Back to Front Page

የቦነነውዱቄት

*የቦነነውዱቄት*

 

ኢየሩ

06-28-21

 

'ፈጨነው ላቆጥነው 

በአየር እንደ አቧራ 

ብን ኣርገን በተነው

ጁንታውን ጌም ኦቨር

ብለን ቀጠቀጥነው' '

የርስት ቦታችንን 

ዳግም  አስመለስነው

ብሎ እንዳልዘፈነ

ጉረኛው ኣማራ

ደቀ መዛሙርቱ 

ጨካኙ ኤርትራ 

Videos From Around The World

ታዲያ ማነው አሁን የሆነው አቧራ 

ትግራይ አትገዛም በግፍና ጒራ

እርማችሁን አውጡ ኢትዮኤርትራ

ጭካኒያችሁ ጥጉ ብልግናችሁ ጫፉ

የፈፀማችሁት ግፋችሁ መቅፈፉ 

ታዝበናችኋል ከአገራችን ጥፉ።

የትግራይ ህዝብማ አያችሁት አይደል 

በሰብአዊ ምግባር ምርኮኛ ሲቀበል?

እኮ ማነው የተሸከመው ውርደትና ውድቀት

ስሙ የናንተ ነው የበነነ ዱቄት።

ቀኑና ሳምንቱ ወራቱ ቢረዝም 

ሳትምበረከኩ ትግራይ ዝምአትልም 

ቅዠት ሆኖ ሳይቀር የኢሱ ና አብይ ህልም።

ኑሩ ተከበሩ 

ቆራጦች ጀግናዎች

ስማችሁ ተጋሩ

እንዳትዘናጉ እንደ ድር እበሩ

እጅ ለእጅ ቁሙ

አንድ ላይ በህብረት

ከሃዲ እስኪጠፋ 

በንኖ እንደ ዱቄት። 

ድል ለናንተ ይሁን

ለደጉ ህዝባችሁ 

ትግራይ ትኮራለች

በቃል ፅናታችሁ

ህልማችሁ ይሳካ 

አለን ከጐናችሁ 

ጥርጥር የለንም 

አሸናፊ ናችሁ። 

 

ትግራይ ትስዕር!!

 

 

Back to Front Page