Back to Front Page

ፈጽመህ እስክታጠፋቸው ድረስ እጅህን እንዳታጥፍ፥ በሎም!

ፈጽመህ እስክታጠፋቸው ድረስ እጅህን እንዳታጥፍ፥ በሎም!

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 06-30-21

 

መንደርደሪያ፥ ኦፕሬሽን ራስ አሉላ አባ ነጋ አይደለም በእንቅልፍ ልቡ ለሚራመደው ለኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ለጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊና እናቱ እንደሞተችበት ህጻን ልጅ ተጎንሶ ምሾ እያወረደና የጊዮርጊስ መባ እንደበላ ክፉ መኖክሴም ሳይጠየቅ እየተለፋለፈና እየሸለለ ለሚገኘው የአማራ ልሒቃን ሊገባቸውና ሊረዱት ቀርቶ በሳይንሱም በአርቱም ብዙ ርቀት ለተጓዙ የምዕራቡ ዓለም ሳይቀር የኦፕሬሽን ራስ አሉላ አባ ነጋ አፈጻጸም ትንግርት ሆኖባቿል። በቀናት ውስጥ የሆነውና የተፈጠረው ተአምር የሆነባቸው የዓለማችን መገናኛ ብዙሐን በትግራይ መሬት ውስጥ የሆነውና የተፈጠረው ተአምር አስመልክተው ተው ሰላም አውርድ እየተባለ ለስምንት ወራት ሲለመን የከረመው ዐቢይ አህመድ ዓሊን ከልበ ደንዳናው ከግብጹ ፈርዖን ጋር በማነጻጸር ብዙሐኑ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ጸሐይ ጠለቀች! ሲሉ በአጭሩ ለመግለጽ ተገደዋል። ላለፉት ስምንት ወራት፥ የትግራይ ህዝብ በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲሁም በአማራ ሚኒሻ ፊታውራሪነት የትግራይ ህጻናትና ሽማግሌዎ ተግደሉ፣ ካህናት ታረዱ፣ መነኮሳት ሴቶችና እናቶች ክብረ ንጽህናቸው ተደፈረ፣ ወጣቶች በጠራራ ጸሐይ ተረሽኑ፣ አብያተ ክርስቲያናት በታንክና በከባድ መሳሪያ ወደሙ፣ ቅድሳት መጻህፍት ተቃጠሉ፣ የትግራይ ህዝብ ሀብትና ንብረት ተዘረፈ፣ ፋብሪካዎቹ ተዝረፉ፣ ከተሞቹን በእሳት ጋዩ፣ የትግራይ ገበሬ ማሳ በእሳት ተቃጠለ ሲባል ሲሰማ ሻምፓኝ ሲራጭና በአደባባይ ወጥቶ ደስታውን ሲገልጽ የነበረ ህሊና ቢስ ዜጋ ዛሬ የሙርከኛ መዓት ሲርመሰመስ የሚያሳይ ዜና ብቻውን ከዕጣን በላይ ሆኖለት ዜናውን እያየና እየሰማ ሐይ! እያለ እያጓራ ያለ፤ እርር ኩምትር ብሎ ህመሙ ጸንቶበት አልጋ ላይ የወደቀ ባለወቃቤ፣ የራሱን ውሸት ለማመን ራሱን አሳልፎ የሰጠ ምዋርተኛና ትምክህተኛ ዜጋ ቁጥር ቤት ይቁጥረው።

 

Videos From Around The World

ሐተታ፥ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች አለ ኤልሳዕም ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ አለው፤ ቀስቱንና ፍላጻዎችንም ወሰደ የእስራኤልንም ንጉሥ እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን አለው። እጁንም ጫነበት፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጭኖ የምስራቁን መስኮት ክፈት አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም ወርውር አለ፤ ወረወረውም። እርሱም የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያዊያንን በአፌቅ ትመታለህ አለ። ደግሞም ፍላጻዎቹን ውሰድ አለው፤ ወሰዳቸውም። የእስራኤልንም ንጉሥ ምድሩን ምታው አለው። ሦስት ጊዜም መትቶ ቆመ። .19 የእግዚአብሔርም ሰው ተቆጥቶ አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ኖሮ ሶርያን እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ አለ” (መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 1314-19)

 

ቁጥር 19 ላይ የእግዘአብሔር ሰው ተቆጣ እንዲል፥ የእግዚአብሔር ሰው ኤሌሳዕ የመቆጣቱ ዋና ምክንያት ንጉሡ ሦስት ጊዜ ብቻ መትቶ በማቆሙ ነበር። ለምን አቆምክ? አንዴ ጊዜ መምታትና ማጥቃት ከጀመርህ ለምን አቆምህ? መምታትህንና ማጥቃትህን ብትቀጥል ኖሮ ፈጽመህ ታጠፋቸው ነበር ሲለው እንመለከታለን። ሰው ጠላቱን ለይቶ ካወቀና አንዴም ከገጠመ እስከ መጨረሻ ድረስ የመሄድ ግዴታ አለበት። የተመታ፣ የተቀጠቀጠና የተገረፈ ጠላት ዳግም እንዳያንሰራራ፣ እንዳያቆጠቁጥና እንዳይመለስ ከተፈለገ አንዴ መትተህና አቆሳስለህ አትተወዉም። መሸነፉን፣ መረገጡን፣ ፈጽሞ መጥፋቱንና መሞቱን እስክታረጋግጥ ድረስ እንዲሁ አይተውም። እርሙን ጨርሶ አንከባሎ እስከሚጥል ድረስ እየተከታተልክ ከገባበት ገብተህ አሳድደህ ማደን ነው። ከታገልክ እንዲሁ ለመታገል ሳይሆን ለመጣል መታገል ይገባል። ዋጋ ቢያስከፍልም ከተዋጋህ ፈጽመህ መዋጋት ነበረብህ! ነው የእግዘአብሔር ሰው የኤሌሳዕ የመቆጣቱ ምሥጢር። ዛሬም የትግራይ ህዝብ፥ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በሶማሊያ፣ በኢምሬትና በሱዳን መንግስታትና አገራት ሞትና ጥፋት የተደገሰለት ህዝብ ሆኖ ሳለ ታግለው በማታገል ህዝባቸውን ከጨለማ ላወጡና ለገላገሉት የትግራይ ጀኔራሎች የማስተላልፈው መልዕክት ይህንኑ የታመነ ቃል ነው። ጠላት በአሁን ሰዓት በትግራይ ግዛት ውስጥ ሊሰፍርና ሊንቀሳቀስ ቀርቶ አንድም የጠላት ሠራዊት በትግራይ ግዛት ውስጥ በህይወት ሊኖር አይገባም እላለሁ። የመጣው፥ ሊገድል፣ ሊዘርፍ፣ ሊያምጽ፣ ሊያጠፋ፣ ሊጨፈጭፍ ነውና የራሱን መድኃኒት ይውጥ ዘንድ ይገባል። ምህረት ማድረግ ምህረትን ለለመነና ለሚጠይቅ እንጅ ለቅጥረኛ ነፈሰ ገዳይ የሚደረግ ምህረት የለም፤ አይኖርምም። ጠላት ጥርሱን እያገጠጠ ስለ ሳቀ አይሳቅም፣ ጠላት ለሰለሰ ተብሎ አቋምና እምነት አይለወጥም፣ አይ ጠላት ከተወውማ እኔም እተወዋለሁ ተብሎ ጉዳይህን አይተውም። ለጠላት ርህራሄ ማድረግና ማሳየት በቁምህ መተስከር ነው። የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊት እንዲሁም የአማራ ኢንተርሃምወይ ሚኒሻ ወደ ትግራይ የመጣ ችግኝ ሊተክልና ውሃ ሊያጠጣ ሳይሆን ለአንድ ግለሰብ የስልጣን ዙፋን መጠበቅና መራዘም ሲባል በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረውን ክቡር ፍጥረት ለማብረስና ለመጨፍጨፍ፤ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ስመ ዝክሩ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በአራት አቅጣጫ እየተመመ የመጣ የሞት መልእክተኛ ነው። በመሆኑም፥ ይህን ዓይነቱ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ንጹህ አየር ሊተነፍስ አይገባውም። የዘረፈውና ያወደመው የህዝባችን ሀብትና ንብረት ማስመለስ፣ ይህን ያደረጉ ጣቶች መቁረጥና መቅጣትና ማስተማር ይጠበቅብናል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጠላት የገባበት ጉድጓድ ውስጥ ገብተን ፈጽመን ልናጠፋው፣ ዳግም ላያንሰራራ ልንሰባብረው ይገባል።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ እግሩ ወደ ትግራይ ከማንሳቱ በፊት የገባ ዕለት እንዲሁ በገባበት መንገድ ዘው ብሎ እንደማይወጣ፤ ከገባም ከሰማይ በታች የሚያተርፈው አንዳች ኃይል እንደሌለና ሊኖርም እንደማይችል በእርግጠኝነት ተናግሬ ነበር። በርግጥ፥ ይህን ዓይነቱ ንግግር በወቅቱ ሲነገር አይመስለም ነበር፤ ሐቅ ግን ሁልጊዜ ሐቅ ነውና የተባለውና የተነግረው ለሚጠራጠር ልብ ይሄው ጊዜው ደርሶ በመቃብሬ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የነበረ ሰውዬ መልዕክቱ ደርሶኛል ለማለት ተገዷል። በነገራችን ላይ፥ ይህ ሰውና እግዚአብሔር የተጸየፈው የውሸት ቋት የሆነ ግለሰብ (ዐቢይ አህመድ ዓሊን) ከበትሪ ወያነ ሊገላግለው፣ እጁን ዘርግቶ ሊያተርፈውና ሊታደገው የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል እንደሌለ የተሸፈነው ዜጋ ቢኖር የወያላዎች አገር ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው። እውነት ነው፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ትግራይ የገባው ሊወጣ ሳይሆን በጭብጨባና በውዳሴ ከንቱ የተሳከረውና የታበየው ልቡ ይተነፍስ ዘንድ፥ ሊሰበር፣ ሊዋረድና ልኩን እንዲያውቅ ወደ ትግራይ ገብቷል። ይህ ሰው ከተረፈም ሊያተርፈው የሚችል ብቸኛ ኃይል፥ ሲሰራ በሰማይም በምድርም ከልካይ የሌለው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው ሊያተርፈው የሚችል። በተረፈ የአማራ ልሒቃን የተለመደ ደንቃራና ኋላቀር ቀረርቶና ሽለላ በሰውዬው ሬሳው ላይ የሚወጋ ሚስማር ከማጥበቅ ያለፈ ሌላ ገንቢ ሚና አይጫወትም።

 

በመጨረሻ፥ አሁን የተገኘ አንጸባራቂ ድል ጠብቀን ወደ ሌላ የበለጠ ድል ለመሸጋገር የሚያስችለን ሁለት መሰረታዊ ነጥቦች በማንሳት ጽሑፌን እቋጫለሁ።

 

1.      የህይወት መስዋዕትነት የተከፈለበት ድል ማክበርና በሚገኙ ድሎችም ደስ መሰኘት መልካም ነው። ዳሩ ግን፥ ከፊት ለፊት የሚጠብቀን የቤት ስራ ከዚህ ሁሉ ደስታ የላቀ ነውና በዚህ ልንረካና ልንዘናጋ አይገባም። ቀጣዩ የቤት ሥራ በባህሪው የሁሉም ትግራዋይ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ አንድነታችንና መሰባሰባችን በማጠናከር አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ግዴታችን ልንወጣ ይገባል። ነፍሰ ወከፍ ትግራዋይ ከላይኛው አመራር ጋር አንድ ልብ ሆኖ ተናቦና ተጠባብቆ መሄድ ስለሚገባ ከአሁን በኋላ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ የሚባክ ጊዜ ሊኖረን አይገባም።

2.     ሌላው፥ ከእንግዲህ ወዲህ ከምንም በላይ ለትግራይ ህዝብ ዋስትና ሊሆንና ሊሰጥ የሚችለው ነገር ቢኖር፥ ትጥቁና ስንቁ የተሟላለት አካላዊና ሞራላዊ ስብእናው በሚገባ የታነጸ፣ በዲስፕሊን የተገነባና የነቃ ጠንካራ ወታደራዊ አቅም መገባት አማራጭ የሌለው ሐቅ ነው። በሰሜን ይምጣ በደቡብ፣ ከምዕራብ ይዝለቅ ከምስራቅ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ በጠላቶቹ መካከል ተከብሮ ሊኖር የሚችለው ለአቅመ አዳም/ሄዋን የደረሰ ትግራዋይ ሁሉ ህልውናውን ጠብቆ ለማስጠበቅ በሚገባ ሲደራጅ፣ ሲሰለጥንና ሲታጠቅ ብቻ ነውና ከራሴ ጀምሮ ሀገረ ትግራይ ለምታቀርብልን ጥያቄ ሁሉ ዝግጅዎች ልንሆን ይገባል። ህዝባችንና አገራችን ማገልገል ክብራችን ነውና።

የቆመውን ማስኬድ የሚሄደውን ማስቆም አይቻልም

E:mail- mahbereseytan@gmail.com

 

Back to Front Page