Back to Front Page

ለኢትዮጵያ አንድነት እንሞታለን የሚለው የአማራ ልሒቃንና የሻዕቢያ ዘፈን ሲገለጥ

ለኢትዮጵያ አንድነት እንሞታለን የሚለው የአማራ ልሒቃንና የሻዕቢያ ዘፈን ሲገለጥ

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 07-28-21

 

መንደርደሪያ፥ ትግራይን ከካርታ፣ የትግራይን ህዝብ መታሰቢያ ላይኖረው ስመ ዝክሩ ከምድረ ገጽ ፈጽሞ ለማጥፋትና ለመደምሰስ የተቃጣው የዘር ማጥፋት ዘመቻ መልኩን ቀይሮ ሌላ ታሪካዊና መስተንክራዊ መልክና ገጽታ ከያዘ ሳምታት አልፏል። በመጠኑም ቢሆን የማስታውሰው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የኢትዮጵያ ህዝብ ለማሰለፍ ሲባል በዚህ ልክ የተከፈተ ዘመቻና የተሰበከ ጥላቻ ነበር የሚል እምነት የለኝም። ሌላው ይቅር፥ የአማራ ልሒቃን አውራ ቂስ የሆነው አገኘው ተሻገር በመንግስታዊ የዘመቻ መግለጫው ላይ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው ሲል እንደተነገረው የኤርትራ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ተብሎ አልተቀሰቀሰም። በዘመናይቱ ዓለምም እንዲህ ያለ ነገር ሲሰማ ይህ የመጀመሪያ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱም፥ ህዝብን በጠላትነት መፈረጅ ማለት ክፉና ደጉን የማያውቁ ህጻናት የህዝቡ አካል እንደ መሆናቸው መጠን ህጻናትን በይፋ ለመጨፍጨር የሚደረግ ጥሪ ነውና።

 

ሌላው አስገራሚ ክስተት፥ ሰዎቹ ትግራይን ለመውረርና የትግራይ ህዝብ ለመጨፍጨፍ ከነግሳንግሳቸው በአውቶቢስ ተሳፍረው ይመጣሉ ወያነ ትግራይ ደግሞ ሳይወሉ ሳያድሩ በምርኮ እየሰበሰበ የሰበሰባቸውን በአይሱዝ እየጫነ ወደ መጡበት የመመለሱ ጉዳይ ነው። በርግጥ፥ አንዳንዶች ይህን የወያነ ትግራይ ተግባር ኢትዮጵያ ትግራይን ለመውጋት ለሁሉም ክልሎች ሠራዊት እንዲልኩ ባስተላለፈችው ትዕዛዝና ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ወያነ ትግራይም የድርሻው መወጣቱ እንደሆነ የሚገልጹ የቀልድ ጸሐፊዎች አልታጡም። ይህ ብቻም አይደለም፥ ኢትዮጵያውን የዐቢይ አህመድ ዓሊ የጥላቻና የደም መንፈስ ተጋብቶባቸው በመላ አገሪቱ የሚገኝ ትግራዋይ ደም ያለው ሰው እየፈለጉና እያደኑ ያለ አንዳች ምህረትና ርህራሄ ሀብትና ንብረቱ በመዝረፍ፣ በማሰር፣ በመቀጥቀጥና በመግደል የዜግነት ግዴታቸው በመወጣት ይገኛሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ፥ ሳውዲ የስራ ፈቃድ የላችሁም ብላ ወደ አገራችን ወደ ኢትዮጵያ ላከችን እያሉ የአዞ እንባ እያነቡ ስለ ፍትሕና ስለ ሰብአዊነት ሲዶሰክሩና ሲጮሁ እየተመለከትን ነው። በርግጥ፥ ማንም ይሁን ማን ለሰው ሁሉ ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ጥብቅና መቆም ሰብአዊነት ነው ድርጊቱም ፈጣሪ ደስ የሚያሰኝ መልካም የጽድቅም ፍሬ ነው። ዳሩ ግን፥ ትናንት ካንተ ጋር አብሮ የነበረ፣ ጎረቤትህ፣ አብሮ አደግህና የስራ ባለ ደረባህ የሆነ ሰው በማንነቱ እየለየህ ያለ አንዳች ምህረትና ርህራሄ እየገደለና እያጎሳቀልክ ሳውዲ ግፍ ፈጸመብን ብሎ ጩኸት አስጸያፊና አስነዋሪ ከመሆኑ በላይ ግብዝነትም ነው። መጽሐፍ፥ የሰው ቁጣ የእግዚአብሔር ጽድቅ አያመጣም እንዲል።

Videos From Around The World

 

ሓተታ፥ እንደ አገር አገራዊ ተቋማት ሊኖሯት ቀርቶ ለተቋማት ህልውና ዋስትና የሚሰጥ ህገ መንግስት የሌላት፣ እንደ አገር ወጪና ገቢዋ የማይታወቅ፣ አገራዊና ማህበራዊ ወጪዎችዋን በሐዋላ በሚገኘው ገቢ የምትደጉም፣ የሰው አገር ሀብትና ንብረት ዘርፋ ዕድገት አስመዘግባለሁ ብላ የምታምን፣ የጎረቤት አገር ፋብሪካና ቁሳቁስ ነቅላ ነቅላ ውስዳ በልማት ጎዳና ነኝ እያለች ፕሮፓጋንዳ የምትነዛ፣ የሰው አገር ሀብትና ገንዘብ ተበድራ ስታበቃ በፈረመችው ውል መሰረት ብድርዋን በመክፈል ፈንታ እንደ አመለኛ ሰው መጥሪያ ወጥቶባት በኩራዝ የምትፈለግ አገር፣ የመንግሥት መልቅና ቅርጽ የሌላትና ያላለፈበት፣ ሁሉም ነገር በአንድ ሰው ቆራጭ-ፈላጭነት ነገርዋ በጓዳ የሚያልቀው አገር ተይዞ፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢፌዲሪ ህገ መንግሥት መጀመሪያ ያየው ሰው እኔ ነኝ፣ ይህ ብሔር ብሔረሰቦች የምትሉት ነገር አይጠቅማችሁም ብዬ ነግራችው ነበር፣ ለመለስ መክሬው ነበር እያለ ሲናገር መስማት የተለመደ ነው። ጥያቄው፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያውያን በላይ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲናገር ስንሰማ የሰውዬው ነጥብ ምንድ ነው? ኤርትራ ትዳሬን ብላ ከወጣች ሦስት አስርት ዓመታት ሆኗታል፣ አቶ ኢሳያይስ አፈቀርቂም የዚች አገር ገዢ ናቸው ስለ ኢትዮጵያ ይህን ያህል የሚያስለፈልፋቸውና የሚያስቃባዥራቸው ምክንያት ምንድ ነው? ኢሳያይስ አፈቀርቂ፥ አስሬ የኢትዮጵያ አንድነት ይገደኛ የሚሉ ዲሞክራሲያዊ መሪ ነኝ ወይስ ሳይወራረድ የቀረ የበቀል ፖለቲካቸው በማር ለውሰው ሊያጎርሱን እያደቡ ነው? የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን የሚለው ኢሳያሳዊ ዘፈናቸው ምን ፍለጋ ነው? ኢሳያይስ አፈወርቂ፥ የሌላ ሉዓላዊት አገር መሪ ሆነው ሳለ ስለ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን በላይ ዕንቅልፍ የነሳቸው ጉዳይማ መጣራት አለበት በማለት የኢሳይያስ አፈቀርቂ መርዛም ፖለቲካ ለመፈተሽ ማስተዋልን የመረጥን ስንቶቻችን ነን? ኢሳይያስ አፈወርቂና የአማራ ልሒቃን ምን ቢያገናኛቸው ነው ከአስመራ እስከ ጎንደር ከስዊድን እስከ ዋሽንግተን ለኢትዮጵያ አንድነት እንሞታለን የሚል ሐሰተኛ ዘፈን እየተቀባበሉ የሚዘፍኑበት ምክንያት ምንድ ነው? ለሚለው ጥያቄ አደጋ ጣዮቹ በየፊናቸው የሚያስጮሃቸው ምስጢር ከብዙ በጥቂቱ እንመለከታለን።

 

የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለም

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ፥ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ የሌላት ኢትዮጵያ የኤርትራ ባሪያ አድርጎ በሚገባ ሊያልባትና ሊጋልባት፣ ሊግጣትና ሊጠቀምባት፣ ሊዘርፋትና ሊያስገብራት እንደሚችል አሳምሮ ያምናል። ይህ ልክ የሌለው የኢሳይያስ ምኞችና ፍላጎትም ከትግራይ ህዝብ በቀር ሌላ አንድም ለያስቆመው የሚችል ኃይልና ህዝብ እንደ ሌለ ብጽኑ ያምናል። ይህ ሐተታ የእኔ ግላዊ አስተሳሰብ ሳይሆን ቀጠናው የእጃው መዳፍ ያህል የሚያነቡትና የሚቆጣጠሩት አገራት መዝገብ ውስጥ የኢሳይያስ አፈወርቂ ህልምና አጀንዳ ተብሎ በሚገባ የተሰነደ ሐቅ ነው። የኢሳይያስ አፈወርቂ ራስ ማታትና ቅዥት የትግራይ ህዝብ ህልውና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ አንድነት ጭምር ነው በማለትም ያክላሉ። ቆይ እንጅ፥ የኢሳይያስ አፈወርቂ ጸሎትና ምኞት የኢትዮጵያ አንድነት ነው እያልክ አሁን ደግሞ እንዴት ነው የኢትዮጵያ አንድነት ለኢሳይያስ አፈወርቂ ራስምታት ነው የምትለው? አባባልህ አይጋጭም ወይ? ማለትዎ አይቀርም። እውነትም ነው አባባሌ የሚጋጭ ሆኖ ሳይሰማዎት ኣይቀርም ዳሩ ግን መጽሐፍ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል እንዲል የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለ፣ ድግስ ሁሉም ድግስ አንዳይደለ እንደምንተማመን አማናለሁኝ። ታድያ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያውያን በላይ ኢትዮጵያ ሆኖ የሚያስተጋባው የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው ዘፈን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚያውቁትና የሚቀበሉት፣ ምስጢሩ ሲገለጥና ሲተረጎም እኔም ሆነ እርስዎ ልንቀበለው ቀርቶ ልንሰማው ስለ ማንፈልገው አንድነት ነው እየዘፈነ ያለ።

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ አፉ በከፈተ ቁጥር እስያስኮመኮመህ ያለ የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው ዘፈን ኤርትራን በቀኝ ግዛት የያዘ ሰይጣናዊ ቀንበር ነበር! ብሎ ለሠላሳ ዓመታት የታገለውና ጥሎት የሄደ ደርጋዊ አንድነት ነው። የጃንሆይ ሆነ የደርግ ወታደራዊና ዘውዳዊና የአሃዳዊ ሥርዓተ መንግሥት ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዴት እንዳንኮታኮታትና እንጦርጦስ እንዳወረት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሚገባ የተረዳ ሰው ነው። ታድያ ኢሳይያስ አፈወርቂ አምርሮ ለሚጠለውና ለሚጸየፈው ህዝብና አገር ይህን ቢመኝለት ምን ይደነቃል? ጥላቻው ለመግለጥ ተግባራዊ ያደረገው ስልት ታድያ ከወዳጁቹ ከግብጻውያን በተዋሰው መሰሪ ስልት ነው ይኸውም፥ ጠላትህን ለማሸነፍ ወዳጅ ሁነው እንዲሉ። ለምን? ቢሉ መርዝህን ስትረጭ የሚጠረጥርህና እንዲሁ በቀላሉ የሚደርስብህ ሰው ስለማይገኝ ነው። እውነትም፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ አንድነት ከማንም በላይ ለእኛ ያሳስበናል እያለ ሲያወራ የሚሰማ ሰው ኢሳይያስ አፈወርቂ ይህን እያለ ያለ ኢትዮጵያን ለመቅበር ነው ብሎ የሚጠረጥር አይገኝም። እንደውም በአንጻሩ፥ ሰውዬው እጁ በንጹሐን ዜጎች ደም የጨቀየ ነፈሰ ገዳይ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ ኢሱ አንበሳ እየተባለ ይዘፈንለታል እንጅ።

 

የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን፣ ብሔር ብሔረሰቦች የሚለው ትርክት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተሰነደ የወያነ ሰነድ ነው የሚለው ኢሳይያሰ አፈወርቂ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነትና ስልጣን የምታከብርና የምትጠብቅ ኢትዮጵያ ለኤርትራ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገትና እንቅስቃሴ ስጋት ናት ብቻ ሳትሆን የሞት ጥላ ናት ብሎ እንደሚያምንና የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን ሲልም ኢትዮጵያ ገዝግዞ ለመጣልና ለማተረማመስ እንደሆነ ግን አይነግረንም። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የምታከብርና የምትቀበል ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ሁለመናዊ ዕድገት በማስመዝገብ የቀጣናው ብቻ ሳይሆን በአፍሪቃ ሪጅናል ፓወር የመሆን አቅም እንዳላት ይህም ለኤርትራ መርዶ እንደሆነና ኢሳያይስ አፈወርቂም ይህን የኢትዮጵያ ጉዞ ለመቅጨት በአድነንት ስም ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ የድህነትና የጦርነት አዙሪት መመለስ አለባት ብሎ እንደወሰነና የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን የሚልበት ምክንያትም ይህ እንደሆነ አሁንም አልነገረንም። የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን የሚለው መቆርቆር የሚመስል የኢሳይያስ አፈወርቂ የምቀኝነት ፕሮፓጋንዳ ምዋርት ከመሆኑ በላይ ግቡና ዓላማው ኢትዮጵያን ማዳከምና አንኮታኩቶ መጣል እንደሆነ ዛሬም ድረስ ያልበራላቸው ኢትዮጵያውያን አውሬውን ኢሳያያስ ማምለክ ምርጫቸው በማድረጋቸው ይሄው የዘሩትን በማጨድ ላይ ይገኛሉ።

 

ኢሳይያስ አፈወርቂ የአንድነት ዘፈን እየዘፈነ ኢትዮጵያን ፈጽሞ ለማዳከም የፈለገበት ምክንያት ከዚህም ሁሉ ያለፈ ነው። በቀጠናው ፈርጣማ ኢትዮጵያ እስከትፈጠር ድረስ እጅና እግሬን አጣምሬ ከተቀመጥኩ ባድመ ቀርቶ አሰብንም አጣላሁ። በትግራይና በኤርትራ አዋሳኝ የሚገኙ የኩናማና የኢሮብ ግዛቶች፣ በአፋር በኩል የኤርትራ አፋር መሄዳቸው ሳይታለም የተፈታ ነው ብሎ የሚያምነው ኢሳይያስ ዓይኑ እያየ ኢትዮጵያን እያፈረጠመና እያጎለበተ ያለ (በወቅቱ) የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብትና ስልጣን ለማጠልሸትና ለማኮላሸት የተነሳው። ይህን ለማድረግ ከተጠቀማቸው ስልቶች መካከል ታድያ በዚህ ጽሑፍ ላይ በስፋት የተመለከትነው ከኢትዮጵያውያን በላይ ለኢትዮጵያ አንደነት የሚቆረቆር ሰው ሆኖ መቅረቡን ነው።

 

በርግጥ፥ ጥላቻና ምቀኝነት እንዲሁ ሳይዘራ የሚበቅል አይደለም። ሰው በሰው ላይ ሲመቃኝና ሲያሟርት መንስኤ እንዳለው እንዲሁ የኢሳይያስ አፈወርቂ የጥላቻና የምቀኝነት በሽታም በተመሳሳይ መንስኤ አለው። የኢትዮጵያ አንድነት እንሻለን የሚለው የኢሳይያስ አፈወርቂ ነጠላ ዜማ ጥንተ ነገሩ የሚመዘዘው ከአስመራ ሳይሆን ከሳሕል ነው። .. 70ዎቹ መጀመሪያ አከባቢ በነበረው ጊዜ የወያነ ትግራይ ማለትም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በፖለቲካና ወታደራዊ አቅሙና አደረጃጀቱ ተጠናክሮ መውጣትና መምጣት ክፉኛ ያስደነገጠውና መርዶ የሆነበት ህዝባዊ ግንባር (ሻዕቢያ) የትግራይ አገር መሆን ቀርቶ በፌዴራል ሥርዓት የምትፈጠረው ኢትዮጵያ ኤርትራን ወደ መንደርነት ይቀይራታል የሚል ድምዳሜ ላይ የፈጠረ ክስተት ነበር። ይህን ተከትሎም በኢሳይያስ አፈወርቂ የሚመራ የሻዕቢያ ቡድን የሚያልማት ዓባይ ኤርትራ እውን ለማድረግ ከተፈለገ መደረግ የሚገባውን ሁሉ በማድረግ ደካማ ኢትዮጵያ መፍጠር እንደሚጠበቅበት ተማምሎ አጀንዳ ቀርጾ ለመንቀሳቀስ የተወሰነው። እንግዲህ የኢሳይያስ አፈወርቂ መቆርቆር የሚመስል ምዋርት፥ ኢትዮጵያን ለማትረፍ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመቅበር፤ ኢትዮጵያውያን ለማሰረፍና ተጠቃሚዎች ለማድረግ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ለማተላለቅና ደም ለማቃባት ያለመ ነው። የደርግና የጃንሆን ዘመነ መንግሥት ልብ ይሏል። በነገራችን ላይ፥ በኢትዮጵያ የትግራይ የበላይነት አለ የሚለው ፕሮፓጋንዳ ያራግቡ ዘንድ ከመጣ ጋር በመለጠፍና በመላላክ ለሚታወቁ ለአማራ ልሒቃን አጀንዳ ቀርጾና አስይዞ ያሰማራቸው ይህ አምባገነን የኤርትራ መንግሥት የሻዕቢያ ቡድን መሆኑን ማወቁ አስፈላጊ ነው።

 

የተላላኪዎቹና ተለጣፊዎቹ የአማራ ልሒቃን የአንድነት ዘፈን ሲፋቅ

 

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሁሉም በተናጠል እንደ አገር የመቆም አጀንዳ ገፍቶ ቢመጣና ኢትዮጵያ ለአስራ አንድና ከዚያ በላይ አገራት የተከፋፈለች ዕለት ኃይማኖት አልባ የአማራ ልሒቃን መሄጃ መደበቂ ስፍራ እንደ ሌላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። የአማራ ልሒቃን የሥነ ልቦና ዓውድ የተዋቀረው አንዱን እየሰደብን ሌላውን እያሳደድን መኖር እንችላለን የሚል አስተሳሰብና አመለካከት ላይ የቆመና የተገነባ ሰላቢ ሥነ ልቦና እንጅ ሌሎች ሁሉም ራሳቸው ቢችሉ እኛም እንደ ትግራይና እንደ ሲዳማ ራሳችን ችለን አገር መቆርቆርና መምራት እንችላለን የሚል ሥነ ልቦና የላቸው። አቶ አገኘሁ ተሻገር ባሰለፍነው ሳምንት ላይ ተጋሩ ያስቀኑኛል፣ ከእነሱ መማር አለብን፣ በሰርግና በለቅሶ ብቻ እየተገኘን ምላሳችን ከትናጋችን እስኪጣበቅ ድረስ መሸለልና ዘራፍ ማለት ዋጋ የለውም ሲል የጓዳው ገመና በአንደበቱ እንደ ዘረገፈው የአማራ ልሒቃን አሉባልተኛ ምላሳቸው እየወለደሉ ወሬ ከማመላለስና ከመቀደድ ያለፈ ቁም-ነገር እንደሌላቸውና እንደማይገኝባቸው የታወቀ ነው። በመሆኑም፥ እነሱ ራሳቸው ተፈናጠው መጥተው በተናኮሱትና በከፈቱት ጦርነት መበላት ሲጀምሩ ይሄው ዛሬ አገር ይያዝልን እያሉ ጩኸታቸው የሚያቀልጡት ምስጢር ሌላ ምንም ሳይሆን ለዘመናት የተደበቁበት ትምክህተኛ ምሽግ እየፈራረሰ መምጣቱ እንጅ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ህልውና አሳስቧቸው አይደለም። ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ህልውናና ደህንነት ስጋትና ጠንቅማ የአማራ ልሒቃን ትምክህተኛ አስተሳሰብና የበከተ እምነት እንደሆነ የኢትዮጵያ የደም ታሪክ መመልከት ብቻውን በቂ ነው።

 

ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አስወግዶና አራቁቶ የአማራ ልሒቃን ብቸኛ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓተ መንግስት የኢትዮጵያ አንድነት የሚያጎለብትና የሚያበረታ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስልጣንና መብት የሚጠብቅና የሚያከብር ፌዴራላዊ ሥርዓተ መንግስት ሳይሆን ልክ እንደ ኢሳይያስ አፈወርቂ በአንድነት ስም የሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብትና ሥርዓት ረጋግጦና ጨፍልቆ የአማራ ልሒቃን ፈቃድና ምኞት የምታስተጋባ ኢትዮጵያ መፍጠር ነው። እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልጽ ሊሆንልን የሚገባ ነገር አለ፤ ይኸውም፥ የአማራ ልሒቃን የኢትዮጵያ አንድነት አስመልክተው በተለይ በአሁን ሰዓት አበክረው ሲጮሁና ሲጯጯሁ ስንመለከት ልክ እንደ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሰዎቹ በእውነቱ ነገር ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ግድ የሚላቸው ሰዎች ሆነው ሳይሆን የአማራ ልሒቃን ከመጣ ጋር እየተለጠፉ ነገር ከመሰልቀጥ ያለፈ እንደ ትግራይ ወይም እንደ ኦሮሚያና ሱማሊ ራሳቸውን ችለው መቆም ስለማይችሉና እንደማይችሉም ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነገሩ እዚያ ድረስ ከመድረሱ በፊት በርቁ አጠር ማበጃጀታቸው (አንድነት የሚለው ዘፈን ማለቴ ነው) እንደሆነ ሊገባን ይገባል። ለምን?

 

v ለኢትዮጵያ አንድነት እንሞታለን የሚለው የአማራ ልሂቃን ዘፈን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጥቅምና ህልውና ግምት ውስጥ ያስገባ ሳይሆን ይህን ዓይነቱ አማላይ ዘፈን እዘፈኑ ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌላቸው፤

v ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ድቡብ፣ ሶማሌ፣ ሐረሬ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ እንደ አገር የቆመና ራሱን የቻለ ዕለት፥ አገር በሽለላና በቀረርቶ ስለማትገነባ፣ የኤርትራ ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥማቸው ስለሚያውቁ፤

v እንጀራቸው በኢትዮጵያ ጥላ ስር የተሰበሰበው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስለሆነ፤

v በኢትዮጵያ ስም እንደ መዥገር በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ትክሻ ላይ ተለጥፈውና ተንጠላጥለው ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌላቸው፤

v የአማራ ልሒቃን ለኢትዮጵያ አንድነት እንሞታለን እያሉ ሲያላዝኑና ሲሸልሉ ስንሰማ ሰዎቹ በእውነቱ ነገር የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰላምና ዕድገት በመመኘት ሳይሆን የምንጠቀመውና ህልውና ሊኖረን የሚችለው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስትኖር ብቻ ነው! እያሉ እንደሆነ፤

v የአማራ ልሒቃን ዕለት ዕለት በሚያወጡት የክተት አዋጅ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በስማቸው እየጠራ ክልልሎች በፈጠራቹ ቅበሩኝ እያለ ያለበት ምክንያትም ወያነ ትግራይ ገፍቶ ከመጣ እውነተኛ ማንነታችን ለአደባባይ ሊያሰጣው፣ ሊገልጠንና ሊያራቁተን ነው ብለው ስላመኑ፤

v በጥቅሉ፥ የአማራ ልሒቃን እንቅልፍ አሳጥቶ እያስቀባጀራቸው ያለ የኢትዮጵያ ህልውና ሳይሆን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተመሰረተ የጥቅማቸው መጓደል እንደሆነ ሊገባን ይገባል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page