Back to Front Page

ዝምታ ወርቅ ነው?

ዝምታ ወርቅ ነው?

ከማህፍቅ

ቀን: መጋቢት 30-2013 ዓ.ም

 

አገር ማለት ህዝብ ነው ያለው ማን ነበር  ? እንደዛ ከሆነ አገር ዝም ብላለች፡፡

አገሪቶ በተለያዩ ጫፍ ከአቅሟ በላይ ተወጥራ አገርን መመራት ምን ያስደስታል ? መሪው የሰይጣን ልጅ ወይም ራሱ ሰይጣን ካልሆነ በስተቀር ምንም አያስደስትም፡፡

አስታውሳለሁ የሆነ ዘመን አገራችን ላይ ወሬው፣ ዜናው ፣ ትክረቱ እና ሁሉም ነገር ግንባታ ፣ መመረቅ ብሎም ዕድገት የሚወራበት ጊዜ ነበር፡፡ ያ ጊዜ ኢትዮጵያ የሄደችበት መንገድ እስካአሁን ተገንብተው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች ብሎም መንገዶች በአጠቃላይ መሰረታ ልማቶች የአባይን ግድብ ጨምሮ የሚታዩ በሙሉ ውጤቶች ሁነዋል፡፡

አዲስ አበባ እንኳን አሁን የያዘችው ግንባታዎች በሙሉ ከተማዎ ከሶስት አመታት በፊት የታቀዱ እና የተሰሩ ናቸው፡፡ብቻ ምን ልበላችሁ የሰው ስሜት እና የፖለቲከኞች ክርክር እና ንግግር የዕድገት ምጣኔው እና ዲሞክራሲ ላይ ብቻ ነበር፡፡

እውነት ነው እዚህ ደረጃ ለመድረስ እና ለመነጋገር መጀመሪያ የሰላም አጀንዳ መዘጋት የግድ ነበር፡፡ አዎ የግድም ነው፡፡ ስለ ዕድገት ለማውራት በዕድገት እና ዲሞክራሲ ለመነጋገር ብሎም ለመኖር መጀመሪያ ሰላም ማስከበር መተኪያ የሌለው ግንባር ቀደም ተግባር ነው፡፡

አሁን ሁኘ ሳስበው ኢትዮጵያ ከዚህ በኃላ እንደዛ ስለ ዕድገት እና ልማት የሚወራበት የሚታይበት ጊዜ እንደ ዋዛ በፍጥነት ይመጣል ማለት ከባድ ነው፡፡ቢመጣ እና የተሻለ ማደግ ብናሳይ ምን ገዶኝ ግን እያየነው ያለው ነገር የአገራችን መጨረሻ መንገድ የሚያሳዩ በርካታ ነገሮች ስላሉ ነው፡፡

Videos From Around The World

እንግዲህ በታሪክ እንደምናውቀው ቀደምት አገራት እና መንግስታት ከወደ አክሱም አከባቢ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ እነዛ ታላቅ ስልጣኔዎች ግዛታቸው አሁን ያለችው ኢትዮጵያን  ጨምሮ የተለያዩ አገራትን ያካተተ እንደነበር ሁሉም ያውቃል፡፡

ታድያ ያ ገናና እና ስፊ ግዛት የነበራት አገር መቸም በዛው እንድንቀጥል የእግዛብሄር ቃል አልነበረም እና በሂደት ግዛቱ እየጠበበ እየተከፋፈሉ በመጨረሻም ብትንትኖ እንደወጣ ታሪክ ያስተምረናል፡፡

ቀጠለ እና ዘመነ መሳፍንት በቴድሮስ ተጠናቆ እንደገና ከጠባብ ግዛት ወደ ስፊ ግዛት እየሰፋ እየተስፋፋ ከሞላ ጎደል አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ላይ ደርሰናል፡፡

አሁን ያለችው ኢትዮጵያ እንደ አክሱም ዘመን የነበረው ግዛት ሰፊ እንኳን ባይሆን በተነፃፃሪ እንደ ኤርትራ፣ ጁቡቲ፣ ስማሊያ ላንድ እንዲሁም ሱዳን ብሎም የመን የመሳሰሉት ግዛቶች ቆረሳ በመተው አሁን ያለችውን ቅርፅ ይዘናል፡፡

እትዮጵያ አትፈርስም ማለት በእውነት ደስ የሚል አባባል ቢሆንም በተጨባጭ ግን አገራችን በተለያዩ ምክንያ እየተቆረሰች እዚህ እንደደረሰች ደግሞ አለማመን ከባድ ነው፡፡ ሌላው ይቅር እና የኤርትራ ጉዳይ እንኳን መካድ ከባድ ነው፡፡

አሁን አሁን እያሳሰበኝ ያለው ነገር ከኢትዮጵያ ተገንጠለው የራሳቸውን አስተዳደር ያቋቋሙ አገሮች ሳይሆን የቀረችው ኢትዮጵያ ናት፡፡እች ኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች እንደ ቀድመዎ ታሪክ የሆነ የሆነ አካሎ ሊከፋፈል እና ራሱን ሊችል የተቃረቡ የሚመስሉ በዛ ያሉ አመላካች ነገሮች እንዳሉ የእውነት እኔ ይህንን መሸሸግ አልፈልግም፡፡

ቀደም ብሎ አለም ላይ የነበረው ታሪክ የግዛት አንድነት በአብዛህኛው የመጣው በሃይል ነበር፡ ዛሬ ግን ጊዜው ተቀይሮ ሰው በሚፈልገው መሬት እና አገር ከልሎ የመኖር መብት በመረጋገጡ ይህንንም ያአለም አገራት አምነው ስለተቀበሉ አብሮ የመኖር መንገድ በራስ ፈቃደኝነት የተመሰረተ ላይ አድርጎታል፡፡ አስተውሉ አንተ ይህንን ፁሁፍ እያነበብክ ያለሀው ሰው የምትኖርበት አገር እና ቦታ ብሎም ዜግነት የምትወስነው ራስህ ነህ፡፡ይህ ስል ግን እንደ ዋዛ በቀላሉ ይመጣል ማለት አይደለም፡፡ ሰው ሁነን አስከተፈጠርን ለመኖር ለማደግ መስራት እና መብላት እስካለብን ድረስ ያኛውም ጥራት እና ምናልባችም መስዋዕትነት ይጠይቃል፡፡

በአጭሩ አገር ያለ ሰው መና ነው፡፡

በቅርብ አመታት መንግስት የቀደምውን መግስት በሃሪያት መላበስ መጀመሩን የሚያሳዩ ነገሮች በስፋት መታየት ጀመረው ነበር፡፡ ማለትም ኢህአደግ ስለ ደርግ ጨካኝነት በስፋት እንደሚያወራው ሁሉ አሁን ያለው መንግስት በመሪው ደረጃ ስለ ኢህአደግ ጨካኝነት አምርሮ ማውራት መጀመሩ በሂደት መጥፎ ነገር እንደሚመጣ አመላካች ነበር፡፡

መሪያችን የአገሪቱ ሰቆቋን ለህወሓት ይሰጣል በእዛ በኩል ደግሞ ጥፋትም ካለ ሁሉም ይጠየቅ የሚል ሙጉት ይታይ ነበር፡፡ እዚህ ላይ የታዘብከውን መናገር የደጋፊ እና ተደማሪ ጫዋታ እንዳልሆነ ከልብ በመገንዘብ የተሻልን መሆን አለብን፡፡ለዛም ነው ከስሜት በፀዳ መልኩ ሀሳቤን ለማቅረብ እየሞከርኩ ያለሁት፡፡

ተረኛው መሪ ይፈርዳል ህወሓት ፍርዱ የጋራ ነው አሁን ፈራጅ የነበርከውም የነበረው ስርዓት አባል እና ዋና አስፈፃሚ ነበርክ ስለዚህ ጥፋቶች በጋራ እንውሰድ መልካም ነገሮች በጋራ እንውሰድ የሚሉ ምልልሶች አይቻለሁ፡፡ ግን ምን ያረጋል የአገሬ ህዝብ ያየውን ያሳለፈውን ሚዛናዊ አርጎ ከማሳለፍ ይልቅ በሚሰማው በሚዘጋጀው ደኩመንተሪዎች የመሪውን ሀሳብ ብቻ መቀበል ሻታ ብሎም አደረገው፡፡በስሜን በኩል በቀሪው ህብረተሰብ እና መንግስት መተማመን እያጣ ሲመጣ የዛን ክልል ህዝብ ለመያዝ ስራዎች መስራት ጀመሩ፡፡ውኩኩሩ በአደገኛ መንገድ በሁለቱም መንገድ ቀጠለ፡፡

አብይ አህመድ በቅርቡ በፓርላማ እንዳወራው እንደልቤ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ መጀመሪያ በፍቅር እና ይቅርታ በሚል ሰበብ ሁሉንም አስፈታን ታጣቂዎችም ወደ አገር እንዲገቡ አደርግን ካሉ በኃላ ራሴን እና ቤቴሰቤን ለማዳን ልዩ ሃይል አደራጀሁ ይላል፡፡

ምን ማለት ነው ? አንድ የአገር መሪ ወደ መሪነት ደረጃ ሲደርስ ማድረግ እሚችላቸው እና እማይችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ እንደ ተራ ሰው ብቻውን አይንቀሳቀስም እንደ ተራ አመራር ተራ አመራሮችን በየትኛውም አገር አይሰጥም፡፡ የአገር መሪ ስትሆን ለህዝብ ተብሎ ስለሚመጣ በዛ ያሉ የግል መብቶች እንደሚከለከሉ እሙን ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ቀርቶ ይቅር እና እጩ ተወዳዳሪ እንኳን በተለየ ሴኩሪቱ ሲተም ከለላ ውስጥ ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከቤቱ ተንስቶ መሄድ እስከሚፈልግበት ቦታ ለመሄድ በራሱ ስር በሚተዳደሩ ነገር ግን ስልጣን ባላቸው መወሰን በሚችሉ ሴክሬት ሰርቢስ ፈቃድ እና እውቅና ማግኘት አለበት፡፡ ታድያ የእኛ መሪ ከአሜሪካ አሰራር የተሻለ በያመጣ ነው እንጂ እሱ ራሱ የሚያዘው ተቋም ወይም ደህንነት እንዲኖር ማድረግ በየትኛው ህግ ነው ተቀባይነት ያለው ? በየትኛውም የለም ምክንያቱም ዲክታተሮች መዋቅርን እና ሰውን ያዛሉ ዲሞክራቶች መሪዎች ግን መዋቅርን እና መመሪያን ያስፈፅማሉ፡፡

ስለዚህ መሪያችን በርካታ ህልሞች ነበሩት እንደነገሩን ከሆነ ንጉስ የሚለው ስም ብቻ ተለየ እንጂ የአንድ አገር መሪ ንጉስ የሚያደርገውን ሁሉ ያደርጋል ብሎ ሲናገር በእውነት የአገሬ ሰው አሁንም አድንቆ ነበር የሚሰማው፡፡ይህ የአገሬ ህዝብ በባህሉ እና በተማረበት አከባቢ እየተጨቆነ ስለመጣ አሁንም አምባገነን ሰው በሚጣ የሚፈልገው እና የሚሸተው መሆኑን በድጋፉ መሰከረ አጀበ አጨበጨበ፡፡

ፍጥጫው ቀጠለ፡፡

በዛ ያሉ ምልክቶች እና ፉከራዎች በሁለቱም በኩል አይኑን እያወጣ መታየት ቀጠለ፡፡ ሁሉም የአገሪቱ ጥፋቶች ለህወሓት እየተሰጡ በመጨረሻው ጥፋት ግን መንግስት ህወሓት ላይ እርምጃ በመውሰድ ከስሩ ማድረቅ እንዳለቡት በአማራ ብልፅግና በኩል መግለጫ ወጣ እንዲሁም በመንግስት ደረጃ እርሚጃ ለመውሰድ እንደ tወሰነ ነገሩን፡፡

አሁን አሁን ስንሰማ ከሰሜን ዕዝ በፊት የተለያዩ ኦፕሬሽኖች በመንግስት በኩል ተደርገው እደከሸፉ እና በኃላም ልዩ ኮማንዶዎች መቀሌ እንደገቡ የትግራይ ልዩ ሃይል ክልሉን እንደተቆጣጠረ ሰማን፡፡

በመንግስት በኩል ደግሞ ሰሜን ዕዝ ላይ ህወሓት ጥቃት እንዳደረሰ እና ህግ የማስከበር እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱ ተገለፀ፡፡ በእውነቱ ሰሜን ዕዝ ላይ የተወሰደው እርምጃ በወቅቱ የሰውን እና የወታደሩን ስሜት ኩፍኛ ስለጎዳው በተለይም በአማራ ክልል ከፀጥታው ሃይል በላይ ማንኛውም ተራ ሰው አገር እንደተወረረ ክትተ ብሎ ዘመተ፡፡

አገራችን ላይ የተፈፀሙ የታላላቅ ሰዎች ግድያ እና ሞቶች ስንመለከት ሁሉም መንግስት ያሸነፈባቸው ነበሩ የሚመስሎት፡፡ የጀነራሉ ግድያ የአማራ ክልል ግድያዎች ፤ የኢንጂነሩ  ሞት አብይ አገር ለቆ በወጣበት ጊዜ፣ የአጫሉ ግድያ ተከትሎ እነ ጃዋር የተያዙበት መንገድ አሁን ደግሞ ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ተብሎ ህዝብ ላይ ስሜት ፈጥሮ እርምጃ የተወሰደበት መንገድ ስናይ መንግስት ፊት ለፊት የማይጋፈጥ በሚመስል መልክ ሁሉንም ያሸነፈበት መነግድ እንደሆነ እኔ እረዳለሁ፡፡

ረጋ ባለ መንፈስ ግን ስናይ አንድ እርምጃ እንወስዳለን ያለ መንግስት ከአሁን አሁን ጦርነት ይከፍታል ተብሎ የሚጠበቅ መንግስት እንዴት ወታደሮቹን በተጠንቀቅ እንዳላስቆመ ሳስበው ግርም ይለኛል፡፡የሆነ ይሁን የአንድም ያለ አግባብ ሞትም ቢሆን እውነት ነው ያሳስበኛል፡፡ጦርነቱ በሁለቱም በኩል የስልጣን እና ስግብግብነት ውጤት ነው፤ ነገር ግን የማን ሚዛን ይደፋል ወደ ፊት ታሪክ የመሰክራል፡፡

እውነት ለመናገር በሶስት ሳምንት የተጠናቀቀ ጦርነት ተብሎ እንደ ድል የሚወራው ለእኔ ትርጉም የለውም፡፡ምክንያም እንዴት አንድ የፌደራል መንግስት አንድን ክልል ያውም የሰሜን ዕዝ የተባለ የአገሪቱ ትልቁ ተቋም ያለበት ሁልጊዜ በተጠንቀቅ የቆመ እንዲሁም ጠንካራ የደህንነት ተቋም ባለበት የክልሉን መዋቅር በአንድ ቀን መቆጣጠር ሲችል ተጠቅተናል ከማለት አልፎ በወር ጊዜ ውስጥ አሸንፈናል ብሎ ያውጃል ?

በዚህ ጦርነት የአብይ አህመድ ተንኮል እና እንዝላልነት ብሎም የስልጣን ጥም እስከ ጥግ የታየበት ነው ብየ መደምደም ተገድጃለሁ፡፡ ታላቁ መሪ አብይ አህመድ በቅርቡ የንጉሳዊ ስልጣን ይመስል ባዕለ ሰመቱን በድምቀት እንዲከበር ያዘዘ የሚከተሉትን ማድረግ አልነበረበትም፡፡

1.   በኢህአደግ ፎርማት ቢያንስ እስከ ምርጫ መቀጠል ነበረበት፤

2.   ህወሓትን እና ኢህአደግ ራሱን ከደሙ ንፁህ በማድረግ ያ ሁሉ የፖለቲካ ቁማር እና ስም ማጥፋት ደረጃ መድረስ አልነበረበትም፡፡

3.   ፍቅር እና ይቅርታ ብሎ የሰውን ልብ ለመግዛት የሄደበት መንገድ ከተንኮል የመነጨ መሆን አልነበረበትም፡

4.   በትግራይ ህዝብ እና በሌላው ኢትዮጵያ ጥላቻ የከረረ እንዲሆን መስራት አልነበረበትም፤

5.   ህወሓት ያደረገው ምርጫ ከቅንነት ተነስቶ እውቅና መስጠት ነበረበት፤

6.   ሁሉም ችግሮች በህወሓት ላይ መለጠፍ አልነበረበትም፤

7.   የትግራይ መንግስት ህገ ወጥ ነው ብሎ ማወጅ አልነበረበትም፤

8.   የትግራይ መንግስት በአመፅ ለመጣል እንደ ፈንቅል ያሉ አደረጃጀትን መፍጠር አልነበረበትም፤

9.   በመንግስት ደረጃ እና በአማራ ብልፅግና መግለጫ ህወሓት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለው መወሰን አልነበረባቸውም፤

10. በመጨረሻም የክልሉን ባለስልጣናት ለመቆጣጠር ኦፕሬሽን መሰራት አልነበረበትም፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን የአሁን ዘመን ሰው መቸም ቅዱስ አደለም ፣ ራሱን እንደ አብራህም ልጅ ሊሰዋ አያዘጋጅም እና ጦርነት ተገብቷል፡፡ጦርነቱ የአማራ ህዝብ እና ልዩ ሃይል ሲሳተፍበት ሮኬቶች ወደ ባህርዳር እና ጎንደር ኤርፖርቶች ላይ ተላኩ፡፡ የኤርትራ መንገስት እያገዛ መሆኑን ሲታወቅ በተመሳሰይ ተፈፀመ፡፡የትግራይ መንግስት ሰሜን ዕዝ የያዛቸውን ወታደሮች በቀይ መስቀል በኩል ለቀቀ፡፡ እንደተጠበቀው ወደ ህዝብ የላከው ሮኬት አልነበረም፡፡በተቻለ መጠን የጦርነት ህግ ለመከተል የሞከሩ ይመስለኛል፡፡

ምክንያቱም ጠቡ ከመንግስት ጋር ባይሆን ንሮ በአስር ሺህ የሚቆጠር ሰራዎት በሰላም አይለቁም ነበር፡፡ ሮኬቶቹ እና ቀድመው የያዣቸው መሳሪያዎች ህዝብን ማወደሚያ ያደርጉባቸው ነበር፡፡ ግን እውነት ነው አላደረጉትም፡፡

በመስዋዕትነት የትግራይ መንግስት መቀሌን ለቆ ሲወጣ የአብይ አህመድ ሰራዎት ትግራይን በተለይም ከተማ ሲገባ በትግራይ ህዝብ በኩል መንም ተቃውሞ አልደረሰበትም ነበር ለምን ምክንያቱም ህዝቡ ጦርነት ሰልችቶታል ብሎም የጦርነቱ ተካፋይ አልነበረም ፤ በኃላ በኃላ ግን የትግራይ ሰቆቆ ከእስራኤላዊያን ጋር ተመሳሰለብኝ፡፡

እንግዲህ ሲጀምር እንዲህ ነበር ይላል ሰሞኑን ያየሁት ስለ አንድ ጀርመናዊ የናዚ አባል የነበረ ነገር ግን በድርጅቱ አይሁዶችን እየቀጠረ የሰውን ነብስ ያተረፈ የእስራኤል ጀግና ትረካ ላይ እንደተገለፀው እና አለም እንደሚያውቀው፡፡

ሲጀምር ሂትለር ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ በከፍተኛ ስልጣን የነበሩትን አይሁዶች መጀመሪያ ከስልጣን አባረረ፤ በመቀጠል በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ ድርጅቶች ባለቤቶች የነበሩ አይሁዶች ባለ ሀብቶች ከንግድ አለም በማሰር እና በተለያየ መንገድ አስወገዳቸው፡፡ በመቀጠልም አይሁዶች ለብቻቸው ተከለው መኖር አለባቸው በማለት ለብቻቸው እንዲኖሩ እና እንዲጠበቁ ካደረገ በኃላ እንዲያው ወደ ማጎሪያ መግባት አለባቸው በማለት ከዛ ብኃላ ያሁሉ የዘር ማጥፋት ፈፀመባቸው፡፡

ህወሓት ላይም የሆነው እና እየሆነ ያለው እንዲሁ ነው፡፡

መጀመሪያ ከስልጣን እንዲወገዱ በሴራ አሁን ያለው መሪ ወደ ስልጣን መጣ ቀጠለእና በለውጥ ስም የነበሩ ባለስልጣናት በስሲቲም አባረሯቸው፣ በመቀጠልም የአገሪቱ ሰቆቃ በሙሉ እንዲለጠፍባቸው በማድረግ ሁሉም የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባን ለቀው ተጠራርገው ወደ መቀሌ እንዲገቡ ተገደዱ፡፡ ቀጠለእና በትግራይ ባላሀፍቶች ስር ያሉ ትልልቅ ድርጅቶች በሙስና እና ሌብነት የመጣ ሃብት ነው ብለው ከንግድ እንዲወጡ አደረጉባቸው ፤ ቀጠለእና ህወሓት የአገሪቱ ጠንቅ ነው በማለት እርምጃ ይወሰድበታል ተባለ ከዚህ በኃላ ጦርነቱን በተለያዩ አገሮች ወታደሮች በማሳተፍ ህወሓትን ወደ በርሃ አስወጡ፡፡ከዛስ ምን ሆነ ?

አብይ አህመድ የኤርትራውን ሰራዎት እና በስሜት ያሰማራቸውን ወታደሮች ስነምገባር እና ድርጊት መቆጣጠር አልቻለም፡፡ በህዝቡ ላይ ማዕቶች መውረድ ጀመሩ፡፡ሴቶች ይደፈሩ ጀመር ሲቪሊያን መገደል መረሸን ተጀመረ ቀጠለ፡፡በህጋዊ መንገድ ሪፖርት የተደረገ ከ500 ሴቶች በላይ ክብራቸውን ተገደው አጡ፡፡የአገሬ ሰው ምን አለ እሰይ እንኳን ተደፈሩ አለ፡፡ በራሱ ልጅ የማይደርስበት ይመስል፣ ፈጣሪ የማይመለከት ይመስል ፤ ሁሉም በልቡ እሰይ አለ፣ ዝም አለ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ወትሮ አንኳን የሁሉ ግፍ እና አንድ ሰው ሲደፈር የሚይዘው የሚቆጣጠረው ያጣ የነበረ ህዝብ ዛሬ ከ500 በላይ ሴቶች ሲደፈሩ ፀጥ ረጭ አለ፤ እሱስ ባልከፋ ይባስ ብሎ እሰይ አለ፡፡አርቲስቶቻችን፣ የመብት ተማጎቶች ፣ ወጣቱ በአጠቃላይ ህብረተሰቡ ዝምታን መረጡ ይባስ ብለው ያስተባብሉ ጀመሮ እረ እንዲያው ጠቅላዩ በፓርላማ የእኛ ወታደር በሳንጃ ነው የተደፈረው የእነሱ ሴቶች ግን በወንድ ነው የተደፈሩት አለ፡፡በእውነት እንዲዚህ የወረዳ ተራ መሪ የትኛውም አለም ላይ ታይቶ ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ልብ ይሰብራል፡፡

በተመሳሳይ ሰሞኑን የተመረቀ አንድ አዲስ ፊልም አለ፤ አዎ ስለ ሴት ልጅ ክብረ እና ሚዛናዊነት ያሳያል፡፡ምናልባችም ፊልሙ ልብ የሚነካ የሚያሳዝን ታሪክ ነው፡፡ አንዲት ለጋ ሴት ላይ የሚደርስ ግፍ እና በደል ነው፡፡ ከዚህ በላይ ፊልሙን ገብተው ይመልከቱት፡፡

ፊልሙ የሚመለከት ሁሉ ምናልባችም በፊልሙ ታሪክ እምባው ይመጣል፡፡ አዎ አዎ እዛ የትግራይ መሬት ላይ ግን ስለሚሆነው ነገር በእውነት የሰው እንባ ወደ ሰማይ መፍሰሱን ቀጥሏል፡፡ እግዛብሄር በጣም ታጋሽ እና ቸር ቢሆንም የህዝብን በደል ግን እስከመቸውም ዝም አይልም፡፡መከራ እና ግፍ ህዝቦች ላይ አመታት ሊፈጅ ይችላል፡፤ እውነቱ ግን የተጎዳ ህዝብ ሁልጊዜ ያሸንፋል፡፡ ሲያሸንፍስ እንደ ኤርትራ የራሱን አገር ከመመስረት የሚያስቆመው ሰው የለም፡፡

እነተ ህዝብ ሲጎዳ ሴቶች ሲደፈሩ የደገፋችሁ ብሎም ያልተናገራችሁ ዝምታየ ወርቅ ነው ብላችሁ የእርኩስ መንፈስ ስራ የተጠናወታችሁ ደግሞ ቅጣቱ በፈጣሪ በኩል ታገኝታላችሁ፡፡ ይህ ነው የአለም ታሪክ ፤ ይህ ነው የፈጣሪ አሰራር ; የሚመስለኝ፡፡አዎ ዛሬ የትግራይ ህዝብ ባልበላ አንጀቱ ባልከበረበት ሃብቱ ሰው ሁሉ ሲወግረው እና ሲፈርድበት ፣  ከዚህ በኃላ መሳሪያ ይዞ ቢሞት ይፈረድበታል ? አይፈረድበትም፡፡ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ደግሞ ምንም ናት፡፡

መፍትሄው ምንድነው፡፡

አንድ አገር ውስጥ መጥፎ ነገሮች እየታዩ መቶ ፐርሰንት የህዝብ ድጋፍ ካለው እና አንድም ሰው ስለ ችግሩ ተቃውሞውን በሰላማዊ መንግድ መግለፅ ካልቻሉ እመኑኝ እች አገር የአምባገነን አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህ ነው መገለጫዋ፡፡ሁሉም ሰው ይጨክናል ብሎ ማሰብ ንፉግነት ነው፡፡ አንድ አንድ ሰው በትግራይ ህዝብ ሰቆቃን ስሜቱን አደባባይ መግለፅ ቢፈልግ ታፍኖ እንደሚገደል ስለሚያውቅ ከሞሞት መሰንበትን መርጦ ዝም ብሏል፡፡

አዲስ አበባ የሚኖረው የትግራይ ህዝብ ነብሴን አውጭኝ ብሎ ዝም ብሏል፡፡

ይህ ግን እስከመቸ እንደሚቀጥል እናያለን፡፡

አዎ መፍትሄው የሚሆነው አብይ አህመድ መውረድ አለበት፡፡

ደመቀ ሞከነን መውረድ አለበት፡፡

ሌላ አዲስ አመራር መምጣት አለበት፡፡

እርግጥ ነው አብይ እና መሰሎቹ ወንጀላቸው በዝቷል፡፡ እነሱ አሁን ስልጣናቸውን ከመልቀቅ ይልቅ መቆየትን መርጠዋል፡፡ግን እስከመቸ ህዝቡ እውነታውን ሲረዳ እነዚህን ሰዎች አይተፋቸውም ? ይተፋቸዋል፡፡ ያኔ ቅጣታቸው ከባድ ይሆናል፡፡ልብ ያለህ ልብ በል ስለ እምነትህ ስትል አደርባይ ውሸታም ሁላ ፊት ለፊት መጋፈጥ ከከበደህ እንደኔ በውስጥ ታገል፣ ፀልይ ምህረትህን ከፈጣሪ እንጠይቅ፡፡አለበለዚህ መጪው አመት ለኢ/ያ የቅጣቶ ጊዜ ነው፡፡

Back to Front Page