Back to Front Page

መስቀል ትሕረድ ጤል ቅዱስ ዮሐንስ ትሕረድ በጊዕ ትስሕቅ

በውሸት ዜና አገር ከማፍረስ እንቆጠብ

ከስዩም አባይ 02-04-21

እነዴት ናቹህ የውሸት ወሬ አመዣኪዎች  አሁን በትግራይ እንቅሰቃሴዎች ይበዛሉ ድካም ጥም ጉዞ ዳገት ቁልቁለት ይበዛል ግን የህዝቡ ሞራል እና ወኔ ደግሞ የመጨረሻ ጥግ ደርሶ ለአብዛኛው ተዋጊ/ታጋይ ጉልበት ነው ።

  እንደ ጎርፍ የፈሰሱት ወራሪዎች በመታገል ዙርያ ብዙ አስቅኝና አሳዛኝ ነገር ያለበት ነው ጭፍጨፋው ፣ረሀቡ፣ መሰረታዊ አገልግሎት መቋረጥ መውደም ሌላ ፈተና ቢሆንም ። እዚህ ላይ ግን የወራሪዎች  ፍርሀት ሆነ መወጭያ መግቢያ ማጣት በየቦታው መውደቅ መቁሰል መማረክ የየእለት ተግባራቸው ነው ።ከሁሉም አቅጣጫ የመጡ ወራሪዎች ጉዞ መጀመርያ የነበረ በጋራ የመንቀሳቀስ አሁን ተቀይሮ አንዱ ሌላውን አንተ ግባ እኔ አልሄድም /ወደ ጦርነት / እያሉ ከመጨቃጨቅ አንስቶ እቃ በመከፋፈል መጣላት ፣አንዱ ሲሸሽ ፣አንዱ እጁ ሲሰጥ ግራ ይገባል። አንዳንዱማ ለምን እነደመጣ አይታወቅምም አያውቅም።

Videos From Around The World

ከተማረኩት ጋር መጫወት ብዙ ቁምነገር አለ እንደሚታውቀው እኛ ጋ ሲማረክ በደንብ ይያዛል ከኛ አብልጠን እንጂ ህዝቡ እንዲስቅበት አይደረግም አይዋረድም ፣ ሲሞትም እንደባሀላችን ቀብረን ነው የምናሳርፈው ወይ ወደ ቤተሰቡ በክብር ሬሳው ይላካል እንጂ ፎቶና ቪድዮ ተቀርፆ አይጨፈርበትም ህዝቡ በወግ ማአርግ ይቀበራል እንዲሁም የተማረከው አረጋግተን ምርጫው ታውቆ ይላካል ይህ ሌላው የየእለቱ ተግባር ነው በስሜት የተማረከ አይገደልም አይሰደብም ከትንሽ ቆይታ በተገቢው ሲያዙ ከተረጋጉ ቦሀላ የሚያወሩህ ብዙ ነገር አለ እንዴት እንደመጡ ፣ምን እንደተባሉ ምን ፍላጎትና አረዳድ እንዳላቸው ትገነዘባለህ አንዳንዱ እማ ሰላም አስከባሪ ለ6ወር ተብለው ይመጣሉ ብርም ተሰጥተው የመጡ ነበሩ።

 በትግራይ ሰው ተማርኮ መንከባከብና ወደ ቤተሰብ ማድረስና  አሁን የሚሰራ ስራ አደለም ከጥንት ከጥዋቱ ከአፄ ዮሀንስ  ለምንሊክ ወይ ለጣልያን ወይም በደርግ ግዜም ቢሆን በነበረ ጦርነት ብዙ ተማርከው ወደ ፈለጉት መሄድ ብቻ ሳይሆን ወደ ወግ መአርግ የደረሱ ጀነራሎች የአሁኑ ጦር መሪዎች እና የባለስልጣናት አማካሪዎች የደረሱበት ደረጃ ምስክር ናቸው አሁንም እስከ አሁን ድረስ 25,000 የ'አገራችን' የኤርትራ እና የሶማልያ ሳይጨመር ተማርከዋል ብዙዎቹ ወደየፈለጉት ተልከዋል በርግጥ ደግመውም የተማረኩ አሉ ግን ስራ አቅላይ ናቸው ለአዲሶቹ ምክር እየሰጡ ተሎ እጅ ይሰጣሉ እውቀቱ ያካፍላሉ።

ዋናው ነገር አሁን የትግራይ ህዝብም ቁጭ ብሎ ከመሞት መታገል መርጧል ሌላውም ትግራይ በኤርትራ ጎንደር በሱዳን ተወሮ ሲያይ እና መንግሰት ለአገር ያለው ተቆርቋሪነት በተግባር እያየ በተለይ  ትግራይ ላይ ያለው እውነት ህግ ማስከበር ሳይሆን ህግ ማፍረስ ወይ ሀገር ማፍረስ መሆኑ አውቋል ብቻ ሳይሆን በትግራይ እየደረሰ ያለው በደልና ክፋት ጥግ ማህል አገር ያለው ፕሮፓጋንዳ በማየት የኛ አካሄድና አያያዝ ተጨምሮበት ሁኔታዎች ተቀያይረዋል።

አሁን ትግራይ ላይ የደረሰ ጥፋት ሳይበቃ ቀጣይ የአገሪቱ ምስቅልቅል ያለ ሁኔታ ተፈጥሯል ከነዛ ውስጥ ቀጣይ የአብይ እና የኢሳያስ ፍላጎት ማስታረቅ ፣የአሀዳዊና ፌደራሊስት ፍላጎት ማጣጣም እንዲሁም ህገመንግስት መቀየር በዛላይም የግብፅ ና ሱዳን ፍላጎት ፣የህዝቡ ፍትህ ፣ልማት ፣ ስራ  ወዘተ ... ጥያቄዎች ተጨምረው 'አገራችን' የባሰ ማንታ መንገድ ቁማለች ።መንግስት ተብየውም እንደቀደመዎቹ ገዢዎች ትግራይ በመጨፍለቅ ወይ በማዳከም /በማደህየት ፣ የህዝብ ቁጥር በመቀነስ ፣ በመደንቆር እና መሬቱ በመውር / ሌሎች ክልሎች በቀላሉ መግዛት እና ማንበርከክ ይቻላል በሚል ፈሊጥ እየተጓዘ ነው።

አሁን ይቅር ሌላው ብሄርና ብሄረሰብ አማራውም ራሱ በራሱ ማስተዳደር ያንሰኛል የሚለውን አሀዳዊ  ትተን ባለፋት 27 የኢህአዴግ አስተዳደር አመታት የተፈጠረው የአማራው ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያለው ፣ አገው፣ ቅማንት ብሎ አይገዛም ወይም ከነበረው ፌዴራላዊ ስርአትና ህገ-መንግስት የተሻለ ካልሆነ ያነሰ መብት አይቀበልም ። ሌላው እስካሁን በተካሄደው የትግራይ ጦርነት ኢኮኖሚው ደቆ ቁልቁል ወርዷል የመንግስት አቅም ተዳክሟል በአፍርካና አለም መድረክ ተከብራ አህጉራችንም ስታስጠራ የነበረች ሀገር  አሁን  ይቅር በአለም ምስራቅ አፍሪካ በትናንሽ አገሮች ክብር ጠፍቶ የነ ኢሳያስ መጫወቻ የደካሞች መሳቅያና መሳለቅያ ሁነናል።

  ለኢ/ያ ህዝብ የተለያዩ ሰበር ዜናዎች እየሰጡ ማስደሰት እና ማደንዘዝ ግዜው አልቋል እና ነገሮችን በትክክል ለማየት መሞከር የወቅቱ ጉዳይ ነው።


Back to Front Page