Back to Front Page

የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ ምላስ መዘዝና መጨረሻው

የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ ምላስ መዘዝና መጨረሻው

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 03-27-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ አዳፍኔ ምስክርነት በመስጠት የታወቀ፣ ዘፋኑ ለመጠበቅና ለማደላደል ሐሰተኛ መረጃ በመፈብረክና በማሰራጨት ላይ የተሰማራ፣ ሐሰትን መናገር የማይሰለቸውና የማያሳፍረው፣ አገር በታሪክዋ ገጥሟት የማይያውቀው ለጠላትና ለወራሪ ኃይል አሳልፎ ሰጥቶ ሲያበቃ የወራሪዎች ብሔራዊ ደህንነት ተቆርቋሪ ሆኖ አገርና ህዝብ የሚያጠፋና የሚበትን፣ አገር በጠላት ተወራ ስታበቃ ወራሪው ኃይል ወራራውን የፈጸመበት ሐሰተኛ ምክንያት በመስጠት ለማስረዳት የሚባዝን፣ በአጠቃላይ፥ አለ ቦታው የተቀመጠ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ ምላስ ያመጣው መዘዝና መጨረሻው ለመግለጥ፤ ብሎም፥ የሐሰተኛውን ሐሰተኛ ምስክርነት በመፀየፍ አገሩን ከጠላትና ከወራሪ ኃይሎች ለማትረፍ በመትጋት ፈንታ ውሸትን ጣመኝ ድገመኝ እያለ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ውሸት እንደ ወተት እየተጋተ ውሸትን በማራገብና አሉባልታን በመሰልቀጥ የተጠመደው ህዝብ የበላውን እንደሚመስልና የሚያጭደውም የዘራውን እንደሆነ ለማሳወቅ ተጻፈ።  

 

ማሳሰቢያ፥ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የጽሑፉ ይዘት ሆነ የጽሑፉ አዘጋጅ ዓላማ ዛሬም እንደ ወትሮ ግልጽ ነው። ከነተረቱ “መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ” እንደሚባለው፥ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቀው አገር ገዳይና ደም አፍሳሽ አገር እውነተኛ ማንነትዋን በክርስትና ኃይማኖት ቀሚስ ደብቃ ለዘመናት ሐሰተኛ ጽድቅ ስታስተጋባ መቶ ዓመታት ያስቆጠረች የግብዞችና የወስላቶች አገር ሆና ሳለች ቀደም ሲል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሽግ በመጠቀም ማለትም ወንጌልን ለማስተማር የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያን አረጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም በመቀባት የተጣለባት ኢየሱስን የመግለጥ አደራ አሽቀንጥራ ጥላ ኢ-ፍትሐዊና ጨፍላቂ የትምክህተኛ አስተሳሰብ ውጤት የሆነው ኢትዮጵያዊነትን ስትሰብክና ስታስተጋባ የፖለቲካ መሳሪያ ከመሆን አልፋም የግፍና የበደል አምባሳደር በመሆን ከመጡ ነገስታትና የአገር መሪዎች ጋር እየተቆራኘች፣ መልከዐ መልክዕ እየጻፈች እየደገመችምና እያስደገመች በፈጣሪ ከማያምኑና ከጣሉ የደርግ ወታደራዊ መንግስት ዓይነቱ ተወዳጅታ ስታሸበሽብና ስታሸረግድ፣ አብያተ ክርስቶያኖችዋን እየዘጋች መሪዎችዋም አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ ደብዳቤ እየጸፈች ዛሬ ላይ የደረሰችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተጠቅመው ንጹሐን ዜጎችን ሲያደቁ፣ ሲያሳቅቁ፣ ሲጨፈልቁ፣ ሲገድሉና ሲያርዱ የመጡበት መንገድ አልበቃ ብሏቸው ፈሪሐ እግዚአብሔር የራቀባቸው የአማራ ልሒቃን አሁን ደግሞ “የጌታ ነኝ” (ጴንጤ) በማለት የሚታወቀው የክርስትና ክንፍ አገልጋዮች አፍ ላይ በመቀመጥ በህዝቦች ላይ አፍዝ አደንግዛቸውንና አዚማቸውን በመርጨት ላይ ተጠመዷል፤ እነዚህን እናራቁታቸዋለን። ሳይሸቃቀት የእውነትና የጽድቅ ቃል የመስማትና የመማር ፍላጎት ላላቹ ወገኖች ደግሞ ጽሑፉ በይዘቱ የእውነት ምስክርነት ለመስጠት ያለመ ጽሑፍ ለመሆኑ ስገልጽ በአክብሮት ነው።  

 

መንደርደሪያ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ መንግሥት የህዝብ አገልጋይ ነው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ከህዝብ የምንደብቀው ነገር አይኖርም፣ የገዢ ፓርቲ ስብሰባዎችም ቢሆኑ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ይተላለፋሉ፣ የሃይማኖት መሪዎች ግልጽነት ይንሩባቹ፣ እርስ በራሳችሁ ተዋደዱ፣ ተፋቀሩ፣ ፍቅር ያሸንፋል፣ ማሰር ማስደድ መግረፍና መግደል መሸነፍ ነው፣ መሳሪያ ማንሳት ኋላቀርነት ነው ዘወተ በማለት ሰማይና ምድሩ ሲያዳርስ የነበረ ና የሰላም ሰው ተብሎም የከበረ ሽልማት የተበረከተለት ሰው ከመቅጽበት እንዴት፥ ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ ጦር ግንባር፣ ህጻናት ሳይቀሩ ሴቶች ተደፈሩ ሲባል ምን ታካብዳላችሁ፣ ዜጎች አለቁ ሲባል ሞትን አታካብዱ ሞት አሜሪካም አለ፣ ሰላም አጣን መንግስት ሊደርስልን ይገባል ሲባል ስታዩኝ የሰፈር ምልሻ እመስላለሁ፣ ጦርነት የሰው ህይወት የሚበላ ነው እያለ ሲመጻደቅ የነበረ ሰው ደመሰስናቸው አጠፈናቸው አወደምናቸው! ወዘተ ወደ ማለት እንዴት ተሸጋገረ? ወይስ ሰውየው ቀድሞውኑ የበግ ለምድ የለበሰ ውሸታም ነበር ማለት ነው? የሚል ጥያቄ የብዙዎች ጥያቄ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለራሱ ካለው የተጋነነ እምነትና አስተሳሰብ የተነሳ መዋሸትንና በሐሰት መመስከርን እንደ ጀብድ በመቁጠር ወደ ማይክ በተጠጋ ቁጥር የሚለጠጠው ምላሱ በጀው ወይስ ፈጀው? በማለት በሰፊው አንስተን እንወያያለን። እውነት ነው መጽሐፍ “ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም” ይላል፤ ዳሩ ግን፥ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰው ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ሐሰተኛ ማሊያና መታወቂያ ለማራገብና ለማስረጽ ሲቅበዘበዝ በመንገዱ ላይ የሚገጥመው ይህን የአዝማሪዎች ትርክትና ትብታብ የማይቀበል ማንኛውም ሰው መሳደብና መራገም፣ ማዋረድና ማኮሰስ የተካኑበት ስራቸው ስለሆነ በአፋቸው “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው” እያሉ በስራቸው ሁሉ ደግሞ ፈጣሪም ቢሆን ሐሰተኛ ነው! ብለው የሚያምኑ ነፈዞች ናቸው። በዚህ ዙሪያም በጨረፍታ አንዳንድ ነጥቦች እንመለከታለን።

Videos From Around The World

 

ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ዘራፊና ነፈሰ ገዳይ ማንነታቸው ለማስፋፋትና ለመደበቅ ያመቻቸውና ያስችላቸው ዘንድ እንደ ጋሻና ጦር ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል የክርስትና ኃይማኖት አንዱና ዋነኛ መሳሪያቸው ለመሆኑ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው። የአማራ ልሒቃን፥ መንፈሳዊ፣ የፍቅርና ስልጡን አስተሳሰብ የሚመስል አደናጋሪ አባባሎችና ቋንቋ በመጠቀም ምቀኛ፣ ወራዳና ነውራም ማንነታቸውን በማድበስበስና በመሸፋፈን እውነትን መሸጥና በአንጻሩ ውሸትንና አሉባልታን በማራገብ የታወቁ፤ ሐሰትን በመፈብረክ፣ አሉባልታን በማሰራጨትና በማራገብ የሚስተካከል የሌላቸው የሐሰት ቋትና ጎተራ ናቸው። በዛሬው ዕለት ንባባችን ይህን ነውራም የአማራ ልሒቃን የበከተ እምነትና ምክር፥ በሰፊው ደግሞ የምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን እና የከሰሩ ምቀኞች የኤርትራ ባለሥልጣናት ምክር እየሰማ፣ የእነሱን መሳሪያና ተላላኪ በመሆን በትግራይ ህዝብ ላይ ወረራን የፈጸመ፣ እሳት ውስጥ ገብቶም እየተጠበሰ ያለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ ምላስ መዘዝና መጨረሻው ኢትዮጵያውያን “የኢትዮጵያ አምላክ” በማለት በከንፈራቸው ብቻ የሚያውቁትን፣ ሰይጣናዊ ግብራቸው ለመደበቅና ለመሸፋፈን የሚጠሩትና የሚመጻደቁብን አምላክ የእውነት ቃል ሚዛን በሚገባ እንፈትሸዋለን።

 

ሐሰተኛ ምላስ እጠላለሁ

 

መጽሐፍ “በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ” እንዲል የዐቢይ አህመድ ዓሊ አለ ቦታው መቀመጥ ተከትሎ በአሁን ሰዓት የትግራይ ህዝብ፥ በኃይማኖት፣ በጋዜጠኝነት፣ በሽምግልና፣ በዳኝነት፣ በፖሊስ፣ በመከላከያና በመንፈሳዊ ማኅበር ወዘተ ስምና ቀሚስ የተደበቀ ያላየው የሰው አውሬ አለ ለማለት አይቻልም። “የጌታ ነኝ” እያለ የጌታ አገልጋዮች ካህናት ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ በሰይፍ አጋድሞ የሚያርድ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይዞት ያልመጣ፣ ያልገለጠውና ያላየነው የጥልቁ የጨለማ ስራ የለም። ሰውን የሚያክል ፍጥረት እንደ በግና እንደ ፍየል ሰውነቱ ቁልቁሊት ተደፍቶ ለህልፈት ሲዳረግ አይተን የተሰማን ጥልቅ ሐዘን ሳንጨርስ፤ አሁን ደግሞ ከቀድሞ ይልቅ በከፋ መልኩ “የኢትዮጵያ አምላክ! ኢትዮጵያ የእመቤታችን የአስራት አገር ናት! ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ናት! ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው!” በሚሉና ሌሎች በርካታ ሐሰተኛ መፈክሮች በማሰማትና በማስተጋባት የሚታወቁ አጉረምራሚዎች፣ ተሳዳቢዎች፣ ተራጋሚዎች፣ ሐሰተኞች፣ አስመሳዮች፣ ምቀኞች፣ መተተኞችና ምዋርተኞች የአማራ ልሒቃን እሸትና በቆሎ የመጥበስ ያህል “ማጅራቱን በለው፤ ጥይት አታባክ” እየተባሉ የትግራይ ወጣቶች በጥይት እየደፉ፣ ልብሳቸውንም እያወለቁ ወደ ገደል ሲወረወሩና ሰውን እንደ ልጣጭ ሲጣሉ ለማየት በቃን።

 

እነዚህ ሰብአዊነት ያልፈጠረባቸው፣ በንጹሐን ደም የሰከሩ፣ መዝረፍ፣ መግደል፣ ለአቅም ያልደረሱትን ህጻናት ሴት ልጆች ጨምሮ የካህናት ሚስቶች ማራከስና ማስነወር የአባቶቻቸው የሆነባቸው ወስላቶች የኤርትራና የኢትዮጵያ ሰው በላ ሠራዊቶች በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለውን ግፍና በደል ስናገር ማንኛውም ዜጋ በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ያየውንና ለማየት የቻልነውን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው። በሌላ አባባል፥ በምድር ክበብ ላይ የተቀመጠ፣ ጣራና ግድግዳ የማይዘው፣ በምክሩ ጻዲቅ፣ በስራው የማይሳሳት፣ ከአመጸኞች ጋር ህብረት የሌለው፣ ክፉ አድራጊዎችን የሚበቀል፣ የዘገየ ቢመስልም የማይመሽበት፣ ፍትህንና ፍርድን ሲያደግ የሰው ምስክር የማይጠራና የማይሻው፣ “የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል” ተብሎ ጻድቁን የተመሰከረለት አምላክ ያየውና የሚያየው ሁሉ አያጠቃልልም። ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ፥ ሦስት ሴት ልጆቹንና ሚስቱን ቤተ መንግሥት ያስቀመጠ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግን፥ ትግራይን ለመውረርና ለመጨፍጨፍ የሏኳቸው ሴቶች ወታደሮቼን የአበባ እቅፍ ይዘው በመቀበል ፈንታ ሠራዊቴን በሳንጃ ተወግተው ሳለ የትግራይ ሴቶች በኢትዮጵያና በኤርትራ ሠራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረዋል! የሚለውን የትግራይ ህዝብ ስምታና የዓለም ማህበረሰብ አቤቱታ ለእኔ ዘፈን ነው አለን። ወለጋ ህዝብ ለወራት ኢንተርኔት በመዝጋት በሰማይ በምድር እንደ ጨፈጨፍኩት እንዲሁ የትግራይ ህዝብ የማልጨፈጭፍበት ምክንያት ምንድ ነው? በማለት ዓለምን ሲሞግትና የአገር ሉዓላዊነት አስደፍሮ ወራሪው ኃይል ማስወጣት አልችልም! በማለት አፉን ሞልቶ ሲናገር የተሰማው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ተደብቆ ሳይሆን በዛሬው ዕለት (ማርች 23/2021) በሚድያ በአደባባይ ከተናገራቸው በርካታ አሳፋሪ የቀቢጸ ተስፋ ንግግሮቹና ካሰማቸው ኑዛዜዎች መካከል ነው። አይደለም የአገር ሉዓላዊነት ሊያስጠብቁ ቀርቶ መቀመጫቸው የማይጠብቁ የአማራ ልሒቅን በበኩላቸው የተለመደና የተካኑበት ባዶ የቃላት ሽለላና ቀረርቶ ማሰማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አጠናክረው ገፍተውበታል። 

 

መጽሐፍ፥ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ (1) ትዕቢተኛ ዓይን፥ (2) ሐሰተኛ ምላስ፥ (3) ንጹሕን ደም የምታፈስ እጅ፥ (4) ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ (5) ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ (6) በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ (7) በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ” እንዲል፤ ዐቢይ አህመድ ዓሊ “አውቀዋለሁ” የሚለው፣ የአማራ ልሒቃን፣ ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ “የኢትዮጵያ አምላክ!” በማለት የሚጠሩት አምላክ ይህ ከሆነ እዚህ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ተብለው ከተዘረዘሩ መጥፎ ባህሪያት መካከል፥ ሐሰተኛ/ውሸተኛ ምላስ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል። ለምን? ሐሰተኛ ምላስ ጽድቅንና እውነትን የሚገፋ አደገኛ ሰይጣናዊ ባህሪይ ነውና። እንግዲህ ሁላችን እንደምናውቀው ለልፉት በርካታ ዓመታት፥ ኢትዮጵያ አገሬ፣ ኢትዮጵያ እናቴ፣ ኢትዮጵያ መቃብሬ፣ ኢትዮጵያ መቀመጫየ ወዘተ በማለት የሚታወቁ፤ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም ባንዴራ ለብሰው ባንዴራ እያውለበለቡ ሰው ሲሳደቡና ሲራገሙ፣ በሰው ላይ ሲያሟርቱ የሚታውቁ፣ ደም የተጠማ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀነቅኑ ግብዞች ልዩና ሁነኛ መታወቂያ አንዱ በዜጎች መካከል ጽብን የሚዘራ፣ የክፉ ልብ መገለጫ የሆነ፣ ደም አፍሳሽ፣ ትምክህተኛና ያልተገራ ተራጋሚ የኤልዛቤል መንፈስና ሐሰተኛ ማላሳቸው ነው። አንድ የትግራይ፣ የደቡብ፣ የኦሮሞ ሰው ወዘተ እንደ’ነሱ ሐሰተኛ ካልሆነ፣ በዓላማ ለሚያስተጋቡት ሐሰተኛ አጀንዳ ተባባሪ ካልሆነና ተቀበል ሲባል ሳይጠይቅ የተሰጠውን እየተቀበለ ትብታባቸውን የማያራግብ ከሆነ፣ አዝማሪ ያነገሰብን ምንሊክ ንጉሤ ነው ብሎ ያልተቀበለና የማይቀበል ሰው ሁሉ “ኢትዮጵያዊ” ተብሎ ሊጠራና ሊታውቅ ቀርቶ እንደ ሰው እንደማይቆጠር ሁላችን የምናውቀው ሐቅ ነው።  

 

እንግዲህ ቀደም ሲል ባነበብነው ቃል የተመለከትናቸው ሰባት አስፀያፊ ባህሪያት ውስጥ ኩልል ብሎ የሚታይ አውራ ቂስ (ዐቢይ አህመድ ዓሊ) ያለ አድማጭ የሚናገር ሰው ሳይሆን ሰውየው ሐሰት ሲነገርና ሲዘራ ጆሮውን ሰጥቶ የሚያዳምጥ፣ በውሸት ደስ የሚሰኝና ሐሴት የሚያደርግ፣ በሐሰት ቤት እገነባለሁ ብሎ የሚያምን፣ የሐሰት ልክፍት የጸናበት፣ እውነት ሲነገር ጆሮው የሚያሳክከውና የሚያቅለሸልሸው፣ የምስራች ተናጋሪና እውነት አብሳሪ አሳዶ ለመግደልና ደሙን ለማፍሰስ እንቅልፉን አጥቶ የሚያድር አከአባዊ ባህሪይ የተላበሰ አካል ስላለ ነው። ሌላው፥ ሐሰተኛ ምላስ እጠላለሁ ያለ እኔ ወይንም ዳዊት፣ አብርሃምና ሙሴ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ አምላክ! በማለት የሚመጻደቁብን አምላክ ነው። ታድያ ይህ ማለት፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ሐሰተኛ ሰው - ለምን ትዋሻለህ? ተብሎ ለሚቀርብለት ጥያቄ/ሲጠየቅ፤ የምዋሽበት ምክንያት እንዲህና እንዲያ ነው፥ በማለት ሊዘረዝረውና ሊደረድረው የሚችለው ምክንያት ሁሉ ምንም ውሃ እንደማይቋጥርና ሊያቀርበው የሚችለው ማንኛውም ምክንያት በምንም ዓይነት መልኩ ከተጠያቂነት ነጻ ሊያወጣው እንደማይችል ግልጽ በሆነ ቋንቋ የሚያስረዳ ነው። እውነት ነው፥ ሐሰተኛና ውሸተኛ ሰው ሲዋሽና በሐሰት ሲመሰክር አንዱና ዋነኛው ምክንያት ሰውየው ውሸታም ስለሆነ ነው።

 

በተጨማሪም፥ ውሸታም ሰው ካልዋሸ ስራ የሰራ ስለማይመስለው ሲዋሽና በሐሰት ሲመሰክር ምንም ስለማይመስለው ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስምዐ ሐሰት በሆኑ ኢቲቪ ዋልታ ፋናና መሰል ልሳኖቹ በአደባባይ፥ “የጌታ ሰው ነኝ፣ ዕለት ዕለት እጸልያለሁ!” ወዘተ እያለ ሰውፊውን ህዝብ ሲያጭበረብርና ሲያዘናጋ የኖረ ሰው ከመሆኑ በላይ፤ በህገ ወጥ መንገድ ዙፋኑን ለመጠበቅና ስልጣኑን ለማደላደል የሄደበት ርቀት የመረመርንና የተመለከትን እንደሆነ ጉዞው ለማመን የሚከብድና ውሸትን መናገርና ሐሰትን መንዛት ቁርስ፣ ምሳና እራቱ ያደረገ ሰው ሆኖ እናገኘዋለን። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ መዋሸት አመል የሆነበት፣ ውሸት ማስተጋባትና ማሰራጨት ሞያው ያደረገና በዚህም የሚመካ፣ በሐሰት ሰፊውን ህዝብ ማደናገና ማወናበድ ትልቅ ስጦታና አቅም ነው! ብሎ የሚያምን ወስላታ ሰው የሚዋሽበት ምክንያት በዋናነት፥

 

1.      እውነትን መቀበልና መሸከም የሚያስችል መንፈሳዊ፣ ስነ ልቦናዊና ሞራላዊ አቅም ስለሌለው፤

2.     እውነትን በመግለጥና ለእውነት በመቆም ይህን ተከትሎም ሊመጣ ሲለመችለው፤ ማለትም እውነት ለሚያስከፍለው ዋጋ የሚሸከም ትክሻ (ቁመናና ስብእና) ስለሌለው ነው።

 

ትናንት ዓይኔን ግንባር ያድርገው! በማለት በአደባባይ የካደው የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ወረራ ላይ መሳተፍ ይህን ተከትሎም የአማራ ጨምሮ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙት ዘር የማጥፋትና የማጽዳት ወንጀል ሳይቀር ለማመን ተገዷል። እየተባለ ያለ ነገር ሁሉ ውሸት ነው፣ ፕሮፓጋንዳ ነው፣ ትግራይን ለመጥረግና ለማጽዳት እኛ መቼ እናንሳለን እያለ ሲደነፋ፤ ነገ ህወሐት መሪዎች ጋር ለድርድር ሊቀመጥ አጥፍተናቸዋል፣ ተደምስሰናቸዋል ወዘተ እያለ ኢትዮጵያውያን ሲያወናብድና ሲያስጨፍር የነበረው ሐሰትን መጎናጸፍያው ያደረገ ሰው ዛሬ ድፍን ዓለም አውሬ ማንነቱና ነፍሰ ገዳይነቱ በተጨባጭ ማስረጃዎችና መረጃዎች ሲመሰክሩበትና ራቁቱን መቅረቱ ሲመለከት ደግሞ አስር ፓውንድ የሚህል ሜክአፕ ተቀባብቶ የሚቀርበው ፊቱ ሳይቀር ጠቁሮበት ጫፍና ጅራት የሌለው ቃሉ ለመስጠት ተገዷል። ታድያ፥ የቆሳሰለችው ነፍሱ ለማባበልና ኢጎው ለማስታመም ዐቢይ አህመድ ዓሊ እውነታውን ለመግለጽና ለመቀበል የተጠቀመበት ‘ego-defense mechanism’ በመባል የሚታወቅ የወደቀ፣ የተመታ፣ የተሸነፈና እጅ የሰጠ የስነ ልቡና ለማባበልና ለማስታመም የሚደረገው ዙሪያ ጥምጥም አገላለጽ ልብ ማለቱ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የገባበት ጉድጓድ ጥልቀት ማናችንም ልንገምተው ከምንችለው በላይ እንደሆነ ለማየትና ለማስተዋል የሚያስፈልገን እጅግ አስፈላጊ መረዳትና ዕይታ ነው። በርግጥ፥ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የተመሰቃቀለ አስተሳሰብ (polarized thinking) ተብሎ የሚታወቅ በሽታ ሰለባ ወደ መሆን ተሸጋግራል። ይህ ማለት በአንድም በሌላም ምክንያት አንዴ የተነገረውን ውሸትን “እውነት ነው!” ብሎ ለማሳመን በውሸት ላይ ሌላ ውሸት መጨመርና ማነባበር ማለት ነው። ይህ ዓይነቱ በሽታ የተጸናወተው ሰው ደግሞ ሲዋሽ ይኖሯል እንጅ ማቆሚያ አይኖረውም፤ ከውሸት የሚለየውም ሞት ብቻ ይሆናል። ጥጉ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በህይወት እስካለ ድረስ ሰላሙን አጥቶ ዘልአለም የንጹሐን ዜጎች ደም እንዳሳደደው ይኖራል።

 

በኢሳይያስ አፈወርቂ አስተባባሪነት በዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ በአማራና በመቃድሾ ሰራዊትና ወታደሮች በትግራይ ህዝብ ላይ ያልተነገረ እንጅ ያልተፈጸመ ግፍና ወንጀል የለም። አራት ሚልዮን የማይሞላ ህዝብ መምራትና ማስተዳደር አቅቶት አገሩን ወደ ጣራ-አልባ ውህኒ ቤት የለወጠና ህዝቡንም የምድረ በዳ አራዊትና የዓሳ ነባሪ ቀለብ ካደረገ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መተሻሸትና መዳራት፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊን የኢሳይያስ አፈወርቂ በሽታ ተሸካሚ ከማድረጉ በላይ ኢትዮጵያ እንደ አገር ተወልዳ ገና እግር ሳትተክል የተጨናገፈችው ኤርትራ የገባችበት ድቅድቅ ጨለማና የቁልቁለት ጉዞ ማህበርተኛ እንድትሆን፣ የድህነትና የእጦት ካምፕ እንድትቀላቀል አስገድዷታል። ለምን ብቻችን እንጠፋለን/እንናጣለን? የሚለው የዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ምቀኛና ምዋርተኛ አስተሳሰብ - ቂምና በቀል ካሰከረው የኢሳይያስ አፈወርቂ ትግራይን የማውደምና ኢትዮጵያን በደም የማጨቀየት አጀንዳ ተዳምሮ ትግራይንና የትግራይን ህዝብ ፈጽሞ እንዲጠፋና እንዲበርስ ግንባር ፈጥረው በውንጀላና በሐሰተኛ ክስ በትግራይ ህዝብ ላይ ወረራን ፈጽሟል። ከዚህ የተነሳም ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት የንጹሕ ሰው ደም የረከሰባት አገር ከመሆናዋ በላይ በንጹሐን ሞት ላይ የሚጨፈርባት በንጹሐን ደም የጨቀየች የደም መሬት ሆናለች። በውሸት ወደ እልቂትና ደም መፋሰስ እንድንገባ ያደረገ ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ያደረገውን ዛሬ ላይ ሆኖ ሲያየው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ሲገነዘብ፣ ሌላ ተጨማሪ ሐሰተኛ አጀንዳ ፈጥሮ የተቀረውን እያተላለቀ ለመኖር የማይመለስ ሰው እንደሆነ በዛሬው ዕለት በፓርላማው ውሎ ግልጽ አድርጓል።

 

በዐቢይ አህመድ ዓሊ ሐሰተኛ አንደበትና ውስላታ ማንነት የተነሳ፥

 

v ትግራይ እንደ አገር በርሳለች፤

v ሚልየኖች ተጋሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤

v አንስትና ህጻናት ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋሩ የሞቀ ቤታቸውን ጥለው በሰው አገር በምድረ በዳ በስደት ለመኖር ተገዷል፤

v ግራና ቀኛቸውን የማያውቁ ህጻናትና የደከሙ ሽማግሌዎች በርሃብ አልቀዋል፤

v የትግራይ መነኮሳትና እናቶች የሰው አገር ሰዎችና ሀብት ንብረታቸውን ለመጨፍጨፍና ለማብረስ ብርና ወርቅ ተከፍሏቸው በገቡ በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች ክብራቸው ተደፍሯል ጅምላዊ የወሲብ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤

v ወጣቶች በጠራራ ጸሐይ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተጨፍጭፏል፤

v ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት በታንክና በቡዝቃ ወድሟል፤

v ሌላ በደል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ ካህናት ስጋወ ደሙ እንደያዙ ከነ መስቀላቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደ ከብት ታርዷል፤

v ታቦትና የጌታ ስጋ ወደሙ፥ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በአማራ ሠራዊት መሬት ላይ ተጥሏል፤ ተደፍቷልም፤

v የታሪክና የኃይማኖትና የህይወት ቅድሳት መጻህፍት ተቃጥሏል ተዘረፏልም፤ 

v ከጥይት ያመለጠውን ህዝብ በርሃብ ለመግደል እህልና አፈር ተስማምቷል፤

v የገበሬ ማሳ በእሳት ተቃጥሏል፤

v ከተሞች ፈራርሰዋል፤

v ጤና ኬላዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ፋብሪካዎች፣ የህዝብና የመንግስት ንብረት በአጠቃላይ፥ ነበሩ ለማለት በማይስችል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤

v እህልና መድኃኒት ለተቸገረች ነፍስ እንዳይደርስ ተከልክሏል፤

v ሚልየኖች ለወራት ያህል እህል ፈጭተው እንዳይመገቡና በጨለማ ብርሃንን እንዳያዩ የኤለክትሪክ አገልግሎት እንዳያገኙ ተፈርዶባቸዋል፤   

v ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድና የአማራ ልሒቃን በትግራይ ህዝብ ላይ በቀንና በሌሊት እየፈጸሙት ያለውን ናዚያዊ ድርጊት ዓለም እንዳታይና እንዳት ሰማ ተብሎ ሚልየኖች ከማኝናውም ዓይነት የመገናኛ አገልግለቶች ውጭ ተደርጓል።

 

ይህ ምስክርነት ቀይ መስቀልና የተባበሩት መንግስታት ጨምሮ የዓለማችን ትላልቅ የመገናኛ ብዙሐን፣ የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት፣ የተለያዩ የዓለማችን አገራት መሪዎች፣ ተወካዮችና አምባሳደሮች ያዩትን በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፈው እንደ አንድ ሰው የመሰከሩት ሐቅ ነው። ላለፉት አራትና አምስት ወራት ብቻ የትግራይ ህዝብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማታሰብና የማይታመን ግፍና በደል በዐቢይ አህመድ ዓሊ፣ በኢሳይያስና በአማራና ሠራዊቶች ተፈጽሞበታል፤ እየተፈጸመበት ይገኛል። ታድያ፥ የዚህ ሰው ከፍ ከፍ ብሎ በአመጻ መናገርና ሐሰተኛ ምስክርነት እስከ መቼ? ፈጣሪ ለምን ዝም ይላል? የሚል ጥያቄ ላላችሁ ወገኖች ይህ በአጭሩ የተዘጋጀ ጽሑፍ መልስ አለው ንባቡን ይቀጥሉ።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ውሸትን እንደ ጥበብ የተለማመደ ሰው  

 

ሰዎች በአጠቃላይ መዋሸት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ውሸታም ሰው እንደሚጠሉም ይናገራሉ። ዳሩ ግን፥ በመንፈሳዊው ዓለም የውሸት ሚዛን የንጹህ ሰው ደም ከማፈሰስና ከመግደል እኩል ከባድ ኃጢአት እንደሆነ የሚረዱና በዘፈቀ ከመናገር አንደበታቸውን የሚገዙና የሚቆጥቡ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በሚፈጥሩትና በሚደረድሩት ምክንያት ራሳቸውን በቀላሉ ማታለል ስለማያቅታቸውና ስለሚቀልባቸውም በትልቁም በትንሹም እንዲሁ ሲዋሹና በሐሰት ሲመሰክሩ ምንም አይመስላቸውም። ኢትዮጵያውያን “የኢትዮጵያ አምላክ” በማለት ስሙን የሚጠሩት አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ራሱን የገለጠ አምላክ ከሆነ መጽሐፉ የሚያስተምረው ትምህርት እንግዲህ ውሸት ፈጽሞ የተናቀ ፅያፍ ባህሪይ እንደሆነ ነው። ለምን? (1) ውሸት የሐሰት አባት የብሎ የተነገረው የሰይጣን ቋንቋ ስለሆነ (2) ውሸት በእውነት ላይ ማመጽና እውነትን መቃወም ስለሆነ ነው።

 

እዚህ ላይ ትኩረት መስጠት የምፈልገው ነገር ቢኖር በእውነቱ ነገር ሰው ጣመኝ ድገመኝ እያለ ሲዋሽና በሐሰት ሲናገር እንዲሁ እንዳይደለ አጽንዖት ለመስጠት እወዳለሁ። ውሸት ምርጫ ነው። እምነት የጣለብህን ሰው ማታለልና ማወናበድ እንደ እውቀትና ችሎታ የሚቆጥሩት የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ (a fraud and a pathological liar) ሰው ሲዋሽ እንዲሁ በድንገት አይደለም የሚዋሸው። ይህን ዓይነቱ ሰው ሲዋሽ አስቦበት፣ የሚያዋጣውን አይቶ፣ የሚበጀኝ ይህ ነው! ብሎ በውሳኔ ነው የሚዋሸው። ምን ነው ቢሉ? ሰው ያልሆነና ያልተደረገ ነገር ሆነ/ተደረገ ብሎ ከመናገር ይልቅ ነገሩን በትክክል ሳይቀንስና ሳይጨምር ያለውንና የሆነውን የመናገር ምርጫ አለው። ሐቁን ብናገር ያንና ይህን አጣለሁ! ብሎ ስለሚያስብና ስለሚያምን ግን በእውነት ላይ ፊቱን አዙሮ ያልሆነውን እንደ ሆነ - ያልተደረገ ተደረገ! በማለት ውሸትን ለመሸጥና ለመቸብቸብ ምላሱን ይስላል።

 

ይህ፥ “ዕለት ዕለት እየጸልያለሁ፣ ጌታ ይባረክ፣ ጌታ መልካም ነው” እያለ በአፉ ያታለንና የደለለን ሰው (ዐቢይ አህመድ ዓሊ) በሚልዮኖች ፊት ዓይኑን በጨው አጥቦ በአደባባይ ፍጥጥ ያለ ውሸት ሲያስተጋባ/ሲዋሽ፥ እውነትም ህይወትም መንገድም እኔ ነኝ ያለ ጻድቅ ጌታ ይልቅ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለሌላ አይመጣም ተብሎ የተነገረለት ሰይጣን ምርጫው ስላደረገ ነው። ምክንያቱም፥ ሰው እንዲሁ ውሸት አይጸናወተው በልቡ ክፉ አሳብ ሲበቅል እንጅ። የሚያምን ሰው እንደ ማንኛውም ሰው ስህተት ይፈጽም እንደሆነ ነው እንጅ የውሸት ፋብሪካና አከፋፋይ ሆኖ ውሸትን በዚህ ደረጃ አይለማመድም። አንድም፥ ዋሾ አንደበትና ሐሰተኛ ምላስ የአመጸኛና ያልተለወጠ ክፉ ልብ መገለጫ ባህሪዎች ናቸውና።

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ለሰሚ ጆሮ በሚሰቀጥጥና በሚያሳፍር ደረጃ በተደጋጋሚ በአደባባይ ሲዋሽ፣ ሀገርና ህዝብ በውሸት ማዕበል ሲያውክና ሲንጥ፤ አንድምታው፥ የፈለኩትን መናገርና ማድረግ እችላለሁ፤ የወደድኩት ከማድረግ የሚከለክለኝ፣ እኔን ሊያስቆም የሚቻለው ማንም የለም! ብሎ ስለሚያምን ነው። በውጤቱም፥ በዚህ ዘመን እንደ ናቡከደነጾር ሳር ያስግጠዋል ባይባልም መንገዱ የማይመረመር አምላክ ትዕቢተኛው በሚገባው መንገድ ግን ያብረክርከዋል። ይሄው በዛሬው ዕለት በፓርላማው ፊት ቀርቦ ሲዘበራርቅ ያየነው ዓቢይ አህመድ ዓሊ ትናንት አፉን ሞልቶ በእውነት ላይ ሲያምጽ የነበረ ሰው ነው። ነገ ደግሞ ለማየት ያብቃን እንጅ ለበደለው የትግራይ ህዝብ ተንበርክኮ ምህረትና ይቅርታ መጠየቁ የማይቀር ነው። እግዚአብሔር የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ በውሸት ልክፍት የበረታ፣ የሐሰት ምስክርነት በመስጠት የንጹሕ ሰው ደም የሚፋስ፣ ነፍሰ ገዳይ ጋር የሚወዳጅ አምላክ አይደለም። እግዚአብሔር የጠላው፣ የተጸየፈውና የናቀው ሰው አይደለም መቶ አሥር ሚልዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ ሰባትና ስምንት ቢልዮን የዓለማችን ህዝብ የድጋፍ ሰልፍ ቢወጣ ከእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ አያስመልጠውም።   

 

ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም

 

ሰይጣን በቆመበትና በተገኘበት ስፍራ ሁሉ ውሸታም ነው። ሰይጣን አፉ የከፈተ እንደ ሆነ እውነት አይገኝበትም። እውነት ለባህሪው ስለማይስማማው፣ ውስላታ ስለሆነ የሚቀናው ውሸትና ቅጥፈት ነው። በገነት ቢቆም ውሸታም ነው፤ በምድረ በዳና በከተማም ቢገኝ ውሸታም ነው። ያልሆነውን ሆኖ ለመታየት፥ የማይለውና የማይፈጥረው ውሸት የለውም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ በፓርላማ ፊት ቀርቦ የሚያሰማው ሪፖርት ውሸት ነው፤ በህዝብ ፊት ቆሞ የሚናገረው ቃል ሁሉ ውሸት ነው፤ ከአገር መሪዎችና ተወካዮች ጋር በስልክ ሳይቀር የሚለዋወጠው መልዕክት ሁሉ ውሸት ነው፤ በልዩ ልዩ የሶሻል ሚድያ መድረኮች ስለ ራሱ ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚያሰፍረው ቃል ሁሉ ውሸት ነው። መጽሐፍ፥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና” እንዲል (የዮሐንስ ወንጌል 844)። ይህ በአማርኛ ያነበብነው ቃል ቀለል ባለ አማርኛ ያመሳጠርነው እንደሆነ ቀደም ሲል እንዳሰፈርኩት፥ ሐሰትን የተለማመደ ውሸታም ሰው የሰይጣን ልጅ ነው እያለን ነው። ሰው በእውነት መንፈስ ሲሞላ/የተሞላ እንደሆነ ለውሸት ቦታ የለውም፤ ሐሰትም አይጠጋውም። ሰው በልቡ ሰይጣን የገባበት እንደሆነ ግን እንደ ዐቢይ አህመድ ዓሊ አፉ በከፈተና ወደ ማይክ በተጠጋ ቁጥር የሚናገረው ሁሉ ውሸት ነው፤ አንዳች እውነትም አይገኝበትም። ሰው የሰይጣን መጫወቻ ሲሆን በነጋ በጣባ ቁጥር ውሸትን መናገርና ሐሰትን መዝራት የመተንፈስ ያህል ነው የሚለማመደው።

 

የዕድሜው እኩሌታ ያህል ሁለመናው የሰለጠነበት ዐቢይ አህመድ ዓሊ የተጸናወተው የመዋሸት ክፉ በሽታ ዛሬ ከራሱ አልፎ በዙሪያው በተቀመጡ ሹማሙንቶቹና በሚልዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቹ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አጋብቶታል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ የገለባና የእብቅ ያህል ክብደት የሌለው፣ የማይታመን፣ የራሱ ውሸት የሚያምን ወስላታ ግለሰብ (Religious narcissist) ብቻ ሳይሆን፤ መጽሐፍ፥ እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል እንዲል ሐሰተኛና ምናምንቴ የኃይማኖት መሪዎች፣ ሐሰተኛ ሽማግሌዎች፣ ሐሰተኛ የፍትሕ ተቋማት፣ ሐሰተኛ ሰራዊት፣ ሐሰተኛ ህዝብ ሳይቀር መፍጠርና ማፍራት የተቻለው ተመዝኖ የቀለለ፤ አለ እየተባለ የጠፋ ሰው ነው።

 

ጠቢቡ በምሳሌ 195 ላይ “ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም” እንዲል፤ በሌላ ስፍራ ደግሞ ኢሳይያስ፥ “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው” እንዲል፤ በትግራይ መሬት በተጋሩ ላይ እየተፈጸመ ባለው ሰቆቆ የተነሳ ፈጣሪ ለምን ዝም ይላል? በማለት በጥያቄ የምንገኝ ወገኖች በዚህ ቃል እንድንታመንና ተስፋ እንድናደርግ እወዳለሁ። ለምን? ዐቢይ አህመድ ዓሊ ያበቃለት ሰው ነው። ዛሬ ላይ ሁኜ ይህን ስል ላይመስል ይችል ይሆናል ዳሩ ግን ነገሩ ለጥቂት ጊዜ ነው እንጅ በቀኑ መጨረሻ ዓቢይ አህመድ ዓሊ በዚህ መልኩ አናየውም። የሐሰት አባት የተባለው ሰይጣንና ተባባሪዎቹ በድርጊታቸው ከተጠያቂነት እንዳላመለጡ ሁሉ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በተመሳሳይ የጊዜ ጉዳይ ይሆን እንደሆነ ነው እንጅ ፍትህ እንደማያመልጥ፣ እንደሚሰበር፣ እዩኝ እዩኝ ባለበት ልክ ከሰው ሁሉ ተለይቶና ተደብቆ ለመኖር እንደሚገደድ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የትግራይ ህዝብ ታሪክ የሚያወሳ መጽሐፍ በትውልድ መካከል ለንባብ በተከፈተ ጊዜ ዐቢይ አህመድ ዓሊ እንደ አህመድ ግራኝ፣ እንደ ዮዲት ጉዲት፣ እንደ ምንሊክ፣ እንደ ኃይለስላሴና የደርግ ወታደራዊ መንግስት አረመኔነቱ የሚያወሳ “ወስላታው/መሽረፈት” ተብሎ እንደሚታወቅና እንደሚወሳ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ።  

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page