Back to Front Page

የኣማራ ጽንፈኞችን በልታ እንጂ ጽንፈኞቹ በልተዋት የምትኖር ኢትዮጵያ ኣይታሰብም። የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ኣንዱ ማሳያ ነው።፡

የኣማራ ጽንፈኞችን በልታ እንጂ ጽንፈኞቹ በልተዋት የምትኖር ኢትዮጵያ ኣይታሰብም።

የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ኣንዱ ማሳያ ነው።፡

ጎደፋይ ተ.ጊዮርግስ 03-29-21

ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው ከኣማራ ክልል የበቀሉ ጽንፈኛ የሆኑ ፖለቲከኞች ኣደገኛ ጉዞ እና በኢትዮጵያ ላይ የደቀኑት ችግር ላይ ነው። የኣማራውን ህዝብ እና ጩሀታቸው የተቀማ ከክልሉ የወጡ ቅን ኣሳቢ የኣማራ ክልል ምሁራንም ይሁን ፖለቲከኞች እይጨምርም። ለነሱ ኣክብሮቴ የላቀ ነው። ይህ ስል በሌላ ክልል ያለ የፖለቲካ ሃይል ችግር የለውም ኣይደለም እያልኩ ያለሁት። በማይተናነስ መልኩ ህዝብ ከህዝብ ጋር በማጋጨት ሃገሪቱን ወደ ዉጥረት ሲከት የነበረና ያለው ብዙ ነው። ጽንፈኞቹ ለየት የሚያደርጋቸው ጠንቅ ለሚባሉትም ጠንቅ መሆናቸው ነው። እኩልነትን ተቀብለዉ በሰላም ከመኖር ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ኣማራነትን በሌላው ክልል ህዝብ ላይ ለመጫን ስለሚፈልጉ ነው። ተዉ ሊባሉ ይገባል። መተዉም ኣለባቸው። ወደዱም ጠሉም ካሁን በኋላ ጽንፈኞችን በልታ እንጂ ጽንፈኞች በልተዋት የምትኖር ኢትዮጵያ የማይታሰብ ነው። የትግራይ ህዝብ ተጋድሎ ደግሞ ኣንዱ ማሳያ ነው።

እትዮጵያ እስከ ኣሁን ድረስ እየደማች ያለችው ከኣማራው ክልል በበቀሉ ባልስልጥናት ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም።፡ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከኣገው ስርወ መንግስት በኋላ ከየት ወዴት እንዳመራ ማየት ነው። ኢትዮጵያ ከተንጣለል ቤተ መንግስት ወደ ድንኳን ኣስተዳደር የተሸጋገረችው በነዚህ ነገስታት ዘመን መሆኑ ልብ ይሏል። ካለፈው መቶ ኣመት ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ የተካሄደው የእርስ በርስ ጥርነትና እልቂት እንደ ኣብነት ብንጠቅስ እንኳ ጠንሳሾቹም ሆነ ወላጆቹ ( የከፊሉ ኣዎንታዊ ኣስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ) ከዚህ ክልል የወጡ ነገስታትና ባለስልጥናት ናቸው። ወይ በቀና መንገድ ሳያስተዳደሩ ወይ ደግሞ የሌላዉን ህዝብ መብት ተቀብለው ስልጥናቸው ሳያጋሩ የስልጣን ዘመናቸው ለማራዘም በሌላው ህዝብ ላይ ሁሌም ጦርነት እንደደገሱ ነው፡፡ የከፋ እልቂትም ኣድርሰዋል። ኣሁን ደግሞ ጽንፈኞቹ ተረክበውን በተራቸው ሃገሪቱን ለእርስ በርስ ጦርነት ዳርገዋት የንጹሃን ደም በከንቱ ሲፈስ እያየን ነው።

Videos From Around The World

ተከባብሮ ለሞኖር ኣልዋጥ ያላቸው ለምንድን ነው? በኣጼ ሃይለስላሴ ጊዜ ኣሉ እንዷ ባልቴት (ቤተሰባቸው ትሁን ኣትሁን ኣላውቅም) ለግብዣ ተጠርተው በተመንግስት ሄዱ ኣሉ። ከግብዣው በኋላ ኣጼ ሃይለስላሴ ተልቅ ሽቶ ይሰጧቸዋል። ስጦታ መሆኑ ነው። ተሰናብተው ሲወጡ ካንዱ ባለሟል ጋር ይገናኙና ንጉሱ ስለሰጧቸው ስጦታ ይነግሯቸዋል። ሽቶውን ማለት ነው። በደስታ ተሞልተው። በስጦታው የተገረሙ (የተናደዱም እንበል) ጓዳቸው እመቴ ምን ያህል ቢሸቷቸው ነው ? ኣሏቸው ይባላል። የኣማራ ክልል ጽንፈኞችም መጠየቅ ያለባቸው ይሄው ነው። ከሁሉም በላይ ስለኣንድነት የሚለፍፉ እነሱ ፡ ከሁሉም በላይ እንድነቱን የሚጋፉት ደግሞ እነሱ ናቸው።፡ኣንድነት ካለ እኩለነት እንደማይኖር ኣልረዳ ያላቸው ለምንድን ነው? ለስልጣን ሲሉ ዘመኑ ከሚጠይቀው የሰብኣዊነትም ይሁን የፖለቲካ መመዘኛ እጅጉን ወርደው እራሳቸውንም ማህበረሰቡንም የሚያምሱበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚለው።

መልሱን ከእነሱ ኣንደበት ግድ መጠበቅ የለብንም። ኣልተስተዋለ እንደሆነ እንጂ ትንቢት በሚመስል መልኩ ቀደም ብሎ በቅኔ ይማርልኝ ብዬ በጌምድር ሰድጄ ቀለም ገባው ኣሉ እሳት ሆነ ልጄ ተብሎ የተነገረ ነው። ማስረጃ ማጣቀስ ኣያስፈልግም።፡ ሃገርን ሳይወክሉ ሃገር ሁነው ፡ ህዝብን ሳይወክሉ ህዝብ ሆነው፡ በታሪክም በትረካም ከኦሮሞው፡ ከቅማንቱ ከሶማልያው፡ከጉሙዙ ከትግራይ ፡ ከኣፋር፡ ወዘተ ጋር እየተላተሙ ሃገርን ሰላም የነሱትን በወቅቱ በኣማራ ክልል በስልጣን ላይ ያሉትን ፖለቲከኞች ማየት ነው። ሳይገድሉ ፎክረው ከእብድ ባላነሰ ኣስተሳሰብና በወረደ ኣንደበት በየብዙሃን መገናኛዎች ህዝብ ከህዝብ ጋር ሲያጋጩ የሚዉሉትን : የትግራይ ህዝብ መጥፋት ኣለበት ብለው የሚያዉጁትን ኢሳት እና የመሳሰሉትን ማየት ነው።

በርግጥ ጽንፈኞቹ ዋናው ጸባቸው (ከሁሉም በበለጠ ማለቴ ነው) ከትግራይ ሕዝብ ጋር ነው። ሰበቡ ደግሞ ህወሓት ነው። የህወሓት ኣመራር ግፍ ፈጽሞብናል መሬትም ወስዶብናል ባዮች ናቸው። ቢረፍድም የፖለቲካቸው ሰለባ ለሆኑት ለማስገንዘብ ሁለቱንም ነጥቦች ኣንስቼ እውነታውን ለማስጨበጥ እሞክራለሁ።፡ ሰሚ ካለ ማለቴ ነው።

የህወሓት ኣመራር የክልሎች የራስ በራስ መወሰን መብት ኣንዲከበር ታግሏል። ቋንቋን መሰርት ኣድርጎ ክልልሎችን ፈጥሯል።፡በርግጥ ለብሄረ ሰቦች ተሰጠ የተባለው መብት ህዝቡ ኣልተጠቀመበትም። ተከበረ የተባለው የብሄረሰቦች መብት ለክልሉ በለስልጣናት ነበር መገልገያ የሆነው። ብሄራዊዉ መንግስት ክልሉን ለመቆጣጠር የሚያስችል መዋቅር እና ኣሰራር (ሙስናው እና ኢዲሞክራሲያዊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ) እስከ እታች ድረስ ኣለመዘርጋቱ ደግሞ ኣንዱ ምክንያት ነው። ህዝቡ ተጠቃሚ ሆነ ኣልሆነ ጽንፈኛው በውሳኔው ለኪፋ ባህርያዊ ነው። ለምንስ ኣይከፋዉ? የኢትዮጵያ ባለቤትና በላመብት የነበረውና በህዝብ ትከሻ መኖር የለመደ ኣሁን ና ከሌሎቹ ጋር እኩል ሁን ፡ራስህን ቻል ነው እየተባለ ያለው። እንደዛም ሆኖ ህወሓት ኣስፈጸመ እንጂ እነ ኢህኣፓም የብሄር ብሄረሰቦች መከበር እንዳለበት በመርህም በተግባርም ላንቃቸው እስኪደርቅ ሲለፈልፉለት የነበረ ነው። ስለዚህ ችግሩ የህወሓት መርህ ወይም ፖሊሲ (ጉድለቱ እንደተጠበቀ ሆኖ) ኣይደለም። ኣማራ ለመሆን የተቸገረው የኣማራው ጽንፈኛ ነው።

ኣገሪቱ ቋንቋ መሰረት ባደረገ ክልል ስትዋቀር መሬቱም ይህን ተከትሎ ካንዱ ወደ ሌላው ክልል ይዞታ ተሸጋግሯል። በሁሉም ክልል ደግሞ ተግባራዊ ሆኗል። በርግጥ ሰፋ ያለ ጥናት የተደረገበት ኣለመሆኑና ህዝብን ኣለማሳተፉ ህዝቡን ለብዙ ችግር ኣንዳጋለጠ ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ ማርክሳዊ ርእዮተ ኣለምን ከሃገር ዉስጥ ጉዳይ ወይም ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሳያገናዝቡ እንደወረድ ለመተግበር የተወሰደ እርምጃ ያመጣው ጣጣ ነው። ጽንፈኞቹ እንደሚሉት ግን የኣማራውን መሬት ለመንጠቅ ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ኣይደለም። ሲጀመር ወደ ትግራይ ተወሰደብን የሚባለው የኣማራው መሬት ቢሆን መልካም ነበር። ኣጼ ሃይለስላሴ ከትግራይ የነጠቁት ነው። ቀጥሎም በፖሊሲው እጅግ የተጎዳ ካለ ደግሞ ኣማራው ኣይደለም። ከተሰጠው ይልቅ የበዛው ወደ ኣፋር እና ኣማራ ክልል የተወሰደበት የትግራይ ህዝብ ነው። ጽንፈኞቹ ይህንን ያወቃሉ። የተጠመዱት ግን በተወሰደብኝ ነው። እየበሉ ማልቀስ ነው።

የህወሓት ኣመራር እንደ ድርጅትም እንደመንግስትም ብዙ ያጠፋው ነገር ኣለ። በሙስናው፡ ብኣድልዎው፡ በጭቆናው በሁሉም በሚባል መልኩ ብዙ ኣጥፍቷል። በጥፋቱ መጠየቅ ኣለበት። ሊጠየቅም የግድ ነው። ኣመራሩ ባልተለመደ መልኩ ስህተቱን ኣምኖ በህግ ለመጠየቅም ፈቃደኝነቱን ኣሳይቶ ነበር። እራሱ ብልጽግና በእነ ጀነራል ክንፈ ኣላስፈላጊ ተውኔት ደርሶ ባያበላሸው። ይህ ማለት ግን በኢህኣዴግ ስር ተጠልሎ የነበረው ድርጅት ወንጀ ነጻ ነው ማለት ኣይደለም። ብኣዴኖችና ኦህዴዶች ካኣዲስ ኣበባ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ መርበባቸውን ዘርገተው መሬት ሲሸጡና ሲያሻሽጡ፡ ሲመዘብሩና ሲያዝመዘብሩ እንደነበሩ ግልጽ ነው። የብዙ ንጹሃን ሂወት በማጥፋትም እንዲሁ ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው። ከቶ በህወሓት ተሰራ የተባለ ጥፋት ሁሉ እነሱም ኣሉበት። ታድያ በምን መለኪያ ነው ኣንዱ ህግ ኣስከባሪ ሌላው ተጠያቂ የሚሆነው? ክሱ ዉሃ ኣይቁጥረም። የሚሻለው፡ ሚዛንም የሚደፋው ከራስ ሲጀመር ነው

ተበቅሎናል የሚሉት ክስም እንዲሁ ብዙ ኣያስኬድም። የህወሓት ኣመራር ኣማራዉን ለመበቀል የተነሳሳ ቢሆን ኖር በሃያ ሰባት ኣመታቱ ጊዜ ብዙ ኣማራ (ኣምስት ሚሊዮን ኣማራ ገድሏል የሚለው ዉሸት ወደ ጎን ትተን) በገደለ ነበር። ኣማራው ደግሞ ኣዲስ ኣበበባ ብቻ ላይ ኣይደለም ያለው።: ወሎ ኣለ። ጎንደርም ኣለ። ለትግራይ ቅርብ የሆነ ማለቴ ነው። በምርኮ እጁ ዉስጥ የገቡ ጀኔራሎችንም ነበሩ። የኣሁኑ ኢሳቶችም የትናንቱ የምርኮ ዉጤትች መሆናቸው ልብ ይሏል:። ሳይበድል የኣማራ ህዝብን ላለማስከፋት ብሎ ጓዱን ኣለጥፋት በህዝብ ፊት ሲረሽንነ እንደነበረም የቅርብ ትዝታ ነው። ለዚህ ደግሞ ከጎንደር በላይ ምስክር የለም። ደባርቆችን መጠየቅ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ከሰራዊቱ እንዲባረሩ የተደረጉትም ኣጥፍተው ሳይሆን የኣማራውን ህዝብ ተሳትፎ ለማካተት ተብሎ ነው። ህወሃት ይቀናቀኑኛል በሚላቸው ሃሎች (ኣማራዉን ጨምሮ) ላይ ኢፍትሃዊና ኢሰብኣዊ እርምጃ ወስዷል። በዚህ እርምጃ በከፋ መልኩ የተበደለ ካለ ደግሞ ኣማራው ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ነው። ስለዚህ ክሱ ከፍየሏ በላይ ነው። ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ ኢላማ ለማድረግ የታሰበ ነው።

በርግጥ የትግራይን ህዝብ ኢላማ ማድረጉ የተጀመረው ኣሁን በጽንፈኞቹ ኣይደለም። ገና ከ ኣጼ ሚኒሊክ ጀምሮ ነው። ኣጼ ሚኒሊክ የመጀመርያ ስራቸው የኢትዮጵያን ኣንድነት ማስከበር ሳይሆን ትግርኛ ተናጋሪው ማጥፋትና መከፋፈል ነበር:: ኣጼ ዮሃንስ ጣልያን እና ግብጽ ሲያስቀድሙ ኣጼ ሚኒሊክ ግን ኣጼ ዮሃንስ ነበሩ ቀዳሚ ጠላታቸው ። ኢትዮጵያ ከገዳሪፍ እስከ መደኒ (ፖርት ሱዳንና ከሰላን ጨምሮ) የነበረው መሬት ለሱዳንና ለጣልያን የተሰጠው ትግሬ ከሚገዛ ተብሎ ነው። ኣሁን በጽንፈኛው ተግባራዊ እየሆነ እንዳለው። ኣጼ ሃይለስላሴም ቅድምያ የሰጡት ትግራይን ማዳከም ነበር። ኣንዱ መንገድ ደግሞ መሬት ከትግራይ ቆርጦ መውሰድ ነበር። ደርግም እንዲሁ ኣለ የተባለ እርምጃ ሁሉ ወስዷል። ኢህኣፓም ትግሬ ኣይገዛህም ብሎ ማጥላላትና መዋጋት የጀመረው ገና ህወሕት ጎንደር እንደገባ ነው። ባጭሩ የትግራይ ህዝብ ይጥፋ የተባለው ህወሓት ከመፈጠሩ በፊት ነው። ጽንፈኞቹም እየተገበሩት ያሉት ኣሁን የተጸነሰ ኣይደለም። ኮቴያቸውን ተከትለው ነው። ልዩነቱ የኣሁኖቹ ዉሸትና መረን የለቀቀ ስነምግባር ያካተተ መሆኑ ነው።

መረን የለቀቀ ነው ስል ኣለምክንያት ኣይደለም። በዚህ ሶስት ኣመት ጊዜ ዉስጥ በጽንፈኛው ፊታውራሪነት በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸሙ ግፎች በከፊሉ ማየቱ በቂ ነው። ከክልሉ ኣባርሯቸዋል ፡ ቤቱን ኣቃጥለዋል፡ ነብረት ተብሎ የተፈረጀ (ዱቄትም ሳይቀር) ሁሉ እየተዘረፈ ወደ ኤርትራ እና ኣማራው ክልል ተጓጉዟል። በረሃብ እንዲያልቅም መንገድ ዘግተውበታል። በጸጉረ ልውጥነት ፈርጀው ለእስርና ለግድያ ዳርገዉታል። በባንክ የውንብድና ታሪክ የየኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የመጀመርያው በሚባል መልኩ የባንክ ሂሳቡን ዘግተው ገንዘቡን እንዳይጠቀም ከልክለዉታል። ገዳማትና ኣብያተ ክርስትያናትም እያቃጠሉ፡ ነዋየ ቅድሳቱንም እየዘረፉ ነው። ሴቶችን መድፈር፡ ህጻናትና ወጣቶችን መግደልም ኣንዱ መለያቸው ሁኗል። ወንድም የሚለው ቀረና ትግሬን መግደል የሚያሸልም ሆኗል። ካህናቶቻቸውም የገነት መግብያ መንገድና በር ትግሬን መግደል ነው እያሉን ነው።፡ የቀረ ነገር ቢኖር እእምሯቸው ረስቶት ወይም ኣቅም ኣጥተው የተዉት ብቻ ነው።

በርግጥ ጦርነቱ ሁሉም የኣማራ ህዝብ የሚጋራው ኣይደለም። እራሱም ጽንፈኞቹ በሚፈጥሩት ችግር የግድያና እና ኣፈና ሰለባ የሆነ ንው። የሰባተኛው ንጉስና የጽንፈኛው ቡድን ጦስ ለኣማራውም እየተረፈ ነው። የኣማራ ህዝብ ፍላጎትም ነው እንበል። የትግራይ ህዝብ የሌላት ኣማራ ወዴት ልትኖር ነው? የትግራይን ህዝብ የበላ ሰይፍ ኣማራውን የሚተውው እንዴት ነው? እሳትና ኢሳት የበላው ካልሆነ ጤናማ ኣእምሮ ያለው ሰው የሚያስበው ኣይደለም። ጽንፈኞቹ ሊመስላቸው ይችላል። መስሏቸውም የዉጭ ሃግራት ሳይቀር ጋብዘው በጦርነት ኣሳትፈዋል። ኣይነጋም ብለዉም ብዙ ግፍ ፈጽመዋል። ዳሩ ግን የማይቻል መሆኑ ከውስጥም በውጭም እያዩት ነው። ባጭሩ ትግራይን ለማጥፋት የለኮሱት እሳት መልሶ እየለበለባቸው ነው። እንደሚቃጠሉም በርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምክንያቱ ወደዱም ጠሉም ካሁን በኋላ ጽንፈኛውን በልታ እንጂ ጽንፈኛው በልቷት የምትኖር ኢትዮጵያ የማይታሰብ ነው።

ጽንፈኞቹ ለትግራይ ህዝብ የደገሰለት ጥፋት በፈለጉት መንገድ ኣይደለም ኣየሄደ ያለው። በሁሉም በሚባል መልኩ የጠነሰሱት ሴራ ከሽፏል። እንደ እባብ የልባቸውን ኣይቶ እግር ነስቷቸዋል። ከኣብይ ጋር ተፈጠረ የተባለው ኣንድነት ከውስጥ መሰነጣጠቅ ጀምሯል።ኦህዴድ ጽንፈኞቹን፡ጽንፈኞቹ ደግሞ ኦህዴድን በልተው ሊቀደሱ በተጠንቀቅ ቁመዋል። ሊቆላ የታሰበ ገብስ ጥጠር ሆኖ ኣስቸግሯቸዋል። በሶስት ቀን ሊበላ የተፈረደበት የትግራይ ጫጩትም ጭልፊት ሆኖ ኣሳዳጆቹን ማሳደድ ከጀመረ ቆይቷል።ለቁርስ የታሰበ ለምሳም ኣልደርስ ብሎ በድል ረሃብ ገድሏቸዋል። ለብቀላ የታደመ ወዳጅ ኢሳያስም ከጅብ የማያስጥል የኣህያ ወንድ ሆኖላቸዋል። ከጥርነቱ ይልቅ በሌብነቱ ነው ተሰማርቶ ያለው። ኪሳራ ይሉሃል እንዲህ ነው። ባጭሩ በሴራቸው ተጠልፈዋል። በቁማሩ ተበልተዋል። የቀረላቸው ቢኖር ኣጥንት ነው ። ኣጥንቱም በኣብይ እጅ ነው። ስለዚህ ጽንፈኞቹ እየጠበቃቸው ያለው የመጨረሻዋን ጽዋ መጠጣት፡ እንድትንቢቱ (ቅኔው) በእሳቱ መጋየት ነው። መጋየታቸው ኣይደለም የሚያሳዝነው። ለኣገሪቱም ለኣማራ ህዝብም እሳት ለኩሶዉበት መሄዳቸው ነው። እንደ መዥገር ኣገሪቱን ገድለዋት መሞታቸው ነው። ነፍስ ይማር።

ማስታወሻው ከህወሓት የትጥቅ ተጋድሎ ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ከትግራይ ህዝብ ጋር ወግነው ሂወታቸው ለሰዉለት እና ችግሩን እተካፈሉ ለነበሩትና ላሉት የኣማራ ክልል ተወላጆች ይሁን። ኣመሰግናለሁ።

Godofai Tgiorgis

tgiorgis12@yahoo.com


Back to Front Page