Back to Front Page

ኣብይ ኣህመድ እና የኣማራ ሊሂቅ ፖለቲካ

ኣብይ ኣህመድ እና የኣማራ ሊሂቅ ፖለቲካ

ገብረ ሥላሴ ኣርኣያ

Feb 2021 ዓ.ም

የኣማራ ሊሂቅ እየተከተለው ያለው ስትራቴጂ ኣንደወትሮው ኣደገኛ እና የኢትዮጵያን መፍረስ የሚያፍጥን ነው። ለምን? ለሚል ጠያቂ እስቲ ፖለቲካውን ኣሳጥረን እንየው። ፈሺሽት ኣብይ ኣህመድ ስልጣኑን እንዲለቅ ሰሞኑን እየፃፉ ወይ ጥሪ እያቀረቡ ያሉት የኣማራ ሃይሎች ‘’ለውጥ’’ የሚሉት ነገር ከመጣ ጀምሮ ኣብይ የፌደራል ስርኣቱ እና ህገ መንግስቱ በኣዋጅ ኣንዲያፈርስላቸው ጉትጎታ ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወቃል። ይህንን ይፈጽምላቸው ዘነድም መጀመሪያ ኣብይን በራሱ ልሳን (ማለትም ኢትዮጵያ፡ ኢትዮጵያዊነት ፣ እምየ ሚኒሊክ ወዘተ የሚለውን) ተጠቅመው እያጀቡ የሴራቸው ኣካል እንዲሆን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በተፅእኖዋቸው ሥር እንዲወድቅ ኣደረጉ። የስልታቸው የመጀመሪያ እርምጃ ተደርጎ የተወሰደው ደግሞ ኣብይ ወደ ስልጣን ለመውጣት ምክንያት ከሆነው ኦሮሙማ (ኦሮሞነት) እንዲፋታ ማድረግ ነበረባቸው። ቀጥሎም ለስልጣን ያበቁትን የኦሮሞ ኣጋሮቹን ለማ፡ ጃዋር፡ በቀለና ሊሎች የኦነግ ኣመራሮችን በማሰር ወይም በማግለል የኣማራ ሊሂቃን ጥያቄ ወደ ቀጣዩ እርከን ከፍ ኣድርጎላቸዋል።  

በዚህም ኣላበቃም፥ ኣብይ ኣህመድ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በተገኘው ኣጋጣሚ የሚደሰኩረው ነገር ኣሁንም በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅበት ነበር። ለዚህ ሲባልም በኦሮምኛ ሲናገር ብሄሬ ነው ከሚለውን ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ጋር መፋታት ነበረበት።  እንዴት? ሲባል ደግሞ ኦነግ ሸኔን ምክንያት በማድረግ ወለጋ፡ ባሌና ጉጂ ላይ ደም ኣፋሳሽ ጦርነት በማስከፈት ዋናው ማህበራዊ መሰረቱ ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ እስከ ወዲያኛው እንዲፋታ መግፋት ነው። ይሄም በደምብ ተሳክቶላቸዋል። ገንዘብ የማይሰራው የለምና የሰሞኑን ሰልፍ ኣይታቹ እንዳትሸወዱ።

Videos From Around The World

ቀጥሎም የኣማራ ሊሂቃን ፈረሳቸው ኣብይ ኣህመድን ተጠቅመው ‘’ታሪክን ወደ ቦታው ለመመለስ’’ ይችሉ ዘንድ እንደ ጋሬጣ ያዩትን የፖለቲካ ሃይል ክእነ ማህበራዊ መሰረቱ ከምድረ ገፅ ማጥፋት ኣሊያ በወሳኝ መልኩ መናድ የግድ ሆኖ ኣገኙት። በመሆኑም ከፍተኛ የኣገር ክህደት በመፈጸም ባእድ ከሆነው ከኤርትራ መንግስት፣ የሶማሊያ እና የዓረብ ኤምሬትስ መንግስታት፣ የኣማራ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን ትግራይን በጦርነት በመግጠም የክልሉን ሀጋዊ ገዥ የሆነውን ህወሓትን ማጥፋት፡ የድርጅቱን ማህበራዊ መሰረ የሆነውን የትግራይ ህዝብም ሰርቶ ያፈራውን ጨርሶ በማውደም ወይም በመዝረፍ፣ ቤት ንብረቱን እና ቀለቡን በመዝረፍ፣ ክልሉን በማፍረስ እና ወደ ኣማራና ወደ ኤርትራ ቆራርጦ በመከፋፈል በቀረችውም የራሳቸው ምስለኔ በመሾም ትግራይ እንደ ኣንድ የፖለቲካ ሃይል የመደራጀት ኣቅም ኣንዳይኖረው ኣድርጎ የትግራይን የፖለቲካ ህልውና እስከ ወዲያኛው እንዲያከትም ለማድርግ በጦር ሃይል ሁሉም ኣይነት የጦር ወንጀል ተፈጸመበት። በዚህ ዘንድም ዘላቂነት ባይኖረውም ቀላል የማይባል ስኬት ኣስመዝግበዋል። 

የቀረው ኣብይ ኣህመድ የኣማራውን ትእዛዝ በመቀበል የፌደራል ስርኣቱ እና ህገ መንግስቱን በኣዋጅ በማፍረስ የክልሎች ህልውና ማክተም ነው። ዚህ ላይ በየክልሉ የብልፅግና ምስለኔዎች ስልጣኑን የተቆጣጠሩት ቢሆንም እንዲህ ኣይነት እርምጃ መውሰድ በኣገሪቱ ላይ ሌላ ያልታሰበ ቀውስና ግጭት ፈጥሮ የስልጣኑን እድሜ ሊያሳጥረው እንደሚችል ሳይገምት ኣልቀረም። የኦሮሚያ ብልፅግናም ቢሆን ሲቻል  ከኣበሻ ነፃ የሆነ የኩሽ ኣገረ መንግስት መመስረት እንጂ ኣንዴ በእጃቸው የገባውን ክል የማፍረስና ህገ መንግስቱን ቀዶ የመጣል ፍላጎት ኣላቸው ለማለት ያስቸግራል። ሌሎች ክልሎች ቢሆኑም በተመሳሳይ መፍረሱን በመቃወም የትግራይን ኣመፅ ሊቀላቀሉ የሚችሉበት ሁኔታ ዝግ ኣይደለም። በእርግጥ የየክልሉ ሊሂቃን ስልጣን ላይ እስከቆዩ ድረስ ክልላቸውን ኣሳልፈው የመስጠት ችግር የለባቸውም የሚሉ ኣልጠፉም። ነገር ግን ሁሉም ሊሂቃን ስልጣን ላይ መውጣት ስለማይችሉ ክልሌ ብሎ ኣመፅ የሚያስነሳ ሊሂቅ ኣይጠፋም። ለምሳሌ በየክልሉ የተደመሩ ሊሂቃን ያሉትን ያክል በሁሉም ክልሎች ያልተደመሩ የፖለቲካ ሃይሎች እንዳሉ ይታወቃል።

የሆነ ሆኖ ኣብይ ኣህመድ ከባድ ቅርቃር ላይ ገብተዋል። የኣማራ ሊሂቃንም ኣብይ ከኣማራው ውጭ ሌላ መሄጃ እንደሌለው ስተገነዘቡ የጠየቁትን እንዲፈጽምላቸው የተቻላቸውን ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው። ያሉትን ሳይሰማ ሲቀር ደግሞ የኣማራ ብልፅግና እንደ ኣብን የመሰሉ ፅንፈኛ ኒዮ-ነፍጠኞችን በማሰማራት ስልጣኑን እንዲለቅ እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ፋሺሽቱ ኣብይ ኣህመድም የኣማራ ብልፅግና እየተከተለው ያለውን ኣጥፊ መንገድ (ማለትም ኣብን እንደ ማስፈራሪያ ተጠቅሞ ፍላጎትን ማስፈጸም) ስለገባው ይመስላል እሱም በበኩሉ የኦሮሞ ደጋፊዎቹን ሰልፍ ኣስወጥቶ ኣብን ላይ በመሳለቅ እና ኦሮሚያ በሚኖረው ኣማራ ላያ ስጋት ለመጣል እየተሞከረ ያለው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ፋሺሽቱ ኣብይ የኣማራ ሊሂቃን ጠቅላይ ኣግላይ የፖለቲካ ስርኣት ተቀብሎ እስከ ጥግ ድረስ ይፈጽምላቸው ይሆን? ወይስ ሰሞኑን እንዳደረገው እሱም የኦሮሞ ፅንፈኛ መጣባቹ እያለ እያስፈራራ ይቀጥላል። እናያለን። 

በትግራይ ጦርነት ወታደሮቹን ያስጨረሰው ኣብይ ኣህመድ ግን ከኣማራ ሊሂቃን ተፅዕኖ ነፃ ሊሆን ባይችልም ከኣሁን ወዲያ ለሚሆነው ሁሉ የሁለቱም ብልፅግናዎች ኣዛዥ የሆነው ሰው በላው ኢሳያስ ኣፈወርቂ ወሳኝ ሚናው በጣም ከፍ ያለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። የኦሮሞ በልፅግና፣ የኣማራ ብልፅግና እና የኢሳያስ ኣፈወርቂ ፍላጎት የሚስማማበትም የሚቃረንበትም ሁኔታ እንዳለ የሚታወቅ ሆኖ የሶስቱም ፋሺሽታዊ ብድኖች ወዳጅነት ግን ታክቲካዊ እንጂ ስትራቴጂካዊ እንዳልሆነ ደግሞ ማስተዋል ያስፈልጋል። በኢሳያስ የማይታመን ባህሪ፣ በኣማራ ሊሂቃን ስስታም፣ ጨፍላቂና ተስፋፊ ባህሪ፣ በኦፒዲ ግራ የተጋባ የኢትዮጵያና የኩሽ መንግስት ፍላጎት፣ በኣብይ ሚኒሊካዊ ድግምትና ብቃት ማነስ ያለው ተቃርኖ በቀላሉ የሚደፈን ስላልሆነ እነዚህ የክፋት ሃይሎች በኢሳያስ ዘዋሪነት ኣገሪቱን ገደል እንደሚከትዋት ከበቂ በላይ ምልክቶች ኣይተናል። ኢትዮጵያ ለ21ኛው ከ/ዘመን የማትመጥን ኣሳቢ፣ መካሪና ትልቅ ሰው ያጣች ኣገር ሆናለች። በእርግጥም ህዝቧን እየጨፈጨፈች የምትኖር ኣገር መኖር የለባትም።


Back to Front Page