Back to Front Page

አብይ አህመድ ኢትዮዺያን ለመምራት ወይስ ለማፍረስ?

አብይ አህመድ ኢትዮዺያን ለመምራት ወይስ ለማፍረስ?

 

ሙሉጌታ በሪሁን 04-18-21

 

እንግዲህ ሾርት ሚሞሪው የኢትዮዺያ ሕዝብእኔ አላልኩምያለው ጋሽ ዝናቡ ወይም መሽረፈት ነው።በዚህ ፫ዓመት በ፴ዓመት የተገነባው የኢትዮዺያ ወታደራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሳያዊ አቅም ድምጥማጡ ጠፍቶ፣ኢትዮዺያ የኤርትራና, የሶማልያ የቅርብ ወዳጅነት ደረጃን ተቀዳጅታለች። ይህ እድገትም በሉት ውድቀት እንደየ እምነታቹህ ወስኑ።

 

እነ ባጫ ደበሌ፣እነ ብርሃኑ ጁላ የሚመሩት የመከላከያ ሃይል፣በምናባዊ አእምሮአቸው የቀረ፣የነበረ እንጂ መሬት ላይ የሌለ ሰራዊት እየመሩ ህዝቡን ድል በድል አርገውታል። ልብ በሉ የኢትዮዺያ ህዝብ፣ የኢትዮዺያ መከላከያ ሰራዊት አልቆ በኤርትራ ሰራዊት ተተክቷል፣እንደሰማችሁት፣ኤርትራም ለተባበሩት መንግስታት፣እሺ ሰራዊቴን ከትግራይ ምድር አስወጣለሁኝ ብላለች።ለናንተ ምስኪን ሾርት ሜሞሪዎች ግን የኤርትራ ሰራዊት ምን ሲደረግ፣ኢትዮዺያን የምታክል ትልቅ ሃገር ከኤርትራ ወታደር ትጠይቃለች ነበር የሚሏቹህ። የኢትዮዺያ ሰራዊት የተቀረውም በነ ጀነራል ፊሊዾስ የኤርትራ የጦር አዛዥ የሚታዘዝ ነው።

Videos From Around The World

 

እነ ጀነራል ካሳየ ጨመዳ፣ጀነራል አባ ዱላ ገመዳ፣እነ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣እነ ጀነራል ባጫደበሌ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፣የወያኔ፣የጁንታው፣የተወርዋሪ ኮኮቦቹ፣የኮቪድ ፳፩ዶቹ ምርኮኞች ናቸው። አብይ አህመድ ፯ተኛው ጨቅላ ንጉስ፣፣እንደምናውቀው፣የአለም የሰላም ተሸላሚ ብቻ ሳይሆን፣በአለም ውስጥ ካሉ የአለም መሪዎች በውሸታቸው ከሚታወቁት የአለም ወንፊት መሪዎች፣ ቢቢሲ በሰራው ጥናት መሰረት የ፪ተኛነት ደረጃን ተቀዳጅቷል። እውነትም እድገት ይሉሃል ይሄ ነው።

 

ከ፴ አመት በፊት ካነበብኩት መፅሃፍአንድ ለአምስትበምትለው መጽሃፍ የኢትዮዺያ ህዝብን ወሬኛነት በምሳሌ ሲያስረዳ፣ በስልጣኔ ከኛ በኃላ ከነበሩት አገራት አንዷ ጃፓን እንዴት ጥላን እንደሄደች ከገለፀ በኃላ፣ ኢትዮዺያዊያን በወሬ ቢሆን ኖሮ፣ ከአለም ቀዳሚዎች ነበርን ያለውን ሳስብ፣እውነትም ይህ ህዝብ ወደፊት ከመገስገስ ይልቅ፣ እንደ ግመል ሽንት ወደኃላ የምንጏዝ መሆናችን ማሳያ ነው።

 

ጋሽ ዝናቡ፣በሰሜን ሸዋና በጎጃም ዝናብ ያዘነበ ሊቅ፣ከ፴ ዓመት በኃላ በአለም ካሚኖሩ ፪ ትላልቅ ሃገራት ኢትዮዺያ አንዷ ነች። ብሎ በአደባባይ የሚናገር መሪ ሲሆን፣ጥያቄው አብይ አህመድ ኢትዮዺያን እየገነባ ወይስ እያፈረሰ ? ለሚለው ጥያቄ ማንሳት ያለበት እያንዳንዱ ኢትዮዺያዊ ራስህን/ራስሽን ጠይቂ/ጠይቅ።

 

አንዳንዴ ህዝብ እንደ ህዝብ መስደብ ወይም መገሰጽ ይከብድ ይሆናል። ይቅርታ ይደረግልኝና፣መሪዎች የህዝቡ የስራ ውጤቶች ስለሆኑ፣ሕ/ሰቡ መወቀስም ሆነ መገሰጽ ያለበት ይመስለኛል። ለምሳሌ እኔ ትግራዋይ ነኝ። የማህበረሰቤ የስነልቦናና፡የእምነት የአስተሳሰብ ውጤት ነኝ። የትግራይ ህዝብ ባለው ስነልቦና፣ሃይማኖታዊ እምነት፣ታሪክና፣ባህል መሰረት፣ የመንግስታዊም ሆነ ፖለቲካዊ መሪዎቹ፣የራሱ የስራ ውጤቶች ናቸው።

 

እኛ ትግራዎት የሰው አንመኝም፣የራሳችንም ከፈቃዳችን ውጭ አንሰጥም፣ ለሃገራችን፣ለክብራችን፣ ለታሪካችንና ለቅርሶቻችን እስከ ሂወት መስዋእትነት ከመክፈል ወደኃላ አንልም።ከአብይ አህመዷ ኢትዮዺያና፣ ከኢሳያስ አፈወርቒ ቅጥረኛ ወታደሮች፣ እንዲሁም ከተስፋፊው፣ ሁሉም የኔ ስግብግቡ የአማራ ሚሊሻና፣ ልዩ ሃይል ጋር የህልውና ፍልሚያ እያደረግን ያለነው የሕዝባችንና፣የያንዳንዳችን መብትም ሆነ ክብር ሊነካብን ስለማንፈቅድ ብቻና፣ብቻ ነው።።

 

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር፣ትግራይ የኢትዮዺያ ሰራዊትም ሆነ፣ የኤርትራ ወራሪ ጦር መቀበርያ እንጂ፣ መፈንጫ አትሆንም። ይህ በያንዳንዱ ትግራዋይ ስነልቦና የተቀረፀ ውቅር ስነልቦናዊ እምነት ነው። እኛ ተጋሩ እስከ ዛሬ ለዚህች አገር ደምተን፣ሞተን ምላሹ ይህ ከሆነ፣ ኢትዮዺያ ለተጋሩ የማትሆን አገር ለማዳን ተብሎ ከአሁን በኃላ የሚፈስ ደምም ሆነ መስዋእት የለም። ይህ ሃቅ መልአክም ይሁን ሰይጣን ያወቁት ተጨባጭ እውነታ ነው።ይህ ማለት ደግሞ ኢትዮዺያ ካለ ትግራይ እንደ ሃገር የመቀጠል እድሏ የዩጎዝላቪያ እጣ ይገጥማታል። ይህ እውነታ ደግሞ እየሆነ ያለው ኢትዮዺያ አትፈርስም በሚለው አብይ አህመድ የመሪነት ጊዜ ውስጥ ነው። እርግጥ ነው ኢትዮዺያ ሱሴ ነው እያሉ ኢትዮዺያን ለበይ ጅብ ጥለው የሸሹት እነ ለማ መገርሳ እንዳሉ ሁሉ፣ወጊድልኝ ለነፃነታችንና ለህዝባችን ክብር ሲባል፣ የሚከፈል መስዋእትነት ከመጣም ከመክፈል ወደ ኃላ አንልም በማለት፣ መተኪያ የሌለውን ሂወታቸው ለሕዝባቸው በክብር ያለፉ፣እንደነ አምባሳደር ስዩም መስፍን፣ተጋዳላይ አባይ ጽሃየ፣ተጋዳላይ አስመላሽ ወስላሴ፣ተጋዳላይ ጌታቸው ሴኮቱሬ የመሳሰሉትንም አይተናል።

 

ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው፣በአጭር ጊዜ በ፫ዓመታት ውስጥ ነው፣የበግ ቆዳ የተላበሱ ቀበሮዎች፣ ሃገሪቱን በአብይ አህመድ መሪነት እየደቀቀች፣ ሕዝቡ ዝም ቢልስ ? አንድ ክፍል የቆጠረ ምሁር፣የፖለቲካ መሪ፣ ጋዜጠኛ፣ ከያኒ፣ የስነጥበብ ሰው፣ የሃይማኖት መሪዎች የሉም እንዴ ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ያልተገኘበት እንቆቅልሽ ሆኗል።

 

እርግጥ ነው አንድ ስርአት ወድቆ፣ሌላ ስርአት ሲተካ፣ ጊዜው የሚፈጥራቸው አድርባዮችና፣ባገኙት አጋጣሚ ስልጣንና፣ሃብት ለማካበት የሚደረገው ሩጫ፣ የእትየ ለሌ ነው። ለዛም የዘመኑ ስልጣኔና፣የመገናኛ ዘዴዎች ወሳኝነት እጅግ የላቀ ጠቀሜታነት ባላቸው ስአት፣እንዲህ ባለው ዘመን ግን፣ ሚዛናዊነት ጠፍቶ፣ በፍርደ ገምድልነት መዳኘት፣ የኢትዮዺያ ህዝብ የእለት ተዕለት ኑሮ ሆኗል።

 

ኢትዮዺያ የሰሩላት ገድላ፣ ፍትህ የምትነፍግ አገር ከሆነች እንሆ ዓመት አልፏታል፣ኢንጅነር ስመኘው፣ ጀነራል ሳዓረ፣ ጀነራል ገዛኢ፣ / አምባቸው፣ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ደማቸው ፈሶ ፍትህ ተነፍጏል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች፣ ያለ ፍርድ በየእስር ቤቱ ታጉሮዋል፣ እነ ጀዋር ማሃመድ፡ ጀነራል ክንፈ ዳኘ፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ በፖለቲካዊ እምነታቸው ምክንያት ዘብጥያ ወርዷል።

 

ሁሉም ተላላኪ፣ሁሉም ሆድ አደር ሆኗል። እንደነ ብርሃኑ ነጋ የመሳሰሉ ለስልጣን ካለው ስግብግብ ምኞት አንዴ ከግብፅ፣ ከኤርትራ ጋር ሆኖ ኢትዮዺያን ለማፍረስ እንዳልሰራ፣ ዛሬ ደግሞ በትግራይ ላይ እየተካሄደ ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ እንዳደነቀ ሰምተናል።እነ ዳንኤል ክስረት፣ በማህበረ ቅርሱሳን ሳቢያ፣ የኦርቶዶክስ እምነትን አፍርሶ የራሱ የአማራዊ ኦርቶዶክስ ለመመስረት ከሚደረገው ሽፍጥ ባሻገር፣ የጁንታው አባላትና ደጋፊዎቻቸው ግፋ ቢል 1 ሚሊዮን ቢሆኑ ስለሆነ፣ እነዚህን አጥፍቶ የተቀረውን የትግራይ ህዝብ ከኛ ጋር ይሆናል።

 

ኢትዮዺያ ከራሷ አልፋ ለአለም የሰላም ወታደሮች የምታቀርብ ሃገር እንዴት ? ከሚጢጢየ ኤርትራ እርዳታ ትጠይቃለች ? በማለት ካለ ምንም ሃፍረት የሚዘላብድ የአብይ አማካሪ ያድነን። አዝማሪው ከመጣው መንግስት ጋር እያጎነበሰ፣የእለት ጉርሱን ከማስተካከል፣ ባሻገር ስለሃገር የሚዘፍነውና፣በተግባር የሚሰራው የተጋጨበት፣ ከያኒና ደራሲ የሞላባት ሃገር። ትናንትና ከወያኔ በላይ ወያኔ ሆነው፣ ስለ ኢትዮዺያ ሲከራሩ የነበሩ ተላላኪዎች፣ እነ ደመቀ መኮነን፣እነ ሬድዋን ሁሴን፣ እነ ዛዲግ አብርሃ፣ እነ ዲና ሙፍቲ፣ እነ ሙፈርያት ከማል፣ እነ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ዛሬ ከብልጽግና ጋር፣ ከአብይ አህመድ በላይ ብልፅግና ሆነው፣ ሃገሪቱን ገደል ውስጥ ጨምረዋታል።

 

በጣም የሚያሳዝነው ሃገር ማለት ምን ማለት ነው? መማር ማለት ምንድነው ? የሰው ልጅ የመኖር ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? ለሚለው ጥያቄ በአሁኑ ስአት ኢትዮዺያ ውስጥ ባሉት ሙሁራን ተብየዎችና፣ ፖለቲከኞች የዘቀጠ፣ የወረደ ተግባርና ድርጊት፣ኢትዮዺያ እንደ አገር የተዋረደችበትና፣ የውሸታሞች አገር መሆኗ በአለም ፊት ያስመሰከረችበት ወቅት ነው።

 

አዎ የኢትዮዺያ ህዝብ ሾርት ሚሞሪ ያለ ህዝብ ነው። ብሎ የሰደበህን መሪ፣ክብርህንና መብትህን የገፈፈህ መሪ፣ በአለም ፊት ቀርቦም አዋርዶሃል። ካስፈለገ ላስታውስህ፣ ፳፭ አመት የጨለማ ዘመን ነበር ሲልህ፣እራሱ የዛ ፳፭ አመት አመራር ነበር።አንድ ሰው የብርሃን ጊዜውስ ? ልማቱስ ?አባይ ሲገደብ፣ባቡር ሲዘረጋ፣የተለያዩ መንገዶች፣ጤና ጣቢያዎች፣ዩኒቨርስቲዎች፣ፋብሪካዎች የልማት አውታሮቹስ ? ብሎ የጠየቀ ሙሁር አልነበረም።ከትግራይ ህዝብ በቀር ወላሂ ወላሂ ግድቡን እናንተን አይጎዳም ብሎ ሲዘባርቅ ምን ማለትህ ነው? ብሎ የጠየቀ ፖርላማ ይሁን ሙሁር አላየንም።

 

ሙሁሮች፣ የህግ ባለሞያዎች፣ የጦር መኮንኖች፣ ሃኪሞች እየሰበሰበ እንደፈለገው ሲዘባነንባቸው፣ አንድ ሰው ወጥቶ ሞያህ ወታደር ሆኖ ሳለ፣ በሞያችን የምትዘላብደው ምን ለመሆንና ማንን ለመምሰል  ነው? ብሎ የጠየቀው አንድም ክፍል ቆጥሬያለሁኝ የሚል ምሁር አልሰማንም። በርግጥ / ደረጀ፣ ጀዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ልደቱና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ከተጋሩ ሙሁራንና ፖለቲከኞች ውጭ   በተላያየ ወቅት ሃሳባቸ ገልፀው ሰምተናል። የሚያሳዝነው ኢትዮዺያ 114ሚልዮን ህዝብ 10 ሚልዮኑ የትግራይ ህዝብ ሲሆን፣ አብይ አህመድን የማይቀበል ነው፣ ከተቀረው 11ሚልየን በአደባባይ የተቃወሙት 5ሰዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው።

 

ታድያ ይህ የኢትዮዺያ ህዝብ፣ የትግራይን ሕዝብ የዘር ማጥፋት ጦርነት ሲታወጅበት፣ከበስተጀርባው የታቀደው የአብይ አህመድና፣ የኢሳያስ አፈወርቒ ተንኮል መሆኑ በግልጽ እየታወቀ፣አብይ ባቀረበላቸው ተልካሻ የሰሜን ዕዝ ተወጋ፣ በሬ ወለደ ታሪክ አምነውና ተቀብለው፣ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ነን በማለት፣ ካህኑ ዻዻሱ፣ ፖለቲከኛው፣ ጦማሪው፣ አክትቪስቱ፣ ጋዜጠኛው፣ አዝማሪው፣ ሆድ አደር ተላላኪዎቹ የማይማገዱበትን ጦርነት ነጋሪት ጎሽመው ለሃገር ግምባታ የሚውለውን የኢትዮዺያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ወጣቶችን ፎጣ ለባሹ የአማራ ሚልሻና፣ ሽፍቶች ማግደውበታል።

 

በርግጥ ለወራሪዎች ሞት የትግራይ ሕዝብ ሃዘኔታ ባይኖረውም፣ ለግለሰቦች የፖለቲካ ስልጣን ሲባል በማይመለከተው ጦርነት ሂወቱን የሚሰዋ ምስኪን ሕዝብ ስናይ ደግሞ፣ ምን ያህል ትልቅ የአላማና የእምነት ልዩነት በኛ በተጋሩና፣ በተስፋፊዎቹ የአማራ ስግብግቦች እንዳለ መረዳት ይቻላል። አማራና የአማራ የሚድያ በሬ ወለደ ትርክት ላለፉት ፳፰ ዓመታት ባደረጉት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሕዝቡን አይኑን ትቶ ጆሮውን እንዲያምን ያለማቋረጥ ሰርተውበት ፣ፍሬ አፍርቶላቸው እነ ሲሳይ አጌና፣ እነ አበበ ገላው፣ እነ ታማኝ በየነ በመድረክ የሚወደሱበት ጊዜ፣ እነ ጀነራል ሳዓረ፣እነ አምባሳደር ስዩም የሚገደሉባት ሃገር ለማየት ችለናልእምየ ኢትዮዺያ እምየ አዶላ፤የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላሆነብን ነገሩ። የሃገሪቱ መጪ ዘመን ፣ የአብይ የጨለማ ዘመን፣ የኢትዮዺያ ፍፄሜ ያሳዝነኛል። ይህ ክስተት ደግሞ የአብይ አህመድ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፣ የሃገሪቱ የሙሁራን መካንነትና ዝምታን መመልከት ያሳፍራል።

 

አብይ አህመድ በራሱ ጭንቅላት የሚመራ ሰው ሳይሆን፣ በኢሳያስ አፈወርቒ የሚመራ፣ ያልበሰለ ጥሬ ከመሆኑ ባሻገር፣ እናቱ ከነገረችው ምኞት ውጭ ሌላ እይታ የሌለው፣ እንዳመጣለት የሚዘባርቅ፣ ከእውቀት ነጻ የሆነ፣ በጥራዝ ነጠቅ ቃላት እያሽሞነሞነ ሰውን የማጭበርበር፣ ችሎታ ያለው ክፉ አረመኔ ፍጡር ነው።

 

አብ አህመድ ጋሽ ዝናቡ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ብሎ ኢትዺያን እስከ ቻለው ይቆራርጣታል። የአባት የአያቶቹ የነሚሊሊክ የስራ አጨራረስ እስከ ስልጣኑ ማስጠበቅ ይሆናል።

ሚሊሊክ ያገኘውን ስልጣን ለማስጠበቅ ሲል፣ ስጋቱ የሆነውን የትግራ ህዝብ ለሁለት በመክፈል ኤርትራን ለጣልያን ሸጦ፣ ትግራይን ረግጦ ለመግዛት፣ አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በማይተናነስ መልኩ መፈጸሙ የታሪክ ድርሳናት ያመላክታሉ።

 

አብይ አህመድ በአንድ ወቅት ሲናገር በአድዋ ጦርነት ጊዜ ብዙ የትግራይ ሴቶች ተዋልደዋል ያለውን አንረሳም (ተደፍረዋል ማለቱ ነው)እኛ ተጋሩ በሾርት ሜሞሪ አንታማም፣ ሚሊሊክ ለስልጣኑ ሲል ጅቡቲን ሸጠ፣ አፍቃሬ ሚሊሊክ ይህንን ጉድ እየደበቁ፣ እምዬ ሚሊሊክ ዘመናዊነትን ወደ ኢትዮዺያ ያስገባው ይሉናል። ሽርሙጥና ስልጣኔ ነው? ሚሊሊክ ስልክ ለራሱ መጠቀሚያ ስላስገባ፣ የኢትዮዺያ ህዝብ ወይም እንደ አገር ተጠቀምን ማለት ነው። ነጮች በተንኮላቸው ለም መሬታችንን ለማዳከም፣ ባህር ዛፍ ስለሰጡን ይህም ስልጣኔ እንበለው። አብይም በብልጭልጭ መናፈሻ አምበሸበሸን፣ ግን ለም መሬትህን ለሱዳን በስምምነት አሳልፎ ሰጥቷል።

 

መለስ ዜናዊ በኩራት ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር ተስማምቶ የጀመረውን ግድብህን፣ሲንቀዠቀዥ ማንም ሳያስገድደው አሜሪካ ታደራድረን ብሎ፣ የአፍሪቃ መሪዎችን ንቆ ሄዶ፣ ኢትዮዺያን አዋርደዋል። ኢትዮዺያ በአፍሪቃና፣ በአለም የነበራትን ክብር አዋርዷል፣ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮዺያ በአለም የመጀመርያዋ ሃገር ፣የገዛ ጏቿን የውጭ ቅጥረኛ ወታደሮች $ ቢልዮን ዶላር ከፍላ የምታስጨፈጭፍ የመጀመርያ አሳፋሪ አገር አድርጏታል። እያልኩኝ የዚህ ሰውዬ ጉድ መዘርዘር እችላለሁኝ። መልእክቴና ሃሳቤ ግን አብይ አህመድ ሳይሆን የኢትዮዺያ ህዝብ ነው። በርግጥ በኛ በተጋሩ የደረሰው ለማንም አልመኝም።

 

 ዳሩ ግን እኛ ጥንካሬው፣ እንደሕዝብ ጽናቱ፣ የመመከት አቅሙም ፣ብቃቱም አለን።  እንደምናሸንፍ 'ኢምንት' ታክል ጥርጣሬ የለኝም። ጊዜው ሊረዝምም ሊያጥርም ይችላል። ከወዲሁ የብርሃን ጊዜው እየወጣ ነው። በኛ የተካሄደው ክህደት ፣በሌሎች እያቆጠቆጠ ስናይ ግን ፣እረ ለመሆኑ ይህ ሕዝብ ሌላ ሃገር አለውን ? ያለው ይመስል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ሆኖ ስመለከት ይገርመኛል፣ ጦርነት በኢኮኖሚ ይጀምርና ሌብነት፣ ስርአተ አልበኝነትና ዝርፍያ፣ የሰላም እጦት፣ እያለ ደጃፍህ በአዲስ አበባና ዙርያዋ ሲደርስ፣ ኤምባሲዎችና የውጭ ድርጅቶች፣ ቀስ በቀስ መውጣት ሲጀምሩ፣ ያኔ ልታቆመው ወደ ማትችልበት ደረጃ ስለሚደርስ፣ ሊብያ የመንና፣ ሶርያ እንዴት አሁን ለደረሱበት ደረጃ ደረሱሳይሆን እንዴት ብለን እዚህ ደረስን ? በላቹህ መልስ ከመፈለጋቹህ በፊት ንቁ። አስተያየት፣ጥያቄ ካላቹህ በነጻነት እድሉን ተጠቀሙበት አመሰግናለሁኝ::

 

ሙሉጌታ በሪሁን mba1277@gmail.com


Back to Front Page