Back to Front Page

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ እኔ ስልጣኔን ከምለቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ይለቅ!

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ እኔ ስልጣኔን ከምለቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ይለቅ!

 

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

10-30-21

 

ስራውና አስተሳሰቡ የህጻን ልጅ የሆነ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ቀደም ሲል፥ ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያና ከኢምሬት መንግስታት ጋር በር ዘግቶ መክሮና ዘክሮ ሲያበቃ፣ በምድር፥ ዘራፊ አመንዝራና ነፍሰ ገዳይ ሠራዊቱ ከኤርትራ፣ ከሱማሌና የአማራ ኢንተርሃምዌ ሚኒሻና ታጣቂ በሰማይ የኢምሬት ድሮኖች አስተባብሮ ወረራ ከመፈጸሙ ከጥቂት ወራት በፊት በትግርኛ በሰጠው ቃለ መጠይቅ፥ ኢትዮጵያ ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንባር ፈጥራ ትግራይን ትወጋለች ብሎ ማመንና ማሰብ እጅግ አስጸያፊ ነው፤ እንደዚ ያለ ሴራ እግዚአብሔር የማይወደው ኃጢአትም ነው ሲል በእግዚ አብሔር ስም ስማማል ከሰነበተ በኋላ ቀደም ሲል የተጠቀሱ ኃይሎች አስከትሎ ትግራይን በሁሉም አቅጣጫ በመክበብና በመነጠል ዘራዊ ጨፍጨፋ የፈጸመ። ሳይቸግረው በራሱ ጊዜ ያነደደው እሳት በላይ ላዩ ተደፍቶ ደህና አድርጎ ሲለበልበውና ነገሩ እየዋለ ባደረ ቁጥርም የሌሊት እንቅልፍ ሲነሳው ደግሞ ከገባበት ጥልቅ ጉድጓድ ለመውጣትና ለማዘናጋት፥ የህጻን ቃል ሰምቶ የሚታለልና የሚዘናጋ ሰው ያለ ይመስልም አንድም፥ ሰላም ወዳድ ለመምሰልና ጦርነት የተወ ለማስመሰል አገሪቱ በደም ጎርፍ እየታጠበች ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመስለ ከሁለት ሳምንት በፊት በአንድ የእርሻ ስፍራ ተገኝቶ እንዲህ ብሎ ነበር፥ የክልል አመራሮች ክላሽ ላይ ያለው አብዮት አስቁማችሁ ወደ ፓምፕ ካመጣቹ፤ ታጠቅ፣ ተደራጅ፣ ዝመት ማለት ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም። ታጠቅ ምን? ፓምፕ፣ ትራክተር፣ ኮምባይነር እያለ ለማደናገር፣ ለማወናበድና ለማምታት ቢቃጣውም ይሄው ዛሬ ደግሞ ምራቁ ሳይደርቅ ፍጹም አንጻራዊ ድምጽ ለማስተጋባትና ለማራገብ ዓይኑን በጨው አጥቦ አገር የማውደምና የማፍረስ ተልዕኮ በመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ብቻ መቀልበስና መቅበር አይቻልም። መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ በማነቃቃትና ባለቤት በማድረግ የሀገርን ህልውና ከሁሉ አቀፍ ጥቃት መከላከል ያስፈልጋል በማለት አገሪቱ አሁን ከምትገኝበት የለየለት እልቂትና ደም መፋሰስ በከፋ የደም ጎርፍ ለማፍሰስ ጥሪ ሲያቀርብ የምንሰማው።

 

Videos From Around The World

ይህ (ዐቢይ አህመድ ዓሊን) ኃፍረት የማያውቅና ያላለፈበት፣ እንደ እስስት መልኩን እየለዋወጠና እየተገለባበበጠ፣ ሐሰተኛ ምላሱ እየወለወለ፥ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንደ በቆሎ እሸት እያገለባበጠ እየጠበሰና የእሳት ራት እያደረገ የሚገኝ ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የእግዚአብሔር ስም በአደባባይ ያሰደቡና እያሰደቡ ያሉ ነቢያት ነን፣ ፓስተር ነን እያሉ፥ በእግዚአብሔር ስም የሚጠነቁሉ ኮከብ ቆጣሪዎችና ጠጠር ወርዋሪዎች እየተመራ አገር በደም እያጨቀያት ይገኛል። መጽሐፍ፥ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና እንዲል (ራእይ 12፥12) የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት በሚል የሌለ መንግስትነት ስምና ሽፋን የተጠሰ መግለጫ ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ያለ ያለው፥ እኔ ስልጣኔን ከምለቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ይለቅ! በማለት ገና ምኑን አይታችሁ ነውና ነው መልዕክቱ።

በምድሪቱ እየፈሰሰ ላለ ደምና እየጠፋ ለሚገኝ ነፍስ ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂዎች

ዐቢይ አህመድ ዓሊና የዙፋኑ ተሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን ናቸው

 

ቅናትና ምቀኝነት ጸንቶበት በነገርና ጥላቻ የተሳከረ ግለሰብና ቡድን፥ ከሰውነት ወጥቶ የአውሬ ማንነት በመላበስ ምንኛ የጥፋትና የእልቂት መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ለማወቅና ለመረዳት ነባራዊ የኢትዮጵያ ሁኔታና አገሪቱን በደም እያጨቀዩ የሚገኙ የአራት ኪሎና የጎንደር ሽፍቶች የዕለት ዕለት ተግባራት መመልከት በቂ ነው። ይህ በዛሬው ዕለት የተሰጠ የክተት አዋጅና መግለጫ አንዱ ገጽታ አንድምታው ታድያ፥ ይህ በዐቢይ አህመድ ዓሊ የሚመራ ሀገራዊነት ያልፈጠረበትና ህዝባዊነት የማይሰማው ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት በትግራይ ህዝብና ከተሞች የፈጸመው አረማዊ ድርጊት ትተን ከቆቦ ጀምሮ ለፖለቲካ ትርፍና ፍጆታ ሲባል በተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ሲያደርገውና ሲሰራው የመጣ ማለትም መድፎቹና ታንኮቹን፥ ዜጎች በሚኖሩበት ማኸል መንደር፣ የከተማ ውስጥ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች፣ መስጊድ፣ ቤተ ክርስትያን፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት ውስጥ ተክለውና አቁመው የሚደርጉት አረማዊ ስራ በይፋ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያበረታታ ጥሪ ነው። በነገራችን ላይ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ውድመት በደረሰበት በዚህ ሰዓት ሠራዊቱ የተረፈችው ነፍስ ይዞ የንጹሐን ዜጎች መኖሪያ ሰፈር ውስጥ ከባድ መሳሪያ ተክሎና በህዝብ መካከል ሆኖ እንዲተኩሱ መምሪያ ለመስጠት የተገደደው የሽንፈት ሽንፈት መቅመሱና በቀቢጸ ተስፋ መወረሩ ብቻ ሳይሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሆነ የአማራ ልሒቃን በአሁን ሰዓት ከምንም በላይ የሚገዳቸው ፖለቲካዊ ሥልጣናቸው መጠበቅና ማራዛም እንጅ ለአማራ ህዝብ ደህንነት ሆነ ህልውና የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ክብር እንደሌላቸው፣ አስነዋሪ ድርጊታቸው ተከትሎ በዜጎች ሊደርስ የሚችል ሞትና እልቂት የማይጨቃቸው ለመሆናቸው ከዚህ በላይ ተጨባጭ ማሳያ ሊኖር አይችልም። ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን፥ ኖርክም ሞትክም የእኛ ጭንቀትና ችግር አይደለም! ሲሉ የናቁትና ያላከበሩት፣ የተዉትና የጣሉት በአማራ ክልል የሚገኙ ከተሞችና ገጠሮች ነዋሪ የሆነ ህዝብ ለማትረፍና ለመታደግ ታድያ የትግራይ ሠራዊት ተጨማሪ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

 

v የትግራይ ፕሬዝዳንት ድብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዲሁም ከፍተኛ የትግራይ ሠራዊት አመራር አባላት በኩል በግልጽ በተደጋጋሚ እንደ ተገለጸ፥ የትግራይ ሠራዊት ዓላማና ተልዕኮ አሁንም አንድና አንድ ነው። ይኸውም፥ በአገርና በህዝብ ስም በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍና በደል የፈጸሙ፣ በህገ ወጥ መንገድ የተቆናጠጡት ስልጣን ለማስጠበቅና ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በቀጣይነት ደም እያቃቡ ያሉና አገሪቱን የደም መሬት ያደረጉ ደም የተጠሙ ወንጀለኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ማስቆም፣ የአገሪቱን ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ነው።

 

v ለቆሰ እያከመ፣ ለደከመ እያበረታ፣ ላዘነና ተስፋ ለቆረጠ እያጽናና፣ ለተራበና ለተጠማ ጁስና አምባሽ፣ ልብስ ለሌለው ልብስ እየሰጠ ሙርከኛ የሚንከባከብ ግፍና በደል የወለደው የትግራይ ሠራዊት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ቀርቶ በግለሰብና በቡድኖች ላይ ትክክል ያልሆነ ነገር የመፈጸም ተልዕኮና ዓላማ የለውም።

 

v የአንድ ትውልድ ዕድሜ ያህል ወታደራዊ ተመክሮ፣ አቅምና ብቃት ባላቸው የተፈተኑ ጀኔራሎች የሚመራ፥ በወታደራዊ ዲስፕሊን የታነጸና የተገነባ የትግራይ ሰራዊት፥ የአማራ ህዝብ ሆነ የአፋር ህዝብ እንደ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ለይቶ የሚያይ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ደህንነትና ህልውና ለማረጋገጥ የታጠቀ የትግራይ ሰራዊት፥ የአፋር ይሁን የአማራ ህዝቦች ደህንነትና ህልውና እኩል ግድ የሚለው ህዝባዊ ሠራዊት ነው።

 

v ንጹሐን መታደግና የአፋር ሆነ የአማራ ከተሞች ኃላፊነት ከጎድለበትና ከማይሰማው የዐቢይ አህመድ ሰራዊትና የአማራ ልሒቃን ስልጣናቸው ለመጠበቅ ሲሉ በገዛ ህዝባቸው ላይ ያሰማሩት ነፍሰ በላይ የታጠቀ የጎበዝ አለቃ ማትረፍ ትግራይ ሠራዊት ቀዳሚ ተልዕኮ ነው። ተልዕኮው በሚገባ ለመወጣትም ይሄው ተጨማሪ መስዋዕት በመክፈል ላይ ይገኛል።

 

v የትግራይ ሰራዊት ከቆቦ ጀምሮ በገባበት ሰፍርና መንደር ሁሉ፥ የተበተነ ሲሰበስብ፣ የታወከ ሲያረጋጋ፣ የተራበ ሲመግብ የመጣ ህዝባዊ ሠራዊት ለመሆኑ መልካም ነገር የማይገኝበት ሰይጣን ሳይቀር የሚመመሰክረው ሐቅ ነው። የትግራይ ሰራዊት የጎንደር ዘራፊዎችና ጋጠ-ወጦች የሚያስቆም ሰራዊት እንጅ ያላስቀመጣት መርፌ የማያነሳ ሠራዊት ለመሆኑ ባለፈበት አከባቢ ሁሉ ምስክርነታቸው በአደባባይ የሰጡ የአማራ ክልል ከተሞችና ገጠራማ አከባቢ ነዋሪዎች አንደበት ሰምተናል። በመሆኑም፥ በአፋር፣ በተለይ በአማራ ክልል ከተሞች የምትገኝ ህዝብ በዓይንህ እያየኸውና እየመሰከርከው ያለ የትግራይ ሰራዊት ህዝባዊነት ነውና ሠራዊቱ በቀጣይ በሚገሰግስባቸው ከተሞችና በሚያልፍበት ስፍራ ሁሉ ተጨማሪ ድጋፍ በመሆንና በመስጠት አገርና ህዝብ ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ የዐቢይ አህመድ ዓሊጋሻ ዣግሬዎቹ ዕድሜ ለማሳጠር በሚደረገው ትግል ከትግራይ ሰራዊት ጎን በመቆም የድርሻህን እንድትወጣ ወንድማዊ ጥሬን ሳቀርብ በአክብሮት ነው።

 

በመጨረሻ፥ እያወቃችሁ በድፍረት ሳታውቁ በስህተት በጭፍን ጥላቻ ሰክራችሁ ትግራይ-ፎቢያ ለጠናባችሁ በውስጥም በውጭም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን፥ አለ ምክንያት እንዲሁ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ መጥላት፣ በህዝቡ ላይ የሞትና የጥፋት ምዋርት ማሟረት መብት ባይሆንም ምርጫችሁ ቢሆንም፥ ጥላቻ፣ ቅናትና ምቀኝነት የሚወልደው አስተሳሰብና እምነት ግን እውነት ሊሆን እንደማይችል በመረዳት፥ በአሉባልታ፣ በውሸት፣ በፈጠራ ትርክት ወዘተ ትክሻ ላይ ተቀምጣችሁ ከምትጋልቡና ህዝባችሁን ለከፋ ሞትና እልቂት ከምትማግዱ፥ ቆም ብላችሁ እንድታስቡና እንድታስተውሉ፣ ኃላፊነት ተሰምታችሁም እየሆነ ያለ ሁሉ አጥርታችሁ እንድታዩና አገሪቱ ለዚህ ሁሉ መርገምት የማገደ እውቀት ጥበብና ማስተዋል የሆነ ሰው ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በምድሪቱ እየፈሰሰ ያለ ደምና እየጠፋ ለሚገኝ ነፍስ ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂዎች ዐቢይ አህመድ ዓሊና የዙፋኑ ተሸካሚዎች የአማራ ልሒቃን መሆናቸው በማወቅና በመረዳት፥ አገሬ የምትሏት አገርና ህዝቤ የምትሉትን ህዝብ ለማትረፍና ለመታደግ እውነትና ፍትሓዊነት እንደ መቀነት ታጥቆ ፍርድና ፍትህ ለማድረግ እየገሰሰገሰ ካለው የትግራይ ሠራዊት ጎን በመቆም ግዴታችሁ እንድትወጡ በድጋሜ ጥርዬን አቀርባለሁ።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

 

Back to Front Page