Back to Front Page

ኢትዮጵያዊነት ምዋርተኝነት ነው

ኢትዮጵያዊነት ምዋርተኝነት ነው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል (ስትራቴጂስት) 01-31-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ በያለበት ስፍራ ሆኖ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ የህልውና ትግል በመታገል የሚገኝ ትግራዋይ አንድን ጠላት ጠላቴ ነው! የሚልበት ምክንያት አንስተን እንመለከታለን። ጸሐፊው፥ ከሻዕቢያ ጋር አሲረው የዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ የሶማል፣ የሶማሌና የአፋር ወታደሮች አሰልፈው፣ ታንኮቻቸው እንደ ችቦ ሲነዱ ድሮንን ከኤምሮቾች አስመጥተው ትግራይን ወረሩ የአማራ ልሒቃን ዛሬም እንደ ትናንት ለመስበርና ለማንበርከክ ጥይት መተኮስ አያስፈንገንም ብሎ ይሞግታል። ስለ ፍቅር፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ሰላምና ስለ ዕድገት ሲባል በእኛ ጥረት የሚሆንና የሚሳካ መስሎን ታስፋ ሳንቆርጥ ለበርካታ ዘመናት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ስንል የጣልነው ትግራዋይ ማንነታችን ዳግም በማንሳትና በመቀስቀስ ትግራዋይ ብሔርተኝነታችን አጠናክረን በአንድነት ለመቆም የተሰባሰብን ዕለት፤ ሬሳ በሬሳ ሆኖውም ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ እያጓራ ያለ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ሽለላና ቀረርቶ ነገ በስፍራው አናገኘውም። የአማራ ልሒቃን ሁለት አፍ ካለው የተሳለ ሰይፍ ይልቅ አጅግ አድርገው የሚፈሩት፣ ሊሰሙት የማይፈልጉት ስም ቢኖር ትግራዋይ የሚል ስም ብቻ ነውና። አያይዘንም የጠላቶቻችን አቅምና ፍላጎት ከብዙ በጥቂቱ እንመዝናለን፤ እንቃኛለን።

 

Videos From Around The World

መንደርደሪያ፥ ወንድፍራው ይባላል። ወንድፍራው፥ በሰፈሩ የታወቀ ሃይማኖተኛ ሰው ሲሆን ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት እየቀረበ ጌታ ሆይ ዲኤክስ መኪና ሲጠኝ! ሲል አበክሮ የሚጠይቅ ሰው ነበር። ፈጣሪ በእውነቱ ነገር መልካም አምላክ ነውና ከዕለታት አንድ ቀን የወንድፍራው ጸሎት መልስ ለምስጠት መጣ። ጸሎትህ ሰምቻለሁ እመልስልህ ዘንድም መጥቻለሁ፤ የለምከው ዲኤክስ መኪና እሰጣሃለሁ፤ ለጎረቤት ለገብረመድህን ደግሞ ሁለት እጥፍ አድርጌ እስጠዋለሁ ይህን ከማድርጌ በፊት ግን ተጨማሪ የምትጠይቀው ነገር ካለ አስበህ ንገረኝ ይለዋል። ወንድፍራው ጸለቱ በአምካሉ ፊት መሰማቱንና ልመናውን መስመሩ ደስ ቢለውም ጎረቤቱ ገብረመድህን ሁለት እጥፍ እንደሚያገኝ መስማቱ ግን በደስታው ላይ ውሃን የሚቸልስ ዜና ነበር። ወንድፍራው እንግዲያውስ ላስብበት በማለት አውጥቶ ካወረደ በኋላ ሌላ ጥያቄ ይዞ ያቀርባል። የእግዚአብሔር መልስ አሁንም ተመሳሳይ ነበር፤ ያሻህን ሁሉ ጠይቀኝ አሁንኑ እሰጥሃለሁ፤ የለመንከኝ ለጎረቤትህ ለገብረመድህን ደግሞ እጥፍ አድርጌ እሰጠዋለሁ የሚል ነበር። ወንድፍራው አሰበና በልቡም እግዚአብሔር የጠየቅኩት ነገር ሁሉ ለገብረመድህን ሁለት እጥፍ የሚሰጥ ከሆነ፥ ሲል አሰበና ደስ እያለው በእግዚአብሔር ፊት ቀረበ፤ እንዲህ ሲልም ጸለየ፤ ጌታ ሆይ የእኔን አንድ ዓይኔን አጥፋ! አለ ይባላል (የገብረመድህን ሁለት ዓይን ያጠፋ ዘንድ)።

 

ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን በትግራይ ህዝብ ላይ ያላቸው ትግራይ-ፎቢያ የወለደው ቅናትና ምቀኝነት የሚፈጥረው ጥላቻ እስከዚህ ድረስ ነው። መተተኞቹ የአማራ ልሒቃን በዘመናት መካከል በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያደረሱት ውድመትና ጥለውት ያለፉት መጥፎ ጠባሳ ለታሪክ በመተው ወደፊት ለመሄድ ከልወሰን በቀር ክፉ ግብራቸውና ሴረኛ ማንነታቸው እያነሳን እንነጋገር የስራቸውም እንስጣቸው ቢባል ኢትዮጵያ የምትባል አገር ታሪክ ብቻ ነው ልትሆን የምትችለው። ጋላ፣ ሻንቅላ፣ ቅማላም፣ ችጋራም፣ መጤ፣ ዘላን ወዘተ እያሉ ዜጎችን እያሸማቀቁ ለዘመናት ዘልቀዋል። አሁን ደግሞ እጥፍ ብለው፥ ፍቅር፣ አንድነት፣ ኢትዮጵያዊነት እያሉ ህዝብን ማደናገርና ማወናበድ ስራችን ብለው ተያይዘውታል። የአማራ ሊሒቃን፥ የሚፈልጉትን ለማግኘት አይደለም የሰው ደም መጠጣት ዕድሉ ቢገጥማቸው ሰማይና ምድርን ከአለመኖር ወደ መኖር ያመጣ በልዑል እግዚአብሔር ሳይቀር መፈንቅለ መንግስት ከማድረግ የማይመለሱ ምዋርተኞች ናቸው።

 

የበከተ የአማራ ልሒቃን አስተሳሰብ ካልተፈወሰ ኢትዮጵያ አትፈወስም

 

በርግጥ ከእንግዲህ ወዲህ፥ ዳር ድንበርዋ በደቡብ ቆቦ በምዕራብ ከሳንጃ መልስ የሆነችው ኢትዮጵያ የምትባል መንግሥት አልባ አገር፥ ኖረች ወደመች፣ ተፈወሰች አልፈወስች፣ ቀናች ተጣመመች፣ ቆመች ፈረሰች፥ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በሰብአዊነት ላይ እንዲህ ያለ ሰቆቋ ይፈጸማል/ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብና የማይታመን ግፍና በደል እየተፈጸመብን ለምንገኝ ከዚህ የተነሳም የህልውና ትግል ውስጥ ላለነው ለእኛ ለተጋሩ አጀንዳችን አይደለም። በመቀጠል ለማሰፍረው አስተያየት ሆነ ለማንጸባርቀው ግልጽ የሆነ አቋም ቀደም ሲል ያሰፈርኩት የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ነው።

 

የኢትዮጵያ ችግር ሰዎች ሊያወሳስቡት እንደሚሞክሩትና የኢትዮጵያ ችግር ውስብስ ነው! ሲሉ እንደሚገልጹት የተወሳሰበ ችግር አይደለም። በመሆኑም፥ የኢትዮጵያ ችግር ለመፍታት ፈረንጆች ከአራቱ የዓለማችን አቅጣጫ ማሰባሰብን አይጠይቅም። የኢትዮጵያ ችግር ውስብስ ነው! የሚሉ ሰዎች ሁለት ዓይነት ሰዎች ናቸው። ይኸውም፥ በዋናነት ይህን ዓይነቱ አባባል በማራገብ የሚታወቁ ፖለቲከኞች ሲሆኑ ዋና ዓላማቸው እውነቱን ከህዝቡ መደበቅ፣ ህዝቡን ማደናገርና ማጭበርበር እንጀራቸው ስለሆነ ነው። ሁለተኛው ወገን፥ አወቀች አወቀች ቢሏት መፅሐፍ አጠበች እንደሚባለው በዘርፉ ብቁ የሆነ ሞያ የሌላቸው ዳሩ ግን መድረኩን የመያዝ ዕድል የገጠማቸው ገራ ገሮች አንድም የልምድ አወላጆች አለማወቅ የሚናገሩት አባባል ነው። በተረፈ፥ የኢትዮጵያ ችግር በቃላት ከምገልጸው በላይ የተራቆተና ኩልል ያለ ነው። መፍትሔውም በዚያ ልክ አጭርና ግልጽ ነው።

 

የኢትዮጵያ ችግር፥ ቢገፈተሩም ስልጣን ላይ ቢወጡም ዘወትር ችግር ፈጣሪዎች የሆኑ፣ ዘመን አልፎ ዘመን በተተካ ቁጥር፥ ኢትዮጵያ በዚህ ዓይነቱ አሳፋሪ የድህነትና የኋላቀርነት ጎዳና ተዘፍቃ እንድትዳክር እያደርጉ ያሉ ኢትዮጵያን የመምራት መለኮታዊ ስልጣን ያለ እኛ ብቻ ነን! ብለው የሚያምኑ አስመሳዮችና አሉባልተኞች የአማራ ልሒቃን የልብ ጠማማነትና ሴረኝነት ነው። የኢትዮጵያ ችግር ራሳቸውን በጽድቅ ማማ አስቀምጠው ሌላውን በመክሰስ፣ በመሳደብና በማሳደድ የሚታወቁ፤ በደም የጨቀየ ጣቶቻቸውን በሌሎች ላይ በመቀሰር የተካኑ የአማራ ልሒቃን ናቸው። እዚህ ላይ ብዥታ ሊኖር አይገባም። የእኛ የተጋሩ ሐጢአት ከምንም በላይ ተጋሩ መሆናችን ሲሆን፤ ቀጥሎም አረጓንዴ ቢጫ ቀይ ባንዴራ እያውለበለበ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም መዝረፍን የለመዱ የአማራ ልሒቃን ትምክህተኛ አስተሳሰብ ፍቱን መድሃኒት መሆናችን ነው። እዚህ ላይ መታወቅ የሚገባው እውነት ቢኖር፤ የአማራ ልሒቃን መሰረት የሆነው የአማራ ህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ነው። ይኸውም፥ የአማራ ህዝብ፥ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከጋምቤላ፣ ከቤንሻጉል፣ ከደቡብ ወዘተ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረቦችና ህዝቦች መከባበርና መቻቻልን የተመሰረተ በእኩልነትና በፍትሓዊነት የመኖር ችግር እንደሌለበት ለሁሉም ግልጽ ነው።

 

ጎበዝ፥ በነገድ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በፖለቲካ፣ በታሪክ፣ በስልጣኔ፣ በስነ ልቦና ውቅር ልዩ ልዩ ብንሆንም በህግ ጥላ ስር እንደ አንድ ህዝቦች መሆን ይቻላል። የማይቻል ነገር የለም። ሰላማና መረጋጋትን የሰፈነባት ሁሉም በእኩልነት ተጠቃሚዎች የሚሆኑባት አገር መገንባትና እንደ አገር መቀጠል ይቻላል። ይህ ሁሉ ዕድልና በረከት እንዳንጠቀምበት፤ አሽክላ የሆነው ኃይል ግን ባንዴራን እያውለበለበ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም ጨፍላቂ የሆነ ስርዓት ዘርግቶ ደረጃ መዳቢ ሆኖ ኢትዮጵያን ሊገዛ የሚቋምጥ ፈሪሃ እግዚአብሔር የራቀው የአማራ ልሒቃን የልብ ጥመትና አመጸኝነት ነው። ሌላው ለህልውናው የሚታገል፣ ይህን አመጸኛ የአማራ ልሒቃን መሰሪነት የሚቃወምና የሚታገል ነው።

 

ቅናትና ምቀኝነት የኢትዮጵያዊነት መቀነት

 

የአማራ ልሒቃን፥ ይህን ያህል ርቀት ተጎዞው ከአስመራና ከመቃድሾ መንግስታት ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍና በደለ የማይገልጸው የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ ግባቸው የትግራይ መሬት ከመምውረር ያለፈ ዓላማ ያነገበ ነው። የአማራ ልሒቃን ህልምና ምኞች ለዘመናት ሲንከባለል የመጣ ከንቱ መሻት ነው። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የትግራይ ህዝብ ዘር ማንዘሩን ማጽዳትና ከካርታ ለመፋቅ የገሰገሰው፤ የትግራይ ህዝብ በዓለም መድረክ፥ ከሌላው ማኀበረሰብ ተለይቶ የሚታወቅበት የታሪክ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ሥልጣኔ፤ ማለትም፥ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ታሪክ የራሳቸው የማድረግ ፍላጎት ስላላቸው ነው። ምክንያቱም፥

 

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ብሉይ ኪዳን ሲነሳ ከይሓ እስከ ጽዮን፥ መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ጥምቀትና ክርስትና ሲነሳ አብርሃ ወአጽብሃ፥ መገኛቸው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ እስልምና ሲነሳ ነጋሽ፥ አሁንም መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ፊደል ሲባል ሳባውያን፣ ግዕዝ፣ ትግርኛ፥ መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ገንዘብ ሲባል ካሌብ መገኛው፥ ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ የእክሱም ስልጣኔ ሲነሳ መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ገዳማትና አድባራት ቢጠራ ከደብረዳሞ እስከ ጉንዳጉንዶ መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ግዕዝ፣ ዕዝልና አራራይ ቢጠራ የዜማው ፈጣሪ ቅዱስ ያሬድ መገኛው ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ንግስተ ሳባ ቢባል መገኛዋ ትግራይ።

v  ኢትዮጵያ፥ ተብሎ ስመ ቅዱሳን ቢጠራ ተስዓቱ ቅዱሳን ብዙሓኑ ማረፊያቸው ትግራይ።

v  በነፍጥ የምንኮራ ህዝቦች ባንሆንም፥ ኢትዮጵያ፥ ተብሎ አድዋ ቢባል መገኛው፥ ትግራይ። የጦር መሪውም ራስ አሉላ ትግራዋይ።

v  በተረፈ፥ ደብረ ሊባኖስ፣ ጣና ሃይቅ፣ ጻድቃኔ፣ ጎንደር፣ ፋሲለደስ ወዘተ የሚባለው ሁሉ ታሪካዊ አመጣጣቸው በጥንቃቄ የተመለከትን እንደሆነ፥ ይሓ፣ ገረዓልታ፣ ጉንዳጉንዶ፣ ደብረ ዳሞ፣ እንዳ-ባገሪማ፣ አክሱም ጽዮን፣ የአክሱም ሓወልት፣ ንግሥተ ሳባ፣ ካሌብ፣ አብርሃ ወአጽብሃ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ዝማሬ፣ ቅዳሴ፣ ዜማ፣ ፊደል፣ ነጋሽ ሲባል በተቀረው ማኅበረሰብ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ቀውስ ለማብረድ ታስቦ ሆነ ተብሎ ለፖለቲካ ፍጆታ የተፈበረኩና አገልግሎት ላይ የሚውሉ ናቸው (ይህ አባባል ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን በትግራይ ህዝብ ላይ ቅናትና ምቀኝነት የሚወልደው ያላቸው ጥላቻ ለማመላከት እንጅ ይብዛም ይነሳም ታሪክ የሌለው ህዝብ የለም)

 

ጎበዝ፥ ኢትዮጵያን በበላይ ዘለቀ የሚያውቃት የዓለም ማኅበረሰብ ሊኖር ቀርቶ በላይ ዘለቀ የሚያውቅ፣ ትግራዋይ፣ ኦሮሞ ወይም የደቡብ ህዝብ የለም። ላሊበላም ቢሆን ዓለም የመሰከረለት የአክሱም ሓወልት ያቆሙ የተጋሩ አሻራ ነው። ሂደን ወንጌል ሰብከን ያጠመቅናቸው እኛ (ትግራዋይ) ሆነን ስናበቃ የቃላት ጨዋታ በመጫወት የሚፍቁት ታሪክ ያለ ይመስል አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው አሉን። አንጀቱ በቅናት ተቋጥሮ የጨነቀው ሰው የማይለው ነገር ስለሌለው፤ ስላለም ነው ማለት ስላይደለ፤ ከተመቻቸው ይሁንላቸው! ብለን በቸልታ አለፍናቸው። ከነተረቱ፥ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ! አለ እንደሚባለው፤ ሌላውን ለማታለልና ለማደናገር በፈበረኩት ስራ ማለትም ጉድጓድ ቆፍረው ውሃ ሞልተው ውሃ የመርጨት ልምምድ በቆይታ የባለቤትነት ስሜት ሊሰማቸው ጀመር። በአሸዋ ያጠመቅነው (የጥምቀት መለኮታዊ ትርጓሜ ለማመሳጠር ተፈልጎ ነው) ማኅበረሰብ ጭራሽ ጉድጓድ ቆፍሮ በሞላው ውሃ እናጥምቃችሁ አሉን። የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይሉሃልም ይሄ ነው።

 

ያም ሆነ ይህ ግን፥ የአማራ ልሒቃን ቅናትና ምቀኝነት የወለደው የታሪክ ሽምያ ያልተበገረ ትግራዋይ የሚያደርጉትን አያውቁም እያለ ከመታዘብ ውጭ ያለው ነገር የለም። በአንጻሩ፥ የአማራ ልሒቃን የትግራይ ህዝብ የታሪክና የስልጣኔ እንዲሁም የተጋሩ የላቀ የፖለቲካ ብስለትና ጭምትነት በተወሳ ቁጥር ዓይናቸው ደም የሚሞላበትና ደም የሚያስቀምጥባቸው ምክንያት ለእኔ እንቆቅልሽ ነው። አንድ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል ሰው ጎረቤቴ እንዴት ከእኔ ይበልጣል ብሎ ጎረቤቱን ለመጣል እንዴት እንቅልፍ አጥቶ ያድራል? እንግዲያውስ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ መንስኤ ይህ ነው። ቅናትና ምቀኝነት የወለደው መርዛማ ጥላቻና እኔነት። ቅናትና ምቀኝነት የኢትዮጵያዊነት መቀነት፤ ኢትዮጵያዊነት ምዋርተኝነት ነው! ያስባለኝም ይህ ነው። ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ በትግራይ ህዝብና በትግራይ ምድር የሆነውና የተገለጠው ሐቅም ይህ ነው። በርግጥ፥ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ክህደትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ መካድ በራሱ ኢትዮጵያዊነት ነው።

 

v  ኢትዮጵያዊነት፥ እግዚአብሔር አምላክ እጅግ የሚጸየፈው ሐሰተኛ ምላስና አሉባልተኛ መሆን ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ህጻናትና ሽማግሌዎችን መግደል፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የንጹሐን ዜጎች ደም በከንቱ ማፍሰስ ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ በአፍህ የኢትዮጵያ አምላክ እያልክ ቀሳውስት ካህናት እንደ ከብት አጋድመህ ማረድ ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ የአገር ሉዓላዊነት ለባዕድ አሳልፈህ መስጠትና ባንዳነት ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ የእናቶችና የአንስት መነኮሳት ክብር ማጉደፍ፣ የውሻ ባህሪ መላበስና ህሊና ቢስ መሆን ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ አፍህን ስትከፍት እግዚአብሔር የሚባል በስራው የማይሳሳት ጻዲቅና ፈታሔ አምላክ አለ፣ ያየኛል፣ ይሰማኛል አለ ማለትና ፈሪሐ እግዚብሔርን መጣል ነው፤

v  ኢትዮጵያዊነት፥ ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባቸው አብያተ ክርስቲያናትን በታንክና በቡዝቃ ማፍረስና ንዋያተ ቅዱሳትን ማውደም ነው፤

v  ኢየሱስም አለ ይሁዳ ሆይ፥ በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እንዲል፤ ኢትዮጵያነት፥ በአፋቸው፥ እትዬ፣ አብዬ፣ ወንድሜ፣ አህቴ እያሉ እምነት በጣለባቸው ሰው ላይ ማሴርና እጅህን የመስደድ የይሁዳ ባህሪ መላበስ ነው፤

v  መጽሐፍ የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፤ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ እንዲል፤ ኢትዮጵያዊነት፥ ሰው በላቡ ጥሮ-ግሮ ያፈራውን ሀብትና ንብረት መዝረፍና ማውደም ነው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት አሁን ባለ ነባራዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለህሊና ቢሶች፣ ለአስመሳዮችና ለግብዞች የሚሰጥ ልዩ መታወቂያ ነው። በገሃድ በትግራይ ምድር የታየውና ዓለም የመሰከረችው፤ ያፈረችበትም ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው።

 

በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ትግራዋይ ጭንጋፍ ነው

 

የሰው ፍቅር የሌላቸው ራስ ወዳዶች፣ ምህረትና ርህራሄ የማያውቁ አጽራረ ጸረ ሰላም፣ ታጥበው የማይጠሩ መርዛማ እባቦችና ጸረ አንድነት ኃይሎች ሆነው ሳለ፥ ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀን የሚታወቁ ሴሰኞቹ የአማራ ልሒቃን፥ በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋ፣ ልዩ ልዩ ወግና ልማዶች፣ በአስተሳሰብ የማትመስላቸው ሆነህ ሳለ በአንድም በሌላም ምክንያት ኢትዮጵያዊነትን የምታቀነቅን፣ የምትቀበልና ሰላም ለኪ እያልክ የባለ አውልያዎች ባንዴራ የምትሰግድ ከሆነ የጸናብህ በሽታ ሌላ ሳይሆን የማንነት ቀውስ የሚወልደው በራስ አለመተማን ነው። በትግራይ መሬት በህጻናትና በሽማግሌዎች፣ በካህናትና በመነኮሳት፣ በእቶቻችንና በእናቶቻችን በአጠቃላይ በተጋሩ ላይ የተገለጠው ኢትዮጵያዊነት፥ የክህደት፣ የግብዝነት፣ የሌብነት፣ የውሸት፣ የአመንዝራነት፣ የአመጸኝነትና የሴሰኝነት ህይወት ነው። ታድያ አንድ ትግራዋይ ይህን ሁሉ ታሪክ ይቅር የማይለው የአመጻ ስራ በወገኖቹ ላይ ሲፈጸም ምስክር ሆኖ እያየና እየሰማ በጤና ኢትዮጵያዊነትን ሊያቀነቅን አይችልም። በአሁን ሰዓት ትግራዋይ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ነኝ አንድም ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅን ግለሰብ ቢኖር ያ ሰው ሌላ ምንም ሳይሆን፥

 

v  ቅርፊቱ ያልሰበረ፤

v  በማንነት ቀውስ የሚሰቃይ፤

v  በራስ መተማመን የሌለው፤

v  ራሱን ችሎ መቆም የማይችል፤

v  ለህልውናው የሌሎች እውቅና የሚሻ፤

v  በራሱ ሳንባ ለመተንፈስ ያልታደለ፤

v  ሌላው በበላው ማግስት የሚቃጣው፤

v  የዘመናዊነትና የስልጣኔ ትርጉም የተምታታበት፤

v  ለሌላ ሊተርፍ ቀርቶ ለራሱ የማይሆን፤

v  ንቃተ ህሊናው የተሰለበ፤

v  አራዳ ነኝ ብሎ ቢያምንም እውነቱ ያልበራለት ልበ ድንጉጥ፤

v  ኮከቡ ጠፍቶበት መንታ መንገድ ላይ የቆመ ምስኪን ሎሌ (ባሪያ/ተላላኪ) የሆነ ሰው ብቻ ነው። እንዲህ ያለ ሰው በስህተት የተገኘው ጎደሎ/ጭንጋፍ ሰው ካልሆነ በቀር ትግራዋይ ሊሆን፤ አንድም ከተጋሩ ሊወለድ አይችልም፤ በተጋሩ መካከልም ርስት የለውም።

 

በመጨረሻ፥ ፈተኳ ጸላእኻ አነ እየ ኣዴኻ በለት ባሪያ እንደሚባለው የሰለጠንክንና ያወቅክ መስሎህ ትግራዋይነትህ ክደህ፤ የሌሎች ማስክ አጥልቀህ፤ ብታሸረግድም ያለ አንዳች ውል ሰራተኛ አድርገው የቀጠሩህ ጌቶችህ እየከነከናቸውም ቢሆን በስምህ ጠርተው ቁጭ ብድግ ሲያደርጉህ የሚያውቁህ ትግራዋይነትን በማይወክ በባንዳነትህ ነው።

 

E:mail- mahbereseytan@gmail.com


Back to Front Page