Back to Front Page

አረጋዊ በርሀ፥ ዶሮ ሲሉ ሰምታ ሞተች እጢስ ገብታ

አረጋዊ በርሀ፥ ዶሮ ሲሉ ሰምታ ሞተች እጢስ ገብታ

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል (ስትራቴጂስት) 02-08-21

 

የፖለቲካ መሪዎች እምነት የማይጣልባቸው፣ የሚፈልጉትን ለማግኘትም የማፈነቅሉት ድንጋይ የማይቆፍሩት ጉድጓድ እንደሌላቸውና ክፉኛ የመዋሸት ባህሪይ እንዳላቸውም በብዙሓኑ ማህበረሰብ ዘንድ የታወቀ ቢሆንም፤ የፖለቲካ መሪዎች እንዴትና ለምን እንደሚዋሹ ግንዛቤ ያለው ዜጋ ግን እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቆማሉ። የፖለቲካ መሪዎች ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ በማለት ውሸት የሚያስተጋቡበት ምክንያት በዋናነት ፖለቲከኞቹ ስለሚመሩት ህዝብ ግድ ስለሌላቸውና ደንታ ቢሶች ስለሆኑ ነው ተብሎ ይታመናል። መጽሐፍ፥ “ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል” እንዲል፤ በመቀጠል፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ህዝብ ላይ ለፈጸመውና እየፈጸመው ላለው ወንጀል እንደ ምክንያት፥ የተጠቀመበት “የሰሜን ዕዝ ተጠቃ” የሚለው ልበ ወልድ በታሪክ መነጽር እንመለከታለን።

 

አሜሪካ ግዛት የማስፋፋት ህቡዕ አጀንዳዋ እውን ለማድረግ የበቃችው

“መርከቤ ተጠቃች” በሚል ሰበብ በስፔይን ላይ በከፈተችው ጦርነት ነበር

 

እ.አ.አ በ1898 ዓ/ም በአሜሪካና በስፔይን (Spanish–American War) መካከል የተካሄደው ጦርነት ዋና መንስኤ ተብሎ የሚታወቀው በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበሩ ዊሊያም ማኪንሌይ “የስፔይን ታጣቂዎች በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ወታደራዊ ጥቃት” ፈጽመዋል ሲሉ ባሰሙት ክስ የተቀሰቀሰ ጦርነት እንደ ነበር ከታሪክ እንማራለን። ከነተረቱ፥ “ሊበልዋት የፈለጉ አሞራን ጃግራ ይሏታል” እንደሚባለው በጦር መርከቧ ላይ ደረሰ የተባለው ጥቃት የስፔይን ታጣቂዎች ያደረሱት ጉዳት ሳይሆን አሜሪካ በስፔን ላይ ያጠመደችው የፖለቲካ ሴራ እንደ ነበር ‘አሜሪካን-ሂስትሪ’ ላጠና/ለተማረ ሰው ግልጽ ነው። “ጥቃት ተሰንዝሮብኛል” ከሚለው የአሜሪካ ክስ ጀርባ የነበረ አጀንዳም ቢሆን በዋናነት ግዛትን የማስፋፈት አጀንዳ እንደነበርና ይህን አጀንዳ ለማሳካትም አሜሪካ “የጦር መርከቤ በስፔይን ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶበታል” ስትል ሐሰተኛ ክስ በማስተጋባት የከፈተችው ጦርነት፥ የስፔን ቅኝ ግዛት በአካባቢው እንዲያበቃ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ ምዕራብ ፓስፊክና የላቲን አሜሪካ ግዛቶች በአሜሪካ ቁጥጥር ስር እንዲውል ምክንያት ሆኗል።

 

በኢራቅ የመንግሥት ግልበጣ አጀንዳ የተከናወነው

ሳዳም “ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አለው” በሚል የሐሰት ድርሰት ነበር

 

Videos From Around The World

አሜሪካ ረጅም ርቀት ተጉዛ ካካሄደችባቸው ወረራዎችና ጦርነቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ በርካታ ጦርነቶች መካከል የቬትናም፣ የአፍጋኒስታንና የኢራቅ ጦርነቶች ይጠቀሳሉ። የኢራቅ ነፃነት (Operation Iraqi Freedom) በሚል ስያሜ የተከናወነ ወታደራዊ ዘመቻ መንስኤ የተመለከትን እንደሆነ፥ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ፥ “የኢራቁ መሪ ሳዳም ሁሴን፥ ለዓለማችንና ለሰው ልጆች በመላ አደገኛ የሆነ ኬሚካላዊና ባዮሎጂካዊ የጅምላ ጨራሽ መሣሪያ (WMD) አለው” የሚል ክስ ነበር። ከዚህ የተነሳም፥ እ.አ.አ መጋቢት 2003 ዓ/ም አሜሪካ የኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ለማውደምና የሳዳም ሁሴን መንግስት ለማስወገድ ጦርነቱን በይፋ አዋጀች። 

 

መቼም የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት አፍ አውጥተው፥ “የኢራቅ መንግስት ስላልተመቸን፣ እኛ ያለው ስለማይሰማና ለቃላችንም ስለማይታዘዝ በዛሬው ዕለት ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገደናል” በማለት የአንዲት ሉዓላዊት አገር መንግስት በጠራራ ጸሐይ ያወድማሉ! ብሎ የሚጠብቅ ባለ አእምሮ ይኖራል ተብሎ አይታመንም። ይህን አእምሮ ስላለው ሰው አልኩ እንጅ ምን ችግር አለበት ብሎ የሚያምን ዜጋ ሊኖር አይችልም ማለት ግን አይደለም። የመንግስት ግልበጣው አጀንዳ በአንጻራዊ መልኩ፥ “ሳዳም ሁሴን እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎችን መታጠቁን ደርሰንበታል። በመሆኑም፥ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጠ የሳዳም ሁሴን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አስቀድመን ካላወደምነው ዓለማችን በአንድ ሃላፊነት የጎደለው አምባገነን መንግስት ታሪክ የምትሆንበት ሰዓት እየተቃረበ ነው” ተብሎ ከጫፍ እስከ ጫፍ በአንድ ድምጽ ሲስተጋባ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት ውሳኔ የማይጋራ ማን ነው? በለው ስቀለው! በማለት ለአሜሪካና ለእንግሊዝ መንግስታት ድጋፉን የማይገልጽስ ማን ነው? እንግዲህ፥ ከ165,000 ሺህ በላይ የኢራቅ ንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ ያደረገ የኢራቅ ጦርነት መጀመሪያና መጨረሻ ይህን መስላል። በመጨረሻም አለ ተብሎ የተነገረና ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ባይገኝም የታሰበው የመንግስት ግልበጣ ግን በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። “ሳዳም ሁሴን ጀምላ ጨራሽ መሳሪያ አለው” በሚል ሽፋን የሳዳም ሁሴን መንግስት ለመገልበጥ ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ አሜሪካ፥ ሁለት ትሪልዮን የአሜርካ ዶላር፤ ወደ 4500 የሚጠጉ የወታደሮችዋ የህይወት ዋጋ አስከፍሏታል።

 

የንጹሀን ዜጎች ደም የሚያስተኛ አይደለምና ጦርነቱን በግንባር ቀደምትነት የመሩ ወታደራዊና ሲቪል ከፍተኛ የዋሽንግተን ባለስልጣናት በውሸት በኢራቅ ላይ የፈጸሙት ግፍ በማስመልከት በተለያዩ ጊዜያት ጸጸታቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። ከእንግሊዙ እኩያቸው ከቶኒ ብሌር ጋር በመምከር ጦርነቱን በፊተውራሪነት በመምራት ኢራቅን ያወደሙ ፕሬዝዳንት ቡሽ ሁለተኛ የምርጫ ዘመናቸው አጠናቅቀው ዋይት ሃውስት በሚሰናበቡት ዋዜማ በዋይት ሃውስ ቆይታቸው ከፈጸሟቸው ትላልቅ ስህተቶች አንዱ በኢራቅ ላይ የከፈቱት ጦርነት መሆኑን በማውሳት በፈጸሙት ድርጊት መጸጸታቸውን ከኤ.ቢ.ሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ በወቅቱ በይፋ ገልጸዋል። የእንግሊዙ ቶኒ ብሌርም እንዲሁ በተመሳሳይ መንገድ ስህተታቸውን አምነዋል። ኒውዮርክ ታይምስ እንዲሁ የዋሽንግተን አስተዳደር የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በማራገብና በማሰራጨት ለጦርነቱ መቀስቀስ ያበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማስመልከት በአደባባይ ይቅርታ ጠይቋል። ይህ ሁሉ የጸጸት ዲስኩር ግን አካላቸው ተቆራርጦ እንዲሁ የሞት ሲሳይ የሆኑ የኢራቅ ንጹሐን ዜጎች ህይወት የሚሰጥ አልሆነም።

 

ሂትለር ፖላንድን የወረረ የራሱ ታጣቂዎች የፖላንድ ወታደራዊ ዩኒፎርም አስለብሶ

በራሱ ግዛት በፈጸመው ጥቃት “ተጠቃሁ” ሲል ባወጀው ጦርነት ነበር

 

ሌላው፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኢሳይያስ አፈወቂና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ጋር በመምከር በትግራይ ላይ ጦር ከማዝመቱ ከአምስት ወራት በፊት ቀደም ብሎ እዚህ አሜሪካን አገር “የምነቅፍብህ ነገር አለኝ” በሚል ርዕስ ባሳተምኩት መጽሐፍ፥ የዓቢይ አህመድ ዓሊ ቆሻሻ ፖለቲካ በሚያትተው ክፍል በገጽ 10 ላይ ያሰፈርኩት ሃሳብ ነው። ይህ፥ “ኦፕሬሽን ሂምለር” ተብሎ የሚታወቀው ዘመቻ በሐሰተኛ ክስ የተቀሰቀሰ ጦርነት ነው። “ኦፖሬሽን ሂምለር” ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በይፋ ከመቀስቀሱ በፊት ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የናዚ አባትና መሪ አዶልፍ ሂትለር ፖላንድን ለመውረር የፈበረከውና የሰራው የሐሰት ድራማና ውንጀላ (false flag) ነበር። ሂትለር ፖላንድን ለመውረር ሲያስብ ብድግ ብሎ የሰው አገር ለመውረር አልተነሳም። ፖላንድ የመውረር አጀንዳ ስላለኝ ለጦርነት ተነስ! በማለትም የጀርመንን ህዝብ ለዘመቻ አላነሳሳም፤ ጦርነትም አልቀሰቀሰምም። ይልቁንም፥ ሂትለር ፖላንድን ለመውረር ስያስብና ለሚወስደው ወታደራዊ እርምጃም ፍትሐዊ መሆኑን ለማሳየት የጀርመንና የዓለም ህዝብ ማሳመን ይጠበቅበታልና ይህን ለማድረግ አንድ ምክር መከረ። ይህ ጥብቅና ምስጢራዊ ምክር (ኦፕሬሽን) በናዚ ልዩ ኃይል (SS) እና የናዚ የደህንነት ክፍል (SD) የተውጣጣ ግብረ ኃይል አማካኝነት ለማከናወን አሴረ። ይህ በአልፍረድ ኗጆክስ (Alfred Naujocks) የሚመራው ግብረ ኃይል ከስር የጀርመን ከላይ ደግሞ የፖላንድ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው በአከባቢው የውሸት ተኩስ በመክፈትና እግረ መንገዳቸውም መጠነኛ የውንብድና ስራ በመስራት በጀርመንና በፖላንድ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የጋሊዊትዝ የሬድዮ ጣቢያ ስርጭት (Gleiwitz station and broadcast) በመቆጣጠርም በፖሊሽ ቋንቋ “የብሮድካስት ጣቢያው በፖላንድ እጅ ወድቋል!” ሲሉ ያውጃሉ።

 

ልብ ይበሉ፥ የፖላንድ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው በገዛ ከተማቸውና የሬድዮ ጣቢያቸው ይህን ሁሉ ግርግርና ውንብድና እየፈጸሙ ያሉ በእውነት የፖላንድ ወታደሮች ሳይሆኑ ሂትለር የፖላንድ መንግስት ለመወንጀል የፖላንድ ወታደራዊ ዩኒፎርም አስለብሶ ያሰማራቸው የራሱ ወታደሮች ናቸው። ጭጉራፍ እራስዋ ገርፋ እራስዋ ትጮኻለች! በሰዓታት ውስጥ የጀርመን የሬዲዮ ጣቢያዎች በጋሊዊትዝ ላይ ስለተፈጠረው ነገር “ሰበር ዜና!” ሲሉ እየተቀባበሉ ይዘግቡታል። ቢቢሲም (BBC) ከምሽቱ 8 ሰዓት አካባቢ የፖላንድ ታጣቂ ኃይሎች በጋሊዊትዝ የሬዲዮ ጣቢያ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውንና የሬድዮ ጣቢያው በመቆጣጠርም በፖላንድ ቋንቋ መግለጫ ማሰራጨት በጀመሩበት በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ ከጀርመን ታጣቂ ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ መክፈታቸውን፤ በርካታ የፖላንድ ወታደሮች መገደላቸውን፤ የሞቱት ቁጥር ግን እስከ አሁን አይታወቅም! ሲል ዜናውን ለመላ ዓለም ያሰራጨዋል። በነገታው ጥዋት ደግሞ ሂትለር ጀርመን በፖላንድ መወረርዋንና የጀርመን ህዝብና መንግሥትም ሉዓላዊነቱን ጠብቆ ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ እንደሚገደድ በማወጅ አስቀድሞ ያቀደውን ፖላንድን የመውረር ህልሙ እውን ለማድረግ ሠራዊቱን አንቀሳቀሰ። ይህ ኦፖሬሽን ከመከናወኑ በፊት ግን የጀርመን መገናኛ ብዙሐን፣ ሂትለርን ጨምሮ ከፍተኛ የናዚ ባለሥልጣናት የፖላንድ መንግስት በፖላንድ ውስጥ የሚኖሩት ጀርመናውያን ላይ ያነጣጠረ የብሔር ማጽዳት ጥቃት ለማካሄድ አመጽ እየቀሰቀሱ ነው! ሲሉ የፖላንድ መንግሥትና ባለሥልጣናት በመወንጀል ከፍተኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ ከፍተው እንደነበር ይታወሳል። በነገራችን ላይ፥ በሬድዮ ጣቢያው ደጃፍ ላይ የፖላንድ ወታደራዊ ዩኒፎርም አስለብሰው የገደልዋቸው ሰዎች በናዚ እስር ቤት ሲማቅቁ የነበሩ እስረኞች ናቸው።

ዶሮ ሲሉ ሰምታ ሞተች እጢስ ገብታ

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ህዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት፥ ሐሰተኛ ክስ መሰረት ያደረገ ለመሆኑ ለማወቅ፥ ቅንነትና ሚዛናዊነት ብቻ ነው የሚጠይቀው። ይህ ማለት፥ ከቂም በቀል የጸዳ፣ እውነትን የተጠማ፣ እውነትን የሚፈልግና በእውነት ደስ የሚለው ልብ ያስፈልገናል። መስማት የምንፈልገው ሳይሆን መስማት የሚያስፈልገንና የሚገባን ለመስማት ራሳችን ያዘጋጀን እንደሆነ ብቻ ነው። “በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ተጽሟል” የሚለው የዐቢይ አህመድ የሐሰት ውንጀላ ከእውነት የራቀ የፈጠራ ክስ ከመሆኑ በላይ በጽሑፌ መግቢያ ላይ ለማስነበብ እንደሞከርኩት ይህን ዓይነቱ ድራማ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሥራ ላይ የዋለና የተነቃበት ትርክት ለመሆኑ ማወቅ አስፈላጊ ነው።

 

ሌላው ይቅር፥ ዐቢይ አህመድ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት፤ ዓይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ የምክር ቤቱ አባላት በሰበሰበበት ወቅት፥ ውሸት ፋይል የለውም! እንደሚባለው፤ የፓርላማው አባላት ያቀረቡት ጥያቄና ልዑል እግዚአብሔር አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ ያናገረው ሐቅ (ራሱ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የሰጠው ምላሽ) በጥሞና ማዳመጥ ብቻውን በቂ ነው “እናንተ ዘገያቹ ያላችሁት፥ ገና ጊዜ ያስፈልገን ነበር እኛ” እንዲል ጦርነቱ ማን እንደ ጀመረው ይህ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ተጨማሪ ማስረጃ ያስፈለገ እንደሆነም፥ የአማራ ልዩ ሃይል ዋና ሃላፊ ጦርነቱ እንዴት እንደ ተጀመረ የተለመደ ጉራቸውን ሲነፉ የሰጡት ቃል፤ ዲና ሙፍቲ ሱዳንን አስመልክተው በሰጡት ቃል፥ ኢትዮጵያ ትግራይን የመውረር ዝግጅትዋን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅዋንና ትግራይን የሚያዋስን የሱዳን ወሰን በተመለከተ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር አስቀድመም መምከራቸው፤ ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ የጦርነቱ አጠቃላይ ገጽታ በሚናገሩበት ወቅት “በሰሜን ከተኮንቢያ የተነሳ ኃይል” ሲሉ አዳልጧቸው የሰጡት ቃል፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር ትግራይን ለመውረር ያደረገው ቅድመ ዝግጅት ምን ይመስል እንደ ነበር የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ናቸው።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ይህ “ሰሜን ዕዝ ተጠቃ” የሚለው ሐሰተኛ ትርክት በሚገባ ለማስራጨት፤ ጉዳዩን በተመለከተም ከትግራይ ክልል አከባቢ ሊገኝ የሚችለው አንጻራዊ መረጃ እንዳይኖር፥ የክልሉ የኤለክትሪክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ በማድረግ ለጊዜው ልበ-ወለድ ትርክቱን ለመሸጥ ተችሎት ነበር። ዳሩ ግን፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ውሸት ረጅም ርቀት ሳይጓዝ፤ ቀደም ሲል፥ ውሸት ፋይል የለውም! በማለት እንደገለጹኩት የጦርነቱን አጀማመር በተመለከተ ዘርዘር ባለ መልኩ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ የሰጠን ሌላ ማንም ሳይሆን ራሱ ዐቢይ አህመድ ዓሊ። በርግጥ፥ በጥላቻ የሰከረ፣ መስማት የሚፈልገውን ብቻ ለመስማት ራሱን ለውሸት አሳልፎ የሰጠ፣ እውነት ሲሰማ ጆሮው የሚያሳክከሰው የአመጽ ሰው ካልሆነ በቀር፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ተገኝቶ የሰጠው ቃል በቅን ልቡና፣ በንጹህ መንፈስና በጥሞና ያዳመጠ ሰው ለጦርነቱ መጀመር እንደ ምክንያት የተነገረው የዐቢይ አህመድ ዓሊ ክስ የለየለት ውሸት መሆኑን የሚጠራጠር ባለ አእምሮ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም።

 

አረጋዊ በርሀ ዓይነቱ በዕድሜ የገፉ አረጋውያን በዚህ ዕድሜያቸው ለምን ይዋሻሉ?

 

ሰዎች ለምን ይዋሻሉ? የሚለው ፍትሐዊ ጥያቄ የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው። በእርግጥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ሶሺዮፓትና ናርሲስት ሰው፥ በሌላ አባባል መዋሸትን ንጹህ አየር የመተንፈስ ያህል የተለማመደ ሰው፥ ባህሪይ፣ ሥነ-ልቡና እና መሻት ለመረዳት መሞከር በራሱ ነፋስን መከተል ያህል ከንቱ ልፋት ነው። ውሸታም ሰው ለምን እንደሚዋሽ በትክክል ለማወቅ ውሸትን የመለየት ያህል ቀላል አይደለም። ሳይንስም ቢሆን ውሸታም ሰው ለመረዳት በምናደርገው ጥረት የላቀ እውቀትም ቢሆን ብቻውን በቂ እንዳይደለ በግልጽ አረጋግጧል። በሌላ አባባል፥ መንፈሳዊ ዓለምን በሚገባ መረዳትና መንፈስን የመለየት ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ እንደሚያስፈልግ በገዳምዳሜ ይጦቁማል፤ “በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው?” እንዲል መጽሐፍ

 

የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሹም አረጋዊ በርሀ ከቀናት በፊት ከአንድ ዩቲዩበር ጋር በነበራቸው ቆይታ “የህወሓት መሪዎች በቀይ ባህር መሳሪያ አስገብተዋል” ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ አባባል፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ላይ ጦርነት የከፈትኩት “ሰሜን ዕዝ ስለተጠቃ ነው” ሲል በአደባባይ የነገረን ሐሰት በተጨባጭ ለማሳመን ስለተሳነው ውሸትን በሌላ ውሸት ለማሳመን የሄደበት ርቀት ማሳያ ነው። ጎበዝ፥ ይህን ዓይነቱ ውሸት ራሱን ችሎ የሚነገር ውሸት ሳይሆን አስቀድሞ የተነገረውን ውሸት እውነት ለማስመሰል የሚነገር ውሸት መሆኑን ልብ ማለቱ አስፈላጊ ነው። የዚህ ዓይነቱ የለየለት ውሸት ዋና ዓላማ፥ በዐቢይ አህመድ ዓሊ የተነገረ ትልቁ ውሸት (“ሰሜን ዕዝ ተጠቃ” የሚለው ልበ-ወለድ) ለማድበስበስና ለመሸፋፈን የሚነገር የፈጠራ ውሸት አካል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። አንድም፥ ናዚዎች “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመሳላልና ግፋበት” እንዲሉ። ጥያቄው ለምን አረጋዊ በርሀ?

 

 

v  አንድ የፖለቲካ ባለሥልጣን፥ በራስ መተማመን ከሌለው፤ ይህ ማለት፥ አለኝ የሚለው የትምህርት ደረጃ ሆነ የስራ ብቃት የማይተማመን ከሆነ፤ አለቃው ለማስደሰትና ለጌታው ያለው ታማኝነት የሚገልጠው ወይም የሚያሳየው ጌታውን በመምሰልና ራሱን ለበርካሽ ተግባራት አሳልፎ በመስጠት ነው። ይኸውም፥ ሐሰተኛ ወሬ ከመፈብረክ እስከ ማሰራጨት፣ ጥቁር ውሸትን ማራገብና አሉባልታን መሰልቀት ቀዳማዊ ስራው በማድረግ የበታች ወይም ባሪያና ተላካኪ መሆኑን ያስመሰክራል። በተጨማሪም፥ አረጋዊ በርሀ ይህን ዓይነቱ ጨርሶ የማይመስል ውሸት በአደባባይ ሲያስተጋቡ ተናጋሪው ባለሥልጣን በዋናነት የአለቃቸው ባህሪይ ነጸብራቅ መሆናቸው ማወቅና ልብም የተነገረው ውሸት ዓላማ አጥርተን እንድናይ ይረዳናል።

 

v  አረጋዊ በርሀ ይህን ዓይነቱ የማይመስል ውሸት ሲያስተጋቡ በዋናነት ሰውዬው አማራነት መመኘታቸው ሲሆን ለጥቆም በትግራዋይነታቸው የሚሰማቸው ሀፍረትና የበታችነት ስሜት ለመሸፈን፣ ብሎም በአማራው ማኅበረሰብ ተቀባይነት ለማግኘት ነው። 

 

v  እኚህ አረጋዊ ባለሥልጣን ይህን ዓይነቱ የለየለት ውሸት ሲያስተጋቡ የትግራይ ህዝብ ይሰማኛል በማለት ሳይሆን፤ ነጩን አጥቁረው ማሩን አምርረው ሲናገሩ ሲሰማ፥ ሳያላምጥ የሚውጥ፣ በሐሰት የተለከፈ፣ እውነት ሲሰማ የሚያንቀው፣ አሉባልተኛ ማኅበረሰብ አለ! ብለው አሳምረው ሲለሚያምኑ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ፥ የህወሓት መሪዎች በቀይ ባህር መሳሪያ አስገብተዋል የሚለው የእኚ አረጋዊ ፖለቲከኛ በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ፤ የሐሰት አባት የተባለው ሰይጣን ሳይቀር ወሬው ሲሰማ በሰውዬው ህሊና ቢስነት መደነቁ የማይቀር ነው።

 

v  ሌላው እንደ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው። እኚህ ሰው (አረጋዊ በርሀ) ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ሊሒቃን ከኢሳይያስ አፈቀርቂና ከመሐድ ፈርማጆ ጋር በመምከር፥ የአፋር፣ የሱማሌ የአማራና የኦሮሞ ሰራዊት በማሰባሰብ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል የመጋፈጥ አቅምና ጉልበት ስለሌላቸው፤ በተጨማሪም ሰውዬው፥ “አረጋዊ በርሀ ንጹሕ ኢትዮጵያዊ! የቁርጥ ቀን ልጅ!” ተብለው ለመወደስ ካላቸው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ አጋጣሚውን ለመጠቀም አስበውበት የሰሩት ስራ እንደሆነ ይታመናል።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com


Back to Front Page