Back to Front Page

አብይ አህመድ፡ የከሸፈበት መሪ

 

 

አብ አህመድ፡ የከሸፈበት መሪ

በሁላችንም ስም

ባለአገሩ  12-27-21

  እውነታን በገባን ልክ እንደምንተነትን የሚተወቅ ነው ፡፡እውነታው ግን የምንቀይረው አይሆንም፡፡አብይ አህመውድ  በአለም አቀፍ ግንኙነት እርያ ሆነዋል ፡፡ አለም የሚጠየፈው መሪ ሆናዋል ማለት ነው፡፡የአብይ ነብስ ትላንት መስኩ አይበቃኝም ብላ እዩኝ እይኝ ስትል ከርማ   ዛሬ ደብቅኝ ደብቅኝ እያለች ነው፡፡ አብይ ከእንግዲህ  በመንደሩ የሚፎክር  ኢሳያስ አፈወርቂ ሆነዋል ፡፡ በሌላ አነጋገር አብይ አህመድ  በራሱ ፈቃድ  የመንደር ሽማግሌ ለመሆን መርጠዋል ፡፡ትላንት የሸለመችው ዓለም ዛሬ  እሱን ለማየት የምትጠየፍ   ሆናለች ፡፡ አብይ በስላጣን  የሚቆይባቸው አመታት  ለኢትዮጵያ ተጨማሪ  ዕዳ ሆኖ ይቀጥላል ፡፡ኣብይ በስልጣን እስከቆየ ድረስ  አገራችን   የተነጠለች አገር ትሆናለች  ፡፡የውጭው ግንኙነት  የተወሰኑ አለም የተስማማባቸው ወጎች እሴቶችን ማክበር ይጠበቅብሃል ፡፡ አለም ጨዋ መሆንን ይጠይቃል ፡፡ ጨዋነት አንዴ ከወረደ    ተመልሶ  አይመጣም ፡፡  ችግሩ የአገር መሪ በአለም ሲዋረድ አገርም የሚያዋርድ መሆኑ ነው፡፡ ተወደደም

Videos From Around The World

ተጠላም አብይ በሰራው ወንጀል  ከአለም ተገልለዋል ፡፡ የጨዋነት አቅሙ ተማጠዋል፡፡ አለም እሱን ትጠየፋለች ፡፡ አፍሪካዊያንም  ቢሆኑ አብይን ይጠየፍታል ፡፡  ከውጭ ዓለም የተገለለ መሪ ለአገራችን የሚያስከትለው ጣጣ ለመተንባይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ጎረቤት አገራትን ማየት ነው ፡፡ ቢያንስ ዘአምን ዘለቀ የሚያቆለጳጵሳት ኤርትራን ማየት ነው፡፡

  አብይ በትግራይ ወራራ ከፈፀመ ወዲህ  እየተነጠለ  መጥተዋል ፡፡የፖለቲካ ልዩነት በጦሩነት  ለመፍታት  የሄደበት የተሳሳተ ኣካሄድ  ቀድሞም ቢሆን  የተወደደ አልነበረም ፡፡ ኣብይ ጦርነቱ ሲጀምር  በአጠረ ግዜ  ጨርሶ   እጁ ታጥቦ ከደሙ  ፁህ ነኝ ለማለት ነበር፡፡  ነገር ግን ራሱ በቀሰቀሰው  ዘረኝት  ወታደሮቹ  በትግራይ መንደረች  ተሰምቶ የማያተወቅ  ግፍ ፈፀሙ፡፡ ይባስ ብሎ ቂመኛው ኢሳያስን ጋብዞ  በትግራይ ህዝብ ላይ ይተነግሮ የማልቅ ወንጀል ተፈፀመ፡፡ ባሩድ የሸተተው ጎሮቤት የኣማራ ሽፍታም እንደነጋበት ጅብ ሃብትና መሬት ለመቀራመት ዘሎ ገባ ፡፡ ሁልም ወንጀል ፈፀሙ፡፡

አብይ የረሳው  ነገር  የፖለተካ ወንጀል  ከፈፀመ መሪ  መነካካት የሚፈልግ   አገር  የሌለ መሆኑ ነው፡፡ መንግስታት ዜጎቻቸውን የመግደል መብት የላቸውም ፡፡ ልእላዊነት መብት የማክበር እንጂ የመግደል መብት አያጎናፅፍም ፡፡ አብይ የሰራው ወንጀል በሁሉም ሰው መንገድ ላይ  የቆመ ጋሬጣ ነው ፡፡እንቅፋት ነው፡፡ አሁን ሁሉም ወገን በስሜት ውስጥ በመሆኑ ይህን የሚያስብበት ወቅት አይደለም፡፡ ስለ ነገ የሚያስብበት  ወቅት አይደለም፡፡ ነገን መሸሸ  ግን አይቻልም፡፡ 

አብይ አህመድ በአጭር ግዜ ውስጥ  የተሰጠውን ፀጋ ያባከነ አሳዛኝ መሪ ነው ፡፡  አለም ጨካኝ  ናት ፡፡ የትላንት ከንቱ ውዳሴና ሽልማት ለማስታወስ አትገደደም፡፡ቦታ የለውም፡፡ ይረሳል፡፡  ችግሩ  በሰራው ወንጀል  የመከሰስ ጉዳይ   አይደለም፡፡እሱ ሌላ ነው፡፡ ወንጀል ስትሰራ ከአለም ትገለላለህ፡፡ዲሞክራሲው አለም ኣብይን  ለመቀበል   ፍቃደኛ አይደለችም፡፡  ከእንግዲህ አውሮጳ መሄድ የለም፡፡ መሪዎች ካልቸገራቸው በስተቀር  ወንጀል የሰራ መሪን ከመጨበጥ ይሸሻሉ፡፡ወንጀል ማጠብ አይቻልም ፡፡  አብይ የመንደር መሪ ሆኖ ሊቀጥል  ይችላል ፡፡ የውጭ የፍይናናስ እርዳታ ፤ኢንቨስትመንት ይቀራል፡፡  ፈጣን ልማት የሚባለው ወሬ ብቻ ይሆናል፡፡ አገሪቱ የስራ አጥ መናሓርያ ትሆናለች፡፡ የአገር ካፒታልም ይሸሻል፡፡በአገር ውስጥም ቢሆን  ውስጣዊ ዲሞክራሲያዊ ትብብር  በአብይ ዘመን ሊከሰት አይችልም፡፡

እንዲህ ያሉ መሪዎች የህዝብን የችጋር ዘመን ያራዝማሉ፡፡የኢሳያስ  አፈወረቂን ማየት ይበቃል ፡፡ ኢሳያስ   ከመንደሩ ወጥቶ ቁም ነገር አይሰራም፡፡ ከአለም የተገለለ መሪ ነው፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀመ  መሪ በአውሮጳና አሜሪካ  ጎደናዎች ሊንሸራሰር አይችልም፡፡   ብራስልስና ፤ዋሽንግተን፤ጄኔቭ መሄድ ኣይቻል ም፡፡ ወደ ተጠቀሱት አገሮች የሚሄዱት እሱን   የሸሹ ኤርትራዊያን  ብቻ ናቸው፡፡ 

 የከሸፈ ዲሎማሲ

ሰሙኑን  ኢትዮጵያ ከአገዋ (AGOA) መሰረዝዋን ሰምተናል ፡፡የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሙሸንም (UNHRC)  በአገራችን የተሰራው የሰብአዊ መብት ጥሰት  በገለልተኛ  ቡድን እንዲጣራ ወስነዋል፡፡ ሁለቱም ብቻ ብንወስድ  የአብይ መንግስት  የዲፕሎማሲ ሚዛን ምን ያሕል እንደዘቀዘቀ   መገምገም እንችላለን፡፡ቀደም ሲልም የአውሮጳ ህብረት  የሚሰጠው የፍይናንስ  ድጋፍም ተሰርዘዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግንኝነት የጦር መሳርያ ከሚሸጡ  በሰብአዊና ዲሞክራሲ  የሚታሙና የተገለሉ  አገራት ናቸው፡፡ከቱሩክ፤ ከኢራን  ፤ከሩሱያ  ሊገኝ የሚችል ጦር መሳርያ ብቻ ነው ፡፡ ቱሩኮች አህመድ ግራኝን በጦር መሳራይ የረድ ወገኖች ናቸው፡፡ ሩሱያ ደርግን ስትረደ ነበር ፡፡ እኒህ አገራት የሚታወቁት  በአሉታዊ  ጎኑ ነው፡፡ስለዚህ አገራችን ከእነዚህ ጋር  በመዛመድ  ማደግ ትችላለች የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡በልመና ይቀናኛል ሲለን የነበረው  ብይ   ከአረብ በሻንጣ ሊረጠብ ይችል እነደሆነ እንጂ  ለህዝብ የሚጠቅም ሊገኝ አችልም፡፡

ከአገዋ  መወገድ ያለው  ትርጉም ማወቁ ተገቢ ነው ፡፡ከአገዋ  መገለል 100000 ሰራተኞች ስራ አደጋ ይወድቃል፡፡ የሚታጣው የውጭ ምንዛሪ  መገመት ይቻላል፡፡ መንግስት ዲያስፖራ እንዲገቡለት የሚማጠነው ገንዘብ ፍለጋ ነው፡፡ የአሜሪካን ገበያ ትኩረት አድርገው  ኢንቬስት ያደረጉ ቻይናዊያን  ወደ ሌላ አገር ይሰደዳሉ፡፡ቻይናዊያን  የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሌላት አገር ዘንድ  መቆየት አይፈልጉም፡፡ቻይና ስለ እኛ  ብላ  የሚሰሩት ተጨማሪ ነገር ይኖራል ብሎ መጠበቅ የዋሕነት ነው፡፡

እገደው ከሁሉም በላይ  ፖለቲካ  ነው፡፡ ብፖለተካ ዘርፍ አገራችን  መስፈረት ስለማታማላ መሰርዝዋ ግልፅ  ነው፡፡  ሌላው  መታየት ያለበት   ዲፕሎማሲው ነው ፡፡ ከአሜሪካ መነጠል ማለት ሰፊ ትርጉም አለው፡፡ የአሜሪካ ወዳኝነት የሚመነዘር  ነው፡፡ የአለም ባንክ ፤አይኤምፍ  የአሜሪካ ይሁንታ ማግኘት አለባቸው ፡፡  አውሮጳ ህብረትም የአሜሪካ እግር ተከትለው  የሚሄዱ ናቸው ፡፡ ቻይናም ብትሆን የሰው ቆሻሻ ለመጥረግ  ብዙ አትሄድም፡፡ሩስያ ቱርክ ራሳቸው ከእገዳ ይሚስጥላቸው  ይፈልጋሉ ፡፡ ቅርቃር ውስጥ የሚገኙ አገራት ናቸው፡፡አንድ ኢትጵያዊ  ቱሩክ ወይም ሩስያ ሄዶ መኖር የሚፈልግ አይኖርም፡፡ አፍረካዊያንም ከአሜሪካ  ትእዛዝ አይወጡም፡፡ከአሜሪካ መገለል በየትኛውም መድረክ አይቀናም፡፡አብይ  ከአራት ኪሎ  ጎትቶ የሚያወጣው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አለም አብይን የመጎተት ሃላፊነት የላትም፡፡ ግንኙነቱ ግን ተበላሽቷል፡፡አገር ለማዳን  ከሰውየው መገላገል ነው ፡፡ 

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሙሽን   የአብይ ወንጀል በአለም አቀፍ ነፃ አጣሪ ቡድን  እንዲጣራ መወሰኑ አብይ አሕመድ ምን ያህል እንደተገለለ ማሳያ ነው፡፡ መጀመርያ በአጀንዳ ያስዙት ያደጉና የበለፀጉ የአውሮጰ አገራትና  አሜሪካ ነበሩ፡፡ ከአብይ ጎን የቆሙት ሩስያና የተወሰኑ አፍሪካ አገራት ናቸው፡፡ውሳኔው በአብይ ሰፈር ድብ ዕዳ ነው፡፡ በመዶሻ መወቀጥ ነው፡፡ የአብይ መንግስት ገና አጀንዳው ተይዘዋል ሲባል  በመግለጫ ጋጋታ  ያደነቆረን ትልቅ ስጋት ስለፈጠረበት ነው፡፡ ውጤቱ በመተንበይ  ብፍርሃት ተውጠዋል፡፡ የፈሰሰው የትግራይ  ደም ድምፅ አውጥቶ እየጨሆ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ነፃ  እርምጃ አይቻልም፡፡ ሰው ገድለህ  በሰላም መኖር አይቻልም፡፡

 

 ችግሩ  አብይ በስልጣን እስከቀጠለ ድረስ  የአገራችን መገለል የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡  ነገ ወንጀለኞች ለፍርድ  አሳልፍቹህ  ስጡ ወደ ሚለው  ሲደረስ    ዛሮ ሚድያን ያስቸገሩ ጄኔራሎች  የሚደበቁበት ቀን ሩቅ አይደለም ፡፡ በሰሩት ወንጀል  ነገ  ለአለም አቀፍ ፍርድቤት ተይዘው ይቀርባሉ፡፡

 በአብይ  መንደር ቄሱም ተኻሹም አለምአቀፍ ማህበረሰብ የሚያጣጥሉ ወገኖች  ማድመጥ የተለመደ ሆነዋል፡፡ ከጎረቤት መማር ተገቢ ነው፡፡ የኤርትራው መሪ በመገለሉ የጎደለው ነገር ምንድ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ኤርትራ አሁን ያለችበት ደረጃ  “በዘራቹህ አይድረስየሚያሰኝ
ነው ፡፡ በኤርትራ ያሉት እስርቤቶች፤ ታሳሪዎች ምን ያህል መሆናቸው ከመብዛታቸው የተነሳ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ አገሪቱ የጎበኘ መሪ አብይ አህመድ ብቻ ነው፡፡  ማንም የለም፡፡ የኤርትራ ኑሮ የሚመኙ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ የወያኔ ልማት ጠልተው የኢሳያስ የውደቀት መንገድ ማድነቃቸው  የጤንነት አይመስልም፡፡ ስለዚህ አፍሪካ ቀንድ ሁለት በወንጀል የሚፈለጉ መሪዎች እንድንተዳደር ፈቅደናል ማለት ነው፡፡

ለዚሁ ሁሉ ያደረሰን  “ፍቅር ያሸንፍል”  የሚለው  እዚህ አድርሶኖል ፡፡ ይህ አልሰራም  ፡፡  መፍትሄው ቆመጥ ይዘህ እባብ በእግርህ እየሄደ ዝም ብሎ ማየት ጥፍት ነው ፡፡

 

 


Back to Front Page