Back to Front Page

የውታፍ ነቃዬቹ የአማራ ልሒቃን እያነቡ ስክስታ ፖለቲካ

የውታፍ ነቃዬቹ የአማራ ልሒቃን እያነቡ ስክስታ ፖለቲካ

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 08-31-21

 

ታሊባን በዛሬው ዕለት የአፍጋኒስታን ርእሰ መዲና የሆነችው ካቡል (Kabul) ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ! የሚል ሰበር ዜና ሰምቶ ያልደነገጠና ያልተቆጣ የዓለም ማህበረሰብ፤ ሰማይ ይያዝልኝ ያላለ ሚድያ የለም። የህዝቡ መደናገጥ ምክንያት በዋናነት፥ የዛሬ አስርት ዓመታት ታሊባን ከስሟል፣ በየስርቻው ሞቷል፣ ተበትኗል፣ የሉም አልቋል ተብሎ በተደጋጋሚ ስለ ተነገረ ከዚህ የተነሳም ታሊባን አለ እየተዋጋ ነው ብሎ የሚያምን የዓለም ማኀበረሰብ በአመዛኙ የለም ተብሎ መደምደም ይቻላል። ሚድያው የታሊባን ጉዳይ በተመለከተ ሰዎቹ በህይወት የሌሉ ያህል በማድረግ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴያቸው በተመለከተ ሽፋን ነፍጎ ስላፈነው የዓለም ማህበረሰብ ታሊባን እንደ ጠፋ ነው የሚያውቀው። ሰሙኑ ደግሞ ታሊባን ተመልሶ መጣ ብቻ ሳይሆን የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ አገር ጥለው ኮበለሉ ሲጨርበት፥ ሰዉ በጆሮው የሰማውና በዓይኑ የሚያየው ዜና ማንመን ስለ ተሳነው ለመደናገጡና ለመቆጣቱ ምክንያት ሆኗል። የትግራይ ሠራዊት ጉዳይም ተመሳሳይ ነው። ወታደሩም ወዛደሩም፣ ፓስተሩም ሊቀ ጳጳሱም፣ ዘማሪውም አዝማሬውም፣ ሼኹም ጠንቋዩም፣ ወንዱም ሴቱም፣ ትልቁም ትንሹም ላለፉት ድፍን ስምንት ወራት በሙሉ፥ ትግራይን ቀበርናት! እየተባለ በየሆቴሎቹና አዳራሾቹ ሐሰተኛ ድል ለማክበር በመንግሥት ወጪ እዘዝ በገላየ እየተባለ ሻምፓኝ እየተራጨ ስለ ከረመና ህዝቡም እውነቱን እንዳያውቅ ታፍኖ ስለ ከረመ ወያነ ትግራይ መቐለ ገባ ሲባል ድፍን ኢትዮጵያ በጆሮው የሰማውን ሰበር ዜና ለማመን ተቸግሯል። ምናልባትም ይህን ሲሰማ ከተቀመጠበት ወንበር ወደ መሬት በግንባሩ ተፈጥፍጦ አንገቱ ተሰብሮ የሞተ ኢትዮጵያዊም አይታጣም። በቀንም በሌሊትም ለወራት የተጋተው ውሸት፥ ወያነ በነፋስ ላይ እንደ ተበተነ ዱቄት በኗል የሚል የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሰይጣዊ መገለጥ የወለደው ፕሮፓጋንዳ ነውና።    

 

የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ጓዶቻቸውና የስራ ባለደረቦቻቸው በጠራራ ፀሐይ ገድለውና አስገድለው የላቀ ልምድ ወዳካበቱበት ለተላላኪነት፣ ፍርፋሬ ለመልቀምና ዘፋኑን ለመሸከም የበቁ ውታፍ ነቃዮች የአማራ ልሒቃን፥ ትግራይን እንዲወርና የትግራይን ህዝብ እንዲያፀዳ ያሰማሩት ዘራፊና አመንዝራ ሠራዊት በየዕለቱ እንደ ቅጠል እየረገፈና እያለቀ መሆኑን እያወቁ መላ አገሪቱን በውሸት ጎርፍ አጥለቅልቀው ሐሰተኛ ዜናና በሬ ወለደ አሉባልታ ህዝቡን ማስኮምኮም ምርጫቸው በማድረግ ህዝቡን፥ ወያነ ጠፍቷል፣ ከስሟል፣ ታሪክ ሆኗል፣ ሞቷል፣ በኗል እያሉ ደህና አድርገው ስለ ሰለቡትና ስላደነዘዙት በነፋስ ላይ እንደ ተበተነ ዱቄት ተበትኗል የተባለው ወያነ ትግራይ መቐን መቆጣጠር ሳያንስ ጭራሽ በምዕራብ ደባርቅ በደቡብ ሃይቅ በምስራቅ አፋርን አጋመሰ ሲባል በውስጥ በውጭ የሚኖሩ ብዙሐኑ ኢትዮጵያውያን ከድንጋጤና ተስፋ መቁረጥ የተነሳ በአሁን ሰዓት ስለ ምንም ነገር መስማት አይፈልጉም። ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን፣ ከጎንደር እስከ ለንደን የመሸገው የአማራ ልሒቃን ከበሮ መቺዎች በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ያለ ጦርነት በትግራይ ከተሞች በአድዋና በተንቤን እየተካሄደ ያለ ይመስል ሰዎቹ፥ መርሳና ሃይቅ ደብረ ታቦርና ደባቅ ጭፍራና ሚሌ ሲባል ከተሞቹ የአማራና የአፋር ከተሞች ለመሆናቸው ሁላ ዘንግቷቸዋል። ከተሞቻቸው እያስረከቡ እግሬ አውጭን በሚፈረጡጡበት በዚህ ሰዓትም ቢሆን የአማራ ልሒቃን ቴሌቪዥን መስኮት ላይ ተቀርቅረው ሐሰተኛ ዜና ማሰራጨትና ማራገብ አልተዉም።  

Videos From Around The World

 

የአማራ ልሒቃን የትግራይ ሰራዊት በየአቅጣጫው እያሳረፈባቸው ያለ ዱላ ሊቋቋሙት ባለመቻላቸውና የፈጠረባቸው ድንጋጤም አጥንታቸው ስር ሰርስሮ በመግባቱ የሚሉትና የሚሰሩት ጠፍቶባቸው፥ ወደ ጦር ግንባር የሚልኩትና የሚያሰልፉት ህዝብ ሁሉ ከሞትና ከምርኮ እንደማያመጥና እንደማይመለስ እያወቁ፥ የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ በጠላትነት ፈርጀው የትግራይ ህዝብ የአማራ ጠላት ነው ከማለት ጀምሮ የምትማርከው ብረት ለራስ ይሆናል እስከ ማለት ደርሰው ተደጋጋሚ የክተት አዋጅ ለማሰማት ተገዷል። በአሁን ሰዓት ትግል ማለት ለአማራ ልሒቃን ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ የቻለ ደግሞ ወደ ውጪ እያስወጡ በአያቶቼ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የአማራ እናቶችና አባቶች ሳይቀር ግደ የለም ይግቡ! እያሉ የአማራ አርሶ አደር ወደ ጦር ሜዳ መላክና የሞት ሲሳይ ማድረግ ሆኗል። ትግል ማለት ለአማራ ልሒቃን፥ የአማራ ሚኒሻ ለቀረጻ አመቺ በሆኑ ለፓርክ አገልግሎት ተስቦ በተለዩ የመናፈሻ ቦታዎች ላይ እየወሰዱ መሳሪያና ገጀራ አሸክመውና አስይዘው ታጣቂው ቆጭ ብድግ እያለ ድራማ ሲሰራ በማሳየት በገዠራ ብረት ማረክን እያለ ሟሸፍ ሆኗል። ሌላው ሙቀቱ እየጨመረ የመጣ ሐሰተኛ ዜና ጉዳይ ነውና በዚህ ዙሪያም ጥቂት ልበል።

 

እያነቡ እስክስታ

 

አምልኮተ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በመፈጸም የሚታወቁ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ልሳኖች የሆኑ እንደነ ኢዜአ፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ፣ ፋና፣ አዲስ ዘመን የመሳሰሉ መገናኛ ብዙሓን ተቀጥረው የሚሰሩ የመንግስት ደመወዝ ተከፋዮች የሆኑ ጋዜጠኞች ዐቢይ አህመድ ዓሊ ቀን በቀን የሚጭምረው የውሸትና የቅጥፈት የሙቀት ልክ መስተካከል፣ በሚፈለገው ደረጃ በሬ ወልደ ሐሰተኛ ዜና ማምረትና መፈብረክ ባለመቻላቸው ዐቢይ አህመድ ፊቱ ወደ ጫት ቤቶች ማዞሩንና የጫት ቤቶች የምርቀና ወሬዎች ዋጋም ጭማሪ ማሳየቱን አንዳንድ ኬብሎች በአግራሞት እየጠቆሙ ነው። በርግጥ ይህ ጥንክር ቀልድ ሊመስል ይችል ይሆናል ዳሩ ግን መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ ችክሻ ላይ የተቀመጠ በዐቢይ አህመድ ዓሊ የሚመራ ወስላታ፣ ዘራፊና ነፍሰ ገዳይ ቡድን የትግራይን ህዝብ በወሬ ብዛት ለማጠልሸት ሐሰተኛ ወሬ አመንጪዎች ፍለጋ በየጫት ቤቱ የሐሰተኛ ወሬ ያለህ፣ ክፍያው እጅ በእጅ ነው፣ ገዴታዎን በመወጣት ኢትዮጵያን ይታደጉ (በሬ ወለደ ወሬ በመፈብረክ መሆኑ ነው) እያለ የገዛ ህዝቡን በምርቀና መንፈስ በሚፈበረኩ ሐሰተኛ ወሬዎችና በሬ ወለደ አሉባልታዎች እያሰራጨና እያስተጋባ ለማጭበርበር፣ ለማደናገርና ለማወናበድ የቻለውን ያህል ለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እውነት ነው፥ ከጫት ቤት በክፍያ የሚገኙ የምርቀና ዜናዎች ከሞትና ከምርኮ የሚያተርፋቸው ወሬ አልሆነም እንጅ ሐሰተኛ ወሬ በቀናን በሌሊት ለዓመታትና ለወራት ቢቆረቆርበትም በቃኝ የማያውቅ የኢትዮጵያን በሬ ወለደ ሐሰተኛ ዜና ናፋቂ ጆሮ ለማደናገርና ለማወናበድ ግን ስራ ላይ ነው። ሰዎቹ፥

 

v ከሞትና ከምርኮ የተረፈች ነፍስ ይዞ ከቆቦ የሮጠ ደሴ የገባው ውታፍ ነቃይ የአማራ ሚኒሻና ታጣቂ፥ እንክርዳዱን እያጨደ አባጣ ጎባጣውን እየደለደለ ከማኸል ትግራይ ተነስቶ ደሴ ግንባር የደረሰ ተአምረኛው የትግራይ ሰራዊትን እያሯሯጥ ነው ይላል፤

v በሁሉም ግንባሮች ውርደትና ሽንፈት ተከናንቦ እንደ ቅጠል እያለቀና እየረገፈ ወያነን በተነው ደመሰስነው ይላል፤

v ታንክና ከባድ መሳሪያ ጥሎ እግሬ አውጭን እየነካው ሲያበቃ የአማራ አርሶ አደር ጀብደ እየፈጸመ አማራ ታሪክ እየሰራ ነው ይላል፤

v የገዛ ራሱ ወገን ቁስለኛ ትቶ የሚፈረጥጥ፣ በወትደራዊ ምግባርና ዲሲፕሊን ያልታነፀ፣ በስሜት የሚከንፍ መንደርተኛ ታጣቂ ስብስብ ሆኖ ሲያበቃ በቅርቡ ወያነ ግብኣቱ ምድር ይፈፀማል ይላል፤ 

v ነፍሱን ለማትረፍ ምሽጎቹንና ከተሞቹን ወደኋላ እየተወ እግሩ ወዳመራው ስፍራ እየነካው አማራ ለክብሩ እየተዋደቀ ወደ ፊት እየገሰሰገሰ ነው ይላል (ወደ ፊት መገስገስ ሲባል በአማርኛ ከማኽል ትግራይ ደሴ መድረስ ካልሆነ በቀር)፤

v መች ይሄ ብቻ፥ ሰዎቹ ሲፈጥራቸው ኃፍረት የሚባል ነገር ስለ ሌላቸውና ስላልፈጠረባቸው በቆቦ በሚጋባ ተገርፈው ቆቦ ሮቢት ሲገቡ ሿሿ ስለ ተሰራን ነው አሉን፤ ከቆቦ ሮቢት ሸሽተው ጎብዬ ሲገቡ ደግሞ አማራ መሪ የለውም መሪ ስላጣን ነው እያሉ ሲያለቃቅሱ ሰማን፣ ከጎብዬ እግሬ አውጭኝ ብለው ወልድያ ሲመሽጉ ደግሞ መሳሪያውን ጥሎ የሚፈረጥጥ ዓቅመ ቢስ ሰራዊት የማይለው ነገር ስለሌለው አፋቸው ሞልተው መሳሪያ ስለ ሌለን ነው ሲሉን ዝም ብለን አደመጥናቸው፣ ከወልዲያ መርሳና ውጫሌ ተዠልጠው ደሴ ሲደርሱ ደግሞ ወያኔ ነፋስ የሆነብን ሓሽሻ ስላጨሰነው እያሉ ፈገግ የሚያሰኝ ወሬ ለቀቁብን። ነገ ደሴ ግንባር በሚገባ ሲገረፉና መሸሽ የኣባቶቻቸው ነውና እንደ ለመዱት ከተማቸውን ለቀቅ ሲነኩት ደግሞ ስፕሪስ ጁስ ስላልቀረበልን ማለታቸው የማይቀር ነው። እንደ እባብ ጉልበታቸው ምላሳቸው ላይ የተሰነጠረችው ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ምን ይሳናቸዋል? ደግሞ በሬ ወልደ ወሬ ለመስለቀጥና ለማናፈስ። እኔ ለመስማት የናፈቀኝ ግን፥ ሰዎቹ ተሰባስበው አዲስ አበባ የከተሙ ዕለት ምን ዓይነት ምክንያትና ውሸት ሊያሰሙን እንደሚችሉ ብዙዎቻችን በጉግት እንደ ምንጠብቅ አምናለሁ። 

 

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

 

Back to Front Page