Back to Front Page

የኣማራ መሪዎች የኣማራ መሪዎች ሊሆኑ የቻሉት ሊያፈርሱ በሚፈልጉት ህገመንግስት መሰረት መሆኑን ዘንግተው ነው?

ኣማራ መሪዎች የኣማራ መሪዎች ሊሆኑ የቻሉት ሊያፈርሱ በሚፈልጉት ህገመንግስት መሰረት መሆኑን ዘንግተው ነው?

ኻልኣዩ ኣብርሃ 02-21-21

በስልጣን ጥም ናላው የዞረ ሰው፣ ለችሎታው የማይመጥን ጋኖች ስላለቁ ብቻ ጥንጥ ምንቸት ሆኖ ስልጣን ላይ ቂብ ያለ ሰው፣ እንደ ሂትለርና ሞሶሎኒ የበላይነትን ዘምሮ በማዘመር ኣርቆ ማሰብ የተሳናቸውን ሚልዩኖች ራሳቸውን ወደሚያጠፉበት እብደት የሚመራ ሰው፣ የሚተነፍሰው ኣየር ስላለ መሆኑንም ሊዘነጋ ይችላል። የኣማራ ክልል መሪዎች የምእራብ ትግራይ ጉዳይ "ፋይሉ ተዘግቷል" እያሉ ሲናገሩ በየትኛው ህግ ተከፍቶ በየትኛው ህግ ተወስኖ እንደተዘጋ ለማሰብ እንኳን ጊዜ የወሰዱ ኣይመስልም። ምን ቸገራቸው? ለምን በማሰብ ጉልበታቸውን ያባክናሉ? አዙሮ የማሰብ ኣቅምስ አላቸው ብላችሁ ነው? ግን ለውጥ የለውም! አንድና አንድ ሲደመር ሶስት ነው ቢሉም ወያኔን የሚኮንን እስከሆነ ድረስ ጭብጨባ ስለሚቸራቸው ችግር የለም። ላያስፈልጋቸው፣ ላያስጠይቃቸው፣ ከስልጣን ላይወገዱበት ለማሰብ የሚቸገሩበት ምክንያት የላቸውም። ለአማራ ህዝብ አመራር የሚያበቃው መመዘኛ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን ከሁሉም ልቆ የመጥላት ስሜትና ህዝቡን ለማዋረድ የሚረዳ ልዩ የአማርኛ ቋንቋ ችሎታ ነው። ማሰብ የሚችሉትና የሚፈልጉት እንደነ ልደቱ ያሉ የአማራ መሪዎችማ ህዝቡን ራሱን ከሚያጠፋበት እብደት ሊመልሱ ሲታገሉ ምን እየተደረጉ እንደሆነ እያየን እየሰማን ነው። ሂትለርና ሞሶሎኒ የጀርመንንና የኢጣሊያን ህዝብ ወደዛ እብደት ለመምራት ሊቃውንት መሆን አላስፈለጋቸውም። ለነሱ የአመራር ችሎታ ማለት ህዝባቸውን "አለምን ትገዛለህ፣ አውሮፓ የቤትህ ጓሮ ይሆናል፣ አለምን መግዛት ያለብህ አንተ ምርጥ ህዝብ ነህ" እያሉ የአለም ታሪክ ሊረሳው የማይችል ወንጀል በሌላ ህዝብ ላይ ሲያስፈፅሙት ነበር። ለጀርመንና ኢጣልያ ህዝብ ያተረፉለት ነገር ቢኖር ውርደትና የዘለአለም ወቀሳና ውግዘት ነው።

Videos From Around The World

የአማራ ህዝብ አሁን ስለልማት፣ ስለኑሮ መሻሻል፣ ስለኢንዱስትሪ እድገት፣ ስለግብርና ምርታማነት ማሰብ አቁሟል፣ ከዚህ በፊት ሲያስብ ለመኖሩም እርግጠኛ አይደለሁም። መሪዎቹ ለዘመናት የህዝቡን አስተሳሰብ የቃኙት የጭንቅላታቸው አቅም በሚፈቅደው የመስፋፋት አላማ ነው። ስለ ልማት ማሰብ ከባድ ነው፣ ለዛ የሚመጥን እውቀትና ክህሎት ይፈልጋል። "ተነስ ዉረር" ብሎ ለማቅራራት ግን የበግ ያህል "አይ ኪው" እንኳ አይጠይቅም። መስፋፋት እንደ ወግ ባህል ወይንም ሱስ ካልተቆጠረ በስተቀር የያዙትን መሬት በዘመናዊ ዘዴ አልምተው ሳይጠቀሙ የሌላውን መሬት ለመውረር ሌላ ስራ ሁሉ ተረስቶ ይህን ያህል ከወረራ ጋር በተያያዙ ተግባራት ላይ መጠመድ ምን የሚሉት አባዜ እንደሆነ እንቆቅልሽ ነው። ልክ የራሱን ዳቦ ሳይበላው በእጁ ይዞ የጓዳኛውን ዳቦ ለመቀማት ሲታገል እንደሚጎዳው አስቸጋሪ ልጅ መሆኑ ነው። ህገወጥና ሞራላዊ ያልሆነ ቢሆንም ናዚ ጀርመንና ኢምፔርያል ጃፓን መስፋፋት የፈለጉት ያላቸው የመሬት ስፋት ከታላቁ ኢኮኖሚያቸው ጋር የማይመጣጠን አነስተኛ ስለሆነባቸው ነበር። "ሊበንስ ራውም" የሚለው የሁለቱም መንግስታት የጂኦፓለቲካ መርሆ "የመኖሪያና መስሪያ ቦታ" ለማለት ነው።

ለብዙ ምእት አመታት ይች መረጋጋት የጎደላት አገር ግዛት በመቀማማት ነው እድሜዋን የፈጀችው። አንዱ አገረ ገዢ ትናንት የራሱ ግዛት የነበረው ዛሬ የሌላ ሊሆን ይችላል፣ ነገም የሌላ። ኢትዮጵያ በትክክለኛ ህዝባዊ መመዘኛ ላይ የተመሰረተና በህገመንግስታዊ አንቀፆች የፀና የግዛት አከላለል አልነበራትም። ሚኒሊክ የራሱ የክፍላተ ሃገር ካርታ ነበረው፣ ሃይለስላሴም ሶስት ጊዜ የኢትዮጵያን የክፍለተ ሃገር ካርታ ቀይሯል፣ ደርግም እስኪወድቅ ድረስ የተገለገለበት ግማሽ ሶሻሊዝም ግማሽ ፊዩዳልዚም የሆነ የክፍላተ ሃገር ካርታ ነበረው። ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዘመናት ያልተመለሰ ህዝባዊ የፓለቲካና ማህበራዊ ጥያቄ ላይ የተመሰረተ፣ የግለሰቦችና ቡድኖች መጫወቻ እንዳይሆን በህገመንግስት አንቀፆች የተደነገገ የአስተዳደር አከላለል ያገኘችው 1987 ዓም ነው። ይህ አከላለል የገዢዎችን ሳይሆን የአማራ ህዝብን ጥያቄ የመለሰም ነበር። በአራት ጠቅላይ ግዛቶች ተበትኖ ፊዩዳል ገዢዎቹ እርስ በርሱ ሲያፋጁት ኖረዋል። በደርግ ጊዜ መበታተኑ ብሶ በሰባት ክፍላተ ሃገር ተከፋፍሎ የነበረው አማራ ወደ አንድ ክልል አስተዳደር አምጥቶ በአንድ አፍ አንድ ቃል እንዲናገር ያደረገው የሚኒሊክ ጨቋኝ ህግ ሳይሆን፣ የሃይለስላሴ የይስሙላ ህገመንግስት ሳይሆን፣ የደርግ የጉልበትና አፈና ደንብ ሳይሆን ይህ አማራው ያጎረሰ እጁን ሰብሮ "ህገ አራዊት፣ የወያኔ መሳሪያ፣ የኢትዮጵያ መበተኛ" ብሎ ያራከሰው ህገ መንግስት ነው። አማራው ህገመንግስቱን መቃወሙና ለማጥፋት መታገሉ የተቀመጠበትን የዛፍ ቅርንጫፍ በመጋዝ በሚገዘግዝ ቂል ይመሰላል።

አማራው ህገ መንግስቱን የሚቃወመው አማራ ክልል የተፈጠረውና ወደ ቀድሞው ሰባት ክፍላተ ሃገር ሳይበተን ባለበት ሊቀጥል የሚችለው በዚህ ህገ መንግስት ህልውና ላይ ተመስርቶ መሆኑን ጠፍቶት አይደለም። አማራው  አንድ ህዝብ በአንድ አስተዳደር የመሆን ዋስትና ያጎናፀፈውን ህገመንግስት አጥብቆ በመያዝና የመስፋፋት ታሪካዊ ሱሱን የሚያረካበት የበፊቱን አሃዳዊነት ያስቀረበትን ይኼው ህገመንግስት ለማጥፋት በመመኘት መካከል ተቀርቅሮ ይገኛል። ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ለመውጣት ይታገላል! ይህ የአእምሮ ህመም እንጂ ጤንነት ሊሆን አይችልም። የአእምሮ ህመም በግለሰብ ሲሆን አይገርምም በህዝብ ደረጃ ግን እንኳን ማየት ማሰቡም ያዳግታል። ይህ ለማሰብ የሚቸግረው እብደት ነው በምእራብ ትግራይና በደቡብ ትግራይ እየተፈፀመ ያለው። ህገመንግስቱ ሳይፈርስ፣ ደሞ ግን ፈርሷል! አንዱ ክልል ሌላውን ክልል ሲወር ተወድሷል። ዘመነ መሳፍንት ተመልሶ አልመጣም ብሎ የሚከራከር ማነው? ድሮም አሁንም የዘመነ መሳፍንት ማእከል የሆነው ጎንደር ነው። ጎንደሮች አለን የሚሉት "ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የላቀ ጀግንነት" ከቀረርቶና ህዝብን መፍጅትና የራሳቸውንም ወጣቶች ከማስፈጀት ይልቅ ለልማትና ትብብር ቢያውሉት ይመከራል፣ ለዘላቂ ህልውናቸው ሲሉ። አማራው ማእከላዊ መንግስትን ተቆጣጥሮ፣ የፓለቲካ ጣሪያ ደርሰው የነበሩትን የኦሮሞ የፓለቲካ ልሂቃንን መሬት አውርዶ፣ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ በመግዛት ትግል ዋና ተቀናቃኙ ከሆነው ህግደፍ ጋር ጊዜያዊ የፀረ ትግራይ ግንባር በመፍጠር፣ ህገመንግስቱን ተጠቅሞ ህገመንግስቱን እያፈረሰ ነው። ከሚያፈርሰው ህገመንግስት ቀጥሎ ፈራሹ ግን ራሱ መሆኑን ለመገንዘብ በሚያስችለው የአእምሮ ሁኔታ ላይ ግን አይደለም። ለአማራው "ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባሁ" እንደሚሆንበት ጥርጥር የለውም። የኤሪትርያ መሪዎች የህገ መንግስቱ ዋልታና መከታ የሆነችውን ትግራይን በማጥፋት ኢትዮጵያን እንቅ አድርጎ ለመግዛት አንድ አንገት እንድትሆንላቸው ይመኛሉ፣ ይታገላሉም። አማራው ደግሞ ትግራይን በማጥፋት የኢትዮጵያን አንዲት አንገት ይዞ፣ ግን ክልሉ አማራ እንዳለ ሆኖ፣ መግዛት ይፈልጋል። ሁለቱ አንድ አላማ አላቸው፣ ይህም ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ መግዛት ነው። ይህ እንዴት ይሆናል? አስቂኝ ጥምር መንግስት ካልመሰረቱ በስተቀር ኢትዮጵያን ሊገዛ የሚችለው ከሁለቱ አንዳቸው ብቻ ነው። "እባብ ለእባብ ይተያያል በካብ" ነው የአማራና የኤሪትርያ ጥምረት ለክፋት። በምእራብ ትግራይ "ቆይታቸው" ደስታ ያሳወራቸው አማሮች "ከኤሪትርያ ጋር ድንበር ተጋራን" እያሉ ይጨፍራሉ። "በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ" ነው ነገሩ። የኤሪትሪያ መንግስትን ድንበር አክባሪ አድርጎ መቁጠር ከማን ጋር እንደተጋባች ሳታውቅ ህልሟን ከምትዘረዝር ኮረዳ ጋር ይመሳሰላል። አማራው በከንቱ ምኞች ታውሮ የኤሪትርያ መንግስትን እንደ ሚካኤል በረዳትነት ቢፈርጀው፣ በኢትዮጵያ ላይ ባለው አላማ ግን ዋናው ተቀናቃኙና የመረረ ጠላቱ ትግራይ ሳትሆን "የልብ ወዳጁ" የሆነው የኤሪትርያ መንግስት ነው። "ምከረው ምከረው፣ ካቃተ መከራ ይምከረው" እንደሚባለው አማራው እያቅራራ ግን የኤሪትርያን ጦር እንደ ብረት ጋሻ ተጠቅም ከገባበት የትግራይ ቅርቃር መውጣት አቅቶታል። የጦር መኮንኖቹና ወታደሮቹ ጌታ ለመሆን ትግራይ ዘምተው የኤሪትርያ መንግስት ሎሌዎች ሆኑ! "ኤሪትርያን ለማስወጣት አቅም አጣን" አሉ። በዚህ ከቀጠሉ የኤሪትርያ መንግስት ሎሌዎች የሚሆኑት ትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቀሪው ኢትዮጵያ ውስጥም ጭምር ነው:- "አተርፍ ባይ አጉዳይ"!

በነገራችን ላይ የኤሪትርያ ጦር እኮ የኢትዮጵያን ጦርንና የአማራ ታጣቂን የናቀው ሁለቱም በገዛ እጃቸው በራሳቸው ላይ ባመጡት ውርደት ነው። ትግራይን መውረር ፈልጌአለሁ ግን ተጋሩን አልችላቸውም፣ እባክህን የኤሪትርያ ጦር አንተ መጥተህ ትግራይን ምታልኝና እኔ ገዳይ ትግራይ ላይ' እያልኩ ላቅራራ ሲሉት የማይንቅ ፍጡር ይኖራል? ኤሪትርያ በኢትዮጵያ ላይ ያላት የመግዛት ፍላጎትዋ ብርቱ እንቅፋት የሆነባት የትግራይ ጦር እንጂ አሁን እንደ ገብስ በሶ ያዩት የኢትዩጵያ ጦርና የአማራ የሽፍታ መአት አይደለም። ለዚህም ነው ትግራይ ውስጥ ህወሓትን ለማጥፋትና መሰረትዋ የሆነውን ህዝብ ለማፍረስ ቅጥ ያጣ የወንብድና ስራ የሚሰራው። የኤሪትርያ መንግስት የትግራይ ጦር ጠፍቶለት የኢትዮጵያና የአማራ ጦር እንዳይጎዳበት ይፈልጋል። ምክንያቱም የትግራይ ጦር ከተመታ የኢትዮጵያና የአማራ ጦርን መደምሰስ ለኤሪትርያ ጦር ኬክ የመብላት ያህል ምቹ ነው። አሁን ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ የገባችው እንደ ደደብ አማራጭ ያልተቀመጠለት አንድ እቅድ ብቻ ይዛ ገብታ ስለነበር ነው። ህወሓት በርግጠኝነት ትጠፋለች፣ ከሶስት ቀን በኋላ ሸገርና አስመራ ላይ ዲል ያለ ድግስ ይደረጋል፣ የድል ቀኑም በኢትዩጵያና በኤሪትርያ የበአላት ቀን ዝርዝር ውስጥ ከመጀመሪያ ቁጥር ላይ ይሰፍራል። መሶብ ሰርቼ ለአጤ አበርክቼ ብላ ከባልዋ ጋር በጥጃ ማሰሪያ ቦታ ክፉኛ የተጣላችው ሚስት ማንን ትመስላለች? ሶቭየቶች ሞስኮን ተቆጣጥሬ አለምን እገዛለሁ ብሎ እርግጠኛ ሆኖ የሄደባቸውን ሂትለርን እንቁላሎቹ ሳይፈለፈሉ ጫጩቶቹን ቆጠረ ብለው አላግጠውበታል። በትግራይ ሳይፈለፈሉ ጫጩቶቹን የቆጠረ ብዙ ነው። ህዝብ የመረጠውን መንግስት ጫካ እንዲገባ አድርገው በትግራይ የመሪዎች ታሪክ ውስጥ ስማችን ይካተታል ብለው የሚያስቡ ትግራይ ከሚባል የብስል አገር ውስጥ የተፈጠሩ አንቀልባዎችም አሉ። ትግራይ ወደመች፣ ህወሓት ድራሿ ጠፋ እያሉ ቄሱ አይቀር ፓስተሩ፣ ቃዲው አይቀር ሃይማኖት የለሹ ሲደንሱና በደስታ ሲቃ ሲተቃቀፉ ሰንብተው ሳቃቸው ክጥርሳቸው ሳይጠፋ ትግራይ የተሰወረ ዘንዶ እንጂ የተጨፈለቀች ሸረሪት እንዳልሆነች በግልፅ ሲታይ በድንጋጤ ብዛት ስንቅ አዘጋጅ: እርዳታ ሰብሳቢ፣ አስታራቂ ሽማግሌ መሆን አማራቸው። ይህ ለትግራይ ህዝብ ስድብ ነው፣ ሞራሉ እንኳን ከሱ ባነሱ ሰዎች አይነካም። የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ መሆኑን አሳይቷቸዋል። እነሱ ግን መስራት የሚችሉት ያልሰለጠነ ህዝብ የተካነበት ሰላማዊ ህዝብን መግደል፣ ሴቶችን መድፈር፣ ንብረት መዝረፍ ነው። ሌላ የሚያውቁት ነገር ስለሌለ! እነዚህ የአውሬ ስብስቦች ከጦር ሜዳ ውጭ በግፍ ሲገድሉ የሰለጠነው የትግራይ ጦር ግን የተዋጉትንና የማረካቸውን አስተምሮ እየላከላቸው ነው። ፈርቶ ሳይሆን ያደገበት ግብረገብነት በውጥረት ጊዜም ቢሆን እንዲጥሰው ስለማይፈቅድለት ነው።ስለ ኤሪትርያው መሪ ትንሽ ብየ ልዝጋ። የኤሪትርያው መሪ ትግራይ ውስጥ ስለገባው የግዢ ጦራቸው ምንም አላሉም ብሎ ሰው ሁሉ ይገረማል። መናገር ቢፈልጉስ ምን ብለው ይናገሩ? ዶላር የተከፈለበት ጦር ላክሁኝ ነው? ከፋብሪካ እስከ ማንካ የሚሰርቅ የአገሬ ሰራዊት ላክሁኝ ነው? መሪዎች እኮ ሚያኮራ ነገር እንጂ የሚያሳፍር ነገር መናገር አይወዱም። በዛ ላይም በከፍተኛ ትምክህት የገባው ጦራቸው በየቀኑ የኮሎኔል አስከሬን ሲልክላቸው ምን አፍ አላቸው? ስለ ኢትዮጵያ፣ አፍሪካና ስለ አለም ያውሩ እንጂ። የተባበሩት መንግስታት የፓለቲካ ትንተና ክፍል ውስጥ ዋና ተመራማሪ አይደሉ።

 

ድል ለትግራይ ህዝብ! ውድቀት ለወራሪ!

Back to Front Page