊ ማዕበል” ሲሉ የሚጠሩት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ስልጣኑ ለመጠበቅና ለማስቀጠል፣ የአማራ ልሒቃን በተመሳሳይ ወያነ ትግራይ ዳግም የገለጠው የተራቆጠ ሃፍረታቸውና ወራዳ ማንነታቸው ለመደበቅ ተግባራዊ እያደረጉት ያለ አረመኔያዊ ወታደራዊ ስልት መሆኑ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከጅብ የማያስጥል የአህያ ባል እንደሆነና ወያነ ትግራይ በመደበኛ ሠራዊት ብቻ የሚቆም ኃይል እንዳይደለ በአደባባይ በመግለጽ ወንዱም ሴቱም/ፍጥረት ሁሉ ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምት ከወደ ባህርዳር ተቀምጦ ያስነገረው አዋጅ ስንመለከት ታድያ ወይ መመሳሰል! ተብሎ በቀላሉ የሚታለፍ ሳይሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለስልጣኑ መጠበቅ ሲል በኢትዮጵያ ስም የሞት ሲሳይ እያደረገው ያለ ስፍር ቁጥር የሌለው የኢትዮጵያ ወጣትና እያወደመው ያለ የአገር ሀብትና ንብረት ታይቶንና ተሰምቶን በቃ! እንድንል ነው።    

 

5.     ዐቢይ አህመድ ዓሊ እንደ የጨርቅ ኳስ ጥባጥቤ የሚጫወትበት ያለ ትልቁም ትልሹም፣ የተማረም ያልተማረም ደጋፊው ለማስደሰትና መቐለ ለመመለስ ከነበረው ጽኑ ፍላጎት የተነሳም አዳዲስ ምልምሎች በሞምላት እንደ ገና ያደራጃቸው ሰላሳ አራት ክፍለ ጦሮች አሰልፎ “ኢትዮጵያ ታሸንፋለች! ይህ የመጨረሻ ዘመቻ ነው!” በማለት በደሴ ግንባር የከፈተው የማጥቃት ዘመቻ የሶቬት ሠራዊት በፊቱ የቆመ ኃይል ሁሉ እየደረመሰ በሚገሰግሰበት ወቅት ነበር እአአ መጋቢት 20 ቀን 1945 ዓ/ም ሂትለርና ጆሴፍ ጎብልስ “Endsieg* is near” (*Ultimate Victory) ሲሉ ያሰሙት ከነበረ ፕሮፓጋንዳ የሚለው የጊዜ ልዩነት ብቻ ነው። ይህ አጋጣሚ ሂትለርና ጀነራሎቹ ያለ የሌለ ሠራዊታቸው አሰባስበው የከፈቱት የማጥቃት ጦርነት ከሽፎ በሂትለር የሬሳ ሳጥን ላይ የተመታች የመጨረሻ ሚስማር እንደነበረች ታሪክ ያስታውሰናል። ተኩስ በከፈቱበት ግንባር ሁሉ ሽንፈትና ኪሳራ ተከናንበው ሲያበቁ በአንጻሩ ግን ሐሰተኛ የድል ዜና እያወጁ ከማኸል ትግራይ ሮጦው ደብረ ብርሃን የደረሱ፣ ዘፍነውና ሸልለው የማይደክማቸው እነ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን “ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ወያነ ሰሜን ወሎ ላይ ይቀበራል፤ ጦርነቱ እዚህ ይጠናቀቃል፤ ይህ የመጨረሻ ጦርነትና ኢትዮጵያ ድል የምታፍስበት ግንባር ነው፤ ድሉ የኛ ነው!” እያሉ በአዳራሹ የተሰበሰበ ህዝብ ሲያስጨበጭቡና ሲቀደዱ ሰዎቹ ነገ ስለ ራሱ ሲል እንደሚነጋ ሳይገዳቸ ነው።    

 

6.    ሂትለር፥ ሠራዊቱና ግዛቱ በከፍተኛ ፍጥነትና ሁኔታ እያጣ በመምጣቱ በአሁን ሰዓት ሁሉም ነገር ወደ መናገሻው ከተማ እየተሰበሰበ ነው። አንድም፥ የቀናው እግሩ ወዳመራው ይኮበልላል - ያልቀናው &##4848;ግሞ ያለ ቀባሪ አፈር ለብሷል። በዚህ ባለቀ ሰዓት ሂትልር ያደረገው ነገር ቢኖር ታድያ ከመላ አውሮፓ በተለይ ከጀርመንና የፖላንድ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ በማንነታቸው የአይሁድ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ሁሉ በጥድፍያ ወደ ማጎሪያ ካምፖች በገፍ ማስገባት፣ መጨፍጨፍና መግደል ነበር የተያያዘው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደም ሲል በተለይ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ከፍተኛ የሰው ኃይል ያሰማረበት የደሴ ግንባር ለገጠመው ሽንፈት የማይገልጸው ውረደት በከተማው የሚኖሩ ንጹሐን የትግራይ ተወላጆች ተጠያቂዎች በማድረግ፣ አሁን ደግሞ አስኳይ የጊዜ አዋጅ በማወጅ በመላ የኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ ንጹሐን የትግራይ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመው የሚገኝ ግፍና ወንጀልና ማለትም ህገ-ወጥ እስር እንዲሁ በድንገት ሳይሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊ የናዚህ ሂትለር አሰር በመከተል እያደረገው ያለ ጦርነት አካል መሆኑ መታወቅ አለበት። የዐቢይ አህመድ ዓሊ ለየት የሚያደርገው፥ ንጹሐን ዜጎች ከማንነታቸው የተነሳ ከሞቀ ቤታቸው እያፈሰ በመውሰድ “ጦር ግንባር የተማራኩ ናቸው” እያለ ናዚ ያላደረገው አረመኔያዊ ድርጊት ጭምር እየፈጸመ ያለ ሰው መሆኑ ነው።   

 

7.     አሁን፥ ሂትለርና ጀነራሎቹ የፈለጉት ዓይነት የጦር መሳሪያና የሠራዊት ብዛት ቢያሰልፉ “በጥገናዊ ለውጥ” ሊያገግሙ የማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ጀርመን፥ ሽንፈቷን በይፋ በማወጅ እዚም እዚያም ተንጠባጥቦ የቀረ ህዝብና ሠራዊት እንዲሁም ከተሞችዋን የማትረፍ ፍላጎት ኖሯት እጅ ካልሰጠች በቀር የጀርመን መደበኛ ሠራዊት በአሁን ሰዓት ግንባር ፈጥሮ ማሸነፍ ይቅር በተሟላ ሁኔታ ጦርነት የመግጠም አቅሙ ሙሉ በሙሉ ለምሷል። ይህ በእንዲህ ሳለ፥ እአአ ሚያዝያ 19 ቀን 1945 ዓ/ም ሂትለር በጀርመን ግዛት የሚገኝ ማንኛውም መሰረተ ልማት ማለትም ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ ፋብሪካዎች፣ የስልክ፣ የውሃና የመብራት፣ መንገድና ሆስፒታል ጨምሮ ሁሉም ነገር በከባድ መድፍና በተዋጊ ጀቶች እንዲደበደብ፣ ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑና ሙሉ በሙሉ እንዲወድሙ የሰጠው ትዕዛዝ “Decree Concerning Demolitions in the Reich Territory” ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን “የኔሮ ትዕዛዝ” ተብሎም ይነገራል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሶማሌና የኤርትራ ሠራዊቶች እንዲሁም የአረብ ኢምሬት ሰው አልባ ድሮን ጨምሮ በትግራይ መሰረተ ልማት ላይ የፈጸመው ውድመት ትተን ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት ከፍተኛ የሰውና የንብረት ኪሳራ ተከናንቦ ከለቀቃቸው የአማራና የአፋር ክልል ግዛቶች የሚገኝ መሰረተ ልማት፥ ሆስፒታሉ ወያነ እንዳይታከምበት፣ መንገዱና ድልድዩ ወያነ እንዳይሻገርበት፣ ስልክና መብራት ወያነ እንዳይጠቀምበት፣ የእርዳታ ስንዴ የሚቀበጥባቸው መገዘኖች ወያነ እንዳይመገበው፣ ነዳጁም ወያነ እንዳይጠቀመበት ዘወተ እያለ የቻለውን ባዶ እያስቀረ ያልቻለውን ደግሞ በቀንም በሌሊትም በከባድ መሳሪያ፣ በተዋጊ ጀቶችና ሰው አልባ ድሮኖች እየላከና እያስወነጨፈ እያወደማቸውና እያፈራረሳቸው እንደሚገኝ የአደባባይ ምስጢር ነው። ወታደራዊ መኮንኑ፥ መቐለን በታንክ ከበናታል የከተማ ነዋሪዎችም የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ተጠቅመው ራሳቸውን ማስመለጥ ይጠበቅባቸዋል ካልሆነ ግን ይደመሰሳል ሲል፤ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በፓርላው ፊት ተቀምጦ ወያኔዎች ወንዶች ከሆነ ለምን መቐለ ከተማ ውስጥ አይጠብቁንም እያለ ሲደነፋ፣ ጀነራሎቹ ወያኔዎች የትግራይ ከተሞች ለቀው ወደ ተንቤን በርሃ ገብቷል እያሉ ህዝቡን ስያስጨበጭቡና ሲሳለቁ፤ ሲቪሉም ቢሆን ቤተ ክርስትያን ይደመሰሳል እየተባለ ወታደራዊ መመሪያ ሲሰጥ ያስታውሳሉ? እንድጊያውስ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን በአማራ ክልል እያደረጉት ያለ ያህንኑ ነው። መኸል ከተማ የሚገኙ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች ላይ፣ ቤተ ክርስትያን፣ መስጊድ፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ ፋብሪካ ቅጽር ግቢ ውስጥ ታንክና ከባድ መሳሪያ እየተከለ የሚተኩስበት አንዱ ምክንያት ዐቢይ አህመድ ዓሊ በሰብ-አስባቡ የአማራ ክልል መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ የማውደም ዕቅድና አጀንዳ ስላለው ነው። ሽንፈት እየተከናነበ መልቀቁ እንደማይቀርለት ጠንቅቆ ስለሚያውቅም የቻለ እንደሆነ እዛው እያለ ይዘረፋቸዋል፣ ያወድማቸዋል የተቀረው ደግሞ ስፍራው ለቆ ከፈረጠጠ በኋላ ካለበት ሁኖ ሆነ ብሎ በሚያስወንጭፈው ተተኳሽ ያወድማቸዋል፤ በተጨባጭ እያደረገው ያለም ይህንኑ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ የትግራይ መሰረተ ልማት ባወደመበት ልክ የአማራ ክልል መሰረተ ልማት በተመሳሳይ መንገድ እያወደመ እንዳለ የክልሉ ነዋሪዎች ከስፍራው በቀጥታ በሚሰጧቸው ምስክርነቶች በተደጋጋሚ ሰምተናል።     

 

8.    በፊቱ የቆመ ተዋጊ ሁሉ እያጨደ ወደ በርሊን መገስገሱን ያላቆመ የሶቬት ሠራዊት ለማስቆም ሂትለር ያደረገው የቀቢጸ ተስፋ ድርጊት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ቀደም ሲል “ኢትዮጵያ ላለፉት መቶ ዓመታት ያልገነባቸው ሠራዊት እየገነባን ነው፣ አሁን እየገጠምነው ያለ ጦርነት መለማመጃችን ነው” እያለ በአደባባይ ወጥቶ በሰው ህይወት ላይ ሲያሾፍ፤ አሁን ደግሞ፥ “መካለያ ሠራዊት፥ አውሎ ነፍስ ነው፣ ወጀብ ነው፣ እሳት ነው” የሚል የቅዠት ማስታወቂያ አሰርቶ ህዝቡን ከማሞኘት በተጨማሪ በመላ አገሪቱ አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ በማወጅ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከሰላሳ ሁለት ሺህ በላይ አደረጃጀቶች ፈጥሮ የከተማ ነዋሪዎች የቻለ ዘነ ዘና፣ ያልቻለ ሹካም ብትሆን የአቅሙ ያዞ እንዲወጣና ሞቱን እንዲሞትለት በይፋ ያቀረበው ጥሪ፥ ናዚው ሂትለር በመጨረሻው ሰዓት ካደረገው የእልቂት ስልትና ድርጊት እጅግ ተመሳሳይ ነው። ሂትለር የሌለ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ህዝቡን ሲያጨርስ ታድያ ለራሱና ለቤተሰቡ ከመሬት ስር ምሽግ ቆፍሮ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊም በተመሳሳይ አገሪቱ በደም ስትታጠብ ሰውዬው ምን ነው ድምጹ አጠፋሳ? የት ገባ? ሲባል እሰማለሁ እኔ ግን የትም አልሄድምኩ! እያለ ራሱን ከኢየሱስ ጋር በማነጻጸር፥ አውቄ ነው የተኛሁት፤ አለሁ! እያለ ወላጆች ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ልጆች ወላጆቻቸውን በከንቱ እያጣ ባለ ህዝብ ላይ በአደባባይ ማሾፍ ገፍቶበታል። በነገራችን ላይ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሰው ነፍስ ከምንም ሳይቆጥር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ደም ደመ ከልብ እያደረገና እንዲሁ እየጠፋ ባለበት በዚህ ሰዓት ፊት ለማስገረፍ ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለክፉ ዓላማ ለመጠቀም የጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ከኢየሱስ የተነሳ የአንድም ሰው ህይወት በከንቱ ሊጠፋ ቀርቶ ለከፋ አደጋ የተጋለጠ ሰው አለመኖሩ መታወቅ አለበት። በተረፈ፥ ከመስኮ ተነስቶ አገር ምድሩን እየጠራረገ በርሊን የገባ የሶቬት ሠራዊት በከተማዋ እንደ ልቡ ሲመላለስባት ይፎክረው እንደ ነበር ሂትለር አጽመ ስጋው እንዳልተገኘ ሁላችን እናውቃለን። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ወረራ ለመፈጸምና ጦርነት ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቆ ሲያበቃ ጦርነት የሰው ህይወት የሚቀጥፍ አስጸያፊ ነገር ነው፣ ጦርነት የአገር ሀብትና ንብረት የሚበላ መወገድ ያለበት ክፉ ነገር ነው እያለ ሲመጻደቅ፤ በራሱ ጊዜ ያነደደው እሳት በላዩ ላይ ተደፍቶበት ሲለበልበውና ከገባበት ጉድጓድ ለመውጣት አስታራቂ ፍለጋ ሲንከራተትና ሽማግሌ ፍለጋ ደጅ ሰንቶ ሲያበቃ ደግሞ ድርድር ብሎ ነገር የለም፣ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ትላለች እንጅ ከወያኔ ጋራ ድርድር ፈጽሞ የማይታሰብ ነው እያለ በሌለው ነገር ሲመካ፤ ተኩስ በከፈተበት ግንባር ሁሉ ከፈተኛ የሰው ህይወትና ንብረት ኪሳራ አስድተናግዶ ሽንፈትና ውርደት ተከናንቦ ሲያበቃ ደግሞ ወያነ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣነው ነው እያለ ሐሰተኛ ዜና በማሰራጨትና በመንዛት፥ ማውናበድ፣ ማጭበርበርና ድራማ በመስራት የተካነበት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ዛሬም ሁለት እግሩ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሳለ ይህች የማታለል ክፉ ባህሪውን አልተወም። ከነተረቱም፥ ማሽላ እያረረ ይስቃል እንደሚባለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ዕርቀ ሰላም የማውረድ ፍላጎት ኖሮት ሳይሆን ከውርደት ለመትረፍ እባካችሁ ከወያነ ጋር አስታርቁኝ! እያለ አማላጆች በመላክ መጠመዱን፣ በሽምግልና ካልቀናው ደግሞ ኢትዮጵያን ጥሎ ለመኮብለል እየተዘጋጀ ነው የሚለው ጭንጭንታ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውስጥ ሳይቀር በከፍተኛ ሁኔታ ሲነገር በመሰማቱ፥ አይ እኔ አልፈራም፣ እየተዘጋጀሁም አይደለሁም ለማለት የኮረኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ትዝታዎቹ እያነሳ መለፋለፍ ጀምሯል። በርግጥ፥ በትግራይ ሠራዊት የምህረት እጅ የወደቀው ዐቢይ አህመድ ዓሊ መጨረሻው በቅርቡ የሚታይ ነገር ቢሆንም ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እየተረባረበና እየተማጸነ የሚገኘው፥ ስልጣን መልቀቅ እንዳለበት ሙሉ በሙሉ አምኖበት ግን ደግሞ እንደ አባቶቹ ከአገር ተሰድዶ እንዳይዋረድና በዘር ማጥፋት አንድም በጦር ወንጀለኝነትና በሰብአዊነት ላይ በሚፈጸም በወንጀል ተከሶ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ ቀሪው ዘመኑ በእስር እንዳይማቅቅ ክፉኛ አሳሳቦት እንዲሁ ስልጣኑን ብቻ አስረክቦ በሰላም ለመኖር እየተማጸነ እናዳለ ነው። ለነገሩ፥ ይህም የሚወስነው ወያነ ትግራይ ነው። ነገሩ ተገልብጧልና “በነፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ሆኗል! ከአሁን በኋላ መልሰን ዱቄት ልናደርገው አንችልም!” ያለው ኃይል “ለመንግስትነቴ እውቅና ይስጠኝ” እስኪል ድረስ ልቡ የጠፋበት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሆነ ሌልች የውጭ ኃይሎች ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር ሲፈቀድላቸው ብቻ ጥያቄያቸው ማቅረብ ብቻ ነው። አንድም፥ ከእንግዲህ ወዲህ ወያነ ትግራይ ይሆናል ያለው ይሆናል፤ አይሆንም ያለውም በተመሳሳይ አይሆንም።  

 

9.    ናዚ በማንነታቸው የአይሁድ ዝርያ ባላቸው ዜጎች ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ስራ ለመፈጽም ትልቁ መሳሪያ ሆኖ የገለገለ የውሸትና የፈጠራ ዜና የሚነዛና የሚያሰራጭ የሂትለር የፕሮፓጋንዳ መሽን የሶቬት ሠራዊት የበርሊንግ በሮች በርግዶ በከተማዋ እንደ ልቡ እስኪመላለስ ድረስ ጀርመን የጠላት ሰራዊት ድባቅ እየመታች ነው፤ እያሸነፍን ነው፤ የወገን ሰራዊት የመስኮ ከተማ ከቧት ይገኛል! የሚል አራምባና ቆቦ የሆነ ዜና እየለቀቁ ማለትም ዛሬ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን የሚያሰሙት ዓይነት የምርቀና ዜና፣ የውሸት ድርሰትና የፈጠራ ትርክት መተንፈስ አላቆሙም ነበር። እነ ኢቢሲ፣ ፋናና ዋልታም በተመሳሳይ፥ በአንድም በሌላም መንገድ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ከስልጣን ተመግሎ መወገድ እውን ሳይሆን ልሃጫም ሚንሊካዊ ትርክታቸው፣ ውሸትና ሐሰተኛ ምስክርነት መንዛትና ማሰራጨት ይተዋሉ ብሎ የሚጠብቅ ሰው ካለ በእውነቱ ነገር ከጅብ አፍ አጥንት መጠበቅ ይሻለዋል።  

 

 

10.   ክፉ ሰው ሁል ጊዜ አጥፍቶ ጠፊ ለመሆኑ ሂትለር ሁነኛ ምሳሌ ነው። ቀደም ብሎ (ከወራት በፊት መሆኑ ነው) ሂትለር ጦርነቱ ሊያሸንፍ እንደማይችል፣ ሠራዊቱም ሙሉ በሙሉ እንደተበላ፣ የቀረው አማራጭ ሽንፈቱን አምኖ ሰላም ማውረድ መሆኑን እያወቀ ለራሱና ለቤተሰቡ የሚሆን ከመሬት ሥር ጉድጓድ ቆፍሮ ሲያበቃ ሁሉም ነገር ጠቅልሎ እስኪወድም ድረስ ማለትም የመንግስቱ መቀመጫ የሆነች ከተማ ጭምር የጦርነት ቀጠና እንድትሆን በማድረግ ያደረገው የአጥፍቶ ጠፊ ድርጊት የሂትለር አገር ወዳድነት የሚያሳይ ሳይሆን በአንጻሩ የሂትለር አረመኔነት የሚገልጥና የሰው ፍጥረት ያልነበረው ሂትለር የጀርመን ህዝብ ጭምር በሚገባ አልረዳኝም በማለት የተበቀለበት ክስተት ነበር። አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ በአሁን ሰዓት ተፈጻሚ ያላደረጋት ብቸኛ ትዕዛዝ አስረኛ ትዕዛዝ ናት። ዐቢይ አህመድ ዓሊ በኦሮሚያ ክልል አስተኳይ የጊዜ አዋጅ ከማወጁ በተጨማሪ፥ ለማስመሰል ሰልፍ ከመውጣት፣ በማህበራዊ ሚድያ ተጥዶ ከመጮህ፣ ከማጉረምረምና ከመተቸት ያለፈ የአዲስ አበባ ህዝብ ተሽጦ ዋጋ የማያወጣ ፋይዳ ሌለው ህዝብ ነው፤ በሚገባ ልክ አልደገፈኝም በማለት ቂም የቋጠረበት የአዲስ አበባ ህዝብ ሳይቀጣ እንዲሁ ይሄዳል ማለት ታድያ የዋህነት ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የአዲስ አበባ ህዝብ ለራሱ ዓላማ ለማስነሳትና ለማስጮህ አስልቶ በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረገው ያለ አንድ ዓመት የሞላው የከበባ ድርጊት መፈጸም አይጠበቅበትም። ምን ሊያደርግ ይችላል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ማስፈር አስፈላጊነቱ ስላልታየኝ ታድያ ጉዳዩ እዚሁ እተወዋለሁ። በተረፈ፥ ከእውቀት የጸዳ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከዚህ የታሪክ እውቀት የራቀ ሰው ቢሆንም አማካሪዎቹ የሂትለርና የናዚ መጨረሻ እያወቁ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የናዚ መጽሐፍ ተከትሎ ባዶ ፍከራና ቀረርቶ እያሰማ ገደል እንዲገባ የሚመክሩት አማካሪዎች ቁመና ግን ለእኔ ትንግርት ለመሆኑ በዚህ አጋጣሚ ለመጠቆም እወዳለሁ።

 

ያለፈ ስህተት ላለመድገም መፍትሔው፥ ካለፈው ስህተት መማርና እርምጃ መውሰድ ነው

 

ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ ተአምር ከሰማይ ካልወረደ በቀር ዐቢይ አህመድ ዓሊ ፍጻሜው አበላሽቷል። ከዚህ ውጭ ሰውዬው የሚተርፍ ከሆነም የሚተርፈው በወያነ ትግራይ ምህረት ብቻ ይሆናል። በሌላ አገላለጽ፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ መጨረሻ የሚወስነው ሞቷል፣ አልቋል፣ ድቄት ሆኗል! እየተባለ ብዙ የተዘፈነበት ወያነ ትግራይ ይሆናል። በርግጥ፥ ወያነ ትግራይ አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ ዐቢይ አህመድ ዓሊን ጋማ ብሎ እንደሚይዘው (መናደፊያው እንደሚመነገለው) የታየውና ፈጣሪ ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ በራሱ ላይ እንዲተነብይ ያደረገው ዛሬ ከአንድ ዓመት በኋላ ሳይሆን የዛሬ ዘጠኝ ወር ነበር። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወያነ ዱቄት ሆኗል! እያለ መላ የአገሪቱ ህዝቦች በውሸት በሚያስጨፍርበት በዚያን ወራት ነበር። ይህን በማስረጃ ላስታውሶት። ይኸውም፥   

 

እአአ በወርሃ መጋቢት 28 ቀን 2021 ዓ/ም “የዐቢይ አህመድ ዓሊ መጨረሻ ምን ሊሆን ይችላል?” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በዐይጋ ፎረም ለንባብ የበቃ ጽሑፍ ሲሆን ይህ ጽሑፍ በትግራይ የተፈጸመ ወረራ ተከትሎ በተመሳሳይ ወር ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርላውን ሰብስቦ ባደረገው ንግግር ላይ መሰረት አድርጎ የተጻፈ ጽሑፍ ነው። በማስቀደም ዐቢይ አህመድ ዓሊ የተናገረው ቃል በቃል እንመልከት፥ “እንበልና የተከበረው ምክር ቤት ፈቅዶ መንግስትንም እረፍ ብላችሁ እዚያ የተሸሸጉ አንዳንድ ሰዎች መጥተው መንግስት ይሁን ቢባል እና መቐለ ቢመለሱ በምን ዓይናቸው ነው ሚድያ ላይ ወጥተው እንደ ትናንትና መናገር የሚችሉ’ - ይህ የሚለው/ያለው ሃፍረት የማያውቀው አያልቅበት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ነው። አማርኛ የማይገባው ሰው ካልሆነ በቀር፥ አጠፋናቸው፣ ደመሰስናቸው፣ በተናቸው ወዘተ በማለት ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ በውሸት ያስጨበጨበ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወራሪ ኃይሎች እየለቀመ የሚገኝ የተራሮችና የኮረብቶች ባለባት ወያነ ትግራይ ጋር ጉዳዩ በጠረጴዛ ዙሪያ ላይ ለመፍታት እንደተገደደና እንደሚገደድ ከወዲሁ እወቁልኝ እያለን ነው ያለ። ሰውየው የፈራው እውን ሲሆን ታዲያ ‘የተከበረው ምክር ቤት ፈቅዶ መንግስትንም እረፍ ብላችሁ’ እንዲል ሽንፈቱና ኪሳራዉ ከወዲሁ ለማቅለል ያህል በእንቅልፍ ልቡ ሚመላለሰው ምክር ቤት እያላከከ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይህን ሲል ታድያ፥ ኧረ እኛ አላልንም፤ አንልምም! ለማለት የደፈረ አንድም ደም ያለው የምክር ቤቱ ማህበርተኛ አልተገኘም፤ ያለ እንደሆነ የሚገጥመውና የሚጠብቀው ጠንቅቆ ስለሚያውቅ። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ሐቅ ቢኖር፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከትግራይ ጋር ያለው ጉዳይ በድርድር ከመፍታት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው አውቆ ለሰላም እጁን እንዲሰጥ ያስገደደው ኃይል ሌላ ማንም ሳይሆን እውነትና ጽድቅ ከያዘ ከትግራይ ህዝብ ጋር መዋጋትና ጦርነት መግጠም ማለት ከግድግዳ ጋር መላተም ስለሆነበት ብቻ ነው። አንድም፥ ጊዜ የወሰድሁ እንደሆነ ወያነ አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ ያንቀኛል ነው አንድምታው” የሚል ነበር። ጥጉ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግፍ የተፈጸመበት ወያነ ትግራይ ቀን ቀጥሮ እንደሚመጣበትና ኃፍረት እንደሚከድነው ፈጣሪ ዓለም ኩሉ ሰውየው በሚገባው መንገድ ገልጦለታል። የጎረቤት አገራትና መንግስታት አሰባስቦ በሰማይና በምድር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወያነ ትግራይ የገባበት ጉድጓድ ገብቶ እንደሚያድነው የተሰወረበት ቢኖር ታድያ ምላሱ እየወለወለ ያሞኘው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጅ ዐቢይ አህመድ ዓሊ አልነበረም።   

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊና ክፉ መንፈሱ የሰለጠኑባት ኢትዮጵያ፥ በተለይ ጨፍላቂና ጸረ እኩልነት የሆነ ምንሊካዊ አስተሳሰብ የተጸናወታቸው በሽተኛ ዜጎች የሚገኙበት ነባራዊ ሁኔታ የተመለከትን እንደሆነ እአአ 1945 ዓ/ም በሂትለር ቀጥተኛ ትዕዛዝ በስቅላት የተገደለ Dietrich Bonhoeffer የተባለ በይፋ ጸረ-ናዚ አቋም በማራመድ ይታወቅ የነበረ ጀርመናዊ የሥነ መለኮት ሊቅና ጸሐፊ በእስር ሳላ የጻፈው ጽሑፍ በሚገባ ይገልጸዋል። እንዲህ ይላል፥ “ሞኝነት (Stupidity) ከክፋት ይልቅ የበለጠ አደገኛና የመልካም ነገር ጠላት ነው። አንድ ሰው ክፉን (evil) ሊቋቋም/ሊቃወም ይችላል፤ ሊጋለጥና ካስፈለገም በኃይል መከላከል ይቻላል። ክፉ ሁል ጊዜ በውስጡ ራሱን የሚያፈርስ ጀርም ስለ ሚሸከምም በሰው ልጆች ህይወት ላይ ቢያንስ የመረበሽ ስሜትን ትቶ ይልፋል ሞኝነት ማስቆም ሆነ መከላከል ግን አይቻልም፤ ተቃውሞ ሆነ ኃይልን መጠቀም ቢሆን ትርጉም የውም። ለሞኝ በምክንያት ለማስረዳት መሞክር በደንቆሮ ጆሮ ላይ የመዝፈን ያህል ነው። የትምክህተኞች ግምትና መላምት የሚያቃረኑ እውነታዎችም ተቀባይነት የላቸውም፤ በዚህ ወቅት ታድያ ሞኙ ሳይቀር አውራ ይሆንና የማይካዱ እውነታዎች ሳይቀር የማይጠቅሙ ናቸው ተብለው ወደ ጎን ይገፈተራሉ” ይላል። አክሎም፥ “ሞኝ ሰው ከተንኮለኛ ጋር ሲነጻጸር፥ ሞኝ በራሱ የሚረካና በቀላሉ የሚታወክ ሲሆን ለጥፋት ወደኋላ የማይል አደጋ ጣይም ነው። በመሆኑም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግን ይሻል” ይልና እንዲህ በማለትም መነሻ ምክር ይለግሳል “ለሞኝ ሰው በምክንያት ለማሳመንና ለማስረዳት ፈጽሞ አንዳንሞክረው፥ ምክንያቱም ትርጉም አልባና አደገኛ ነውና” ይላል።   

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ያልደናገረውና ያላምታታው፣ ያላወናበደውና ያላጭበረበረው፣ ያላማለለውና ያልሰለበው፣ እንደ ቦንሆፈር አገላለጽ ያላሞኘው የኢትዮጵያ ዜጋ በኩራዝ ተፈልጎ አይገኝም። በተለይ ትግራዋይ ተብሎ ሲጠራ ከክፉ ቅናትና ከምቀኝነት የተነሳ ደም የሚያስቀምጣቸው፣ የትግራይ ስም ሲነሳ ብርክ የሚይዛቸውና ያለ አንዳች ምክንያት ትግራዋይ በመጥላት የታወቁ በመራራ ጥላቻ የታወሩ ምንሊካውያን ጨምሮ ቁጥሩ የማይናቅ ህዝብ በዐቢይ አህመድ ዓሊ ቅሌትና ውሸት ከመወናበዱ በላይ ሰውዬው ሰው ሁሉ በትግራይ ጠል ፖለቲካ አጥምቆ ለዝርፍያና ለነፍሰ ገዳይነትና የበረታ ሞኝ አድርጎታል። “ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው” በማለት የሚታወቁና ከእግዚአብሔር ጋር ቁማር መቀመር የለመዱ ዜጎች አገር የሆነችው ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ አሁን በዚህ ሰዓት፥ መስቀል የያዘ ሊቃነ ጳጳሳት ግባ በለው እያለ የሞትና የእልቂት ነጋሪት የሚጎስምባት - ከዘፋኞች껓 ከሴተኛ አዳሪዎች በሚገኘው ገቢ ካዝናቸው እየሞሉ ዘፈን ኃጢአት ነው እያለች የምትመጻደቅበት ዘፋኝ በተቃራኒው ደም መፋሰስ በመቃወም ስለ ስላምና ዕርቅ አውርዱ! በማለቱ ስቀለው ስቀለው እየተባለ የሚሳደድባት ከዚህም በላይ ለባለ አእምሮ የሚከብድ አስነዋሪና ሰይጣናዊ ስራ በመፈጸም ላይ የምትገኝ በታሪክ ዘልአለም የማይረሳ አጽያፊ ሰይጣናዊ ድርጊት ውስጥ የተዘፈቀች የፈራረሰች አገር ሆናለች።

 

በትግራይ ከተሞች የከተመ የማንም ብሔር ተወላጅ ሁሉ እንደ ማንኛው ትግራዋይ በሰላም ተዘሎ ሲኖር፥ በመላ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአንጻሩ ያለ ስማቸው ስም እየተሰጠ፣ በጎረቤቶቻቸውና አብሮ-አደጎቻቸው ሳይቀር እየተገፉ ለአላስፈላጊ እንግልት ከዚህም አልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ ለህልፈት እየተዳረጉ ይገኛሉ። ጎበዝ፥ ከዚህ በላይ ህዝባዊ ሞኝነትና ነፍሰ ገዳይነት የለም፤ ሊኖርም አይችልም። በአመዛኙ የመጥፎ ተጽዕኖ ውጤት ነው ተብሎ የሚታመነው ሞኝነት “ምናልባት ከስነ ልቦናዊ ይልቅ ማህበራዊ ችግር ይመስላል፤ የአንዱ ኃይል የሌላውን ሞኝነት ይፈልጋልና። ኃይማኖት ጨምሮ ለፖለቲካ ስልጣን በሚደረገው ሩጫና ጠንካራ መሻት ሰፊው የማህበረሰብ ክፍል በሞኝነት እንደሚበከል ግልጽ ነው” የሚለው ቦንሆፈር፥ ሞኝነት ምን እንደሆነ በሚገባ ለማወቅ ሞኝነት ተፈጥሮ በአግባቡ መረዳት ግድ ነው ይላል። ሞኝነት ምን እንደሆነና እንዳልሆነ አጠር ባለ መልኩ ሲያብራራል፥ “በእርግጠኝነት፥ ሞኝነት የአእምሮ ዘገምተኝነት ሳይሆን ሞኝነት essence ነው” ይላል አባባሉ በምሳሌ ሲያስረዳም “በጣም የተማሩና አዋቂዎች የሆኑ ግን ደግሞ ጅል የሆኑ ሰዎች አሉ፤ ምንም ያልተማሩ ሆነው ደግሞ ንቁ የሆኑ ሰዎች አሉ” በማለት ሞኝነት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል። 

 

ማርከን፣ አስተምረንና አሰልጥነን፣ ሱሪ አስታጥቀን ሰው ካደረግናቸውና ለወግ ለማረግ ካደረደረስናቸው ይሁዳዎች መካከል አንዱ የሆነ ብርሃኑ ጁላ፥ ከጥቂት ወራት በፊት የኢሳያስ አፈወርቂ ተከፋይ የኢሳት ሰራተኛ ከሆነ ግለሰብ በነበረው ቆይታ ብርሃኑ ጁላ “በግልጽ ተሸንፈናል ብለን እንድንናገር ነው የሚፈለው?” ሲል በታላቅ ቁጣ የሰጠው ምላሽ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኢትዮጵያ ህዝብ የደበቀው ሽንፈት በአደባባይ መናገሩን እናስታውሳለን። እንግዲህ፥ የትግራይ ሠራዊት ከማኸል ትግራይ ተነስቶ የአማራና የአፋር ክልሎች አጋማሶ በአገሪቱ ጉሮሮ ላይ ለመቀመጥ በተቃረበትና በአዲስ አበባ ከተማ ደጃፍ እያኳኳ ባለበት በዚህ ሰዓት፥ የአሜሪካና የአውሮፓ፣ የተባበሩት መንግስታትና በትግራይ ላይ የተፈጸመ ወረራ ተገቢና ህጋዊ ነው በማለት ጦርነቱን የደገፉ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችና ልኡካን፣ እንዲሁም የአፍሪካ መሪዎች አሁን በዚህ ሰዓት ውሎ ማደራቸው አዲስ አበባ በሆነበት ሰዓት ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግንባር ላይ ድል እያፈሰ ነው ብሎ የሚያምን ሰው ካለ በእውነቱ ነገር ጠቢቡ እንዳለው ጭንጋፍ ቢሆን፤ አንድም፥ ባይወለድ ይሻለው ነበር። ተወደደም ተጠላም ግን በሦስት ዓመታት ቆይታው ውስጥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የፈጠረው ዜጋ ሰውዬው ያለውና የተናገረው ነገር ሁሉ እውነት ነው ብሎ የሚያምንና ሳያላምጥ የሚውጥ፤ ቀደም ሲል የተመለከትነው የሥነ መለኮቱ ሊቅ በግልጽ ቋንቋ ያሰፈረው የክፉ ተጽዕኖ ውጤት የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተችሎታል። እዚህ ላይ፥ ሰዎቹ (ምዕራባውያን) አንድ ዓመት ሙሉ የቃላት ጨዋታ ከመጫወት ያለፈ የውጣ የፈየዱት ቁም-ነገር ሳይኖር የጭፍራና የደሴ ግንባር ምሽጎች ተደረመሱ ሲባልና ወያነ ትግራይ ፍትሕና ፍርድ ለማድረግ ወንጀለኞች ወደ ተደበቁባት ከተማ መገስገሱን ሲሰማ የአፍሪካ ህብረት ጨምሮ ምዕራባውያን በድንገት መጮህና ጉዳዩ “የፖለቲካ መፍትሔ ያሸዋል” ማለት ጩኸታቸው የሚያቀልጡበት ምክንያት ምንድ ነው? ብሎ የሚጠይቅ ሰው አይታጣም።  

 

ያስታውሱ እንደሆነ የዛሬ ስምንት ወር አከባቢ “ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ገቢ የሚያደርግ ኃይል ሌላ ምንም ሳይሆን ወያኔ ትግራይ ነው” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በዐይጋ ፎረም ለንባብ የበቃ ጽሑፍ ላይ፥ “ከምዕራቡ ዓለም እጅ ይልቅ የወያነ ትግራይ እጅ ትከብዳለች ለክብሩና ለህልውናው በታንክና በቡዝቃ ሳይሆን በህዝባዊ መስመር የሚታመን ወያነ ትግራይ ቼክ-ሜት! (Checkmate) በማለት ያለ ግብዣ በራሱ ጊዜ ተጠራርቶ የትግራይ መሬት የገባ ወራሪ ኃይል ሁሉ የትግራይ መሬት መቀበሪያቸው ሲያደርገው ሰውዬው (ዐቢይ አህመድ ዓሊን) የወደቀና የተጣለ ሆኖ ሳለ ደጋግፈው ያቆሙት፣ በትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት የራሳቸው ጥቅም ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው! በማለት እየተረባረቡ የሚገኙ ርዕሰ ኃያላኑ ወደው ሳይሆን ተገደው ገቢ ያደርጉታል። የወያነ ትግራይ እጅ በጠላቶቹ ላይ ስትከብድ፣ የትግራይ ህዝብ በልጆቹ የህይወት መስዋዕነት በድል ማማ ላይ ሲቀመጥ እንደ ኤሊ እየተራመዱ ያሉ ኃያላን አገራትና መንግስታት ሁሉ እንደ ጥንቸል ይፈጥናሉ” የሚል ንባብ ማንበባች ይታወሳል።

 

እንግዲያውስ፥ ነጩም ጥቁሩም “ጉዳዩ የፖለቲካ መፍትሔ ያሸዋል” የምትል ባንዴራ እያውለበለቡ ሽርጉድ የማለታቸው ምስጢር፥ ዐቢያቸው ከሽንፈትና ከውርደት ማትረፍ ያለፈ ሌላ የላቀ ተልዕኮ ያለው በመሆኑ ሰዎቹ ሸንጋዮች ሳሉ ሸምጋዮች በመምሰል “ጉዳዩ የፖለቲካ መፍትሔ ያሸዋል” እያሉ ያሉበት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ላስቀምጥ። ይኸውም፥

 

1.      ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሚስተካል ለመንግሥትነት የማይበቃ፣ ከትምህርትም ከእውቀትም ሰፈር ተፈልጎ የማይገኝ ባዶ ሰው፥ ግን ደግሞ በስህተት አለ ቦታው በመንግስትነት ቦታ ላይ የተቀመጠ አገር ሻጭ ገለሰብ ለሚቀጥለው መቶ ዓመታት ፈልገው ስለማያገኙ  

 

2.     በቁ. 1 የተጠቀሰው ምክንያት ጨምሮ ሰውየው በጦር ሜዳ ያጣው ድል በመጠኑም ቢሆን በፖለቲካ መድረክ ያካካስንለት እንደሆነ ወደ ስልጣን በወጣበት ወራት የነበረው ስምና ዝና እንዲሁም ቅቡልነትና ያክል ባይሆንም ዓላማችን ለማስፈጸም በሚበቃ ልክ ማገገም ይችል ይሆናል በሚል አጉል ተስፋ ራሳቸው ለማታለል ስለ ከጀላቸውና ዐቢይ አህመድ ዓሊ በዋናነት ወደ ስልጣን ያመጣንበት ምክንያት ግቡ ይመታል ብለው ስለሚያስቡ ነው። ይህ ግን ተስፋ ከማድረግ ያለፈ እውን ሊሆን እንደማይችል ርዕሰ ኃያላኑ ቢሆኑም በውስጣቸው አሳምረው ያውቁታል ብቻ ሳይሆን እንደማይሳካላቸውም ተረድቷል።

 

መፍትሔው ምንድ ነው?

 

የትግራይ ሠራዊት፥ ጠላቱ ማን እንደሆነ፣ ብቻ ሳይሆን የገጠመው ጠላት ባህሪይና ማንነት በሚገባ በመለየት የገጠመው ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ለማቃበጽና ለመቅበር ግልጽ የሆነ የትግል ስልት ነድፎ ዛሬ ላይ የደረሰ፣ መነሻውና መዳረሻው የሚያውቅ፣ የነጻነትና የእኩልነት የእውነትና የፍትሓዊነት ህዝባዊ ሠራዊት ለመሆኑ በዓይኑ ያየና ህዝባዊነቱን የቀመሰ ሁሉ ምስክር ነው። በመሆኑም፥ ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ሸለፈታሞቹ የአማራ ልሒቃን የወያነ ትግራይ ህዝባዊነት ለማደብዘዝ፣ ከተሳካላቸው ደግሞ መልካም ስሙና ዝናው ፈጽመው በማጠልሸት ለማጨናገፍ አስበው እንደሚነዙት ሐሰተኛ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳቸው ቢያጧጥፉትም ሐቁ ግን፥ የትግራይ ሰራዊት ነኝ እንደሚለው እንዲሁ እውነተኛ ህዝባዊ ሠራዊት ለመሆኑ ጠላቶቹን እንደ አዝመራ እያጨደና እየመነጠረ ባለፈባቸውና በተቆጣጠራቸው የአማራና የአፋር ከተሞች ሁሉ የተደረገለት ህዝባዊ አቀባበል መመልከት ብቻውን በቂ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ስልጣን ላይ እስከቆየና ህዝቦች የትግራይ ሠራዊት ህዝባዊነት በዓይናቸው እስካላዩና እስካልቀመሱ ድረስ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ፣ ውሸትና አሉባልታ የአባታቸው የሆነባቸው አማራ ልሒቃን ትግራዋይ ጠል ዘመቻ (ቦንሆፈር ህዝባዊ ሞኝነት በማለት ሲል የገለጸው) ህዝባዊ ዕብደትና የአገሪቱ አየር የተቆጣጠረ ጥላቻና ደምነት የትም አይሄዱም። መፍትሔው ምንድ ነው? ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ፥ “ሞኝነት ማሸነፍ የሚቻለው የመግለጫ መዓት በማንጋጋት ሳይሆን ከእስራት ነጻ በማውጣት ነው” ሲል የመፍትሔ ሃሳብ የሚጠቁመው ቦንሆፈር ምን እያለ እንደሆነ በእኛ ነባራዊ ሁኔታና ዓውድ ልተርጉመው። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰ፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በወታደራዊ ዲሲፕሊን በሚገባ የታነጸና የተገነባ፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ ዓላማና ተልዕኮ ያለው፣ ግዳጁን ተጠያቂነት ባለበት አኳህን የሚፈጽም የትግራይ ሠራዊት ህዝባዊ ሠራዊት ለመሆኑ በአሁን ሰዓት አዋጅ መንገርና መግለጫ መስጠት ሳያስፈልግ ህዝባዊነቱና ፍትሓዊነቱ የቀመሱ የአማራና የአፍር ክልል ተወላጆች ምስክሮች ናቸው። የትግራይ ሠራዊትና አመራር ስለ ራሱ ከሚናገረው በላይ ሠራዊቱ ባለፈባቸው የአማራና የአፋር ህዝቦች ህዝቦች የትግራይ ሠራዊት ፍትሓዊነቱና ህዝባዊነት አስመልክተው በዓይናቸው ያዩትና እውነተኛ ምስክርነት ይበልጣል። ቀለል ባለ አማርኛ፥ ከአሁን በኋላ መሆን ያለበትና ሊሆን የሚገባው የቀረው ያልተጠናቀቀ ግዳጅ በብቃት ማጠናቀቅ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የህግ የበላይነት ማረጋገጥ እንጅ የትግራይ ሠራዊት ህዝባዊነት ለማስረዳት የምናባክነው ጊዜ ሊኖር አይገባም። የትግራይ ሠራዊት ህዝባዊነትና ፍትሓዊነት ለማየት የሚሻ የተገኘ እንደሆነ ደግሞ ማድረግ የሚጠበቅበት አንድና አንድ ነው፤ ይኸውም፥ ራሱን ከዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ውሸትና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ማራቅና ጆሮቹ ለእውነት መስጠት ነው። በመሆኑም፥

 

ዋናው ሰው (አዶልፍ ሂትለር) መታሰቢያ ላይኖረው ስር መሰረቱ ተመግሎ መጣሉ ተከትሎ ራሱን ችሎ የሚቆም አሽከር ሆነ የሂትለር ክፉ መንፈስ ተጋብቶበት “እኔ የተለየሁ ዜጋ ነኝ፣ ፈጣሪ እጁን ታጥቦ የሰራኝ ምርጥ ዘር ነኝ!” እያለ ሌሎችን በማንነታቸው ሲያሳድድ፣ ሲገፋና ሲገድል የነበረ በትምክህት የተሳከረና በክፉ ድርጊት የበረታ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጀርመናዊ ዜጋ ሁሉ በጠራራ ጸሐይ በአገርና በባንዴራ ስም ያሞኘው የሂትለር መመታት ተከትሎ እንደ ጎማ መተንፈሱና ወደ ልቡ መመለሱን ማስታወሱ እጅግ አስፈላጊ ነው። የቀጠናው ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ የሰላምና የዶቦ ዕጦት እያፍገመገማቸው የሚገኙ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከገቡበት አዘቅትና መቀመቅ ለመገላገል የሚያስችል ብቸኛና ዘላቂ መፍትሔ፥ ይህ ለምንም ነገር የማይበቃ፣ በስህተት አለቦታው የተቀመጠ፣ በውሸትና በማስመሰል የተለከፈ ውስላታ ግለሰብ እንዲሁም በትግራይ ላይ እጃቸው የሰደዱ ግብረ አበሮቹ በሙሉ በአንድም በሌላም መንገድ ማሰናበትና ቅጥረኛ ነፈሰ ገዳዮች በፈጸሙት ወንጀል በህግ ፊት ተጠያቂዎች ማድረግ፣ ህግና ሥርዓት በአገሪቱ እንዲከበር ማድረግ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ከትግራይ መሬት ያለ ምህረትና ርህራሄ እሱ በታመነበድ መንገድ ተመግሎ እንደተነቀለ ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ መንገድ ሳይገባው ከተቀመጠበት ዙፋን በሚገባውና በመረጠው መንገድ መመንገል ለትግራዋይ ምርጫ ሳይሆን ይህን የማድረግ ህዝባዊ ግዴታና ኃላፊነት አለበት።  

 

በጽሑፋችን መግቢያ የተመለከትነው ጸሎትና የእግዚአብሔር ምላሽ ያካተተ ብሂል ፍሬ ሃሳብ ግልጽ ነው ብዬ። በርግጥ፥ ይህ በጽሑፋችን መግቢያ ያነበብነው ብሂል በእኛ ነባራዊ ሁኔታ ሲተረጎም ሎተሪ ሳይቆርጥ እንዲሁ ሎተሪ እንዲደርሰው በጸሎት ራሱን ያደከመ ሰው በመካከላችን ኖሮ ሳይሆን ሎተሪ ቆርጦ ሲያበቃ ሎተሪዋን ሳይመነዝር ሸፋፍኖ ቁም ሳጥን ውስጥ ቆልፎ ለለቶሪዋ የተከፈለ ዋጋ ሲተርክ ጊዜ ስላመለጠው ነው። ሰው ሎተሪ የሚቆርጥበት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንዱና መሰረታዊ ምክንያት ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ግን ከድህነት/ከችግር ለመገላገል ነው። ሎትሪ ቆርጦ የደረሰው ሰው አንድም ከስስት የተነሳ ያልነበረው በሽታ ገዝቶ ዕድሜው ካላሳጠረና ለጥቆም የመጣበት መንገድ ረስቶ ዓላማ የሌለው ርካሽ ህይወት ለመኖር ራሱን ሲማግድ በጥጋብ ራሱን ካላጠፋ በቀር ሎተሪ ከድህነት የሚገላግል ለመሆኑ ብዙ የሚያከራክር አይደለም። ለክብርና ህልውና የሚከፈል ዋጋና መስዋዕትነትም ተመሳሳይ ነው። ጸረ ህልውናችንና ክብራችን የሆነ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ዳግም እንዲያንሰራራ ዕድል ያገኘ ደም አፋሳሽ ምንሊካዊ እምነትና አስተሳሰብ ሎተሪ የመቁረጥ ያህል መቆረጥ፤ ቀጥሎም በህግና ስርዓት እንዲከበር ማድረግ ውሳኝ ነው (የአማራ ልሒቃን፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የተቆረጠ ዕለት ጥላቸው አይገኝም)።

 

በተረፈ፥ በራሱ ጊዜ በራሱ ላይ ውስኑነት ካላበጃጀ በቀር ከእንግዲህ ወዲህ የትግራይ ሠራዊትና አመራሩ ከፍ ሲል የተመለከትነው ከማድረግ የሚከለክለውና የሚያስቆመው አንዳች የውስጥም የውጭም ኃይል እንደሌለ ወዳጅም ጠላትም ሊያውቅ ይገባል። ትግራዋይ፥ ትግራይ ትስዕር! ብሎ የአራትና አምስት መንግስታት ጉልበት አጥመልምሎ ለድል ስለበቃ እኛም ከተጋሩ ኮርጀን “ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” እንላለን እየተባለ ስለ ተጮኸና ስለ ተዘፈነ ኢትዮጵያ የምትቋደሰው ፖለቲካዊ ሆነ ወታደራዊ ድል የለም። ዕድልዋን ሞከረች ደግሞም ተሸነፈች። በነገራችን ላይ፥ ኢትዮጵያ ከገባችበት መቀመቅ ለመውጣት “የፖለቲካ መፍትሔ ያስፈልጋል” እየተባለ ሽርጉድ እየተባለ ያለበት ምስጢር ሌላኛው አንድምታ፥ አገሪቱ ወታደራዊ ሽንፈት ስለ ቀመሰችና ስለ ተከናነበች እንደሆነ ሊሰወርብን አይገባም። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሰው ልጆች ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብና የማታመን ግፍና በደል ተፈጽሞበት ሲያበቃ አፈሩን አራግፎ እዚህ የደረሰ የወያነ ትግራይ መልካምነት ታድያ ገደብ እንዲኖረውና ትክክለኛ የሆነ ነገር እንዲያደግ ጥሪዬን ሳስተላልፍ በአክብሮት ነው። “ጉልበትና ገንዘብ የማያንበረክከው ሰው የለም!” ብሎ የሚያምነው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከተቀመጠበት፣ ለእሱ ያልተገባ፣ የከፍታ ሲፍራ እስኪፈጠፈጥ ድረስም የውሎ አበል እየከፈለ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሴቶችና ህጻናት እየሰበሰበ እያሳየው ያለ ሰልፍና ጩኸት እንደሆነም ከዚህ ቀደም የማይታወቅና ያልታየ አዲስ ክስተት ወይም የላቀ የፖለቲካ ፈጠራ ሳይሆን ትናንትና ከትናንት ወዲያ በቆቦ፣ በወልዲያ በመርሳ፣ በሃቅ፣ በደሴና በኮምባልቻ ያየነው የአመራሩ ጭንቀትና መታወክ የሚፈጥረው የሽንፈት፣ የውርደትና የኪሳራ መሳለሚያ ደጆች መሆናቸው ታውቆ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ጋሻ-ዣግሬዎቹ በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂዎች ለማድረግና ለፍትሕ ለማቅረብ የተጀመረ ወያናይ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሳበረታታም ታላቅ ደስታ እየተሰማኝ ነው።  

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page