Back to Front Page

ኢትዮጵያዊነት፥ ፍጥረት ሁሉ ሊጸየፈው የሚገባ በርያሱሳዊ ላሜ-ቦራ ነው

ኢትዮጵያዊነት፥ ፍጥረት ሁሉ ሊጸየፈው የሚገባ በርያሱሳዊ ላሜ-ቦራ ነው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

10-12-21

 

ትርጓሜ፥

 

       በርያሱስ፥ አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው! እያሉ በእግዚአብሔር ስም ሳይቀር መሸቃቀጥ፣ መሸጠና መለወጥ የለመዱ፥ ሐሰተኞች፣ ምቀኞች፣ ምዋርተኖች፣ እምነት የማይጣልባቸው ወስላቶችና አመንዝሮች ሳሉ፥ በአንድነት፣ በፍቅር፣ በሉዓላዊነት ስም በመነገድ ጥራሳቸው የነቀሉ ጸረ-እኩልነት ጸረ-ፍትሕ የሆኑ የአማራ ልሒቃን የአገርና የህዝብ ጉልበት የበላ እውነተኛ ማንነት፣ ሰይጣዊ ስራና ተግባራት ለማስረዳት የተመረጠ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ፥ መጨረሻው ያላመረለት፣ አመጸኛ፣ አጽራረ ጽድቅ፣ ምቀኛ፣ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የነበረ ሰው ሲሆን የስሙ ትርጓሜም የኢየሱስ ልጅ ማለት ነው። ለዝርዝር ማብራሪያ፥ ቁ.5 ይመልከቱ።

 

       አፈ-ህጻን፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የአፍዝ አደንግዝ፣ የድግምትና የመተት የምዋርትና የአስማት መጻህፍት በአጋንንት የሥልጣን ተዋረድ ዝቅተኛውና የመጨረሻ ጭፍራ ነው።

 

       ህጋዊ ሽፍታ፥ የሽፍታ ብሎ ህጋዊ እንደሌለ የታወቀ ነው ቢሆንም ግን የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ሳይገባው አለቦታው የተቀመጠ፣ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አንድም በተጭበረበረና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ፣ በውንብድና፣ ሥልጣን ላይ የወጣ ስጋን በልቶ አጥንት የሚቆረጥም ዘራፊ ቡድን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የዋለ ኃይለ ቃል ነው።

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ ከአመጽና ከወንጀል፣ ከውሸትና ከአሉባልታ፣ ከነፍስ ቅትለትና ከሴራ ፖለቲካ አልስማማም፤ የንጹሐን ዜጎች ደም መፍሰስ፣ ለሞትና ለእልቂት እጄን አልጨምርም ፈቃዴንም አልሰጥም! በማለት እውነትና ጽድቅ ከመፈለግና ከማድረግና ይልቅ፥ በአፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊና የጦርና የኃይማኖት ጀኔራሎቹ እንዲሁም ፍርፋሬ ለቃሚዎች የአማራ ልሒቃን ሐሰተኛ ምላስ በኢትዮጵያዊነት ስም የሚነገረው የውሸት መዓት ተውጦና ተዘፍቆ፣ ውሸትና አሉባልታ ግፍና አመጻን ጣመኝ ድገመኝ እያለ ሳይታወቅበት የአጋንንት ጸበልተኛ የሆነ፣ ፍትሓዊነትና ሚዛናውነት ተጸይፎ እውነት በማሳደድ ላይ ያለና የሚገኝ፥ አገሬ በሰማይ ነው፣ ክርስትያን ነኝ፣ አማኝ ነን፣ ኃይማኖተኛ ነኝ ባይ ህዝብ የእግዚአብሔር የምህረት ደጅ ፈጽሞ ከመዘጋቱ በፊት ወደ ነፍሱ እንዲመለስ፣ መነጽሩን እንዲያስተካክልና መንገዱን እንዲሰልል ተጻፈ።

 

መንደርደሪያ፥ ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ነገር፥ በሰው ግንባርና ጀርባ ላይ የሚሰፋና የሚነቀስ፣ የማይፋቅና የማይለወጥ፣ ህያውና የማይሻር ሰማያዊ ምልክት ወይም ማህተም ሳይሆን ይልቁንም ኢትዮጵያዊነት እንደየ ሁኔታው ማለትም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ወደውና ፈቅደው በስምምነት የተቀመጡ እንደሆነ የሚለብሱትና የሚያጠልቁት፣ እንደ ኤርትራ ትዳሬን ያሉ እንደሆነ ደግሞ የሚያወልቁትና ጥለውት የሚሄዱት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ጥቅም ላይ መሰረት ያደረገ በህግ አግባብ የሚጎናጸፉት ማሊያ አንድም ካፖርት ለመሆኑ ከዚህ ቀደም በሪፖርተር ጋዜጣ ኋላም ራሱን ችሎ በታተመው ኢትዮጵያዊነት ምንድ ነው? በሚል መጽሐፌ ላይ የመፍትሔ ሃሳብ ጨምሮ በስፋትና በጥልቀት አስረድቻለሁ። ወቅቱና ሰዓቱ በሚመጥን መልኩ አጠር ባለ መልኩ ለማስቀመጥ ያህል ግን አንዳንድ ሃሳቦች እንደሚከተለው ለማንሳት እወዳለሁ። ይኸውም፥

 

v ሰዎች፥ እኔ ትግራዋይ ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ፣ አገው ነው፣ ሲዳማ ነኝ፣ አማራ ነኝ፣ አፋር ነኝ፣ ሐረሬ ነኝ፣ ጋምቤላ ነኝ፣ ወላይታ ነኝ፣ አላባ ጠንባሮ ነኝ የሚሉበት ዋና ምክንያት እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፥ ኖሯቸውና ህይወታቸው የሚመሩበት፣ ማን ነህ? ባይ ጠያቂ ቢመጣ ራሳቸው በሙላት የሚገልጹበት፣ የስነ ልቦናቸው ውቅር ማንንም ላይ ያልተንጠለጠለ፣ አንዱ ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት፣ ራሱ የቻለ የስነ ልቦናና የአስተሳሰብ ውቅር፣ ስልጣኔ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ማህበራዊ ኑሮና የአስተዳደር ዘዬ፣ ወግና ልማዶች ስላሏቸው ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚባል ደም አንድም ኢትዮጵያዊነት የሚባል ማንነትና ኢትዮጵያዊ የሚባል ህዝብ የለም የምልበት ምክንያትም ይህ ነው። እንግዲህ፥ ዛሬ በሰው ሬሳ ላይ ተቁሞ የሚዘመርለት ያለ ኢትዮጵያዊነት የሚጀምረው ከዚህ ነው። ይህ ማለት፥ ኢትዮጵያዊነት ምንድ ነው? ተብሎ ጥያቄ ሲነሳ ሳይንሳዊ ጭብጥና ምክንያት ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት በመጣል ትቀበል እንደሆንክ ተቀበል እየተባለ የሚዘፈነው ኢትዮጵያዊነት ክቡር ማንነት የሚል የጠንቋይ መፈክር ማስተጋባት ነውና።

 

v ሲጀምር፥ ኢትዮጵያዊነት ማንነት ነው ለማለት ኢትዮጵያ ቋንቋ፣ ኢትዮጵያዊ ባህል፣ ኢትዮጵያዊ ወግና ልማድ፣ ኢትዮጵያዊ ታሪክና ስልጣኔ፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ የሚባል ስነ ልቦናና ያለው ብሔርና ህዝብ ሲኖር ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ የአማራ ልሒቃን እንኳ ቢሆኑ የእኛ ነው የሚሉት ባህል፣ ቋንቋ፣ ስነ ልቦና፣ ወግና ልማድ ከራሳቸው አልፎ ማንንም አይወክልም። ትግራይ ሆነ ኦሮሞ አፋር ሆነ ሶማሌ ሁሉም የየራሱ የሆነ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ የስነ ልቦና ውቅር፣ ወግና ልማድ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። ለምሳሌ ያህል፥ እኔ ትግራዋይ ነኝ ይህ ማለት፥ የአማራ ሆነ የደቡብ፣ የአፋር ሆነ የሱማሌ ሰዎች ህይወት ልኖር አልችልም፤ እንዴት እንደሚያስቡና ነገሮች በምን ዓይነት መልኩ እንደሚያዩ ማወቅ ቀርቶ ልገምትም አልችለም። ለምን? በአስተሳሰቤም በአኗኗሬም እኔነቴን የቀረጸ ማንነት ከሁሉም የተለየ፣ ራሱን የቻለ ማንነት ስለሆነ፤ በትግራዋይ ስነ ልቦና ያደግኩ ትግራዋይ እንጅ አማራ ወይም ደቡብ ስላደለሁና ልሆንም ስለማልችል ነው። አማርኛ ቋንቋ መጻፍና መናገር የተማርኩት መጽሐፍ ቅዱስ ሳጠና በግል ጥረቴ ነው። በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል (በአዲስ አበባ ከተማ) የነበረኝ ቆይታም በጣም አጭር ጊዜ ነው። ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋርም.. እንዲሁ ከመምሰል ያለፈ አንዳቸው ሌላኛው መሆን አይችሉም።

 

v ጎበዝ፥ ኢትዮጵያዊ የጋራ ማንነት ሳይሆን ቀሚስ/ዜግነት ነው። በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ወደውና ፈቅደው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በህግ የሚጎናጸፉት ህጋዊ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ይባላል። የጋራ ማንነት ሊፈጠር አንድም የጋራ መገለጫ እውን ሊሆን የሚችለው ግን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በቁጥር ብዛት ወይም በሌላ መመዘኛ ሳይሆን ይብዛም ይነስ በማንነታቸውና በህልውናቸው ብቻ የብሔር ብሔረሰቦች ሙሉ መብትና ስልጣን የሚጠብቅ፣ የህዝቦች እኩልነት ያረጋገጠ፣ ሁሉም በእኩል ዓይን የሚያይና የሚዳኝ፣ ተግባራዊ የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የጋራ ማንነት የሚባለው ነገር እንደ ትግራዋይነት አልያም ኦሮሞነት የሚጨበጥና የሚዳሰስ ተፈጥሯዊ ነገር ሳይሆን ከበጎ ፈቃድና ስምምነት የሚመነጨው ህግ የሚፈጥረው የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ የጋራ መገለጫ ነው። ከዚህ ውጭ የሚነገረው ቱሪናፋ ታድያ ህጋዊ መሰረት የሌለው የፖለቲካ ሸቀጥና ሸፍጥ ነው። ሐቁ፥ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ይቅር የጋራ የሚባል ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖራት ቀርቶ የጋራ የሚባል ህገ መንግስትና ባንዴራ የሌላት ኮምፓስዋ የጠፋባት አገር ናት። ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ሶማሊያ ወዘተ የእኔ ነው ብሎ የተቀበለው ህገ መንግስት አማራ የእኔ ነው ብሎ አይቀበለውም። አሁንም፥ ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ሶማሊያ ወዘተ የእኔ ነው ብሎ የተቀበለው ባንዴራ አማራ የእኔ ነው ብሎ አይቀበለውም። ኢትዮጵያዊነት ክቡር ማንነት እየተባለ እየተዘፈነለት ያለ ሐሰተኛ መፈክር እንግዲህ ይህ ነው። ይህ ደግሞ ከምኞች ያለፈ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም።

 

v ትግራይ/ሲዳማ/ቅማንት/ቤንሻንጉል/ኦሮሞ/ሃረር/አፋር/ሶማሌ/አማራ/ጋምቤላ የሚባል ብሔርና ህዝብ እንጅ ኢትዮጵያዊ የሚባል ብሔርና ህዝብ የለም። ትግርኛ/አፋርኛ/አማርኛ/ሱማሊኛ/ኦሮምኛ/ጉራጊኛ የሚባል ቋንቋ እንጅ ኢትዮጵያዊ የሚባል ቋንቋ የለም። የትግራይ፣ የሲዳማ፣ የአገርው፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የሐረሬ ስልጣኔ እንጅ ኢትዮጵያ የሚባል ህዝብ ኖሮ የኢትዮጵያ የሚባል ስልጣኔ የለም። የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባለው የትግራይ፣ የወላይታ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የቤንሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአገው፣ የቅማንት፣ የአፋር እንጅ በደምሳሳው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ነገር የለም። የኢትዮጵያ ታሪክ ተብሎ የሚጠቀሰው የአድዋ ታሪክም ቢሆን ምኒሊክ ትግራይን ለማዳከም በጠነሰሰው ሴራ በዓላማና በዕቅድ በግብዣ የገባው ጣሊያን በራስ አሉላ መሪነት ትግራይ ጣሊያንን በአድዋ ድል የነሳችበት ታሪክ ነው። ልክ ትግራዋይ በአስተሳሰቡና በአኗኗሩ ትግራዋይ፣ ኦሮሞን በአስተሳሰቡና በአኗኗሩ ኦሮሞ የሚባል ህዝብ እንዲኖር ያደረገ የስነ ልቦና ውቅር እንዳለ ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ ኢትዮጵያዊ የሚባል ህዝብ ኖሮ ኢትዮጵያዊ የሚባል የስነ ልቦና ውቅር የለም። ቢኖር ኖሮ እዚህ ሁሉ ጦስ ባልገባን ነበር።

 

v ኢትዮጵያ ሰማያዊት፣ ማርያማዊት አልያም ዲያመንድም አይደለችም። አፈ ጮለዎችና ስልጣን ፈላጊዎች ግን ስልጣን ለመቋደስ ሲያደቡ ጊዜና ወቅት እየጠበቁ የማይሉትና የማይሸቃቅጡት ነገር ስለ ሌላቸው ከአፋቸው እየተቀበልክ፥ አንዴ ሰማያዊት ሌላ ጊዜ ዲያመንድ የሚያስብልህ ያለ የሚባለው ነገር እውነተኝነት ስላለው ሳይሆን እንደ ገደል ማሚቶ የሚያስጭክህ ያለው ድህነት ነው። አንድም፥ ሰው የሚሰራው ስራ ቢኖሮው ኖሮ ስራ ፈቶች የሚሉትና የሚቀባጥሩት የቀን ቅዠት እየሰማህ ባልከነፍክ ነበር። ጥጉ፥ ኢትዮጵያ፥ አንዲት ጥምቀት አንዲት ኃይማኖት እየተባለ ከአውዱ ውጭ ተተርጉሞ እንደ ባንዴራ የሚውለበለበው ቃል የአንድ ህዝብ አገር ሳትሆን፤ ኢትዮጵያ፥ የራሳቸው ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ባህልና ልዩ የስነ ልቦና ውቅር ያላቸው፣ ራሳቸው የቻሉ ሰማኒያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ወደውና ፈቅደው ያቀኗት አገር ናት። እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፈቃዳቸው ያነሱ እንደሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትኖርም። ጎበዝ፥ ይህ ሐቅ ለመረዳት የሃርቫርድ ዲግሪ አይጠይቅም። ጥያቄው፥ ከፍ ሲል ነጥብ በነጥብ የተቀመጠው ሃሳብ ለመረዳት የሃርቫርድ ዲግሪ የማይጠይቅ ከሆነ ይህ ሁሉ ዲፕሎማሲያዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀትና ውድቀት፣ ጦርነት፣ እልቂትና ደምነት የመሰለ የቁልቁለት ጊዞ ከወዴት መጣ? የሚል ነው። ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እንደሚከተለው ከብዙ በጥቂቱ ቀርቧል እነሆይ።

 

ሰባቱ ኢትዮጵያዊ ነውሮችና ኃጢአቶች፥

 

በሐሰተኛ ውንጀላና ክስ ከዚህም ከዚያም በተሰባሰቡ አገራትና መንግስታት በተቀናጀና በተዋደደ መልኩ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመ ወረራ መልኩንና ቅርጹን ለውጦ እሳቱ የለኮሱ ሰዎች በገዛ እጃቸው በለኮሱት እሳት ሲጠበሱ፣ ሲለበለቡና እሳቱ በላያቸው ላይ ሲነድባቸው እያየን ነው። ክፋትና ጥመት የተሞላ አመጸኛ ልብ ግን ሁሉጊዜ አመጸኛ ነውና፥ ከጥይት ያመለጠ ህዝብ በርሃብና በመድኃኒት እጦት ለመጨረስና ለማብረስ በአዋጅ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው ብሎ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ስመ ዝክሩ መታሰቢያ ላይኖረው ለማጥፋትና ፈጽሞ ከታሪክ ለመፋቅ ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም እየሰራው ያለ ስራ በተጨማሪ የከፈተው ሰይጣናዊ ዘመቻው ለማጧጧፍ ተጨማሪ የሰው ኃይል፣ ከቻይና፣ ከኢራን፣ ከቱርክና ከማዕከላይ ምስራቅ አገራት የተገኘ አዳዲስ የጦር መሳሪያ ታክሎበት ነገሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። ዓለም፥ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ፈጽሞ ለማብረስ እየሄደበት ያለ መንገድ ቆማ እየተመለከተች ባለችው ሰዓት ትላልቅ የዓለም መገናኛ ብዙሐን፥ ኢትዮጵያ፥ ዜጎችዋን በርሃብ እየገደለች ያለች አገር (FT) በማለት እየጮኹ ነው። ሌሎችም በተመሳሳይ ኃይሉና ጉልበቱ ያላቸው መንግስታትና አገራት ንጹሐን ዜጎች እንዲታደጉ የየህግ ያለህ! እያሉ ነው።

 

ይህ እልቂትና ደም መፋሰስ በኢትዮጵያዊነት ስም እየተፈጸ እንዳለና ኢትዮጵያም እንደ አገር በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸመችው ያለ ግፍና በደል በዕቅድና በዓላማ እየፈጸመችው ያለ አረማዊነት ከመሆኑ በላይ ደስተኛ እንደሆነችም ለሁላችን ግልጽ ነው። በውስጥዋ ያሉ፣ ትግራይ ጠል ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የሰለጠነባቸው፣ በቅናት በምቀኝነትና በጥላቻ የሰከሩ ህዝቦችም ቢሆኑ የዚህ ሰይጣናዊና አረመኔያዊ ድርጊት ደጋፊዎች ናቸው። አሁን ቀደም ሲል ወዳነሳነው ጥያቄ እንመለስና፥ ለዚህ ሁሉ ሞትና ዕልቂት ዋና መንስኤና ምንጭ የሆነው፣ አሁንም በቀጣይነት በንዚን ሆኖ እሳቱን እንዳይጠፋ በማቀጣጠል ያለና የሚገኝ ኢትዮጵያዊነት የሚባል የበከተ አሃዳዊ እምነትና አስተሳሰብ ዙሪያ ሰባት አንኳር አንኳር ነጥቦች በአጭሩ አንስተን እንመለከታለን። እነዚህ ነጥቦች ደም የተጠሙ፣ የጦርነቱ ደጋፊዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግላጭ የሚጸባረቁና የሚታዩ የተገለጡ ሰይጣናዊ ባህሪያትም ናቸው።

 

1.      ሐሰተኛና ውሸታም ምላስ፥

 

ሐሰት/ውሸት፥ ትክክል ባልሆነና በከንቱ ንግግር ሌላውን ወገን ለማሳመን መመኮር፣ ያልሆነ ቃል መናገር፣ እምነት ማጉደል፣ ሐሰተኛ መረጃ መስጠት ተብሎ በቀላሉ ሊተረጎም ይችላል። ውሸት፥ ለራስ ጥቅም ሲባል ባለንጀራህ የሚገባው ጥቅም በማሳጣት ባልሆነና ባልተገባ፣ በሴራና በተንኮል፣ በቅጥፈትና ቅንነት በጎደለበት መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን የሚደረግ የማታለል፣ የማወናበድ፣ የማጭበርበር፣ መንገድ ነው። በርግጥ፥ የውሸት ዓይነትና ደረጃ እንዳለው ማወቁ አስፈላጊ ነው። የአፈ ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊና ፍርፋሬ ለቃሚዎች የአማራ ልሂቃን ዓይነቱ ከልደታቸው ጀምሮ በውሸት መናገርና ሐሰተኛ ምስክርነት መስጠት የተጋባባቸው ሰዎች በነገር ሁሉ ሳያጭበረብሩ፣ ሳያወናብዱ፣ ሳያምታቱና ሳይቀደዱ ስራ መስራት ስለ ማይችሉና ስለ ማይሆንላቸው ውሸት ለእነዚህ ሰዎች ንጹህ አየር የመተንፈስ ያህል የተለመደ ነው። የትም ቦታ በማንኛውም ሰዓት ለመዋሸት ምክንያት ሳያስፈልጋቸው እንዲሁ አፋቸው በከፈቱና ወደ ማይክ በተጠጉ ቁጥር እንደ ዱቄት የመብነን እንደ አቦጀዲ የመቀደድ ክፉና አደገኛ ባህሪይ ያላቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ሲዋሹ እየዋሹ እንደሆነም አይታወቁባቸውም፤ ጸጸትም የለባቸውም። የባጫ ደበሌና የብርሃኑ ጃላ ዓይነቱ ዋሾ ምላስ ተመሳሳይ ሚዛኑ እኩል ነው። አንድም፥ በራስ መተማመን የሌለው፣ ክፉኛ የአቅም ማነስ የሚታይበት፣ ለቦታው የማይመጥን ሰው አፉ ሲከፍት ጥረቱ ሁሉ ጌታው ማስደስትና በጌታው ፊት ሞገስና ተቀባይነት ማግኘት እያሰበ ስለ ሚናገር አፉ ሲከፍት ከጌታው አይተናነስም፤ ሲቀደድም ድጋሜ ላለመሰፋት ነው የሚቀደደው።

 

Videos From Around The World

እንግዲህ፥ ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ የውሸት ፋብሪካ ግለሰብ አደገኛ የሚያደገው ታድያ ዋሾ ምላሱ የሚፈጥረውና የሚፈለፍለው ዛምቢ ዜጋ (Zambie) በቁጥር ስፍር ቁጥር የሌለው መሆኑ ነው። መጽሐፍ፥ ምስለ ጠዋይ ትጠዊ እንዲል ውሸት እንደ ወረርሽን የመጋባት አቅም ያለው ነፍስን የሚያቀጭጭ አደገኛ ቫይረስ ነው። ለምሳሌ፥ በተፈበረከ ውሸትና በሀሰተኛ ክስ በትግራይ ላይ የፈጸመ ወረራና መንስኤው በተመለከተ ብዙሐኑ ኢትዮጵያውያን ብንጠይቅ ከዚህ ቀደም ይሰጡት የነበረ ምላሽ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ አፍ የሰሙት የተቀናጀ ሐሰተኛ ምስክርነት የተቀዳ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የኤርትራ ሰራዊት አልገባም ሲል ኢትዮጵያውያን የኤርትራ ሠራዊት አልገባም እያሉ ሽንጣቸው ገትረው ሲሞግቱ ነበር። ዐቢይ አህመድ ዓሊ አንድም ሰው አልገደልንም ሲል ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ የትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት ፕሮፓጋንዳ ነው እሉን ሲሳለቁ ነበር። አሁንም ቢሆን በተፈበረከ ውሸት የከፈተው ጦርነት በማስቀጠል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ ያለ አካል ቢኖር ውሸት እንደ ጀሪካ ተቆርቁሮለት በቃኝ የማያውቅና ሐሰት ሰምቶ የማይጠግብ ራሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሂቃን በሚጋግሩት ውሸት የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ደረጃ ህሊናው አጥቶና ጥሎ ለሞትና ለእልቂት ሽር-ብትን እያለ ያለበት ምክንያትም ሰው ኢትዮጵያዊነት በሚባል ክፉ መንፈስ ስለ ተሰለበ ነው። ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር፥ በኢትዮጵያዊነት ስም የሚፈጸም ማንኛውም ዓይነት ግፍና ወንጀል ኢትዮጵያዊነት በሚያቀነቅኑ ዜጎች (ምኒሊካውያን) ፊት ወንጀል ነው ተብሎ እንደማይታመንበትና እንዳይደለ ነው።

 

ውሸትና ሐሰት ኢትዮጵያዊነት ማንነት ተብሎ ለሚታወቀው የንጹሐን ደም መጠጣት የለመደ ምኒሊካዊ አሳስተሳሰብ በማስቀጠል ረገድ ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ ሁነኛውና ዋነኛው አሳላጭ መሳሪያዎች ብሎም ትጥቅና ስንቅ ናቸው። ኢትዮጵያን እንደ አገር በማድማት፣ ሰላምዋን ነስተው በመረበሽና በማወክ የሚታወቁ የአማራ ልሒቃን አፋቸው በከፈቱ ቁጥር፥ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው፣ ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው፣ ኢትዮጵያዊነት ቸርነት ነው፣ ኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ነው፣ ኢትዮጵያዊነት እንግዳ ተቀባይነት ነው፣ ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፣ ኢትዮጵያዊነት የአንድነታችን ዋልታና ማገር ነው እያሉ ያለ መቋረጥ ፕሮፓጋንዳቸው የሚነፉበት ምክንያት ሰዎቹ የፍቅር ሰዎች ሆነው ሳይሆን እንዲህ ያለ ቅጥፈት የሞላበት ሐሰትና ውሸት መዝራት የህልውናችን ምሰሶ ነው ብለው ስለሚያኑ ነው። የአማራ ልሒቃንና አጨብጫቢዎቻቸው ኢትዮጵያዊነት ማለት እያሉ የሚዘረዝሩት ድርሰት ሁሉ ውሸት ነው፤ አንድም እውነተኝነት የሌለው የመተትና የድግምት ቃል። ይህ ኢትዮጵያዊነት የሚባል የንጹሐን ዜጎች ደም የለመደ ክፉ መንፈስ ለማስቀጠል ታዲያ እንደዚህ ያለ ነጭ ውሸት በቀጣይነት ያለ ማቋረት መዋሸት ስላለባቸው ዛሬም ገድለው ወደ ገደል እየወረወሩንና በእሳት እያነደዱን ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው ይሉናል። አንድም፥ የውሸት ቋት የአማራ ልሒቃን ውሸታቸውና ምዋርታቸው ካቆሙ ኢትዮጵያዊነት የሚባል ጨፍላቂ ምኒልካዊ አስተሳሰብ ሊቀጥል አይችለም። ለምን? ምኒልካዊ ኢትዮጵያዊነት መቀጠል የሚችለው ውሸትና ሐሰት በቀጣይነት መነገር፣ መዘራትና መሰራጨት ስላለበት ነው። ይህ እንዴት እንደሚሰራ በቀላሉ በምሳሌ ላስረዳ። ይኸውም፥ ታመመ ሲባል ሞተ፣ ተደናቀፈ ሲባል ተሰበረ፣ በፖሊስ ሰፈር ሲያልፍ ታየ ሲባል ታሰረ፣ የመኪና ጎማ ፈነዳ ሲባል ቦምብ ተፈነጀረ እየተባለ ተባራሪ ወሬዎች መቀበልና መቀባበል እንደ ባህል አድርጎ መኖር በጥቂቱ ነው። ያልሆነ ሆነ፣ ያልተደረገ ተደረገ፣ ያላዩት አየን፣ ያልሰሙት ሰማን እያሉ ጻፍና ማውራት ጀብድነት፥ ከዚህም አልፎ ዜግነታዊ ግዴታ የመወጣት ያህል የሚበረታታ ተግባር የሆነበት ምክንያት አሁንም ኢትዮጵያዊነት በውሸትና በሐሰት የማስቀጠል አጀንዳ አካል ነው። በርግጥ፥ ኢትዮጵያዊነት የምታቀነቅን ነፍስና የኢትዮጵያ ሰማይ የተቆጣጠረ የውሸት መንፈስ ሰው በቃላት ጽፎ የሚገልጸው ነገር አይደለም።

 

  ዲፕሎማቱ አሜሪካና አውሮፓ ቁጭ ብሎ ዓይኑን በጨው አጥጦ ይዋሻል፤

  የብሔር አስተዋጽዖ ሊኖር ይገባል በሚል እሳቤ በምርኮ ከተሰበሰቡ መካከል ተመርጠው ለጀነራልነት ማዕረግ የበቁ የሰራዊት አለቆች ሲዋሹ እግዚኦ ነው፤

  እንደ ነገሩ ስልጣን የተቆጣጠጡ የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት አፋቸው ሲከፍቱ ውሸታቸው የመቃብር ሽታ ያስንቃል፤

  ዳኛው የፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ይዋሻል፤

  ጋዜጠኛው በሺዎች ፊት ቆሞና ተቀምጦ ደረቱን ገልብጦ ይቀደዳል፤

  ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንድሪስና ሼኮቻቸው በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ወገባቸው ታጥቆው ሲዋሹ አላህ ፍቅር ነው የሚባለው ነገር ቀልድ ነው ያስብላል፤

  ጳጳሳቱ ለሰው ልጆች ኃጢአት መድኃኔ-ዓለም የተሰቀለበት ነው ተብሎ የሚታመንበት መስቀል በእጃቸው ጨብጠውና አንጋታቸው ላይ አንጠልጥለው ኢትዮጵያዊነት የሚባል ክፉ መንፈስ አስምጧቸው በእግዚአብሔር ስም በጠራራ ጸሐይ ሲዋሹ አይደለም ሰው እግዚአብሔር ራሱ ጆሮው እንደሚደፍን ነው፤

  እልፍ ያሉ የፕሮቴስታን መሪዎችና ሰባኪዎች በስብከትና በትንቢት ሰበብ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ተናገረኝ፣ ገለጠልኝ፣ እያሉ በእግዚአብሔር ስም ሲዋሹና ሲቀጥፉ የእግዚአብሔር ስም በአደባባይ ሲያሰድቡና ሲያጎድፉ ማየት የተለመደ ሆኗል፤

  ባለ ሃብቱ ዋሾችን በገንዘቡ እየመለመለ ማሰማራቱ ሳያንስ በአፉ ሲዋሽ አይጣል ነው፤

  ምሁራን በመረጃ ይዋሻሉ፥ ለማሳጠር ያህል ይህ የአፈ-ህጻን የዐቢይ አህመድ ዓሊና ፍርፋሬ ለቃሚዎች የአማራ ልሒቃን በጠራራ ጸሐይ ዓይንህን በጨው አጥበህ የመዋሸትና የመቅጠፍ መንፈስ ያልተጋባበት ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅን ሰው ፈልጎ ማግኘት በእውነቱ ነገር ብርቅ ነው። የሚያሳዝነውና የሚያሳስበው ሃይማኖት ያለውም የሌለውም ሁሉ አመጻን በመቃወም ከእውነት ጎን ሊቆሙ ቀርቶ፥ እውነቱ ምንድ ነው? ብለው እውነት የመፈለግ ሆነ የማወቅ ፍላጎት ፈጽሞ የሌላቸው ሰዎች መሆናቸው ነው።

 

በአሁን ሰዓት፥ ጳጳሳቱና ሙፍቲው፣ ዳኛውና ጋዜጠኛው ጨምሮ ለሁሉም የሚሳሳባቸው ያለም እውነቱ ምንድ ነው? እውነት የት ነው ያለችው? ከማን ጋር ነው ያለችው? በማለት በቅን ልብና በእውቀት በሚደረገው ጥናትና ምርምር ጥረትና ፍለጋ የምትገኝ ሐቅ ፈልፍሎ ማውጣት፣ ማወቅና ማሳወቅ ሳይሆን የሚያሳስባቸው ያለ የንጹሐን ደም የለመደ ኢትዮጵያዊነት የሚባል የዛር መንፈስ ማለምለም እንዲሁም በኢትዮጵያዊነት ስም በትግራይ ህዝብ ላይ በግፍ የተፈጸመ ዘር የማጥፋት ወንጀል እንዴት ማድበስበስና ማጥፋት እንሚቻልና እንደሚገባ ነው ጭንቀታቸው። ፈጣሪ የሚያመልክም የማያመልክም ተቀላቅሎ እያሰማው ያለ ጩኸት፣ ግርግርና ትርምስ አግራሞት ጥሎብን፥ ውሸት በዚህ ደረጃ የኢትዮጵያ አየር ተቆጣጥሮ ፍጥረት ሁሉ ዋሾ የሆነበት፣ ኢትዮጵያውያን ለሞትና ለእልቂት በዚህ ልክ ያሰፈሰፉበት ምን የሚሉት ነፋስ በኢትዮጵያ ሰማያት ላይ ቢነፍስ ነው? ማለታችን አይቀርም። ሐቁ፥ ማግኔት ብረትን እንደሚስብ እንዲሁ ምኒሊካውያን ከውሸት ጋር ያላቸው ልዩ ፍቅርና ትስስር በዋናነት፥ የእኛ ነው፣ ማንነቴ ነው፣ ኩራቴ ነው፣ ክብሬ ነው የሚሉት ኢትዮጵያዊነት (ጨፍላቂ እምነትና አስተሳሰብ) ከውሸትና ከሐሰት ተለይቶ መኖር ስለ ማይችል ነው። ሌላው፥ ምኒሊካውያን ምኞታቸው ለማሳካት ሆነ ፍላጎታቸው ለማሟላት በስራ ሳይሆን በውሸትና በአሉባልታ ስለ ሚያምኑም ነው። በፖለቲከኞች የሚታየው አውሬነትና ህሊና ቢስነት በተመሳሳይ በሃይማኖት መሪዎች በባሰ መልኩ ያየንበት ምክንያትም ሃይማኖት ሽፋን እንጅ በሃይማኖት ወንበር ላይ ተቀመጠው የሃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች የሃይማኖት ሰዎች እንዳይደሉ ነው። በተረፈ፥ ኢትዮጵያዊነት ክቡር ማንነት የሚል ጉንጭ አልፋ መፈክር በማሰማትና በማስተጋባት የሚታወቁ ሰዎች የበከተ ምኒሊካዊ አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸው ይደግፍል፣ ያጠናክራል፣ ይጠቅመናል የሚሉት ነገር ሁሉ በመጠቀም ምኞታቸው ለማሳካት የማይሆኑት ነገር እንደሌለ ነው። ትንኝም ታክል በእጃቸው የገባ ሁሉ ማለትም ትንኝዋን ግመል አሳክለው፣ ነገሩን ከሚገባ በላይ ለጥጠው፣ አጋነው፣ ጨምረውና ጨማምረው የማውራትና የማስወራት የተመሰከረለት የውሸት ባህል የተጸናወታቸው ሰዎችም ናቸው። በጠላትነት የፈረጁት አካል ላይ ሲዘምቱም በተመሳሳይ መንገድ በሐሰተኛ ወሬና በአሉባልታ መልካም ስሙና ዝናውን የጥላሸት መቀባት፣ ማኮላሸትና ማሳጣት ተክነውበታል። በአጭሩ ምኒሊካዊ ኢትዮጵያዊነት አካፋን አካፋ ማንኪያን ማንኪያ ብሎ መጥራት ስለ ማይሆንላት ነውርም ስለሆነ አካፋን ማንኪያ ማንኪያን አካፋ እያለች ውሸትና ሐሰት እያራገበች፣ እያሰራጨችና እየበተነች መኖር ምርጫዋ ያደረገች ርካሽ ነፍስ ናት።

 

2.     ተሳዳቢና ተራጋሚ አንደበት፥

 

ስድብ፥ አንድ ቃል ጊዜና ሁኔታ ሳይጠብቅ፣ በዘፈቀደ፣ ሆነ ተብሎ አለ አግባብ የሚነገር፤ መሰረት የሌለው፣ ምክንያታዊነት የሚጎድልበት፣ ዒላማውን የሳተ ቃል ነው። እርግማን በተመሳሳይ ከአፍ በሚወጣ ቃል ሲሆን ግቡ በባለ-እንጀራህ ላይ ክፉ ነገር እንዲሆንበትና እንዲደርስበት፤ አንድም፥ ሆኖ ማየት የምትሻው ክፉ ነገር ሁሉ ማዥጎድጎድ ነው። በነገራችን ላይ፥ ተራጋሚ ሰው ዕድሉና አጋጣሚ ገጥሞትና አግኝቶ በአካል ያገኞት እንደሆነ እንደ ቅርጫ ስጋ አርባ አራት ቦታ እንደሚበልቶት ሊጠራጠሩ አይገባም። በሌላ አገላለጽ፥ ተራጋሚ ሆነ ተሳዳቢ ሰው አቅመ ደካማ ሰው እንደሆነ ማወቁ ጥሩ ነው። ተራጋሚና ተሳዳቢ ሰው፥ ነኝ ወይም አለኝ እያለ የሚመካበት ነገር አሳይና እኛም እንቀበልህ እንመንህ ተብሎ ዕድሉ ሲሰጠው የተሰጠው ዕድል ነኝ ወይም አለኝ የሚለው በተጨባጭ ከማሳየትና ከመግለጥ ይልቅ፥ እንደ ተልባና የእሳት አደጋ ከመንጣጣትና ከመጮህ ያለፈ ቁም-ነገር የማይገኝበት የምላስ አርበኛ ነው። የእነዚህ ሁለት ነገሮች (ስድብና እርግማን) ምንጭ የተመለከትን እንደሆነም ወደኋላ የምናነሳው ከቅናትና ከምቀኝነት የሚመነጭ ነው። የምላስ አርበኝነት ካነሳን ዘንዳ ግን፥

 

  ሽለላና ቀረርቶ ፉከራና ድንፋታ በማሰማት የሚደርስባቸው የሌለ፤

  እንደ ቢራቢሮ ሲለቀቁ ምድርን የሚሞሉ ሲያዙ ደግሞ እፍኝ የማይሞሉ፤

  በስርቆትና ባማስመሰል በተላበሱት የሰው ታሪክ ተሸፍነው ዛሬ ላይ የደረሱ፤

  ሐሰተኛ ምስክርነት በመስጠት፣ በውሸትና በሬ ወለደ አሉባልታ ገነው የሚታወቁ፤

  ጽንስ የሚያጨናግፍ መርዛም አሉባልተኛ ምላስ ባለቤቶች የሆኑ የአማራ ልሒቃን ማንሳታችንና መመልከታችን የግድ ነው።

 

የአማራ ልሒቃንና በጋዜጠኝነትና በአክትቭስትነት ስም ከጎንደር እስከ ለንደን ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን የመሸጉ አማራ የሰው ልክ ነው ብለው የሚያኑ ተለላዎች፣ አጨብጫቢዎችና ከበሮ መቺዎች አሉባልታ በማናፈስና የውሸት ወሬዎች በማሰራጨት ቀዳሚና ተከታይ የሌላቸው በካና ፍጥረቶች ናቸው። የአማራ ልሒቃንና ከበሮ መቺዎቻቸው ውሸትና አሉባልታ እንደ መቀነት ታጥቀው የተሰለፉበት ዋና ምክንያት መረዳት ታድያ አሁንም እጅግ አስፈላጊ ነው። የአማራ ልሒቃን በዘመናት መካከል ማድርግ የሚፈልጉትና የሚሽቱ (ሌላውን ረግጠውና አጉብጠው ኢትዮጵያን በብቸኝነት የመምራት ህልም) ማድረግ ባለመቻላቸው፥ ከዚህ የተነሳም ላለፉት ረጅም ዘመናት ከዕለት ወደ ዕለት እየተቦረቦረና እየደቀቀ የመጣ የተመታ በሽተኛ ሥነ ልቦናቸው በሂደት የማንነት ቀውስ ውስጥ እንደ ጨመራቸው ሰዎቹ በአሁን ሰዓት እያሰሙት ያለ የሞት ጣር ድምጽ መመልከት በቂ ከበቂም በላይ ማስረጃ ነው። ይህ እውነተኛ የአማራ ልሒቃን ነባራዊ ሁኔታ ማለትም የተቀጠቀጠ፣ የደቀቀና የወደቀ የእኔነት ሥነ ልቦና መመታቱ ብቻ ሳይሆን ተንኮታኩቶ መውደቁን በተለይ ትናንት ወላሞ ጋላ ሻንቅላ እያሉ ሲያጋፉት፣ ሲያጣድፉት፣ ሲያቃልሉ፣ ሲሳለቁበትና ሲመጻደቁበት የኖሩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ዘንድ ጉዳቸው ገሃድ እንዳወጣና እንዳይገለጥባቸው ስለሚፈልጉ ነው።

 

የአማራ ልሂቃን ከትግራይ ጋር የሚደረግ ጦርነት የህልውና ጦርነት ነው ያሉበትና የሚሉበት ውስጠ ወይራ (ዋና ምክንያት)፥ ከአማራ ህዝብ ጋር ጸብ ያለው ትግራዋይ ኖሮ ሳይሆን በአማራ ህዝብ መነገድ የለመዱ የአማራ ልሒቃን፥ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሙሉ አሰልፈው ትግራይን ማሸነፍ ካልቻሉና ያሰቡት ሳያሳኩ ቀርተው የትግራይ ህዝብ ድጋሜ በሁለት እግሩ የቆመ እንደሆነ፤ ኢትዮጵያን በአማራ የበላይነት (ባህልና ቋንቋ) ለመጠቅለል በኢትዮጵያዊነት፣ በሉዓላዊነት፣ በአንድነትና በፍቅር ስምና ሽፋን የምንሰራው ፕሮፓጋንዳ በሽንፈታችን ማግስት ውሃ ይበላዋል፣ የአባይ ወንዝ ይዞት ይሄዳል! የሚል የማይቀርላቸው ስጋት ስለ ወረራቸው ነው። ልብ ይበሉ፥ የአማራ ልሒቃን ህልውና የሚሉት ያለ በውሸት የገነቡት ለዘመናት የነገዱበት ሐሰተኛ ክብራቸው ማለት እንደሆነ ሊገባን ይገባል። ለአማራ ልሂቃን፣ ምኒሊካዊትና ደርጋዊት ኢትዮጵያ የሚናፍቁና ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ ደጋፊዎቻቸው፥ ቀደም ሲል ከተመለከትነው በላይ እጅግ ያስጨንቃቸውና የሌሊት እንቅልፍ የነሳቸው ሌላ የማይቀርላቸው ስጋትም አላቸው። ይኸውም፥ ህልማችን ሳይሰምርልን ቀርቶ ትግራይ ያንሰራራች እንደሆነ ነገ ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር እኩል እንቆጠራለን ነው። ኢትዮጵያን ሰጥ ለጥ አድርገን ለመግዛት የተመረጥን ስዩማነ እግዚአብሔር የአፋርና የሶማሌ፣ የሲዳማና የሐረሬ፣ የከፋ ሸኪሶና የስልጤ መሳቂያ መሳለቂያ እንሆናለን፣ ብሔር ብሔረሰቦቹ ይነቃሉ እኛ የአማራ ልሂቃንም እንዋረዳለን በሚል የማይቀርላቸው ስጋት ክፉኛ ስለ ተዋጡ ነው። ከዚህ የተንሳም፥ ኢትዮጵያ በተመለከተ ትንፍሽ ለሚልና ጥያቄ አለኝ ብሎ እጁን ለሚያወጣ ሰው የአማራ ልሒቃንና ደጋፊዎቻቸው ትዕግስት የሌላቸው።

 

እኔ ትግራዋይነት ማንነት ነው ብዬ ሃሳቤን በየትኛውም መድረክ የመግለጽ፣ የማስተማርና የማስረዳት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ማንነት ነው ብሎ ሊያስረዳ የሚሞክር አንድ ባለ አእምሮ ሰው ከተገኘ በተመሳሳይ መንገድ በስርዓት የማዳመጥ ችግር የለብኝ። በአንጻሩ፥ ሰዎቹ አይደለም ትግራይዋይነት ማንነት ነው የሚለው ጭብጥ ላይ መሰረት ያደረገ የእኔ እምነትና አቋም በትዕግስት ሊያዳምጡ ቀርቶ ኢትዮጵያዊነት ማንነት ነው የሚሉት ጭብጥ ላይ ያልተመሰረተ ዙሩው አስተሳሰብ ለደቂቃ ሳይሳደቡና ሳይራገሙ ተረጋግተው ሃሳብቸው መግለጸ አይችሉም። ለምን? አስተሳሰባቸውና ኑሯቸው የቀረጸ ኢትዮጵያዊነት የሚባል ክፉ መንፈስ ምክንያታውያን እንዲሆኑ ስለ ማይፈቅድላቸው። ከዚህ የተነሳም፥ ጥያቄ ያነሳ ሁሉ ዝም ለማሰኘትና ለማሸማቀቅ የስድብና የእርግማን መዓት ለማውረድና ለማዥጎድጎድ የተፈጥሮ ነፋስ የማይቀድማቸው። ኢትዮጵያዊነት ማንነት ነው እያለ ሲዘፍን የሚውል ኢትዮጵያዊነት ማንነት ለመሆኑ አስረዳ ዕድሉ ሲሰጠው ምላሱ መርዛም ምላሱ ወልውሎ ዘራፍ የሚለው እወቀት ያላለፈበትና ከእውቀት የጸዳ ባዶ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊነት ማንነት ነው ብለው የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችና ቡድኖች አመክንዮ ሲሰሙ የሚያስጮሃቸውና የሚያጓራቸው ሌላው ምክንያት ማንነት ማለት ይህ ነው ተብሎ በዝርዝር የሚቀርበው ምክንያትና ጭብጥ ሐሰተኝነታቸው ስለ ሚገልጥበታቸውና ስለ ሚያራቁታቸው ነው። በተረፈ፥ ጨፍላቂ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ የአማራ ልሒቃንና ደጋፊዎቻቸው ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጅ ማንነት አይደለም ሊሆንም አይችልም የሚል ሐቅ ሲሰሙ ጨርቃቸው አስጥሎ የሚያስጮሃቸውና መርዛም ምላሳቸው ስለው ዘራፍ የሚያስብላቸው በእውነቱ ነገር ሰዎቹ ስለ ሰላምና ስለ አንደነት ግድ የሚላቸው መልካም አሳቢና አድራጊ ዜጎች ስለሆኑ ሳይሆን ሰዎቹ የለየላቸው አሳመሳዮችና ግዝብዞች ስለሆኑ ነው።

 

3.     አስመሳይና ግብዝ ማንነት፥

 

አስመሳይነትና ግብዝነት ሁለቱም የሌለህን እንዳለህ ያልሆንከውን ሆነህ ለመቅረብ የሚደረጉ ጥረቶችና ሜክአፖች በመሆናቸው በመጠኑም ቢሆን ተመሳሳይና ተወራራሽ የሚመስሉ ቃላት ቢሆንም ማስመሰል ብዙውን ጊዜ በተራው ማህበረሰብ የሚንጸባረቅ የአለመብሰል፣ የብልጣ ብልጥነት፣ አንዳንዴም በክፋትና በተንኮል የታጀበ የማታለል ጸባይ ሲሆን ግብዝነት ግን ይህን የመስመሰል ጸባይ ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ በከፍተኛ የተጽዕኖ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ለጥቆም በተቋም ደረጃ የተለመደ አሰራርና ባህል ሆኖ የሚታይና የሚንጸባረቅ ክፉና አደገኛ ሰይጣናዊ ባህሪይ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚባል ምኒሊካዊ ዝሩው እምነትና አስተሳሰብ የሚያቀነቅኑ ዜጎችና ቡድን ታድያ በባህሪያቸው ከማስመሰል ያለፈ ግብዝነት የተጸናወታቸው ናቸው። በአጭር አባባል፥ ምኒሊካዊ ኢትዮጵያዊነት ግዝብነት ነው። ወደኋላ ተመልሰን ታሪክ ማውሳትና መምዘዝ ሳያስፈልገን ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራትና መንግስታት ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ላይ የተፈጸመችው ወረራና ይህን ተከትሎም በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሰችው ግፍና በደል ጋር በተያያዘ የሰው ተፈጥሮ የሌላቸው ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ኃይማኖት አልባ ዜጎች አቋምና ምላሽ መመልከት በቂ ነው።

 

  ኤርትራ ከ40 በላይ ክፍለ ጦሮች አስከትላ በመምጣት የትግራይ ህዝብ በጠራራ ጸሐይ ስትጨፈጭፍ ሀብትና ንብረቱን ስትዘርፍና ስታወድም፥ አንድነት፣ ፍቅር፣ ሉዓላዊነት! እያሉ በመዝፈን የሚታወቁ የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞች ኤርትራና ሶማሊያ ለምን? ይገባሉ በማለት ለሚዘፍኑለት ሉዓላዊነት ዘብ አልቆሙም እንደውም፥ ሉዓላዊነት ለጊዜው እንርሳው ነበር ያሉት። አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ኤርትራ የዋለችን ውለታ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል ሲል የሰጠው ቃል በፓርላማው ፊት ቀርቦ ነው። አሁንም ግን፥ ኢትዮጵያውን ይህ ሲባል እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ራሳቸው ለማጽናናት መኮሩ እንጅ፥ ይህ ሰው በአገር ክህደት መከሰስ አለበት በማለት ድምጹን ያሰማ ሰው የለም። ለምን? ኢሳይያስ አፈወርቂ የትግራይ ህዝብ ዘር ማንዘሩን ቢያጠፋ፣ ከተሞቹንም ቢያወድም ምን ችግር አለበት?! ብሎ ማመን፣ በንጹሐን ዜጎች ላይ ግፍ ሲፈጸም ሰምተህና አይተህ እንዳልሰማህና እንዳላየህ ማሳለፍ ኢትዮጵያዊ ግዴታህ መወጣት ነው! ተብሎ ስለ ሚታመን ነው።

 

  የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ በኩል ወደ ትግራይ መግባት ለኢትዮጵያውያን የወያነ ፕሮፓጋንዳ ነበር። እውነት ትመነምናለች እንጅ አትበጠስም እንደሚባለው ግን፥ የተባበሩ መንግስታት በባደረገው ጥናት መሰረት የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ትግራይ መግባታቸው ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊቶች በአክሱም ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተሳታፊዎች እንደ ነበሩ ጭምር በተጨባጭ ሲያረጋግጥ ግን ኢትዮጵያውያን የትግራይ ህዝብ ለማንበርከክና ለማጥፋት ሌላም ቢያደርጉ የሚጸጸቱ ዜጎች አይደሉምና መርቀው የሸኙት ሰራዊት ከሰው አገር ሰራዊት ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ በጋራ የፈጸሙት ወንጀል በመረጃና በማስረጃ ሲቀርብላቸው አምኖ ከእውነት ጎን ለመቆም የደፈረ ዜጋ የለም። ለምን? ኢትዮጵያዊነት እውነትን በመቅበር ሁሉም ደህና ነው እያሉ የውሸትና የማስመሰል ግብዝነትም የሞላበት ህይወት መኖር ነውና።

 

  ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ሰዎች ከሚሰሟቸው ተደጋጋሚ ሐሰተኛ ድርሰቶች መካከል አንዱ ኢትዮጵያዊ ለሉዓላዊነቱ አይደራደርም አገሩን አሳልፎ አይሰጥም የሚል ይጠቀሳል። ኢትዮጵያውያን፥ ትግራይ ለማውደምና የትግራይን ህዝብ ለማጽዳት በዕቅድና በዓላማ የተፈጸመ ወረራ የሉዓላዊነት ጦርነት ነው እያሉ ሲያፏጩ ሱዳን በአማራ በኩል ሃያ አምስት ሺህ ሄክታር የኢትዮጵያ ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን ሰራዊት አስረክበው ነው። የሱዳን ሠራዊት የአማራ ገበሬ በማፈናቀል መሬቱ የእኔ መሬት ብሎ በጉልበቱ ገንዘቡ ሲያደርግ ሉዓላዊነታችን ተደፈረ ብሎ ድምጹን ያሰማ ኢትዮጵያዊ በኩራዝ ተፈልጎ አይገኝም። እንደውም በአንጻሩ፥ የትግራይ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው ተብሎ አዋጅ ሲነገር የኢትዮጵያ መሬት ወራ የያዘችው ባዕድ አገር ደግሞ የሱዳን ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው ተባለ። ለምን? ምኒሊካዊ ኢትዮጵያዊነት ከእውነታ ጋር መፋታት ማለት ነውና።

  የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊት እንዲሁም ኢንተርሃምዌ የአማራ ታጣቂና ሚኒሻ እንደ ሰዶምና ገሞራ የትግራይ ሴቶቻችና እናቶቻች ለሰው አእምሮ በሚከብድ ሁኔታ ደፍረውና አስነውረው ሲያበቁ፣ የትግራይ ሴቶች የተደፈሩት በወንዶች ነው ሲባል ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው የሚል ዘፈን በመዝፈን የሚታወቀው ህዝብ ከመቀመጫው ተነስቶ አንጨብጭቧል። የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሌያ ሰራዊት በአክሱም ከተማ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች ህጻናትና ሽማግሌዎች በጅምላ መጨፍጨፋቸው ዓለም በማስረጃ አስደግፋ የህግ ያለህ ስትል ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው፣ ደግነት ነው የሚል ዜማ በማቀንቀን የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን አሁንም፥ ምን ታካብዳላቹ? አሉን። እንደነ ደብረ ዳሞ የመሳሰሉ ጥንታውያን ገዳማትና ሌሎች አብያተ ክርስትያናት በታንክና በመትረየስ ሲፈራርሱ አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፥ የተዋህዶ ሰማዕት ነኝ የሚል ቲሸርት ለብሶ የሚፎክር ስመ ክርስትያን ኢትዮጵያዊ እምነቴ ተነካ ብሎ ድምጹን ለማሰማት አልሞከረም። ንጹሐን ዜጎች በተገኙበት ስፍራና ቦታ ሁሉ በጅምላ ሲረሸኑ፣ ተገድለው ወደ ገደል ሲወረወሩና በእሳት ሲቃጠሉ በዓይኑ እያየ አሁን ይበቃል ያለ ኢትዮጵያዊ የለም። ለምን? ኢትዮጵያዊነት ማለት እንደ ሰው ማሰብ ማቆምና ከሰውነት ተርታ ወጥቶ የአውሬነት መንጋ መቀላቀል ነውና።

 

  ከጥይት ያለመለጠ ህዝብ በርሃብና በመድኃኒት እጦት ፈጽሞ እንዲያልቅና እንዲረግፍ ዙሪያ መለሽ ታጥሮ በሚሰቃይበት ወቅት የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ነን፣ የእግዚአብሔር ተጠሪዎችና ወኪሎች ነን የሚሉ የሃይማኖት መሪዎችና ጳጳሳት ጨምሮ ጦርነቱን ለማሸነፍ እርዳታን መቆለፍ ለማለት የደፈሩ በኢትዮጵያዊነት ስም ነው። ለምን? ኢትዮጵያውነት ሲፋቅ፥ ምድራዊ፣ አጋንንታዊና ሰይጣናዊ አስተሳሰብና እምነት ስለሆነ ነው።

 

4.    ምዋርተኝነት፣ ቅናትና ምቀኝነት

 

በቁ. 2 ላይ በሰፋት እንደ ተመለከትነው ሻል ብሎ የተገኘ ሰው ጠልፎ ለመጣል፣ ያልደረሰብህ ሰውና ህዝብ ምክንያት ተፈልጎ መድረስ፣ ማዋረድና ማኮላሸት በምኒሊካውያን ዘንድ የተለመደ የዕለት ዕለት ተግባር ነው። ሰው በሃሳብ ሞግተው መርታትና ማሸነፍ ሲያቅታቸው፣ ሳይሆንላቸው ሲቀር ወደ ስድብና ማንጓጠጥ መግባት የሚኮሩበት ሞያና ኑሮራቸው ነው። በርግጥ፥ የሃሳብ ድርቅት ያለው ግለሰብና ቡድን ሃሳብ ይዞ የመጣን ሰው በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ በሃሳቡ ባለቤት ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ውርጅብኝ ማዥጎድጎድ፣ የስድብ ናዳና የጭቃ ዶፍ ማውረድ ብሎም መዛትና ማስፈራራት የኢትዮጵያዊነት ግዴታ መወጣት ነው። ኢትዮጵያዊነት ክቡር ማንነት እያለ በሃሳብ የማይመስለው ሰውና ህዝብ ክብር ሲያጎድፍና ሲያቆሽሽ ጸሐይ የምትጠልቅበት ቡድን በእውነቱ ነገር ከስድብና ከዋልጌነት ውጭ ጠብ የሚል እውቀት የማይገኝበት የሰላቢዎች ካምፕ ለመሆኑም የታወቀ ነው። ይህ ሐሰተኛ ምስክርነት በመስጠትና በውሸት የተካነ ማህበረሰብ ሃሳቤን አልተቀበለም በሚለው ሰውና ህዝብ ምቀኝነቱንና ምዋርተኝነቱ የሚገልጸው በምን ዓይነት መንገድ ነው? እንል ይሆናል። እንደሚከተለው አብራራለሁ።

 

የቅናት ምንጭ በራስ አለ መተማመን፣ ባለህ ነገር አለ መርካት፣ ራስህን ከሌሎች ጋር በማነጻጸርና በማወዳደር የሚጸነስ ጤናማ ያልሆነ ተመስጦ ሲሆን ሃሳቡ ወደ ድርጊት ሲመጣ ደግሞ ምዋርት ይባላል። ምዋርት፥ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ የእርግማን እኩያ ሲሆን አሉታዊ፣ የአመጽ ቃልም ነው። ሰው በሌላ ሰው ላይ የሚናገረው ክፉ ምኞት የሚገልጹ ቃላት ጨምሮ በራሱ ላይ የሚናገረው አሉታዊ ቃልም ምዋርት ነው። ምዋርት የአመጽ ቃል ነው ሲባል ሩቅ መሄድ ሳያስፈልገን የቅርቡ ምሳሌ እንመልከት። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አገኘሁ ተሻገር በትግራይ ላይ የክተት ጦርነት ባወጀባቸው በርካታ አጋጣሚዎች መካከል አንድ ጊዜ የትግራይ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው ማለቱን ይታወሳል። አገኘሁ ተሻገር እያደረገው ያለ ስራ በጥንቃቄ እየተመለከትን እንደሆነ ይህ በስልጣን ቦታ ላይ የተቀመጠ ግለሰብ በትግራይ ህዝብ ላይ ያለው ጥላቻ የመንግስት መድረክ በመጠቀም ህዝብን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ አጀንዳው ለማስፈጸም የሄደው ርቀት እንመለከታለን። የትግራይ ህዝብ ህልውና የሚከነክነው አገኘሁ ተሻገር ብቻውን ብድግ ብሎ ተነስቶ ትግራይ ሊወጋ እንደማይችል አሳምሮ ያውቃል። በተመሳሳይ፥ የልቡን ሃሳብና መሻት በኢትዮጵያዊነት፣ በአንድነትና በሉዓላዊነት ስምና ሽፋን የትግራይ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው በማለት ሐሰተኛ ምስክርነት በመስጠትና ውሸትን በማሰራጨት፣ የልቡን ሃሳብ በሰዎች ልብ ላይ እንዲገባና እንዲሰርጽ፣ ተካፋችም እንዲሆኑ በማድረግ ሰዎች ብረት እንዲያነሱና ደም እንዲፋሰሱ ማድረግ እንደሚችል በመረዳቱ ማድረግ አለብኝ ብሎ ያመነበት ሰይጣናዊ ስራ ዓይኑን ሳያሽ አድርጎታል።

 

ሌላው፥ ሰዎች በራስ መተማመን ከሌላቸው ማለትም ባላቸው ነገር የማይረኩ ከሆነ፣ ራሳቸውን የማይቀበሉና የሚገልጻቸው ነገር ወደውና ፈቅደው የመቀበል ችግር ያላቸው እንደሆነ የሚመኙት ሰውና ህዝብ ለመምሰል ሁለ መናቸው የሚሰመሩት መሆን የሚመኙት ግለሰብና ህዝብ ላይ ይሆናል። ማንነቱ የማይቀበል፣ በማንነቱ ሙላት የማይሰማው፣ ጎደሎነት የሚሰማው፣ እርካታ የራቀበትና የሌለው ሰው፥ ሌሎች ለመሆንና ለመመሰል ሲቋምጥና ሲመኝ የሚያረግዘው ጤናማ ያልሆነ ሃሳብ ቅናት ተብሎ የሚታወቅ ነገር ሲሆን፥ ቀደም ሲል እንደተገለጸው የተረገዘው ቅናት ሲያዋልድ ደግሞ ሟሟረት ይጀምራል። ለምሳሌ፥ በጓደኛዋ የዓይን ጥርስና ፊት ውበትና ማማር የምትቀና ከሆነች፥ አሲድ ይድፋብሽ፣ ጥርሽ ያርግፈው፣ ዓይንሽ ይጥፋ ትላለች። የሰው ጉብዝናና ቁመና እያየ እርር የሚል ከሆነ፥ ከፎቅ ይጣልህ፣ መኪና ይግጭህ፣ ያሰንክልህ ይላል። በጉረቤቱ የሚቀና ሰው ከሆነ፥ መድኃኔ-ዓለም አይቅናህ፣ ይድፋህ፣ ይቀንጥስህ፣ ይቦቅስህ ይላል። የትግራይ ህዝብ ህልውና፣ የህዝቡ ጀግንነትና ታታሪነት እንቅልፍ የሚያሳጣቸውና የማይዋጥላቸው እንደ ኢትዮጵያ (የአማራ ልሂቃን) ኤርትራ ቅናትና ምቀኝነት ያሳበዳቸው ዓይነቱ ደግሞ ፊታቸው ወደ ትግራይ አዙሮው በቀንም በሌሊት ትኩስ የመቃብር አፈር አየበተኑ፥ ያጥፋህ፣ አይለፍልህ፣ አመድ ያድርግህ፣ ውድቀትህ ሞትህና እልቂትህ ያሳየን የሚሉ ምዋርት ቃሎች ከብዙ በጥቂቱ ነው። በሰሜን በደቡብ በምዕራብና በምስራቅ በመዝመት ትግራይ አውድመው ሲያበቁ በኃይል ተመንግለው ከወጡ በኋላ፥ ከትግራይ የወጣነው ግባችን ስላሳካን ነው፤ ወደ ትግራይ የሄድነው እዛው ለመቀመጥ አልነበረም፤ ይልቁን፥ እኛ እየታመስን እነሱ ለምን በሰላም ይቀመጣሉ፣ እኛ ቁልቁል እየወረድን እነሱ ለምን ያድጋሉ ይለወጣሉ በማለት ነበር የሄድነው፥ ወደ ትግራይ ስንሄድና ለቀን ስንወጣ ደግሞ ትግራይ በቀድሞ ውበትዋ በመተው አይደለም ስርዓት አልበኝነት የነገሰባት ቦታ አድርገን ነው የወጣነው፤ ዛሬ ትግራይ በቀድሞ ውበትዋና የፖለቲካ ስበትዋ የሚያውቃት ሰው የለም፣ አበላሽተንና አጠልሽተን በሻሻ አድርገናት ነው የወጣነው፤ ይህ ደግሞ የሚያስወቅስ ሳይሆን የሚያስመሰግን ሰራ ነው! የሚል የአፈ ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይፋዊ መግለጫ ልብ ይሏል። ይህ አረማዊ ተግባር ከምዋርተኝነት ያለፈ፥ ቅናት፣ ምቀኝነትና ጥላቻ የወለደው የአመጽ ስራ ለመፈጸሙ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በአንደበቱ የሰጠው ምስክርነት ነው። ሌላው፥

 

  ከምስረታዋ፥ ማለትም ከምንሊክ ወዲህ ባለው ዘመን ሁሉ የምድሪቱ እርግማን ሆነው አገርና ህዝብ ሲያምሱና ሲያተረማምሱ የመጡና ያሉ፤

  በራስ መተማመን ብሎ ነገር ያላለፈባቸው፤

  ዘመናቸው በሙሉ የሰው እንደተመኙ፤

  የሰው ዕድገትና መልካምነት የማይዋጥላቸው፤

  የሌላው ህዝብ መጎዳትና ማዘን ደስ የሚያሰኛቸውና የሚያስቦርቃቸው፤

  ሰርተው ከመለወጥ ይልቅ ሰርቶ የሚገባ ሰው ጠልፈው ለመጣል በሰው ደጃፍ ላይ የማይታጡ፤

  በሰው ጀርባና ትክሻ ላይ ታዝለውና ተፈናጠው ካልሆነ በቀር ራሳቸው ችለው መቆም ሆነ መቀመጥ ያልፈጠረባቸው፤

  ዛሬ በዚህ ዘመንም አገርና ህዝብ በውሬና በአሉባልታ በነፍጥና በዱላ መግዛት ይቻላል ብለው የሚያምኑ፤

  አዲስ ነገር በመቀበል፣ በመለወጥና ፈቀቅ በማለት ፈንታ በትዝታ መኖር የመረጡ መናኛ ናፋቂዎች የአማራ ልሒቃን አውራ ችግር እንግዲህ ቀደም ሲል በዝርዝር እንደ ተመለከትነው ቅናትና ምቀኝነት ያረገዘው ጥላቻ ነው። ጥላቻ ደግሞ በባህሪው በአእምሮ መፈወስ ካልሆነ በቀር ክኒን በመወጣትና መርፌ በመወጋት የሚድን አይደለም።

 

የአማራ ልሒቃንና ከበሮ መቺዎቻቸው ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ህልውና በራሱ ራስ ምታታቸው ነው። ፈረንጆች እንዲህ ያለ ችግር Intersectionality ይሉታል። ልብ ይበሉ፥ እዚህ ላይ የችግሩ ምንጭ ትግራይ አይደለችም። ይልቁንም፥ የትግራይ ተፈጥሯዊና ሰማያዊ ሀብተ በረከት እየተመለከቱ በምኞት የነደዱ፣ የትግራይ ጥፋት የሚመኙ የአማራ ልሒቃን ናቸው። በአጭሩ፥ ትግራዋይ የሚባል ማንነት ብቻውን ለአማራ ልሒቃን ናይትሜር (Nightmare) ሆኖባቸዋል። የአፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ስልጣን መውጣት ተከትሎ የአማራ ልሒቃን ትግራይ ተዳክመዋል ራያም ወልቃይትም የራሳችን የምናደርግበት ሰዓት አሁን ነው ብለው ወታደር በገፍ መመልመልና ማሰልጠን የጀመሩ የአማራ ልሒቅን ናቸው። ከሱዳን ጋር መክረው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራና የሶማሊያ ቅጠረኛ ነፍሰ ገዳዮች፣ የኢምሬት ድሮን ይዘውና ጋብዘው ትግራይ ከካርታ ለመፋቅ የትግራይ ህዝብም ስመ ዝክሩ መታሰቢያ ላይኖረው ለመደምሰስ ትግራይን የወረሩና የትግራይ መሬት ውስጥ ዘልቀው በመግባት ህጻን ሽማግሌ ሳይሉ ህዝብን እንደ ህዝብ ያበሳበሱና የጨፈጨፉ፣ ሀብቱና ንብረቱን የዘረፉ፣ ከተሞቹን ያወደሙ ኃይማኖት አልባ የአማራ ልሒቃን ያሰማሯቸው ሚኒሻዎና ታጣቂዎች ናቸው። አሁን ችግር የሆነው ታድያ የልሒቃኑ ትግራይ ጠል ፖለቲካ በኢትዮጵያዊነት፣ በአንድነት፣ በፍቅርና በሉዓላዊነት ስም በመሰበኩ ኢትዮጵያዊነት በሚያቀነቅኑ ዜጎች ህይወት ውስጥ ዘለቆ መገባቱ ነው። ጦርነቱ በቀጣይነት በማቃጣጠል ያለም በኢትዮጵያዊነት ስም ቅናትና ምቀኝነት ያሰለፈው ሳይውቅ በስህተት እያወቀ በድፍረት ጦርነቱን በመደገፍ የቆመ ህዝብ ነው። ሰው ግን አመጽ፣ ጦርነት፣ ሞትና እልቂት ሲባል ዘወር ይላል እንጅ እንዴት ነው የሐሰትና የውሸት ሰለባ በመሆን ለሞትና ለእልቂት የሚሰለፈው? በማለት ጥያቄ ያነሱ እንደሆነ ንባቡን ይቀጥሉ።

5.     አመጽና በደል በመስራትና በመፈጸም ደስ መሰኘት፥

 

ሌላው ኢትዮጵያዊነት የሚባል ክፉ መንፈስ መታወቂያ፥ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም አመጽና በደል በመስራትና በመፈጸም ደስ መሰኘት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅን ሰው አልያም፥ እገሌ/እገሊት እኮ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፣ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው ተብሎ በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ በክብር ለመጠራት፥ መጀመሪያ በክፉ ወሬ፣ ቀጥሎ በቅናትና በምቀኝነት፣ ከዚያም በጥላቻ፣ ከፍ ሲል ደግሞ የሰው ሀብትና ንብረት ማውደምና የሰው ነፍስ ማጥፋት የሚጨምር በአመጽ ተግባራት ላይ መጠመቅና መሰለፍን ይጠይቃል። ክፉ ወሬን የማይቀበል፣ ቅናትና ምቀኝነት የሚጸየፍ፣ ጥላቻና አመጽ የሚቃወም ሰው በአሁን ሰዓት ራሱን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ አይጠራም። ምኒሊካዊ ኢትዮጵያውነት፥ አጋንንታዊ ላሜ-ቦራ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ከሰብአዊነት መውጣት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት አረማዊነት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት የክፉ መንፈስ መገለጫ ነው! ሲባል በምክንያት ነው። በተለይ በደርግ ዘመነ መንግስት ላልነበርና ነፍሳችን ለማናውቅ አዲስ ትውልድ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ስልጣን መውጣት ተከትሎ በተጨባጭ ያየነው ኢትዮጵያዊነት የወስልትናና የአመንዝራነት የጋጠ ወጥነትና የነፍሰ ገዳየነት መገለጫ ማንነት ነው።

 

  በዓይናችን ያየነው ኢትዮጵያዊነት ሰውን የሚያክል ፍጡር ገድሎ እንደ ቋንጣ እንጨት ላይ ማንጠልጠል ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት የሰውን ሬሳ እንደ ግንድ መጎተት ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ነፍስ በተለየው ሬሳ ላይ ቆሞ መሸለልና ቀርርቶ ማሰማት ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት የሰው ነፍስ እያጠፉ መዝፈንና መዝለል ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት በታላቅ ጭንቅና መከራ ባለፈች ነፍስ ዙሪያ ላይ ተሰብስቦ በደስታ መፈንጠዝና መቦረቅ ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ሰውን እንደ በግና እንደ ፍዬል በገመድ አስሮ ማረድ ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ሰውን እንደ ቆሎ በጥይት መቁላት ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ሰውን ገድሎ እንደ ልጣጭ ወደ ገደል መወርወር ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ሰውን በግፍ ገድሎ ወደ ወንዝ መጣል ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት ሰውን ገድሎ እንደ ቆሻሻ በእሳት ማቃጠል ነው፤

  ኢትዮጵያዊነት የስምንት ዓመት ህጻን ልጅ፣ የሰማኒያ ዓመት የዕድሜ ባለ ጸጋ፣ የካህን ሚስት፣ ዘመናቸው በሙሉ ከዓለም ተለይተው የኖሩ ባህታዊያን ሳይቀር እንደ ሰዶምና ጎመራ ለአስርና ለአስራ አምስት እየተፈራረቁ ማራከስና ማስነወር ነው። ይህን ሁሉ ለሰው አእምሮ የሚከብድ ሰቆቃ የተፈጸመው፣ የሆነውና የተደረገውም በኢትዮጵያዊነት ስም ነው። ይህ ሰይጣናዊ ድርጊት ባያደርገውም ያደረውን ደግፎ የቆመና ዝምታን የመረጠ ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር የራቀ የተረገመ ፍጥረት ነው።

 

ሌላው ሁሉ ትተን፥ ጽድቅና ኩነኔ እናውቃለን እንስተምራለን፣ ጽድቅና ቅድስናን የምትሰብክ የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ነን፣ የእግዚአብሔር ባለሟሎች ነን የሚሉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች፣ ሲኖዶስና ሊቃነ ጳጳሳት ፓስተሮችና ወንጌላውያን ይህ ሁሉ ሰይጣናዊ ግፍና በደል በንጹሐን ዜጎች ላይ መፈጸሙ ሲያዩና ሲሰሙ ለሚመጻደቁለት እምነት መቆም የተሳናቸው ደግ አደረጉ ማለታቸው እንደሆነ ልናውቅ ይገባል። እንደ ሰው ለማሰብ የታደለ፣ ሰብአዊነት የሚሰማው፣ ለደንቆሮው እግዚአብሔር ይሰማላታል ለዕውሩም እግዚአብሔር ያይለታል ብሎ የሚያምንና ሞራል ያለው ሰው፥ ለአንድ ያልበሰለ ሰው በስልጣን ላይ ማሰንበት ሲባል ይህ ሁሉ ግፍና በደል መንግስታዊ ውሸትና ቅጥፈት ሲያይ የእኔ ስም ከዚህ ማንነት ጋር እንዲጠራ ሆነ እንዲስተካከል አልፈቅድም! በማለት አመጻን በመቃወም ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጮክ ብሎ ቢቃወም ማን ይፈርድበታል? ዓለም በሁለት ዓይኗ ያየችውና የመሰከረችው ግፍና በደል እያየና እየሰማ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰው ሰውነቱ ምኑ ላይ ነው?

 

የክፉ ሰው መንገድና አሰራር ሁል ጊዜ፥ የአመጽ፣ የማስመሰል፣ የማታለል፣ የማጭበርበር፣ የማወናበድና የማምታታት መንገድ ነው። ክፉና አመጸኛ ሰው ክፉ ነኝ ብሎ ራሱን አይገልጥም፤ ሊያጠቃህና ሊጥልህ ሲያደባም እያፏጨ አይመጣብህም። እንደውም፥ ክፉ በፊታችን ሲቆምና ሲሻገር ማናችንም ልናስበውና ልንገምተው በማንችለው ሁኔታና መንገድ ራሱን ለውጦ፣ መልካምነት ድግነትና ተቆርቋሪነት የሚመስል ሐሰተኛ ማስክ አጥልቆና ቀለም ቀባብቶ ነው። በሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ 13 ቁጥር 6 ላይ የሚከተው ድንቅ ቃል እናነባለን፥ ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ በርያሱስ የሚሉትን ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ፤ እርሱም አስተዋይ ሰው ከሆነው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህም በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ፈለገ። ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው። ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ሲመለከተው፥ አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፥ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፥ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ። በዚያን ጊዜ አገረ ገዡ የተደረገው ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ ይላል።

 

በርያሱስ (በር-ያሰሱ) የስሙ ትርጓሜ፥ የኢየሱስ ልጅ ወይም የአዳኙ/የፈዋሹ ልጅ ማለት ነው። ይህ ሰው ምንም እንኳ ስሙ የኢየሱስ፣ የፈዋሹ/የአዳኙ ልጅ የተባለ የሚጠራ ሰው ቢሆንም ስራው ግን በንባቡ እንደ ተመለከትነው ወደ ኢየሱስ የሚመጡ ነፍሳት የሚያጨናግፍ፣ አሰናካይና እንቅፋት ሆኖ የሚከለክል ጠንቋይና ሐሰተኛ ሰው ነበር። የሚደንቀው፥ ይህ የኢየሱስ ልጅ ተብሎ የሚጠራ ሰው ንጉሡን ሳይቀር ማወናበድ የተቻለው እንዲህ ያለ ክፋትና አመጻ ይሰራል ብሎ የሚጠረጥር ሰው ነበር። ለምን? በርያሱስ ክፉ ስራው ሰው እንዳያውቅበት፣ እንዳይጠረጥረውና እንዳይደርስበት ሰይጣዊ ማንነቱ በሰማይና በምድር እጅግ በከበረ፣ ባማረና በተዋበ ስም ሸፍኖ የሚሰራ መሰሪ ሰው በመሆኑ ነበር። የኢየሱስ ልጅ ተብሎ የሚታወቅ ሰው አጋንንት ይጠራል፣ ከሙት መንፈስ ያወራል፣ ይጠነቁላል፣ ይመቃኛል፣ ያሟርታል ተብሎ ስለ ማይታሰባና ስለ ማይታመን ነው። በዚህ ሁሉ ህዝብ መካከል ግን የኢየሱስ ልጅ የሚል ትርጓሜ ያለው ስም ስለ ያዝክ ብቻ የማታልፈውና የማታጭበረብረው ሰው ነበር። ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ሲመለከተው፥ አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? አለው እንዲል። የኢየሱስ ልጅ ተብሎ የሚታወቅ ሰው የዲያብሎስ ልጅ የጽድቅም ሁሉ ጠላት ብሎ ሲጠራው እንግዲህ ያሳዮት። ጥያቄው፥ ዛሬ እኛ ከዚህ ንባብ የምንማረው ትምህርት ምንድ ነው? በእውነቱ ነገር ፈጣሪ ዓይነ ልቦናው ያበራለትና አእምሮው የከፈተለት ሰውና ህዝብ ካልሆነ በቀር፥ የአማራ ልሒቃን ሰውነታቸው በሰንሰለት እየገረፉና በእምባ እያጠቡ፣ እንደ እባብ አፈር እየቃሙ መሬት ለመሬት እየተንፏቀቁ፣ ጸጉራቸው እየነጩና ፊታቸው እየቧጨሩ፥ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት፣ ፍቅር፣ ሉዓላዊነት እያሉ ሲጩሁ፥ አይ ሿሿ ይሰሩኛል፣ ጠልፈው ይጥሉኛል፣ ያጎሳቁሉኛል፣ ባርያ አድርጎው ይዞው ፍርፋሬ ያስለቅሙኛል፣ ያጎብጡኛል፣ ያሳጡኛል፣ ያጠፉኛል ብሎ የሚጠረጥርና የሚያምን ሰው ሊኖር አይችልም። ደግነቱ የአማራ ልሒቃን አጭበርባሪና አዋናባጅ መንታ ማንነት ያልበራለት ፍጥረት ደጋፊዎቻቸው ብቻ ናቸው።

 

6.    የራስ ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበርና ለማርካት ሲባል ሐቅን መካድ፣ መደፍጠጥና ማጨናገፍ፥

 

ኢትዮጵያዊነት ተለይቶ የሚታወቅበት ሌላኛው መታወቂያ እውነት መካድና አለ መቀበል ነው። ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀንቅን ሰው የአማራ ልሒቃን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ሐሰተኛ ትርክትና ልበ ወለድ ድርሰት እየተቀበለ ከማስተጋባት ያለፈ፥ እውነቱ ምንድ ነው? ብሎ መጠየቅ፣ እውነት መፈለግ፣ እውነት መናገር፣ ለእውነት ማደርና መገዛት ብሎ ነገር በህልሙም አያስበውም። ሐቅና እውነት የሚባል ነገር ምንሊካዊ ዘንድ ስፍራም ቦታም የለውም። ለምንሊካውያን እውነት ኢትዮጵያዊነት የሚሉት ክፉ መንፈስ ነው። ለኢትዮጵያዊነት ሲባል የሚሰራ ሸፍጥ ይሁን ወንጀል ሁሉ ለምንሊካውያን ትክክል ነው። ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት ለሚያቀነቅኑ ሐቅ/እውነት የሚባል ነገር በጥቅሉ የእነሱ ጥቅምና ፍላጎት የሚያሟላና የሚያረካ እንደሆነ ብቻ ነው። ሌላው ቢቀር፥ ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ሰዎች እግዚአብሔር እውነት ነው ብለው ለመቀበልና ከእግዚአብሔር ጋር ለመስማማት መጀመሪያ እግዚአብሔር ራሱ ኢትዮጵያዊነት መቀበልና ከምንሊካውያን ጋር መስማማት ይጠበቅበታ። ኢትዮጵያውያን እውነት ነው ያሉትን እውነት ሐሰት ነው ያሉትን ሁሉ ደግሞ ሐሰት ነው ብሎ የማይቀበል እግዚአብሔር ለኢትዮጵያውያን ቀልድ ነው። በትግራይ መሬት የሰሩት ሰይጣናዊ ስራ አሳምረው የሚያውቁ ግን ደግሞ ለክስ ያመቻቸው ዘንድ የአብያተ ክርስትያናት ቆሮቅሮ እየነቀሉ ፎቶ ግራፍ በማንሳት ሌላ ጊዜ ደግሞ ትግራይ ውስጥ ያወደሙት ቤተ ክርስትያን በማሳየት ወያነ አፈረሰብን የሚለው ለባለ አእምሮ ሰው የማይመጥን ርካሽ ሸቀጥ ትተን፤ ግባ በለው እየተባለ ገብቶ በትግራይ አብያተ ክርስትያናት የተፈጸመ ግፍና ድብደባ አይደለም ተራ ምእመን መንበረ አጋንንት የሆነ ሲኖዶስና በዙሪያው ያሰባሰባቸው ምናምንቴ ሊቃነ ጳጳት ዝምታ የሚጠቀስ ነው።

 

በዘርፉ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ የሚታወቁ የስነ መለኮትና የስነ ባህሪይ ሊቃውን ይህን ዓይነቱ አዙሪት motivated reasoning ይሉታል። ይህን በምሳሌ ላስረዳ፥ መጀመሪያ፥ የኤርትራ ሠራዊት ወደ ትግራይ መግባት በተመለከተ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ውሸት ነው አሉ፤ ቀጥሎም፥ የኢትዮጵያ ወታደር በየትኛውም ዓለም በኩራዝ ተፈልጎ የማይገኝ ሰራዊት ነው፥ መቐለ እስክንገባ ድረስም አንድም ሰው አልገደልንም አሉን። ከቆይታ በኋላ ደግሞ የኤርትራ ሠራዊት ከጫፍ እስከ ጫፍ ትግራይ በመግባት በትግራይ ህዝብ ላይ ስላደረሰው ግፍና በደል ስለ ዘረፈው የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት በራሱ በአፈ ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሳይቀር በፓርላማው በሰጠው የእምነት ቃል የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ መግባቱ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሰራዊትና ከኢንተርሃምዌ የአማራ ሚሊሻና ታጣቂ በህብረት ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ውድመት እንዳደርሱ ምስክርነታቸው ሰጥቷል። ይህን ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለምን እውነቱ ይናገር፣ ይህ ሰው ለመንግስትነት የማይበቃ ቅሌታም ሰው ነው ሲሉ ተረባረቡበት። ለምን? ሰውየው አድበስብሶም ቢሆን ሐቁን ከመናገር ውጭ ሌላ አማራጭ አጥቶ የተናገረው ሐቅ ኢትዮጵያን መስማት የሚፈልጉት ሐቅ ስላይደለ ነው። አንድም፥ ኢትዮጵያዊነት ማዕከል አድርጎ የሚያጠነጥነው እውነትን በመሸጥና በማጠልሸት ከሚገኝ ምድራዊ፣ አጋንንታዊና ሰይጣናዊ ጥቅም ላይ ነውና። ንጹህ ህሊና ያላቸው ሰዎች በውሸትና በአሉባልታ በቅናት በምቀኝነት የተነከሩና የጠሰጠሱ ከምንሊካውያን ጋር የማይስማሙበት ምክንያትም ይህ ነው። አንድ ሰው ከምንሊካዊት ኢትዮጵያዊነት ሚያቀነቅን ሰው መስማማት የሚችለው በዋናነት ምንሊካውያን የሚምኑት እምነት ያለ አንዳች ጥያቄ ሳያላምጥ ሲቀበልና ሲያምን ብቻ ነው። በሌላ አገላለጽ፥ ሌላው ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊነት ከሚያቀነቅኑ ላሜ ቦራዎች ጋር በሰላም አብሮ መኖር የሚቻለው ምንሊካውያኑ የሚመርቁትን መመረቅ የሚረግሙትን መርገም፣ የተቀበሉን መቀበል የገፉትን መግፋት፣ የሾሙትን መሾም የሻሩትን መሻር፣ የወደዱትን መውደድ የጠሉትን ደግሞ መጥላት፣ ትክክል ነው ያሉትን ትክክል ነው ስህተት ነው ያሉን በተመሳሳይ ስህተት ነው ብሎ ማመንና መቀበል ሲችል ብቻ ነው። በተጨማሪም፥ ምንሊካዊነት ራስህን ችለህ መመላለስ፣ መኖር፣ መቆመና መቀመጥ አይፈቅድም። ለምን? ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት የትምክህተኛና ጨለምተኛ አስተሳሰብና እምነት ውጤት ነውና። መፍትሔው? ትምክህተኝነትና ጨለምተኝነት መስበርና መቅበር ነው።

 

7.     ትምክህተኛና ጨለምተኛ አስተሳሰብና እምነት፥

 

ለጊዜው የመጨረሻ ነጥባችን የሚሆነው የኢትዮጵያዊነት ሌላ መታወቂያ የሆነው ትምክህተኛና ጨለምተኛ አስተሳሰብና እምነት ነው። የትምክህተኝነትና የጨለምተኝነት ዘፍጥረት ጤናማ ያልሆነ እኔነት ስሜት ሲሆን፥ ሰዎች የሰው ልክ ነን የሚል ወፍ ዘራሽ እምነትና አስተሳሰብ ሲያዳብሩ፣ በዙሪያቸው ያለ ሁሉ ከእግራቸው መረገጫ በታች እንደሆነ ሲሰማቸው፣ የሚሰማቸው ስሜትና ሞቅታ ማመን ሲጀምሩና በሃሳብ ሲጸንሱት ትምክህተኝነት ሆነ ጨለምተኝነት ሁለመናቸው የሚቆጣጠር ጭንቁር ይሆናል። በቀጣይነት የሚቀሰቀሰው ሁከትና ግርግር፣ የማያባራ ትንኮሳ፣ የሰላምና መረጋጋት እጦት፣ ጥላቻ፣ አድሎና መገለል፣ ብሎም መለያየት በስንፍና በሃሳብ ተጸንሶ የተወለደ ትምክህተኝነትና ጨለምተኝነት ውጤቶች ናቸው። ትምክህተኝነትና ጨለምተኝነት፥ የጥላቻ፣ ሁከትና ግርግር ከዚህም አልፎ የጦርነት፣ የእልቂትና የደም መፋሰስ ምክንያት የሚሆንበት በዋናነት ትምክህተኛ፥ ከላይ ወደታች እንጅ ከታች ወደ ላይ የሚወጣ ማንኛውም ዓይነት ቅብብሎሽ ስለ ማይቀበልና በባህሪው አሳታፊም ስላደለ ነው።

 

  ትምክህተኛ፥ በእኩልነት አያምንም፤

  ትምክህተኛ፥ ባሪያ እንጅ እኩያ እንዲኖረው አይፈልግም፤

  ትምክህተኛ፥ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ሲል በራሱ ህዝብ ሳይቀር የሚቆምርና የሚነግድ ነፍሰ በላ ነው፤

  ትምክህተኛ ግለሰብና ቡድን፥ ወደ ውጭ እንጅ ወደ ራሱ ለማየት ያልታደለ አጉረምራሚ ነው፤

  ትምክህተኛ ግለሰብና ቡድን፥ እኔ ያልኩት ብቻ ይሆናል ከማለት በቀር በተሳትፎ አያምንም፤

  ትምክህተኛ ግለሰብና ቡድን፥ ሌሎችን አይቀበልም፤ ለህልውናቸውም እውቅና አይሰጥም፤

  ትምክህተኛ፥ የፍትሓዊነት ጥያቄ ሲነሳበት ራስ ምታትና ሆድ ቁርጠት የሚይዘው አምባገነን ነው፤

  ትምክህተኛ ለክስና ለዘለፋ ተኝቶ አያድርም፤ ሁልጊዜ አልቃሽና ከሳሽም ነው፤

  ትምክህተኛ፥ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አሮጌ ፋይል እያገላበጣ ሰው ማንጓጠጥና የጥላሸት መቀባት ልዩ መታወቂያው ነው፤

  ትምክተኞች፥ ስህተት መፈጸማቸው ሳያንስ መሳሳታቸው በተጨባጭ ከተረጋገጠና የፈጸሙት ነገር ስህተት መሆኑ ካወቁ በኋላም ቢሆን ተሳስተናል በማለት ስህተታቸው አምነው አይቀበሉም፤

  ትምክህተኞች፥ ቀደም ሲል በቁ. 1 ላይ እንደ ተመለከትነው ያለ ልክ የማጋነንና የመቀደድ ባህሪይ ያላቸውም ናቸው፤

  ትምክህተኞች፥ በባህሪያቸው የተሸነፉና ሃሳብ አልባ ስለሆኑ ትንሽ የተነኩ፣ የተንሸራተቱና የተላጡ ሆኖ ሲታያቸውና ሲመስላቸው እንደተጠቁ በማስመሰል መጮህ፣ ማልቀስና ሙሾ ማውጣት ያውቁበታል።

 

ጨለምተኝነት በተመለከተ ብዙ ማለት ሳያስፈልገን ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ፍርፋሬ ለቃሚዎች የአማራ ልሒቃን ነባራዊ ሁኔታ መመልከት ብቻውን በቂ ነው። ጨለምተኛ ግለሰብና ቡድን በዋናነት መስማትና ማየት የሚፈልገው ብቻ ካልሆነ በቀር መሬት ላይ ያለው ሐቅ ዓይኑን ከፍቶ የማየት ሆነ የመስማት ፍላጎት የሌለው ግለሰብ/ቡድን ነው። ጨለምተኝነት ከራሱ የሚመነጭ የበከተ አስተሳሰብ ውጭ ሌላ አማራጭ ሃሳብ አይቀበልም። ጨለምተኞች፥ በጭፍን የሚደግፋቸውን ወዳጅ በምክንያት የሚሞግታቸውን ጠላት በማለት በፍረጃና በውንጀላ ፖለቲካ የሚያምኑና በዚህ ክፉ ድርጊትም የተካኑ ናቸው። እንግዲህ ይህ አባባል ኢትዮጵያዊነት እየተባለ በሚራገበው ሐሰተኛ ማንነት ሚዛን የተመለከትነው እንደሆነ የዚህ እምነትና አስተሳሰብ አራማጆች ክፉኛ በትምክህት የተለከፉ ሰዎች ለመሆናቸው የሚያከራክር አይደለም። የጨለምተኝነት መለኪያ ሚዛን እንዲሁ ማዛናዊነት እንደ መሆኑ መጠን ምንሊካዊ ብሎ ሚዛናዊነት ሊኖር እንደማይችል ሳይታለም የተፈታ ነው። አንድ ሰው ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት የሚያራግብ ሆኖ ሚዛናዊ ሰው መሆን አይችልም። ሚዛናዊነት ምክንያታዊነት፥ ምንሊካዊ ኢትዮጵያዊነት ለሚባለው የጠንቋይ ማንነት አላርጅክ ነው። አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ያልገባው ነገር መጠየቅ፣ አንጻራዊ ሃሳብ በሃሳብ ደረጃ ማንሳት፣ ሃሳቡን በነጻነት መግለጽ አይችልም፤ እንዲህ ያለ ነገርም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፤ የዋለው እንደሆነም ወያነ ተብሎ እንጨት ላይ እንደ ቋንጣ ትሰቀላለህ። አንድም መሬት ለመሬት ትጎተታለህ። ጠቅለል ባለ መልኩ፥ ትምክተኛ ግለሰብና ቡድን ጨቋኞች ሲሆኑ፥ ጨለምተኛ አስተሳሰብ የሰለጠነበ ግለሰብ/ቡድን በተመሳሳይ አሽክላ፣ ጸረ ለውጥ ኃይል ነው። ትምክህተኛ ውዳሴ ከንቱ ፈላጊ ሲሆን ጨለምተኛ እንዲሁ ነፍሰ ገዳይ ነው። አሃዳዊት ኢትዮጵያም የዚህ ሁሉ አረማዊ ተግባር ምሳሌና ምስክር ናት።

 

መቋጠሪያ

 

በመጨረሻ ለማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት ለትግራይ ህዝብና አመራር ይሆናል። ይኸውም፥ የትግራይ መፃኢ ዕድል በተመለከተ፥

  አንዴ አይደለም አስር ጊዜ ደግሞ ደጋግሞ መልሶ መላልሶ እንዲያስብበት፣

  በዘመናት ፈጽሞ የማይቆጭበትና የማይጸጸትበት፣

  በላያችን የሆነብንና የተፈጸመብን ዳግም ላይሆንና ላይፈጸም ትውልድ ለአንዴና ለመጨረሻ ፈጽሞ የሚያሳርፍ፣

  የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ የሚገባው ሁሉ የሚያጎናጽፍ

  የዛሬ ውጥረት፣ በየቅጣጫው የሚወረወር የጠላት ጦርና ፍላጻ ሳይበግረው መጪ ዘመናት በሩቅ አይቶ መታሰቢያ ያለው ቆራጥ ውሳኔ ላይ እንዲደርስና እንዲወስን እጠይቃለሁ፤ እመክራለሁም።

 

ኢትዮጵያዊነት ምንድ ነው? - መጽሐፉን ለማግኘት ከታች የተቀመጠው ሊንክ ይጫኑ

(https://www.amazon.com/gp/product/B08DF24BWW/ref=dbs_a_def_rwt_bibl_vppi_i2)

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page