Back to Front Page

የበሻሻ ቆሻሻና የአያቶቹ አሁዳውያን ቆሻሻ አስተሳሰብ

የበሻሻ ቆሻሻና የአያቶቹ አሁዳውያን ቆሻሻ አስተሳሰብ

ኦርዮን

06/02/2021

ኢትዮጵያን ስናስባት ጥንታዊት፣ የረጅም ጊዜ ባለታሪክ፣ በእምነቷ የጸናች፣ እግዚአብሔር ክብርና ሞገስን ያጎናጸፋት፣ እንግዳ ተቀባይ፣ የመቻቻል ተምሳሌት፣ በባእድ ያልተገዛች፣ ወዘተ..... የሚሉ ገላጭ የቅጽሎች ጋጋታ የተለጠፈባት አገር ሁና ነበር አብዛሃው ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ የሚያውቋት ። በርግጥ ይኸ ትርክት ካንድ ወገን የሚሰጥ የማደናገርያ ትርክት እንጂ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ የሚገልጽ አልነበረም። በተለያዩ ውቅቶችም የነበረውን ትርክት ትክክል እንዳልነበረ የተለያዩ ሰዎች ለማሳየት ሞክረዋል። ለምሳሌም ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ በመጽሃፋቸው አፄ ምኒሊክ የትግራይን ሕዝብ እንደ ሕዝባቸው አያዩትም እንዳሉም ይነገራል። ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህልም በግዕዝ አቆጣጠር በ1958 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር አባልና አክቲቪስት የነበረው ዕውቁ ዋለልኝ መኮነን ኢትዮጵያ የብሄር ብሔረሰቦች እስር ቤት ናት የሚል ጽሁፍ እንደጻፈ እናስታውሳለን። እናም ለዜጎቿ የማትመች ቆሻሻ። በርግጥ ቆሻሻ የሚባል አገር የለም ሊኖርም አይችልም። ቆሻሻ ሊሆን ከሆነም ሰዎች ናቸው ሊያቆሽሹት የሚችሉ። አገር ሙሉም እስር ቤት ሊሆን አይችልም ዳሩ ግን ቆሻሻ አስተሳሰብና አሰራር ያላቸው ያገር መሪዎች የሚያስተዳዱሯቸውን አገሮቻቸውን ያቆሽሻሉ ዜጎቻቸውም እስር ቤት ታሰረው እንደሚሰቃዩ መስሎ እንዲሰማቸው ይሰራሉ። አሁን መሬት ላይ የምናየውም ይኸው ነው። ለመሆኑ የኢሃደግ ዘመን አመራርን ሳይጨምር ባለፉት 150 ዓመታት ኢትዮጵያን የመሩ አመራሮች ተመሳሳይነት ምን ይመስላል?

ከምኒልክ በፊት የነበረችውን ኢትዮጵያ ትተን ንጉሥ ምኒልክ ለህዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች ለሰብአዊነትም ከነበረው የቆሸሸ አስተሳሰብ በመነሳት የዎንዶችን ብልትና የሴቶችን ጡት በመቁረጥ፣ እሱን በማይመስሉት ሕዝቦች ላይ ሰቆቃ በመስደድ ተጠፍጥፋ የተሰራች የሚኒሊኳ ኢትዮጵያ ናት አሁን ያለችው። የንጉሥ ምኒሊክ ቆሻሻ አስተሳሰብና ፖለቲካ አፄ ዮሃንስን የሚዋጋበት መሳርያ ለማግኘት በለውጡ ጂቡቲን ለፈረንሳይ አሳልፎ እንደሰጠ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ ሕዝብን ለማወናበድና እራሱን ጻድቅ ለማስመሰል የጂቡቲ መሄድ ከትዮ-ጂቡቲ ባቡር ዝርጋታ ጋር ሊያይዘው ሙከራ አድርጓል።

ንጉሥ ሚኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የመሆን ህልም ስለነበረው ቆሻሻ አስተሳሰብ ቀጣይ ሥራው ከግብጽ፣ ከእንግሊዝና ከጣልያን ጋር በመሆን ባሴሩው ሴራ ደርቡሾች ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው ገብተው ውግያ እንዲከፍቱና አፄ ዮሓንስም ሄደው በሚዋጉበት ወቅት በደርቡሾች ካልተገደሉ ንጉሥ ሚኒልክ አስርጎ ባስገባቸው ወታደርች ዮሃንስ እንዲገደሉ አደረገና ንጉሠ ንገሥት የመሆን ህልሙን አሳካ። ምኒሊክ አፄ ከሆነ በኋላ በፍጥነት ባገር ላይ አራት ታላላቅ ክህደቶችን ፈጽሟል። አንዱ የኢትዮጵያ ግዛትና መሬት የነበረው ከሰላ (ቦገሳ) በመባል የሚታወቀው ሰፊ አውራጃ በዛን ጊዜ ከምእራብ መረብ ምላሽ ግዛት (ያሁኑ ኤርትራ) ቆርሶ በወቅቱ በንግሊዝና በግብጽ ትተዳደር ለነበረቺው ሱዳን ሰጥቷል። ሁለተኛው ደግሞ ዙፋኑን ከተጎናጸፈ ብኋላ ንጉሠ ነገሥት የመሆን ህልሙ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት ግብፆች ውለታ ለምክፋል ግብፆች ለዘመናት ትፈልገው የነበረውን ኢትዮጵያ ባብይ ወንዝ ላይ ግድብ ላለመገንባት የሚያስር እኤእ 1902 ዓ ም ስምምነት ተፈራረመ። ሶስተኛው የራሱ አገር የሆነውን ትግራይን ስልጣኔን ሊቀናቀኑኝ ይችላሉ በሚል ሰበበ ኃይላቸውን ለማዳከምና ለመስበር ሲል ሁለት ላይ ገምሶ አንዱን ክፋል ለጣልያን የሚሰጥ የውጫሌውና የፈረስ ማይ ስምምነች ናቸው። አራተኛ ምኒልክ የንግድ መውጫ መግቢያ ሳያሳስበው ከነ ጠቅላላ የባህር ጠረፉ ለጣልያን የሸጠበት እኤአ 1902 እና 1908 ዓ ም ናቸው። የተሸጠውም የትግራይ አካል ብሎም የኢትዮጵያ ግዛት ኤርትራ የሚል ስም ተሰጠው። የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽንም በ 1902/1908 አ ም እኤእ በተደረሰው የድንበር ማካለል ስምምነት ከጣልያን ለምኒልክ የገንዘብ ክፍያ እንደተደረገ ተጠቅሷል። ቆሻሻ አስተሳሰብ ያሰከረው ምኒልክ በዚህ ብቻ አላበቃም። አንጨፈለቅም ባሉት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ባልሆኑ የትግራይና የየኦሮሞ ጨምሮ በህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋና የዘር ማፅዳት ዘመቻ በስፋትና በጥልቀት አካሂዷል። እነዚህ በሙሉ ታልቅ ያገር ክህደቶች ናቸው።

አፄ ኃይል ሥላሴ ቢሆኑም የምኒልክን ያህል አይሁን እንጂ በትግራይ በጎጃምና በባሌ ክፍላተ ሐገሮች ሰፋፊ ጭፍጨፋ አካሂደዋል በተለይም በትግራይ ክፍለ ሐገር ሙሉውን በራያና ቆቦ አውራጃ፣ በእንደርታ አውራጃና በከፊሉ ተምቤን አውራጃ መጠነ ሰፊ ያየር ጥቃት ፈጽመዋል። በተለይም በጨካኙና አረመኔው ራስ አበበ አረጋይ የተመራው የእግረኛ ሠራዊት በእንደርታና በራያ አውራጃ ዎች ሕዝብና እንስሣት ላይ ክፍተኛ መቅሰፍት አውርዷል። ይባስ ብሎም አፄ ኃይል ሥላሴ የወሎ ገዢ የነበረው ልጃቸው አልጋ ወራሽ አስፋወሰን የወሎ መሬት የቆዳ ስፋት አነሰኝ ስላለ የትግራይ መሬት የሆነውን የራያኖ ቆቦ ከትግራይ ተቆርሶ ወደ ወሎ እንዲካለል አድርገዋል።

ደርግ በመባል የሚታወቀው የወታደር ስብስብ አመራርም ከሱ በፊት እንደነበሩት ሁሉ የሰቆቃና የሽብር አመራር ስልትን ነው የተከተለው። የደርግ ቆሻሻ አስተሳሰብና አሠራርም ተገቢ የሆኑ የመብት ጥያቄዎችን ባነሱ በአዲስ አበባና ባብዛኛው የክፍለ ሃገራት ዋና ከተሞች በሚገኙ ተማሪዎችና ወጣቶች ላይ ቀይ ሽብር በሚል የጭፍጨፋ መርህ እንዲታሰሩ፣ እንዲደበደቡና፣ ባሰቃቂ ኔታም እንዲገደሉተደርጓል። የኤርትራና የትግራይ ከተሞች፣መንደሮች፣ ተራሮች፣ ኮረብቶች፣ ሜዳዎችም ጭምር በያኔው ሶቭየት ሕብረት፣ ምስራቅ ጀርመን፣ ሰሜን ኮርያ፣ ኩባ፣ ወዘተ....በተለያየ ተሳትፎ በመታገዝ በምድር በታንክና በመድፍ በሰማይ ደግሞ በቦምብ (በተከለከለ ናፓልም ጭምር) አቃጥለዋል፣ አጋይተዋል፣ አፍርሰዋል፣ ብሰዎችና በእንሦሶች ላይም ብዙ እልቂት አድርሰዋል። የበሻሻው ከደርግ የማመሳስል ዘገባ በኢትዮ ፎረም (Ethio Forum -- https://www.youtube.com/watch?v=bDjVnG5yOfU) የዩትዩብ የ27/05/2021 ስርጭቱ ትንታሌ ስለሰጠበት ይኽንኑ ማየት ስለሚቻል እዚህ መድገም ስለሚመስል አልገፋበትም።

Videos From Around The World

የበሻሻ ቆሻሻ እላይ ከተጠቀሱት ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር ንግስናን ከመፈለግና ህዝብን ከመጨፍጭፍ ሌላ ብዙ የሚአመሳስላቸው ነገር የለም። እንዳውም የበሻሻው ከአፄውና ከመንግስቱ ኃይለማርያም አብዝቶ የሚለይበት ባገር ሉአላዊነት ላይ የነበራቸው አቋም ፍጹም ተቃራኒ መሆኑ ነው። አፄ ኃይለ ሥላሴና ኮሎኔል መንግስቱ ባገር አንድነትና ሉአላዊነት በፍጹም ላፍታም ቢሆን ሳይይደራደሩ ያገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ብዙ የደከሙ ሲሆን አሁን ያለው መሪ ግን ያገሪቷን ሉአላዊነት በብርሃን ፍጥነትና በሚአስደነግጥ ሁነታ እንዳውም በራሱ ፍላጎትና ጥያቄ ኢትዮጵያ በባእዳን እንድትደፈር፣ እንድትንኮታኮት፣ እንድትዋረድ፣ እንድትናቅና እንድትወረር አድርጓል። አፄ ኃይለ ሥላሴ ባካባቢያቸው ካሉ አገሮች፣ ከመላው የአፍሪካ ብሎም ከተቀረው አለም አገሮች ጋር ጥሩ የዲፕሎማሲና የወዳጅነት ግንኙነት ለመፍጠር ብዙ ጥረት አድርገው በዘመኑም ተሳክቶላቸውብዙ ያፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን እንዲያደንቋትና እንዲናፍቋት የቻሉም እንዲጎበኟት አድርገዋል። የመንግስቱ አስተዳደር በጦርነት ተጠምዶ ስለነበረ ይኸ ነው የሚባል የዲፕሎማሲ ሥራ አልተሰራም። እንዳውም ኮሎኔል መንግስቱ ለኢትዮጵያ ያበረከተው ቢኖር ስሟ የድህነት ተምሳሌት ሁኖ በኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት እንዲሰፍር ነው።

የበሻሻው ካፄ ምኒሊክ ጋር ከውሸት በስተቀረ ተመሳስይ የአመፅ ባህሪ ያላቸው ግን ሁለቱም በተለያዩ ዘመናት የኖሩና የኢትዮጵያን እጣ ፈንታን የወሰኑ ብየ ብገልጸው እመርጣለሁ። እንደሚኒሊክ ሁሉ የበሻሻውም ንጉሥ የመሆን ህልም አንግቦ ነው የተነሳው። እንግዲህ እሱ እንደሚለው እናቴ በ7ዓመቴ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኝ ነበር ብሎ ህዝብን ለማወናበድ ሞክሯል። ክራሱ አንደበት እንደሰማነው እናቱ የድሃ ድሃ የነበረች ናት። ታድያ ለሆዷ ከማሰብ ውጭ ስለንግሥና ምን እምታውቀው ኑሮ ነው ንግሥናን ልትተነብይለት ልትመኝለት የምትችለው ወሬ ለማጣፈጫ የፈጠረው ስልት ካልሆነ በስተቀር? ደግሞም ልብ በሉ፣ እሱ ደጋግሞ እንዳለው ንጉሥ ትሆናለህ ነው እንጂ የኢትዮጵያ ንጉሥ ትሆናለህ አለችኝ የሚል እስካሁኗ አልወጣውም። በበኩሌ አልሰማሁም። ምናልባትም ብላው ከሆነ ድሮ ልጆች ሆነን ፖሊስና ሌባ እንደምንጫወተው ተመሳስይ የንጉሥ ገጸ ባህሪ ያለው የልጆች ጨዋታ ኖሮ እንደሆነ እሱ እዛ የልጆች ጨዋታ የንጉሥ ገጽ ባህሪ ተላብሶ የሚጫወተው ሊሆን የችላል። በርግጠኝነት መገመት የሚቻለው እናቱ ውሸት አስተምራው ሊሆን ይችላል የሚለውን ነው ምክኛቱም ውሸት አብሮት ያደገ እንደ ምርጥ ክህሎት አርጎ የወሰደውና የተካነበት ይመስላልና ነው። እኔ እንደሚመስለኝ ንጉሥ የመሆን ህልሙ የሚመነጨው ከመጠን ያለፈው ሰይጣናዊ ጭካኔውና ብዛት ያለው ሰው ለመግደል ካለው ፍላጎትና ፍቅር ነው። እንዲህ ዓይነት ባህርይ የተላበሰ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ አገርን ለመምራት ንጹህ መሆንን፣ ሰባዊነት የተላበሰ፣ በዲሞችራሲና በእኩልነት የሚያምን ና የህግ ተገዢ መሆንም ይጠይቃል። ለበሻሻው ይህ እንኳን ሊታሰብ ጭራሽ ለጆሮ የማይጥም ነው። ሆኖም ንጉሥ ቢሆን ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ እንዲሉ ንግሥናን ከተጎናፀፈ በኋላ ሰይጣናዊ ህልሙ የሆነውን የፈለገውን የማሰርና የመግደል በደሎችን ካለመከሰስ ለማሳካት ከንግሥና ውጭ አይታለምም። እንደምናስታውሰው ደጋግሞ ሚልዮኖች ይሞታሉ ኢትዮጵያ ግን ትኖራለች ያለው እንዲሁ ባጋጣሚ ሳይሆን በሚገባ ያሰበበት ስለነበረ ነው።

ምኒልክ ወደ ስልጣን የመጣው አካባቢውን በማመስና ተንኮል በተሞላው ጠላቶቹን አንድ ባንድ በኃይል በማስወገድ ነው። የበሻሻው እንደጠላት የወሰደው ግ ን እሱ ራሱ ያደገበት፣ የኖረበት፣ ላወግ ለማዕረግ የደረሰበት፣ የተሾመበትንና የተሸለመበትን ፓርቲና አመራሩን ስለነበረ እግቡ ለመድረስ ረጂም ጉዞ መጓዝ ነበረበት። እናም በስለላው ተቋም ውስጥ የነበረውን ስልጣን ተጠቅሞ እራሱንና አገሩን በመሸጥ ለቀለም አብዮት ማሳኪያ ባገኘው ገንዘብ ተጠቅሞ ተደጋጋሚና አውዳሚ አመጾችን መጀመርያ በአማራ ክልል የትግራይ ተወላጆች ላይ ብኋላም በኦሮምያ ክልልና በአዲሳበባ አካባቢ አመጾችንና ጭፍጨፋዎችን አካሄደ። ይባስ ብሎም ባገሪቱ የማይታወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰን ክልል ጥያቄ በሚል ስም በኦሮምያና የኢትዮጵያ ሶማልያ ክልሎች መካከል የበሻሻው ዋና ተወናይ በሆነበት ቲም ለማ በሚባለው ስብስብ በኩል በሰውና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰና ከሶስት ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ከቤታቸውና ከቄያቸው መናፈቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት ከፈተ። ፕላኑ በወቅቱ የነበረውን መንግስትን ማጨናነቅ ነበርና መንግስትም ተጨናንቆ ግን ደግሞ ሃላፊነት በተሞላው፣ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ባሟላና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በሚል ምንም እንኳን ህገመንግስቱ የሚፈቅደውን ባያሟላ ከስልጣን ወርዶ እስከ ቀጣዩ የምርጫ ዘመን የበሻሻውን ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ እንዲመራ ካለምንም ኮሽታ መረጠው። እንግዲህ የዚህ ሰው ቆሻሻ ያመራር ስልትና ድርጊቶች ከብዙው በጥቂቱ ከምኒልክ ጋር ይመሳሰላሉ የምላቸው የሚከተሉት ናቸው።

        ብዙም አልቆየም ወደ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከሚባሉት አገሮች መካከል አንዷ ከሆነችው ግብፅ ተጉዞ ልክ ምኒልክ እንዳደረገው ኢትዮጵያ የባልቤትነትና ሕጋዊ መብቷን ተጠቅማ ባባይ ግድብ ላይ በምትገነባው ግድብ በተያያዘ ለኢትዮጵያ ህዝብና ፓርላማ፣ ለኢትዮጵያ የፌደራሽን ምክርቤትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ላገሪቱ የደህንነትና የጸጥታ ኃይሎች ያልተነገረና ግልፅ ያልሆና ሚስጥራዊ ስምምነት በመፈጸም ያገሪቱን ጥቅም ለግብፅ አሳልፎ ሰጠ እናም ባገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈፀመ።

        ከግብፅም ተመልሶ የግድቡን ኝባታ ፕሮጀችት ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን እንቁና ብርቅየው ያገርና የወገን ኩራት የሆኑት አቶ ስመኘው በቀለ እንዲገደሉ ሆነና ገዳያቸውም የሞቱበት ምክን ያትም እንዳይታወቅ ተድብስብሶ ፋይሉ በፍጥነት እንዲዘጋ ሆነ።

        ቀጣዩ ጉዞ ወደ አረብ ኤሚሬትና ወደ ሳኡዲ አራብያ ሆነና በአረቦቹ አሸማጋይነት በኢትዮጵያና በኤርትራ የኦርቅ ስምምነት አደረገ። የዚህ ስምምነት ምንነትና ይዘት የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ተወካዮች ምክር ቤቶች፣ የፀጥታ ኃይሎችም ሆኑ ያገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አያውቁትም። በኤርትራ በኩል እንደዚሁ። ያገሪቱ ሕገ መንግስትም ኢትዮጵያ ለምትገባቸው ማንኛውም ስምምነቶች የህዝብ ተወካዮች ማወቅና ማፅደቅ አለባቸው ይላል እናም ልክ እያቱ ምኒልክ ክጣልያን ጋር በፈጸመው የስምምነት ክህደት የበሻሻውም ከፍተኛ ያገር ክህደት ፈፅሟል።

        ምኒልክ አሁን ያለችውን የኢትዮጵያ ቅርጽ ለማስያዝ ሰራዊቱን በየአቅጣጫው አሰማርቶና ጨፍልቆ በማምበርከክ ሲሆን የበሻሻው ቆሻሻም በተመሳሳይ ሠራዊቱን ወደ ሶማልያ ክልል ልኮና ኃይል ተጠቅሞ የክልሉን ፕሬዚደንት አስሮ ሌሎች ክልሎችም ሰጥ ለጥ ብላችሁ ካልተገዛቹህ የሶማሊያ ክልል እጣ ፈንታ ይደገጥማችኋል ብሎ በማስፈራራት ከትግራይ ክልል በስተቀር ሁሉንም በቁጥጥሩ ስር አዋለ። ይህም ሕገ መንግስቱን የሚጻረር ስለሆነ ከፍተኛ ያገር ክህደት ተብሎ ይወሰዳል።

        በተጨማሪ ምኒልክ የከሰላን አውራጃ ከኢትዮጵያ ቆርሶ ከላይ እንደተጠቀሰው ለሱዳን እንደሰጠ ሁሉ የበሻሻውም ከም ዕራብ በኩል የአልፋሽጋን አካባቢ ከአማራ ክልል ቆርሶ ለሱዳን በመስጠት እንዲሁም በስሜኑ በኩል ከትግራይ ክልል ሰፊ የሚባል መሬት ለኤርትራ በመስጠት ባገር ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈፅሟል።

        እንደ ምኒልክ ሁሉ በትግራይ (በኦሮሞም ጭምር ከመጠን ስፋትና ጥልቀት ልዩነት በስተቀር) የዘር ማጥፍት ወንጀል ፈፅሟል።

        በተለይም ስልጣን በጨበጠ ባጭር ግዜ ውስጥ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከአማራ ክልል ጋር የሚአገናኙትን መንገዶች በመዝጋት የንግድ ልውውጥ እንዳይደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር ተጠቅሞ በክልሉ ድህነት እንዲስፋፋ አድርጓል። በተለይም ድህነቱ ዘለቄታ እንዲኖረው ታስቦ የጋማና የቀንድ ክብቶቹ ባማራና በኤርትራ ተዘርፈዋል አልያም ተገድለዋል። ይህም ምኒልክ በትግራይ ላይ ከፈጸመው ተመሳሳይነት አለው።

        ለትግራይ ክልል የሚላከውን ዓመታዊ በጀት በማቆም፣ ወደ ክልሉ ካገር ውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ምንም ዓይነት የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዳይደረግ፣ ዲፕሎማቶችም ሆኑ ቱሪስቶች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ካውሮፕላን ጭምር ተሳፋሪዎችን በመከልከል ይኽ ነው የማይባል የህዝብ መብት፣ የሕገ መንግስት ጥሰትና ያገር ክህደት ፈጽሟል።

        ባሁኑ ጊዜ ዓለምን እያስጭነቀና የብዙ የዓለም ሕዝብ ሕይወት እየቀዘፈ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሚሆን ከለጋሽ አገሮችና ከዓለም የጤና ጥበቃ የተላከውን ቆሳቁስ በመከልከል በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል ፈፅሟል። ይህም ድርጊት በሚኒሊክ ዘመን በትግራይ አጋጥሞ ከነበረውና ሚኒልክም ትግራይን ለመጨፍለቅ የተጠቀመበት እስከ 90% የሚሆነውን የቀንድ ከብት የጨረሰው የከብት በሽታ (rinderpest) ተመሳስይነት አለው።

        የበሻሻው ቆሻሻ ሆነ ብሎ በወቅቱ አጋጥሞ የማያውቅ ጭራሽ በመገናኛ ብዙሃን ባንደበቱመደመር በትክክል የተረድ ብሎ ያሞካሸው እጅግ ግዙፍ ያንበጣ መንጋ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ያንበጣ መከላከያ በመከልከል ትግራይ ያለው ሰብል ከተቻለ ሙሉ በሙሉ እንዲወድምና የትግራይ ሕዝብ ወደ ድህነት አረንቋ እንዲገባ ለማድረግ ካላንዳች ሃፍረት ተንቀሳቅሷል። ካንብጣ መንጋ የተረፈውን ያልተሰበሰበ ሰብል ደግሞ ምኒልክ እንዳደረገው የበሻሻውም በሳት አጋይቷል።

        የበሻሻውና ምኒልክ የሚያመሳስላቸው ላቅመ ሔዋን ባልደረሱ ህፃናትና ሴቶች ላይ ያደረሱት ይኸ ነው የማይባል የአስገድዶ መድፈርና አመጽ ነው። ይኸ ወንጀል በትግራይ ሴቶች ላይ በስፋት እየተደረገ ያለና ማቆምያ የሌለው በደልና ወንጀል ነው። የሰላም ሚኒስቴር ተብየዋ የሰላም ሳይሆን የጦርና የነውጥ ሚኒስቴር እንደሆነች አስመስክራለችና ከሷ በጎ ነገር ለትግራይም ሆነ ለኦሮሞ ህዝቦች ተጎጂዎች የምንጠብቀው አይኖርም። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን የሴቶች መብት ተሟጋችና ጠበቃ ነኝ የምትለዋ የፍትህ ሚኒስትሯ በአስር ሺዎች ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ሰለባና አካለ ስንኩላን ሲሆኑ ምንም አለማለቷ ነው። ታድያ ያ ተሟጋችነትዋ የት ሟሟ? እንዲያውስ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንዲሉ እሷምአልነበረች እንዴ ባንድ ወቅት አሜሪካ ባንዷ ክልልዋ (state) የሕግ ማስከበር በሚል ሰራዊት አስገብታ የገጠማትን ችግር ፈትታ ነበርና እኛም አገር የሕግ ማስከበር በሚል ሽፋን በትግራይ ላይ ጦርነት ማካሄድ ይቻላል ብላ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ምክረ ህሳብ የሰጠች?

        ሌላው ምኒልክ በትግራይ ብዙ መንደሮችን አቃጥሏል ሰፋፊ ደኖችንም አውድሟል። ይኽ ነው የሚባል መሰረት ልማት በወቅቱ ስላልነበረ እንጂ መሰረተ ልማቶችን ከማውደም ይታቀባል ተብሎም አይገመትም። የበሻሻው ግን በትግራይ ብዛት ያለው ቤትና ንብረት አውድሟል አቃጥሏል። ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የጤና ጣብያዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የመንግስትና የግል ኩባን ያዎች፣ መንገዶች፣ ወዘተ... እንዲዘረፉ እንዲፈርሱና እንዲቃጠሉ በዕቅድ አድርጓል። የትግራይ ሕዝብ ውንድ ሰት ህጻን ሽማግሌ ሳይል ከቀየው ተፈናቅሎና ሸሽቶ በዱር በገደሉ ተበትኖ ላውሬ ሲሳይ አርጎታል። በጠቅላላ የትግራይን ክልል ወደ ምድራዊት ሲዖል በመቀየር በሕዝብና በአገር ታላቅ ክህደት ፈጽሟል።

        የበሻሻ ቆሻሻው ከቀዳሚዎቹ የማያመሳስሉት የራሱ የሆኑ ብቸኛ ባህርያቱ ውሸት፣ ማጭበርበር፣ ማወናበድና ክህደት የመሳሰሉት አስጸያፊ ድርጊቶቹ ናቸው። ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ በዙርያው ካሉት ጀምሮ እስከ ታች በተዋረድ እሱ በሚያሰማው የውሽት ክምር ደንዝዘው ብሎም ከዕውቀት ማነስና ከሃፍረተቢስነቱ የተነሳ ከሌሎች እየኮረጀ የራሱ በማስመሰል ያለቦታቸው ለማይመለከተቸው የሚወረውራቸውን ቃላቶችና ስንኞች እንደገደል ማሚቶ በማስተጋባት ተጠምደዋል። ከዚህም የተነሳ ባሁኑ ወቅት የዓለም ሕብረሰብ መነጋገርያ የሆነው እንዴት ያንዲት አገር ፕሬዚደንቷ፣ ጠክላይ ሚኒስትሯ፣ መላው የፓርላማ አባሎቿ፣ መላው የፈዴረሽን አባሎቿ፣ መላው የካቢኔ አባሎቿ እንዲሁም በተዋረድ በተለያዩ እርከኖች የሚገኙ አመራሮቿ፣ መላው በተለያዩ የዓለም አገራት በተከፈቱት ያገሪቱ ኢምባሲዎች በሚገኙት ዲፕሎማቶቿ፣ መላው በከፍተኛና በመካከለኛ አመራር ላይ የሚገኙት የመከላከያ፣ የጸጥታና የደህንነት አባሎቿ፣ መላው በመንግስት ይዞታ ስር በሚግኙት የመገናኛ አውታሮቿ፣ ወዘተ.... ዋሾዎች መሆን ቻሉ? የሚለው ነው። በርግጥ የሚያስደነግጥ ነው።

        ሌላው ዓለምን ያስደመመ ነገር ቢኖር በሕገወጥ መንገድ እራሱን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብሎም የዓለምን ሕዝብ በውሸት በማጭበርበርና በማወናበድ ስልጣን የጨበጠው የበሻሻው ቆሻሻ በራሱ መሬቴ ሕዝቤ በሚለው በትግራይ ላይ የሶስት የውጭ ሓገራት ቀጥተኛ የሚታዩና የሚዳሰሱ ሌሎችም አገሮች ቀጥተኛ ያልሆኑ የማይታዩና የማይዳሰሱ ተሳትፎ የዘር ማጥፋት ነው። ለነገሩ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ኬንያም በትግራይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እንዲሳተፉ ሰራዊት እንዲልኩ ተጠይቀው ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ነው እንጂ ሊያሰፋው ፍላጎት ነበረው።

        በመጭረሻም ብልጽግና የሚባለው የወንጀለኞችና (ብዙዎቹ ውንጀላቸው በፍርድቤት በማያወላዳ ማስረጃና የእምነት ቃላቸው የተፈረደባቸው የነበሩ ስለሆነ ነው) የደናቁርት እንዲሁም ጥቂት እውቀት አላቸው የሚባሉ ካሉም በሆዳቸው የሚያስቡና ለሆዳቸው ያደሩ ስብስብ ሰብስቦ ምርጫ ሳይካሄድ ገና በገናው እንዳሸነፈና ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ክሱ በስተቀር ማንም እንደማይሆን እሱን ለማስወገድ የሚመጣ ካለ ግን ታላቅ የሰው እልቂት ተደርጎም ቢሆን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለሌላ አሳልፎ እንደማይሰጥ ነገረን። ይህ ቆሻሻ አስተሳሰቡ እላይ እንደጠቀስኩት ብዙ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ያለው መሆኑን ደጋግሞ አረጋግጦልናል። ይኸን ቆሻሻ አስተሳሰብ እንግቦ የተነሳ መሪ ነኝ የሚል የሰው ልጅ ነው ለማለት አቅም ይጎድለኛል። ሆኖም አስተሳሰቡ ሰይጣናዊ በመሆኑ ምናልባትም ባሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በሰይጣኖች ማለትም በሉሲፈር የምትመራ ሆናለች። ሉሲፈር የበሻሻውን መስሎ ይሆን አራት ኪሎ የገባው? ለመሆኑ ይኸ አስር ዓመት ያንድ ምርጫ የስልጣን ዘመን ነው ወይስ የሁለት? ሕገ መንግስቱ ያንድ የምርጫ ስልጣን ዘመን አምስት ዓመት ነው ብሎ ስለገደበው እንግዲህ አስር ዓምቱ የሁለት የምርጫ ስልጣን ዘመን ነው። ታድያ እሺ እሱ እንደሚለው ያሁኑን ምርጫ በወጠነው መንገድ ቢሳካለት የሁለተኛውን አምስት ዓመት ምርጫ ገና ካሁኑ ማሸነፉን እንዴት እርግጠኛ ሆኖ ሊናገር ይችላል?

ኦርዮን (orion.demame@gmail.com )

 

Back to Front Page