Back to Front Page

ራሽያ፣ ቻይናና የዐረብ አገራቱ ከትግራይ ህዝብ ጋር ያላቸው ፀብ ምንድ ነው?

ራሽያ፣ ቻይናና የዐረብ አገራቱ ከትግራይ ህዝብ ጋር ያላቸው ፀብ ምንድ ነው?

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 03-14-21

 

መንደርደሪያ፥ በደማስቆ ከተማ ይኖር የነበረ አንድ የታወቀ ነጋዴ ነበር ይባላል። ነጋዴው አንድ አገልጋይ (ባሪያ) እንደ ነበረውም ይነገራል። ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ነጋዴው ባሪያውን ወደ ገበያ ይልከዋል። ባሪያው መልዕክቱን አድርሶ በተመለሰ ጊዜም በጣም ተጨንቆ፣ ታውኮና ተደናግጦ ነበርና በጌታው ፊት ሲቀርብ እጅግ መታወኩንና መናጡን በሚያሳብቅ መልኩ ነበር። በሁኔታው ግራ የተጋባ ነጋዴ፥ ሰላም አይደለህምን? ምን ሁነህ ነው እንደዚህ የተደንገጥከውና የተዋከብከው? ሲል ይጠይቀዋል። እጅግኑ የተርበተበተና የተደናገጠ ባሪያ መለሰና፥ ጌታዬ የላከኝኝ መልዕከት ይዤ ማልጄ ወደ ገበያ ወርጄ ነበር፤ ታድያ በገበያ ማኸል ሳለሁ በድንገት ሞትን አገኘሁት፤ እኔን ሲያይ ያሳየው ፊት በቃላት የሚገለጽ አይደለም። አስፈራራኝ፣ ነፍስ እስከማይቀርልኝ ድረስ አገላመጠኝ፣ አስደነገጠኝ፤ ይልቁንስ፥ በተቻለ መጠን በፍጥነት ከደማስቆ ርቂ መሄድ እሻለሁ፤ ከቻልኩ ሞት ፍልጎ ሊያገኘኝ ወደማይቻለው ስፍራ ወደ ሰማሪያ ርቂ መሄድ አለብኝ፤ እንደውም በፍጥነት ከዚህ ከተማ እንድወጣና ወደ ሰማሪያ በፍጥነት እንድደርስ ከፈረሶቹህ አንዱ ስጠኝ፥ በማለት ይማጸነዋል። ነጋዴውም ፈረሱን ሰጥቶ ባሪያውን ይሸኘዋል። አመሻሹም ነጋዴው ራሱ ወደ ገበያ ይወርዳል፤ በዚያም በድንገት ከሞትን ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ። በነገሩ እጅግ የተቆጣው ነጋዴ፥ ስማ አንተ ለምንድ ነው ባሪያን ነፍሱ እስክትወልቅ ድረስ ያስፈራራኸውና የዛትክበት? በማለት ይጠይቀዋል። በነገሩ የተደናገጠ ሞት፥ ኧረ እኔ ማንም አላስፈራራሁም፤ ባሪያህ እንደሆነ ዛሬ ማታ በሰማርያ ቀጠሮ ስላለን በዛሬው ዕለት በደማስቆ አየዋለሁ ብዬ ፈጽሞ ስላላሰብኩትና ስልገመትኩት ከመደነቄ የተነሳ እጅጉን መገረሜን የሚገልጽ ፊቴን አይቶ ነው ይለዋል። ባሪያው ጌታውን ሲማጸን፤ ነጋዴው ለባሪያው አስቦ ፈረሱ ሲሰጥ ለካ ፈረሱን ሰጥቶ በፍጥንት እንዲያቀጥነው የረዳው ለሞት ነበር። የአማራ ልሒቃን የኤርትራው አምባገነን መሪ ኢሳይያስ አፈወርቂ ለዐቢይ አህመድ ዓሊ ያደረጉትና የዋሉለት ውለታ ቢኖር ይህ ነው። ምክራቸው፥ በፈጣን ባቡር ትኬት ቆርጠው ነው ወደ ጥፋት የላኩት።

 

ሰብአዊነት የሌለው ስለ ዜጎች ሰብአዊ መብት መደፈር አይገደውም

 

ተፎካካሪ ርዕሰ ኃያላኑ ራሽያና ቻይና፤ ከባቢያዊ ፊርጣማዎቹ (regional power) ቱርክና ሳውዲ ጨምሮ፥ ግብጽ፣ ኤምሬት፣ ካታር በቀጠናው (በቀንድ አፍሪካ) ላይ ያላቸው ፍላጎት እጅግ ልዩ ልዩ ቢሆንም አገራቱ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አጀንዳ ግን አንድና አንድ ነው። ይኸውም፥ ሁሉም በየፊናው እንዳሻቸውና እንደወደዱ ገብተው የሚወጡባት ደካማ ኢትዮጵያ መፍጠር ነው። ይህን አጀንዳ እውን ለማድረግም፥ መጽሐፍ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል እንዲል፤ ኃያላኑ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ለእነሱ በምትመች መልኩ ለመቅረጽና ለማሰናዳት ያስችላቸው ዘንድ የኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና የሥልጣኔ ማዕከልና ምሰሶ የሆነ ህዝብ ማለትም የወራሪ ኃይሎች አጀንዳና ዕቅድ መና የማስቀረት አቅምና ብቃት ያለው የትግራይ ህዝብ ማጥፋትና ማጽዳት ላይ ይስማማሉ። በመሆኑም፥ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ድንገተኛ ፖለቲከኛ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ጌቶቻቸው የሰጥቷቸው የቤት ስራ በአግባቡ ለመፈጸም፤ ኃያላኑም ከኢትዮጵያ የሚፈልጉትን ሁሉ ያለ አንዳች መስተጓገል በተገቢ ሁኔታ እንዳያገኙ እንቅፋት ነው ተብሎ የታመነበትና ጥርስ የተነከሰበት የትግራይ ህዝብ ዘሩን ለማብረስ ተረባርበዋል።

 

Videos From Around The World

እነዚህ አገራት ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ቢመቻቸውም ባይመቻቸውም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጥቅም ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደ ማንኛውም አገር በልክ/በህግ ሲገቡና ሲወጡ የነበሩ አገራት ናቸው። ዕድሉን ስያገኙ ግን ይህ ሁሉ ታሪክ ሆኖ በማንኪያ እየሰጡ በአካፋ ለመውሰድ አሰፍስፈው በመነሳት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ግንባር ፈጥረው በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄዱትና እያካሄዱት ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊዎች ለመሆን በቅቷል። ይህ ማለት ግን፥ ራሽያ ሆነች ቻይና ሳውዲ ሆነች ኤምረት ኤርትራም ሆነች ሶማሊያ፥ የትግራይ ህዝብ ዘሩ እንዲጠፋ እየተደረገ ባለው ግልጽ የሆነ ዘመቻ ተሳትፏቸው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በመደገፍ ሳይሆን ራሱ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በመጠቀም ኢትዮጵያን እንደ አገር የማጠልሸት፣ የማንኮታኮትና የማዳከም አጀንዳቸው ላይ መትጋታቸው መሆኑን ልብ ማለቱ አስፈላጊ ነው። በተለይ ቻይናና ራሽያ በአሁን ሰዓት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ማንነት መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በተመለከተ በጸጥታው ምክር ቤት ያሳዩት ዝምታ፥ ዐቢይ አህመድና ደጋፊዎቹ እንደሚሉት አገራቱ የኢትዮጵያ ደጋፊዎችና ወዳዶች መሆናቸው ሳይሆን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እርስ በርሳቸው በሚፈጥሩት ጦርነትና እልቂት የተነሳ ልትፈጠር የምትችለው ኢትዮጵያ እንደ አገር ተመጽዋች አገር ሆኗ የማየት ፍላጎት ስላላቸው ነው። ራሽያኖች ይህን ዓይነቱ መጫወቻ ህግ ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ የመዘዙት አዲስ ካርታ ሳይሆን ሶቬት-ህብረት በተለይ ቀዝቃዛ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ዘመን፥ በአፍሪካ፣ በማዕከላይ ምስራቅና በላቲን አሜሪካ በተደጋጋሚ ተግባራዊ ስታደርገው የነበረ በዚህም የዳበረ ልምድ ያላቸው ሰዎች ናቸው።

 

በተጨማሪም፥ ራሽያ ሆነች ቻይና የአገራቱ ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል ያደረገ በዋናነት ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ተቃርኖ የተነሳ በየትኛው ስፍራ አብረው የመስራት ዕድሉ እጅግ ጠባብ መሆኑን ልብ ይሏል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ በጋራ በትግራይ ላይ የፈጸሙት ወረራ፥ የኃያላኑ አገራት አለመግባባት ከፈጠሩ ኹነቶች መካከልም አንዱ ለመሆን በቅቷል። ሌላው፥ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ከሆኑ አገራት መካከል ራሽያና ቻይና በሰብአዊ መብት አያያዝ ሆነ የዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብት በመጠበቅ ረገድ አስከፊ የሚባል ታሪክ ያላቸውና አሁንም ቢሆን ከዚህ የጨለማ አሰራር ያልተላቀቁ አገራት ለመሆናቸው የሚያከራክር አይደለም። በሌላ አገላለጽ እነዚህ አገራት፥ በዜጎቻቸው በሚፈጽሙት አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰት የታወቁ አገራት እንደ መሆናቸው መጠን ስለ ሌሎች ዜጎች መገፋት ትርጉም ይሰጣቸዋል የሚል ሰው ይኖር እንደሆነ ሲበዛ የዋህ ነው። አገራቱ በሰብአዊ መብት ጥሰት የታወቁ፣ ነጻና ገለልተኛ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት የሌሏቸውና እንዲኖሯቸውም የማይፈቅዱ አገራት ከመሆናቸው በላይ የተለየ ሃሳብ የሚራምድና የሚንጸባርቅ ዜጋ በወጣበት በማስቀረት የሚታወቁ አገራት ናቸው። ከነተረቱ፥ ግማታም ግማታምን ቢስመው አቤት ሽቶህ አቤት ሽቶህ ይባባላሉ እንደሚባለው ላለፉት አራት ወራት ሙሉ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመውና እየተፈጸመው ያለው ማንነት መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ ራሽያና ቻይና ያሳዩት ዝምታ አንድምታው ቀደም ሲል እንደተገለጸው የአገራቱ ተፈጥሯዊ ባህሪይ ነጸብራቅ ነው።

 

ራሽያኖች፥ በኢትዮጵያ አልያም በኤርትራ ላይ ካላቸው ፍላጎት ይልቅ ከግብጽ ቀጥሎ (ግብጽ በህግ ስለማትፈቅድ) በሌሎች የአፍሪካ አገራት ላይ ጦር መሳሪያ ለመሸጥና ሸቀጣ ሸቀጠችዋን ለማራገፍ እንደ መግቢያ በር ለመጠቀም፣ በአከባቢው የሚተላለፈው የንግድ መስመር ለመቆጣጠር ያስችላት ዘንድ በሱዳን ላይ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላት ላለፉት ዓመታት ከሱዳን መንግስት ጋር ያሳየችው መተሻሸት መመልከት በቂ ነው። ነገሩም ከመተሻሸት ያለፈ በሱዳን ፖርት ላይ ራሽያኖች ትልቅ ሊባል የሚችል ህልውና እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል። ጠቅለል ባለ መልኩ፥ ኢትዮጵያ በዘመነ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ምንም ዓይነት እምነት የማይጣልባት አገር እንደሆነችና ድካም የማይጠይቅ አጋጣሚ ሲፈጠር ግን ደግሞ አጋጣሚውን መጠቀም አይጎዳም! በሚል መርህ ካልሆነ በስትቀር በአሁን ሰዓት ኃያላኑ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለመታደግ ሰባራ ሳንቲም ወጪ አያደርጉም።

 

ቻይናም ብትሆን ይህን መሰል አጋጣሚዎች በመጠቀም አገሪቱ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በባለቤትነት ለመዘወር የሚያስችላት ወጥመድ ከመዘርጋትና ከማመቻቸት ያለፈ ለኢህአዴግ ያልጠቀመች ቻይና ዐቢይ አህመድ ዓሊን ከምንም ዓይነት አደጋ የመታደግ ፍላጎት ሆነ ልማድ የሌላት አገር ናት። ከነተረቱ፥ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም እንደሚባለው ቻይና ካለው ጋር መመሳሰልን፤ ያለውን ሲያልፍ ደግሞ ከሚመጣ ጋር አብራ የምትሰራ አገር እጅ ለዐቢይ አህመድ ዓሊ ስትል በተለየ መልኩ የምትከፍለው መስዋዕትነት የለም፤ አይኖርምም። ቻይናውያን እስካለ ድረስ ካለው ጋር አብረው ይሰራሉ ዘወር ሲል ደግሞ ከሚመጣው ጋር የመስራት ባህል ያላቸው ህዝቦች ናቸው። ቻይና ከአውሮፓ አገራት በምታደገው የንግድ ልውውጥ አርባ በመቶ የሚሆነው የሚንሸራሸርበት አከባቢ ለመጠበቅ ያሽላት ዘንድ ስታስብም ከኤርትራ ይልቅ በጅቡቲ ላይ ራስዋን አደላድላለች። በጥቅሉ፥ ራሽያም ሆነች ቻይና ግብጽን ሳያማክሩና ከግብጽ ጋር ሳይስማሙ፤ አንድም የግብጽ ብሔራዊ ጥቅም ሊጋፋ በሚችል ሁኔታ ኢትዮጵያን ለመርዳትና ለማጠናከር ሁለት እጃቸው ሰብስበው የሚፈተፍቱት ጉዳይ አይኖራቸውም። በተጨማሪም፥ አገራቱ (የራሽያና የቻይና) ከምዕራባውያኑ በተለይ ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ተቃርኖ የተነሳ የሚያራምዱት አንጻራዊ አቋም ሳዳምና ጋዳፊ የመሳሰሉ አምባገነን መሪዎች ከተጠያቂነት አላስመለጠም።

 

በተመሳሳይ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የቱርክ መንግስት ደጅ እየጸናበት የሚገኝበት ምክንያት የተመለከትን እንደሆነ የቱርክ መንግስት በአሁን ሰዓት ሱዳንን እያስተዳደረ ከሚገኘው ግዢ መንግስት ጋር ላይ ያለው አንጻራዊ አቋም ብቻ የተያያዘ ነው። በአሁን ሰዓት በጦርነት እየተናጠችና ኢኮኖሚያዊ ቁጠባዊ ቁልቁል እየወረደ የምትገኘው ኢትዮጵያ ዓይነቱ አገር ለቱርክ አዋጪ አይደለችም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከሱዳን በኩል የተፈጸመበትን ወረራ ለመካላከል አቅም በጣበት ሰዓት የቱርክ መንግስት ደጅ የሚጸናበት ምክንያትም ከኢትዮጵያ አጀንዳ ይልቅ የቱርክ አጀንዳ ለማራመድ ዝግጁ መሆኑን ለማሳየትና የቱርክ መንግስት ወክሎ የኢትዮጵያውያን ደም ደመ ከልብ ለማድረግና ለመገበር፤ ቱርክ እንድታስታጥቀውና እንደ ፈረስ እንድጋልበው መማጸኑን እንጅ ኢትዮጵያ በቱርክ መንግስት ፊት ለመደራደር የሚያስችላት አንዳች አቅም የላትም።

 

ኤርትራም ብትሆን አገሪቱ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የገባችበት ድቅድቅ ጨለማ፤ በዓለም መድረክ የተከናነበችው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ወጥታ እንደ አገር ለመቆምም ሆነ ለመቀጠል ደካማ ኢትዮጵያ መፈጠር እንዳለባት አበክራ የምታምን የበከተች አገር ናት። ይህ እምነትና አስተሳሰብ የኤርትራ መሪ የሆኑት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጠንካራ እምነት ነው። ፕሬዝዳንቱ፥ የዐቢይ አህመድና የአማራ ልሒቃን ጥሪ በደስታ ተቀብለው የትግራይ ህዝብ ዘሩ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራዊታቸውን ያሰማሩበት ምክንያትም ፕሬዝዳንቱ በትግራይ ላይ የፈጸሙት ወረራና ያደረሱት በደል ለሃያ ዓመታት ሙሉ ሲመኙት የነበረ ነው። አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ የመቅድሾ ወታደር ሳይቀር በማስተባበር ከዐቢይ አህመድና ከአማራ ልሒቃን ጋር ግንባር በመፍጠር ትግራይን የወረሩበት ምክንያት ኢትዮጵያን ለማቆምና ለመትከል ሳይሆን አጋጣሚውን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለመንቀልና ለማኮላሸት ነው። ኢትዮጵያን እንደ አገር፥ ማጠልሸት፣ ማተረማመስ፣ ማንኮታኮትና ማዳከም የሁሉም የውጭ ኃይሎች የከረመ ምኞትና ፍላጎት ነውና።

 

የዐረብ አገራቱ የድጋፍ አጀንዳና አሰላለፍስ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?

 

በሚቀጥሉት አርባና አምሳ አመታት የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት ወደ አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ከፍ እንደሚልና ከዚህ የተነሳም ኢትዮጵያ በዓለም በህዝብ ብዛት በአስረኛ ደረጃ ልትመደብ እንደምትች ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ ፈጣን የህዝብ ብዛት ዕድገት ታድያ በቀጠናው ልዩ ፍላጎት ላላቸው፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል ያለማቋረጥ በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ሲያሴሩ የኖሩ የረጅም ዘመናት ታሪክ ያላቸው የባህረ ሰላጤ አገራት፥ የምስራቅ አፍሪካ አገራት የመቀራመት፣ ቀጠናው በበላይነት የመቆጣጠርና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለማስፋፋት ያሰሉት ሂሳብ ውሃ የሚቸልስ ሰበር ዜና እንደሆነባቸውም ይነገራል። የባህረ ሰላጤ አገራቱ ዐቢይ አህመድና ኢሳይያስ አፈወርቂ በማግባባት፣ በማስተባበርና በማስታጠቅ በቀጥታ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊዎች የሆኑበት ምክንያት እንደሚከተለው በአጭሩ እንመለከታለን።

 

(1) ዐረብ አገራቱ ደካማና ኤርትራን የምትመስል የበከተች ኢትዮጵያ ለመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘመቱበት ምክንያት፥ እነዚህ የባህረ ሰላጤ አገራት በብዙ አቅጣጫ እየተለወጠች የመጠችውን፤ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ያላትና ባለቤት ከሆነችው ከአፍሪካ ጋር በተለይ ደግሞ ከቀንድ አፍሪካ ሀገራት ጋር ልዩ ኢኮኖሚያዊ ትስስርና ትብብር እንዲኖራቸው ስለሚፈልጉ ነው ከዚህ ባሻገርም፥ የቀንድ አፍሪካ በቀጠናው ያለው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ተጽዕኖ፤ የሚያስገኘው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትርፍ የራሳቸው ለማድረግ ስለተነሱ ነው። ታድያ ይህ የዐረብ አገራቱ ፍላጎትና ምኞት ላለፉት 30 ዓመታት ከህልም ያለፈ ተጨባጭነት አልነበረውም። በርግጥ፥ የባህረ ሰላጤ አገራት ኢኮኖሚ ከመላ ጎደል የነዳጅ ድፍድፍ በመሸጥ ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው። እንደነ አይ.ኤም.ኤፍ (IMF) የመሳሰሉ የዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅቶች የእነዚህ አገራት ኢኮኖሚ ዘለቄታነት እንደ ሌለውና እንደ ማይኖረው በተለይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል ከጀመረ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ ስጋታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተያይዞ የባህረ ሰላጤ አገራቱ በነዳጅ ላይ ያላቸው ጥገኛነትን በመቀነስ ኢኮኖሚያቸውን ለመደጎምና ለማስቀጠል ልዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። ከዕቅዶቻቸው መካከል አንዱ፥ በአፍሪካ ገበያዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ በአፍሪካ ውስጥ የጎላ ሚና ለመጫወት ያሳዩት ፍላጎት ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ ምድር ትልቁና ከፍተኛ ውጪ እንደሚጠይቅ የተነገረለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነባው የመሰረተ ልማት ባለቤት ዓረብ ኤምሬት መሆኗን ልብ ይሏል።

 

ዐቢይ አህመድና ኢሳይያስ አፈወርቂ በሁለቱም ሀገራ መካከል የነበረው መቆራቆስና የለየለት ጸብ አክትሞ ሰላምን ለማውረድ በሳውዲ ዓረቢያ አስታራቂነት የተፈራረሙት ሰነድ ያረፈበት ቀለም ሳይደርቅ በሦስት ወራት ውስጥ .. ታህሳስ 2018 / በሳውዲ አዘጋጅነት የጅቡቲ፣ የሱዳንና የሶማሊያ ተወካዮች የሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ በሆነችው በሪያድ ከተማ አዲስ የቀይ ባህር የደህንነት ጥምረት ለመፍጠርና ለመወያየት ተሰባስበው እንደ ነበር የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያን በቅርብ ርቀት በጥንቃቄ ሲከታተሉና በገደብ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህ የባህረ ሰላጤ ሀገሮች የዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በአደባባይ ጣልቃ ሲገቡና ሲፈተፍቱ በተደጋጋሚ ተስተውሏል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ስልጣን በወጣ ማግስት የመጀመሪያ ጉዞው ያደረገው ወደ ኢምሬት ነበር። እንደሄደም እንዲሁ በባዶ እጁ አልተመለሰም። ይልቁንም፥ ዕርዳታ መልክ የተበረከተለትን ሦስት ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ይዞ ነበር የተመለሰው። ከአንድ ወር በኋላ ሱዳን ከኢምሬቶች አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘትዋን ይታወቃል ታድያ፥ አገራቱ ይህ ሁሉ ሀብትና መዋዕለ ነዋያቸው በኢትዮጵያ ላይ ፈሱ ሀብታቸውና ገንዘባቸውን የሚጥሉበት ቦታ ስላጡ፣ እንዲሁ ቸሮች ስለሆኑ በነጻ መስጠት ባህል ስላላቸውና ስለፈለጉ፣ ለጋሶች ስለ ሆኑ፣ ሀብታቸውን ማካፈል ስለወደዱ/ስለሚወዱ፣ ስላዘኑልን፣ ኢትዮጵያ ማደግና መለወጥ አለባት! ብለው ስለሚያምኑ፣ የኢትዮጱያ ህዝብ ብልጽግና ማየት ስለሚናፍቃቸው ነው! አይደለም ሐቁም ከዚህ ሁሉ የራቀ ነው። ኤርትራና ሱዳን ቢልዮን ዶላሮችን ከሳውዲስና ከኢምሬቶች ሲቀበሉ እንዲሁ በነጻ አልነበረም። ሁለቱም አገራት ከአረብ አገራቱ የተሰጣቸው ገንዘብ ቆርጠም አድርገው በልተው እናመስግናለን! በማለት ብቻም እጅ ነስተው ለማምለጥ አልተቻላቸውም። ይልቁንም፥ እንደተቀበሉ ሁለቱም አገራት ከኢራን ጋር የነበራቸው ግንኙነት ከማቋረጣቸው ባሻገር ሳውዲ በድሃዋ የጎረቤት አገር በየመን ላይ ለከፈተችው ጦርነትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ኤርትራ አሰብ ለወታደራዊ አገልግሎት ስምሪት የሚውል ስፍራ በመስጠትና ወትደሮችዋንም በማይመለከታት ጦርነት በመላክ የበላችውን ለመትፋት ተገዳለች ሱዳንም በተመሳሳይ የሳውዲ ጦርነት ይዋጉ ዘንድ ወታደሮችዋን ወደ የመን የጦርነት ግንባር በመላክ የዜጎቻቸው ደም ደመ ከልብ በማድረግ ለዓረብ አገራቱ ያላቸውን ፍቅርና መገዛት አስመስክሯል።

 

ጥያቄው፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከአረብ አገራቱ የተቀበለው የገባበት ያልታወቀው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በምን መልኩ ያካክሰው ይሆን? ብለን መጠየቃችን አይቀርም። በኢትዮጵያ እስላማዊ ባንክ በመክፈት? በአፍሪካ ትልቁ የእስልምና እምነት ተከታዮች የመስገጃ ስፍራ በመገንባት? እስልምና ኃይማኖት የፈለገውን ያክል በፈለገው አቅጣጫ እንዲያድግና እንዲስፋፋ እንዲሁም በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ የአንበሳ ድርሻ እንዲይዝ በመፍቀድ? ብሎም ክርስትና በኢትዮጵያ በማዳከምና በመገዝገዝ? የአገሪቱ የልማት አውታሮች አገ ተወላጅ በሆኑ ባለሀብቶች እጅ እንዲወድቅ በመፍቀድና ሰፊ ዕድል ለእነሱ በመስጠት? ዜጎ እያፈናቀለ የአገሪቱ ለም የእርሻ መሪት በኢንቨስትመንት ስም አሳል በመስጠትና በመቸብቸብ? ኢትዮጵያ በቀንድ አፍሪካ ያላትና ሊኖራት የሚችለውን ተጽዕኖ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅምና መብትን መከበር በማዋል ፈንታ ሉዓላዊነትዋ በማስደፈርና አሳል በመስጠት? አረብ አገራቱ በሚከፍቱት ጦርነት ሞታቸውን ለመሞት ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይሎችዋን ላከች እየተባለ ወታደሮችዋን እየላከች የመቃብር ሲሳይ በማድረግ? ምን አለፋዎት፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከአረብ አገራቱ የተቀበለው ገንዘብ ልክ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማክሰም ተግቶ እየሰራ ነው። የሚያሳዝነው የትግራይ ህዝብ የዚህ ሁሉ ግፍና መዓት ሰለባ መሆኑ ብቻ ነው።

 

(2) ዐረብ አገራቱ ደካማና ኤርትራን የምትመስል የበከተች ኢትዮጵያ ለመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘመቱበት ምክንያት፥ የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ ስለሚፈልጉ ነው። ኔዘርላንድስ መቀመጫው ያደረገ ክሊኒዳል ኢንስቲትዩት (Clingendael Institute) የተባለ ቲንክታክ ባደረገው ጥናት መሰረት ዓረብ አገሮቹ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሱዳን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ለም የእርሻ መሬት ለመግዛት 13 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ማድረጋቸውና ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰሳቸውን ዘግቧል። ይህ ድኃውን ማኅበረሰብ እያፈናቀለ ለባለሀብቶች የሚቸበችበው መሬት የመሬት ንጥቂያና ችብቸባ (ንግድ) ሆኖ ሳለ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግን የእርሻ ኢንቨስትመንት ሲል በቁልምጫ መጥራት ገፍቶበታል።

 

ሳውዲ ዐረቢያ የዝናብ እጥረት ያለባትና እምብዛም ለም የእርሻ መሬት የሌላት አገር ናት። ታር በተመሳሳይ የራስዋ ምግብ የማታመርት ከውጪ በማስገባት ክፉኛ ጥገኛ የሆነችና ንግድ ላይ የተመስረተ ኢኮኖሚ ያላት አገር ናት። ከዚህ የተነሳ በተወዳዳሪነት ለመቀጠል የንግድ አድማስዋን ማስፋትት ትሻለች። ሳውዲዎቹ አምስት መቶ ሺህ ሄክታር ለም የእርሻ መሬት ታንዛንያ ውስጥ ገዝተው እርሻ ላይ ለመሰማራት የተገደዱ ወደው አይደለም። ታሮች በተመሳሳይ .. 2018 / የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ግማሽ የአሜሪካን ቢልዮን ዳላር ወጪ አድርጓል። ይህ በቀይ ባህር ላይ ስፍራ ለማግኘት ያወጡትን አራት ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ ሳይጨምር ነው። ታድያ ይህ ሁሉ ለሱዳን አስበው አላደረጉትም። በርግጥ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት የገባችበት የድህነት ጥልቀት የዐረቡ አገራት እጅ እንድትመለከትና እንድትጠብቅ አስገድዷታል በአንጻሩ ደግሞ፥ እነዚህ አረብ አገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውና ለወደፊቱም ሊመሰርቱት የሚፈልጉት ግንኙነት በዋናነት የራሳቸውን ጥቅም ያስቀደመ እንጅ የኢትዮጵያ ጥቅም ማዕከል ያደረገ አለመሆኑ ስንመለከት በረጅም ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ፈጥረው የሚችለው ጠባሳ በቀላሉ የማይሳት ያደርገዋል። የተፈጥሮ ሃብት የተገኘ እንደሆነ ቀድመው እንዲቆፍሩት እንዲመዘብሩና እንዲዘርፉ፤ የሀገራቱ ምርት እዚሁ አምጥተው እንዲያራግፉ ንግዳቸውን እንዲያጧጥፉ፤ በአጠቃላይ፥ በኢትዮጵያ ለሚደረገው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለመቆጣጠር ያስችላቸው ዘንድ የአገራቱ ባለሀብቶች በተለየ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ኔትዎርክ ለመዘርጋት ትግራዋይ የሚባል ህዝብ የከሰመባት ኢትዮጵያን በብርቱ ይፈልጓታል። ይህን ፍልጎታቸው ለማሳካት ያስችላቸው ዘንድ ደግሞ ራሱን ችሎ የሚቆም ጠንካራ ህዝብና መንግስት ማየትም ሆነ መስማት አይፈልጉም። የሚፈልጉት የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ያልበሰለ፣ ወስላታ፣ የተልፈሰፈሰ ደካማ መንግስትና እርስ በርሱ የሚናከስና የሚባለ ህዝብን ማየትን ይሻሉ። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ደግሞ ይህን የዐረብ አገራቱ ፍላጎት ለማሟላት አመ ሰው በመሆኑ አገሩንና ህዝቡን በገዛ እጁ እንዲያወድምና እንዲጨፈጭፍ ከጎኑ መቆማቸው ደንቀን አይገባም በመሆኑም ዐረብ አገራቱ ድሮንና ዘመናዊ መሳሪያ ሲያታጥቁት ኢትዮጵያን ስለሚወዱና ዐቢይ አህመድን ስለሚደገፉ ሳይሆን አገራቱ ሊፈጥሯትና እውን ሆና ማየት የሚፈልጓትን የበከተች ኢትዮጵያ ለመፍጠር የተመቸ ሰው በመሆኑ ነው።

 

(3) ዐረብ አገራቱ ደካማና ኤርትራን የምትመስል የበከተች ኢትዮጵያ ለመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘመቱበት ምክንያት፥ በእምነት የምትመስላቸው አስተማማኝ የሆነች እስላማዊ ወዳጅ አገር መፍጠር ስለሚሹ ነው። ቀለል ባለ አማርኛ፥ እነዚህ የባህረ ሰላጤ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ልዩ ፍላጎት ሲጠቃለል በሸሪዓ የምትተዳደር ኢትዮጵያ መፍጠር ነው ሳውዲ ዓረያ፣ ቱርክ፣ ዓረብ ኤምረትና ግብጽ የመሳሰሉ በኢትዮጵያ ላይ ልዩ ልዩ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊና ኢኮኖሚ ፍላጎት ተልዕኮ ያላቸው እስላማዊ ሀገራትና መንግሥታት እንደፈለጉ ገብተው ለመውጣት ያስችላቸው ዘንድ (መተማመን ለመፍጠር) በሸሪዓ ህግ የምትተዳደር እስላማዊት የጎረቤት አገር ኢትዮጵያ መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ። ይህ ኢትዮጵያ በማሰለም ኢትዮጵያ የዓረብ አገራት ፖለቲካ ተባባሪ የማድረግ አጀንዳ እንዲሁ በቀላሉ ሊያሳኩት እንደማይችሉ አሳምረው ቢያውቁም የኢትዮጵያ ክርስትና ጠንካራ ይዞታና ምሰሶ የሆነው ትግራይንና የትግራይን ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ በመምታትና በማዳከም እውን ሊሆን እንደሚችል ግን ያምናሉ። ህግ የማስከበር ዘመቻ በሚል ሽፋን በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት ዓላማዎች መካከል አንዱ ይህን የዐረቡ አገራት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ መሬት ላይ የሚገኘው ማንኛውም የክርስትና እምነት አሻራ ያለፈበት ሁሉ ሙሉ በሙሉ የማውደምና የማብረስ ዘመቻ የሚያጠቃልል ነው።

 

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጠንካራ ይዞታ ምሰሶ (strong hold) በሆነችው ትግራይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ገደማት እንዲሁም በካህናቶችዋ ላይ የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ድንገተኛ ሳይሆን በዓላማ የተፈጸመ በክርስትና ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። በአሁን ሰዓት ሰባ አምስት መቶ የሚሆኑትን የትግራይ አብያተ ክርስትያናትና ገዳማት፥ ክርስትና በትግራይ ምድር ላይ ነበር ለማለት በማይስችል ሁኔታ በኢትዮጵያ፣ በሱማሌ፣ በሶማል፣ በአፋር፣ በአማራና በኤርትራ ጦር ሠራዊቶች ወድመዋል፣ ቅድሳት መጻሕፍት ተቃጥለዋል፣ ተዘርፏል ካህናት እንደ ከብት ታርደዋል፣ የካህናት ሚስቶች ተደፍሯል። የትግራይ አብያተ ክርስትያናትና ገዳማት በታንክና በከባድ መሳሪያ እንዲወድ ተደጓል። የሚደንቀው፥ ሃይማኖት የሌለው የሻዕቢያ ሰራዊት እየመራ ይህን ያደረገና ያስተባበረ ኃይል ሌላ ምንም ሳይሆን በነጋ በጠባ ቁጥር፥ ኢትዮጵያ የእመቤታችን የአስራት አገር ናት፣ ትዮጵያ የክርስትና ደሴት ናት ወዘተ በማለት የሚታወቁ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ያሰማሩት የአማራ ሰራዊት መሆኑ ነው። እውነት ነው፥ ክርስትና በኢትዮጵያ ምድር ታሪክ የሚሆንበትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ /ያን ወደ ሙዝየምነት የምትለወጥበት ዘመን በደጅ ነው።

 

(4) ዐረብ አገራቱ ደካማና ኤርትራን የምትመስል የበከተች ኢትዮጵያ ለመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘመቱበት ምክንያት፥ ዐረብ አገራቱ ቀጠናው የመቆጣርና የመቀራመት ከፍተኛ ፖለቲካዊ አጀንዳ ስለላቸው ነው። ኤምሬቶች በአከባቢው ላይ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ካላቸው የባህ ሰላጤ አገሮች በግንባር ቀደምትነት የምትመደብ አገር መሆንዋን ይታወቃል ላለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ አየርና ምድር ላይ ማፈናፈኛ ያጡ አገራቱ ኢትዮጵያን የመክበብና በኢትዮጵያ ዙሪያ ላይ የሚገኙ አጎራባች አገራት ላይ ህልውናቸውን ማስፈን ጀመሩ ከራርመዋል ኢምሬት .. 2017 ወዲህ ጀምሮ በኤርትራና በሶማሊያ ላይ ወታደራዊ ካምፕ የገነባችውና ወታደሮችዋን ያሰፈረች ሲሆን በሱዳን የሚገኘው የባህር በርዋንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደሰችና እያጠናከረችው ትገኛለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም፥ ሳውዲ ዓረብያ በጅቡቲ ቱርክ በሶማሌ ምድር ላይ የገነቡትን የጦር ካምፖች በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ መልዕክቱ ግልጽ ነበር ይህ ኢትዮጵያን የመክበብ ስትራቴጂ ዓላማ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመቆጣጠር የኢትዮጵያ የደህንነትና ዲፕሎማሲ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመዘወርና ለመቆጣጠር ያለመና ያነጣጠረም ነው። ሳውዲ ዓረቢያ፣ ኳታር፣ ኢምሬት፣ ግብጽም ሆነች ሱዳን ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ያለባት ኢትዮጵያ በጦርነት ሊወሩ፣ ሊያሸንፉ፣ ሊቆጣጠሩና ኢትዮጵያን በሠራዊት ብዛት ሊያንበረክኩ እንደማይችሉ ከታሪ በቂ ትምህርት የቀሰሙ ሀገራትና መንግሥታት ናቸው። ኢትዮጵያን ማንበርከክ የሚችሉበት መላ ፈጥረው ተግባራዊ ከማድረግ ግን ተኝተው ያደሩበት ሌሊት የለም። በኢትዮጵያ ታሪክ የውጭ ኃይሎች በመመከት የታወቀና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ጠብቆ በማስጠበቅ የአንበሳ ድርሻ የሚወስደው የትግራይ ህዝብ በጥቂቱ ቀደም ሲል የተመለከትናቸው አራት ነጥቦች ዐረብ አገራቱ ጨምሮ ሌሎች በቀጠናው ጠንካራ ፍላጎት ያላቸው አገራት አጀንዳ ፍላጎታቸው ምኞት ብቻ ሆኖ እንዲቀር በማድረጉ፣ ብሎም በማምከኑና በማክሰሙ ጥርስ የተነከሰት ህዝብ የትግራይ ህዝብ፥ አገራቱ ኃይማኖት የሌላቸው ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃንና ዐቢይ አህመድ ዓሊ በመጠቀም ዘሩን ለማብረስ ተረባርበውበታል። በርግጥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የራሽያ፣ ቻይና፣ የሳውዲ፣ የኢምሬትና የኤርትራ ጠልቃ ገብነት እኔን ስለ ሚወዱኝና ስለሚደግፉኝ ነው! እያለ ቢያሟርትም ሐቁ ግን አገራቱ የአገሪቱን ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያስችላቸው ዘንድ ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ሊኖር አይችልም ብለው ስለሚያምኑ ደካማ ኢትዮጵያ መፍጠር ተረባርቧል

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page