Back to Front Page

የመርገም ጨርቅ የአማራ ልሒቃን ድሮና ዘንድሮ

የመርገም ጨርቅ የአማራ ልሒቃን ድሮና ዘንድሮ

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 07-31-21

 

ትርጓሜ፥ የመርገም ጨርቅ ማለት በኦሪት ሥርዓት መሰረት ያልነጻች ሴት በወር አበባዋ ወቅት የምትጸዳዳበት ጨርቅ ሲሆን ወደ ቆሻሻ መጣያ ስፍራ ሊጣል የሚገባው የረከሰና የተበላሸ ማለት ነው።

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ ለዘመናት በቅጥፈትና በሌብነት፣ በአገር ክህደትና በባንዳነት የተደጎሱ ኩነኔዎች ሆነው ሳሉ የሐሰት አባት የተባለው ሰይጣን የሚስንቅና የሚያስቀና ረጅም የውሻ ምላሳቸው እየወለወሉ በውሸትና በአሉባልታ የሌላቸውና የማይገባቸው ምስል ፈጥረው ህዝብና አገር ሲያወናወዳብዱና ሲያደናግሩ ዛሬ ላይ የደረሱ ሸለፈታሞቹ የአማራ ልሒቃን በትግራይ ህዝብ ላይ በፈጸሙት ወረራና የዘር ማጥፋት ዘመቻ የተገለጠ ወራዳ አጭበርባሪ ማንነታቸው ለመደበቅ እያደረጉት ያለ ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ዓላማው ምን እንደሆነ በግርድፉ ለማብራራትና ለማስቀኘት ያለመ ጽሑፍ ነው።

 

መንደረደሪያ፥ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የተማከለ ሞያዊ ትንተናና ሐተታ ለመስጠት የሚያመች እንዳይደለ በርካታ ባለሞያዎች ይስማማሉ። አንድ መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር የሚመራ ሰው ለተቀመጠበት መንበር የሚመጥን እውቀትና ጥበብ በመሸመት ኃላፊነቱን በመወጣት ፈንታ በዋናነት ሲጠግቡ የሚመርቁ ሲራቡ የሚራገሙ የፕሮቴስታን ሐሰተኛ የሃይማኖት መሪዎችና በተሰፈረላቸው ቀለብ ልክ አፋቸው የሚከፍቱ ዘራፊ ነቢያቶች ሐሰተኛ ትንቢትና ህልም እንዲሁም የአራት ኪሎ የቤተ ክህነት ሞራ ገላጮች፣ ጠጠር ወርዋሪዎችና ኮኮብ ቆጣሪዎች እየተመራ አገር እየተሰባበረችና እየፈራረሰች ይታለኛል ትሻገራለህ፣ ትጥሳለ፣ ትሰብራለ፣ ትለብሳለህ፣ ትሄዳለህ፣ ትወጣለ፣ ታሸንፋለ እያለ ከንቱ የቃላት ጋጋታ ማስተጋባት፣ መለፈፍና በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቁስል ላይ እንጨት መስደድ ቀጥሎበታል። ኢትዮጵያ፥ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ተሰምቶ የማይታወቅ እገሌ/እገሊት እርምጃ ተወሰደበት/ባት እየተባለ ትናንት አብሮህ አንድ መዓድ ላይ ተቀምጦ እንጀራ የቆረሰ ባለንጀራህን በድንጋይ፣ በዱላና በጥይት በመደብደብ በአደባባይ ነፍሱን መውሰድና መግደል ፋሽን ሆኗል። አባባሉም ሲነገር የሚያኮራ ህዝባዊና መንግስታዊ ቋንቋ ሆኗል። የሰላም ሚኒስትር ተብሎ የተቋቋመው መስራያ ቤት ለይቶለት ጸረ ሰላም መስሪያ ቤት ሆኖ የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ሞት ቀጠና ማስዘመት የዕለት ዕለት ተግባሩ አድርጓል። ከሚያዝኑ ሰዎች ጋር ማዘን ኋላቀርነት ሆኖ ዘማሪውም ዘፋኙም ሁሉ በትግራይ ህጻናትና ሽማግሌዎች ሞትና እልቂት በሴት እህቶችቻችንና እናቶቻችን ሰቆቆ ደስታውን ለመግለጽ አንዴ አገሬ ደስ ይበልሽ ሌላ ጊዜ እልል በይ ኢትዮጵያ! እየተባለ በንጹሐን መቃብር ላይ ተቁሞ ሰይጣናዊ ዜማ ማዜም፣ መዝፈንና አስረሽ ምቹ የሚደልቁባት አገር ሆናለች። በዘራችሁ አይደርሰ ማለት ታድያ አሁን ነው።

 

Videos From Around The World

ሐተታ፥ የውሸትና የሽንፈት ፍቺና ትርጓሜ ብቻ ሳይሆን የህይወት ትርጉም ሳይቀር የለወጠ ያልተለወጠና ያልበሰለ የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ እናቴ ነግራኛለች ለሚለው ንጉሥ የመሆን ህልም እውን ለማድረግ የደርግ ሊቀ መንበር የነበሩ ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጥያቄ ለመቀልበስ አንድ ሰውና አንድ ጠብ-መንጃ እስኪቀር ድረስ እዋጋለሁ የሚለው መፎክር በማደሳ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የዙፋኑ ተሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን የኢትዮጵያ ወጣቶች በቀጣይነት የእሳት ራት ማድረግ፣ በአገርና በህዝብ ህልውና ላይ መቆመር አጠናክረው ቀጥለውበታል። ወደ ማይክራፎን ተጠግቶ አፉን በከፈተና በሶሽላ ሚድያ ላይ ብቅ ባለ ቁጥር ውሸትና ቅጠፈት በመንዛትና በማሰራጨት በአሁን ሰዓት በዓለም መድረክ ቀዳሚና ተከታይ የሌለው ጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ከመቐለ የወጣነው የትግራይ ገበሬ እርሻው እንዲያርስ ነው፣ ሌላ ጊዜ ስልታዊ ማፈግፈግ ነው፣ ሲያሻው የጥሞና ጊዜ ላይ ነኝ፣ ሞቅ ሲለው የምንፈልገው በትግራይ ተከማችቶ የነበረ ትጥቅና ስንቅ ማውጣት ትግራይን በሻሻ መድረግ ነበር ይህን ተልዕኳችን ስላሳካን ደግሞ ከመቐለ ወጥተናል፣ ኧረ ሰዎቹ አላማጣ አልፈው ቆቦ ደረሱኮ ሲባል ደግሞ ስትራቲጂካዊ የቦታ ለውጥ ነው ያደረግነው እያለ ሲያወናብድ ይሄው ወያነ ትግራይ ወልዲያና ደባርቅ ተሻግሯል።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከኢምሬት፣ ከሶማሊያ ጋር መክረውና ዘክረው በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙት ወረራ ከትግራይ መሬት ተመንግለው ከወጡ በኋላ የተከናነቡት ሽንፈትና ውርደት፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት አለ ለማለት በማይስችል ሁኔታ ለደረሰባቸው ኪሳራና ውድቀት ለመደበቅና ለመሸፋፈን የትግራይ ገበሬ እርሻው እንዲያርስ ነው የወጣነው እያሉ ሲያጭበረብሩ ሰንብተው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ደግሞ አማራ ሆይ ስማ ገጀራ ያለ ገጀራ ምንሽር የያዝክ ምንሽርን ጓንዴ የታጠቀው ጓንዴህን ተሸክመህ የራስህ ስንቅ ይዘህ ክተት! እያለ ስፍር ቁጥር የሌለው የአማራ ገበሬ መፎርና ቀንበሩን አስጥሎ ለሞትና ለሙርኮ ሲማግድ እየተመለከትን ያለን። ከመቐለ መጣታችን ስትራቴጂክ ነው ሲል የከረመ ሰውዬ ወያነ ትግራይ በአሁን ሰዓት ቆቦ አላማጣና ቆልቦ አልፎ ወልዲያና ላላሊላ፣ በምዕራብ ደባርቅ፣ በአፋር ግንባር የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ደጃፍ ላይ እያንኳኳ ባለበት ሰዓት ውሸትና ቅጥፈት ስንቁ ያደረገ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ስልኩ ሳይቀር ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ ጭጭ ማለቱ ብዙዎችን አስገርሟል፤ በነጋ በጠባ ቁጥር ውሸትን እንደ ወተት መጋት በደለመዱ በኢትዮጵያውያን ዘንድም ነገሩ ታላቅ ፍርሃትና ድንጋጤ ጥሏል። ወገን፥ ከዚህ በላይ ዐይነ መርፌው የጠፋበት ዥንጉርጉር ፖለቲካ ታድያ ከወዴት ቢገኝ ነው?

 

ሸለፈታሞቹ የአማራ ልሒቃን ምኞትና ጸሎት

 

ትናንት፥ ትግራይ ምናችን አይደለችም እንጨብጣታለን እያሉ አደራሽ ውስጥ ተቀምጠው ጠላቸውን እየተጎነጩ ሲፎክሩና ዘራፍ ሲሉ የነበሩ የአማራ ልሒቃን ወያነ ትግራይ አፈር ልሶ አፈሩን አራግፎ ሲነሳ ደግሞ ሰዎቹ በትግራይ ሉኣላዊ ግዛት ሊቀመጡ ቀርቶ የአማራ ክልል ተብሎ በሚታወቀው ስፍራዎች ሳይቀር ይዘውት የተሰለፉት ታንክና ከባድ መሳሪያቸውን ጥለው እግሬ አውጭን ሲሸሹና ሲፈረጥጡ የተረፈች ምላሳቸው ውሸትን መቀባጠርና የባህሪዋ የሆነ መቀደድ አትተውምና የገጠማቸው ሽንፈትና ኪሳራ ላለመቀበል ትናንት አፋቸው ሞልተው ኩራታችን ነው እያሉ ሲመሰክሩለት የነበረው በዐቢይ አህመድ ዓሊ ሿሿ ተሰርተናል አዲሱ የአማርኛ ነጠላ ዜማ ሆናለች። በርግጥ፥ ወያነ ትግራይ የዐቢይ አህመድ ድጋፍ አግኝቶ ነው እንዴ የኤርትራና የሶማሊያ ጨምሮ እልፍ አእላፍ ሰራዊቱ በትግራይ ምድር መዳበሪያ ሆኖ የቀረውና ከትግራይ መንግሎ ያወጣው? ተብሎ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ምላሽ የላቸውም። የአማራ ልሒቃን እኛ ሃያ አምስትና ሰላሳ ሚልዮን ነን ስድስት ሚልዮን ለማይሞላ የትግራይ ህዝብ ደግሞ እያሉ ሲደነፉ ታድያ ሰዎቹ ማንን ተማምነው ነበር? ኦሮሞን? ሲዳማና አፋር? ወይስ ደቡብና ጋምቤላ? መቼም ራሳቸው ተማምነው እንዳይደለ ግለጽ ነው። ለምን? ቢባል በምዕራብ ደባርቅን በደቡብ ወልዲያን ጥለው ባልፈረጠጡና እየገጠማቸው ላለ አሳፋሪ ወታደራዊ ሽንፈትና ውርደት ሌላው ስላልረዳን ነው እየተባለ ኦሮሞን ወይንም ሌላውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተጠያቂ ባላደረጉ ነበር። የትግራይ ህዝብ ምናችን አይደለም ሲሉ የነበሩ ሰዎች እገሌ ስላልረዳን ነው እያሉ ሲያለቃቅሱ ከመስማት በላይስ የሚሳፍር ነገር ምን አለ?

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ የአማራ ልሒቃንና ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን የከተሙ ከበሮ መቺዎቻቸው ከራሽያ ፕሮፓጋንዲስቶች በውጭ ምንዛሬ (በዶላር) እየሸመቱ የሚሰራጩት ሐሰተኛ ውንጀላና በሬ ወለደ አሉባልታ ዋና ዓላማ ሽንፈታቸው ለማካካስ ያለመ ሳይሆን ተሸራርፋ እያለቀች የምትገኘው ነፍሳቸው አትርፈው በሰላም መድረክ ተገኘተው የሚሰጣቸው መድኃኒት ውጠው ሳይነቃባቸው እንዲሁ ለመኖር ያለመ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ሌላው ሁሉ አልቆባቸው፣ ሰው ምን ይለናል ሳይሉና ዓይናቸው ሳያሹ የኤርትራ የጦር መሪ እንዲህ አለ እየተባለ የኤርትራ ፕሮፓጋንዳ ተሸክመው ማላዘን ላይ የተጠመዱበት ኹነት ሰዎቹ የገጠማቸው የሽንፈት ጥግ ምስክርነት ነው። በነገራችን ላይ ጠቢቡ ሰሎሞን፥ ውሻ አነስተኛ አንበሳ ደግሞ የተከበረ እንስሳ አድርጎ በንጽጽር ባሰፈረው አንቀጽ ላይ እንደ አንበሳ የተከበረ ሆኖ ከመሞት እንደ ውሻ አነስተኛ ሆኖ መኖር እንደሚሻል ያመሳጠረው ከሞተ አንበሳ በህይወት ያለ ውሻ ይሻላል በማለት ነው። ነገሩ ወደ ድመትና ወደ አይጥ ካወረድነው ደግሞ ከሞተች ድመት ይልቅ በህይወት ያለች አይጥ እንደሚሻል የሚጠራጠር ሰው ሊኖር አይገባም።

 

የአማራ ልሒቃን፥ በትግራይ የታሪክ አሻራ ላይ ተለጥፈውና ተንጠላጥለው ለዘመናት በዚህ ዋሾ ምላሳቸው ያላሸማቀቁት፣ ያላሳደዱት፣ ያላቆሰሉት፣ ያላሸበሩትና ያላራዱት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተፈልጎ አይገኝም። አንዱን ጋላ ሌላውን ሻንቅላ እያሉ ያልተገባ ስም እየሰጡና ታፔላ እየለጠፉ ሰው በሰውነቱ ሊያገኘው የሚገባ ክብር ገፈውና አሳጥተው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሲያጋፉ የሚታወቁ ግፈኞች የማይገልጻቸው አረምኔዎች (barbarian bully) ለመሆናችን ሁላችን ያስማማል። ዘንድሮ ምን ቢፈጠር ነው ታድያ ሌላውን በማንጓጠጥና በማብጠልጠል የሚታወቁ የምላስ አርበኞች ራሳቸው መጠበቅና መከላከል ተስኗቸው ክልሎች በፈጠራችሁ ድረስሉን! እያሉ ምላሳቸው ከትናጋቸው እስኪጣበቅ ድረስ በመጮህ ላይ የሚገኙ? አማራነት አትንኩኝ ባይነት ነው እያለ በመጮህና በመሸለል የሚታወቁ የአማራ ልሒቃን አይደለም ዙሪያ መለስ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ታግለው በመታገል ሊጠብቁ ቀርቶ ቅዘናሞቹ መሬታቸው ለሱዳን አስረክበው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ያሳስብልኝ እያሉ እናቱ እንደ ሞተችበት ህጻን ልጅ እያለቃቀሱ ያሉ የአገር ማፈሪያዎች ምን ዓይነት ዱላ ቢያርፍባቸው?

 

የአማራ ልሒቃን ዛሬ እንዲህ በአደባባይ በይፋ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስም አንድ በአንድ እየጠሩ ሊያለቃቅሱና፥ ክልሎች ሆይ በፈጠራችሁ ድረሱልን፣ አንድ ሺህም ይሁን አስር ሺህ ልዩ ኃይላችሁን በመላክ ታደጉን፣ በመድኃኔ ዓለም ከጎናችሁ ነን በሉን፣ ኧረ ነውር ነው ዝም ብላችሁ ቆማችሁ አትዩን፣ ግፍ ይሆንባችኋል፣ ለእናንተም ቢሆን ነገ አይቀርላችሁም እያሉ የራሳቸው ገባና በሌሎች ላይ በማላከክ ሊያሟርቱና ሊጮሁ በትግራይ ላይ የተፈጸመው ወረራ ከመፈጸማቸው ከአንድ ዓመት በፊት ሳይቀር ግን የማይሉት ነገር አልበረም። ዝግጅታችን አጠናቅቀናል፣ ልናውድማቸው ተዘጋጅተናል፣ ውስጥ ለውስጥ የቤት ስራችን ጨርሰናል፣ ሞያ በልብ ነው፣ ልናጠፋቸው ነው፣ ልንቦቅሳቸው ነው፣ ልንነቅላቸው ነው፣ ልናፈራርሳቸው ነው፣ ልንቀብራቸው ነው፣ ልናነዳቸው ነው ሲሉ ነበር የከረሙ። የኢምሬት ድሮን፣ የዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያ፣ የሱማሌ፣ የአፋርና የኦሮሞ ሠራዊትና ታጣቂዎች ተንጣላጥለው መጥተው ትግራይን በአራት አቅጣጫ በመውረር የትግራይ ህጻናትና ሽማግሌዎች ሲገድሉና ሲጨፈጭፉ ደግሞ የልብ ልብ እየተሰማቸው አማራ ታሪክ ሰራ! እያሉ እርስበርሳቸው ድል የሚሸከም ትክሻ ስጠን ብላችሁ ጸልዩ! እያሉ ሲሳለቁብንና ሲመጻደቁብን ሰው ምን ይለናል አላሉም። ለሐማ አልሰግድም! በማለት ለእስራኤል አምላክ ታማኝነቱ የገለጠ የመርደክዮስ አምላክ ይባረክ ነገሩ ተገለበጣና አሳዳጁ ተሳዳጅ ሲሆን ደግሞ፥ ሲዳማ፣ ጋንቤላ፣ ሐረሬ ጨመሩበት። ይህም ሆኖ ግን ርስታቸውን ጥለው ከመሮጥ አልታደጋቸውም። አሁን ሁሉን ትተን ይህ ሁሉ የአማራ ልሒቃን ሽርጉድ ምን ነው? መሻታቸው ምንድ ነው ያልን እንደሆነ ግን የቢራቢሮዎቹ የአማራ ልሒቃን ምኞችና ጸሎት፥

 

አማራ ሲነሳ ፍጥረት ሁሉ ይብረከረካል፣ የዓለም ኮረብቶች ይናወጻሉ፣ ወንዞች ሽቅብ ይፈሳሉ፣ ተራሮች ደልዳላ ሜዳ ይሆናሉ፣ አማራ የተቆጣ እንደሆነ ከብቶች አፍ አውጥተው ስለ ሰው ልጆች ምህረት ይለምናሉ፣ ሳር ቅጠሉ መጠሊያ ፍለጋ ስራቸው ነቅለው ወደ ውቅያኖስ ይፈልሳሉ ወዘተ የሚለው (ስንቱን ልዘርዝር ብቻ ግን ሰዎቹ የሚታወቁበት፣ ለዘመናት የነገዱበት ቅዥትና ልብ ወለድ ድርሰት) ቀርቶባቸው በአሁን ሰዓት ሸለፈታሞቹ የአማራ ልሒቃን ምኞትና ጸሎት ወያነ ትግራይ (TDF) ዳግም በላቀ መልኩ የገለጠውና የቀነጠጠው ሐሰተኛ ማስካቸው፣ ዋሾና ሽንታም ማንነታቸው በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ዘንድ በሚገባ እንዳይታወቅባቸውና ሳይታወቅባቸውም እንዲሁ ተሸፋፍነው ወደ ሰላም መድረክ ቀርበው ይህች ክፉ ቀን ማምለጥ ነው ትልቁ መሻታቸው።

 

 

በትግራይ ላይ የተፈጸመ ወረራና በትግራይ ህዝብ ላይ ተግባራዊ የተደረገ ማንነት መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማን ምን እንደሆነ ለአደባባይ ያሰጣና የገለጠ ክስተት ከመሆኑ በተጨማሪ አሁንም በትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት እንዲሁ የህይወት መስዋዕነት ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መጻኢ ዕድል ለአንዴና ለመጨረሻ የሚወስን ትልቅ ገጸ በረከትም ነው። ለምን? ከእንግዲህ ወዲህ በውሸትና በአሉባልታ፣ በሌብነትና በተውሶ ታሪክ፣ በዘፈንና በቀረርቶ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እያሸማቀቀ የሚኖር የአማራ ልሒቅ ህልውና ሊኖር ስለማይችል ነው። የአማራ ልሒቃን በአሁን ሰዓት ያለና የሌለ ዓቅማቸው አጠራቅመው ለሰልፍ የወጡበት ምክንያት እነሱ እንደሚለፍፉት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ህልውና ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ሳይሆን ቀደም ሲል እንደተገለጸው በትሪ ወያነ ትግራይ የገለጠውና ያራቆተው አሳፋሪ ማንነታቸው ፈጽሞ ከመገለጥ ለመትረፍና ለመሸፈን እያደረጉት ያለ መፍጨርጨር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

 

 

ማሳረጊያ

 

ጽሑፌን ከመቋጨቴ በፊት ሁለት ማሳረጊያ ፕሪስክሪፕሽን ለማስፈር እወዳለሁ። ይኸውም፥

 

1.   የአማራ ልሒቃን የራሳቸው ያልሆነ ታሪክና መታወቂያ ገንዘባቸው ለማድረግና ለማምታታ ሲፈልጉ የአንበሳ ድርሻ ያለን ነን ሲሉ መስማት የተለመደ ነው። ሐቁ ግን የአማራ ልሒቃን በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የአንበሳ ድርሻ አላቸው ተብሎ ሊነገርላቸው የሚችል ነገር ቢኖር የልሒቃኑ የሌብነትና የአገር ክህደት፣ የባንዳነትና የተላላኪነት፣ የስስትና የሴሰኝነት፣ የውስልትናና የግብዝነት፣ የውሸትና የአሉባልታ፣ የአረመኔነትና የነፍሰ ገዳይነት ታሪክ ነው። ከዚህ ውጭ የአማራ ልሒቃን እዚህ ግባ የሚባል በኢትዮጵያ ታሪክ የረባ አውንታዊ ታሪክ ኖራቸው አያውቅም፤ አሁንም የላቸውም። ትናንት ትግራይን ለመውጋት ከጣሊያንና ከኢንግሊዝ ከሶቬት ህብረትና ከኩባ ዛሬ ደግሞ ከኢምሬት፣ ከኤርትራ፣ ከሱማሌና ከሱዳን መክረውና ዘክረው ግንባር ፈጥረው 21ኛው ክፍለ ዘመን በሰው ልጆች ላይ ይፈጸማል ተብሎ የምታሰብና የማታመን ማንነት ማሰረት ያደረገ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ የሰው አውሬዎች ናቸው። ይህን ሲያደርጉም ከአስምት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን መሬታቸው ለሱዳን አስረክበው ነው።

 

2.   የአማራ ልሐቃን ከበሮ መቺዎች ለንደንና ዋሽንግተን ዲስ ስትዲዮ ውስጥ ተቀምጠው ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ የሸጠችውን ሽጣ ድሮን መግዛት አለበት! ድሮን ድሮን ድሮን! እያሉ በነጋ በጠባ ቁጥር የሚወተውቱበትና የሚጮሁበት ምስጢር ሌላ ምንም ሳይሆን ኢትዮጵያ ወያነ ትግራይን ታግላ መጣል አትችልም። ወያነ ትግራይ በምድር ጦር አንችለውም፤ ከዚህ ቀደም አባቶቻችን ሞክረው አልተሳካላቸውም፤ ያተረፍነው ሞትና ሙርኮ ብቻ ነው። አይደለም ኢትዮጵያውያን ብቻችን የኤርትራና የሶማሊያ ስፍር ቁጥር የሌለው ሰራዊት ይዘንና ጨምረንም አልቻልናቸውም፣ የኢትዮጵያ አምላክ ድሮን ነው! ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ኢምሬት ድሮን ትዘረጋ! እያሉ እንደሆነ ሊገባን ይገባል።

 

3.   በመጨረሻ፥ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰላምና ደህንነት ዳግም ተረጋግጦ ህዝቦች በሰላም የሚኖሩበት ቀን በፍጥነት እየተቃረበ ነው፤ በደጅም ነው። የሚረጋገጠውና እውን የሚሆነው ታድያ ይህ በሞት አፋፍ ላይ ያለው የልሃጫሞቹ የአማራ ልሒቃን የበከተ የትምክህት አስተሳሰብ ወያነ ትግራይ እንደ ጤዛ አብንኖ ዳግም በሚያበራው የነጻነት ብርሃን ነው። ደግሞም በቅርቡ እውን ይሆናል። ከዚያ በኋላ ታድያ የአማራ ልሂቃን አፋቸው ከፍተው የሚያቃልሉት፣ በክፉ ዓይን የሚያይቱና የሚያገላምጡት ብሔር ብሔረሰብ አይኖርም። አይሞክራትም እንጅ የሞከራዋትም ክልሎች ድረሱልኝ እያለ በታላቅ ጩኸት እርዳታቸው የጠየቃቸው ክልሎች የወያነ ትግራይ ታሪካዊ መዋዕለ ዜና የሚያትት መጽሐፍ እየገለጡ የሚሰጡት አጥንት የሚሰብር መልስ የአማራ ልሒቃን የሚሸከሙት ነገር ስለማይሆን ሰዎቹ አፋቸው ሰብስበው መቀመጥን ይማራሉ፤ ከዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰላማቸው አግኝተው በሰላም ይኖራሉ! በማለት ጽሑፌን እዚህ አጠናቅቃለሁ።

 

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page