|
ኣናሳ.... ኮሳሳ.... ኣቨሳ.!
አሉህ በቁጥር ኣናሳ መብት የለህ ባደባባይ ምታነሳ::
በስጋ ነብስም ኮሳሳ: እያወቁህ በግብርህ ነብር: ኣንበሳ::
ረገጡህ እንደኣሽዋ ዳግም እንዳትነሳ ጠፍትህ እንድትረሳ::
ወይ ኣበሳ ኣንተ የድር ኣንበሳ መቼ ነው ምታገሳ!
ረጭቡህ በሽታ ቀጥሎም የጥይት እሩምታ: ገደሉህ በተርታ እየጨፈሩ በደስታ እየጨሁ እልልታ::
ይህ እንዳያበቃ ጭሆትህ ተነጥቃ ወነጀሉት መኸተ ላንተ ለቆመው ጥበቃ::
ወይ ኣበሳ ኣንተ የድር ኣንበሳ መቼ ነው ምታገሳ!
ዘግተው በሩ በስንስለት: እንደ ቤተ ትምህርት, እድገት በል ጤንነት ትካላት በጨለማ እንድትኖር ግዞት እስከ ምፃዓተ እለት::
ወይ ኣበሳ ኣንተ የድር ኣንበሳ መቼ ነው ምታገሳ!
በሁለት እግር ሚራመዱ ግን በሌላ ባለ ሁለት እግር የሚናደዱ በስላም ካደረ ከጠገበ ሆዱ ራስ ቀና ካለ ማየት ካሰተዋለ መራመድ ከቻለ ንሮ ካሽነፈ ከተስተካከለ::
ሌላ ስው ከረዳ ከወደቀው ጏዳ በምስቅልቅል እዳ: እይናቸው ደም ስርፆ በቅናት ሚፈነዳ: ሆዳቼው በተቅማጥ ናዳ::
ይቅር ከዚህ ዘር መጋባት ይሁን እብሮ መኖር::
ተመስገን ከበደ 03-05-21 Back to Front Page |