Back to Front Page

የትግራይ ልጅ ነኝ

የትግራይ ልጅ ነኝ

 

የጻድቃኖች ማጀት ... የጀግኖች መፍለቂያ

የደጎች የዋሆች ... የቆንጆዎች መራቢያ

የጽናት አላማ ... የስብዕና መናኸሪያ

የኦሪት የጥንቱ...  የፊደል የዜማ የአቋቋም መጀመሪያ

የቁርዐን መጽሀፍ ቅዱስ ... የሀይማኖት መከበሪያ

የፀሀይ የጨረቃ ... የተፈጥሮ አምሳያ

ጥልቅ እንደ ውቅያኖስ ... ሰፊ እንደ እናት ሆድ

ትግራይ ነኝ የትግራይ ልጅ ... የቆቦ የራያ

መቐለ ውቅሮ ..  ዘላምባሳ ዓድዋ

የአዓብይ ዓዲ .. ነበለት ... ዘላምበሳ ማይጨው

ሽራሮ ዓዲግራት ... ወልቃይት ፀገዴ

ፀለምት ሁመራ  የአክሱም ... ሽረ እንዳስላሴ

ትግራይ ነኝ ... የትግራይ ልጅ ... በስጋም በነፍሴ

 

ሳገኝም ሳጣ ... ስራብም ስጠማ ... ትግራይ ነኝ ትግራይ

ስታስር ስፈታ ... ስጨቆን ስበደል ... አንገት የማልደፋ

ትግራይ ነኝ ትግራይ ... ምንም ማልቀየር

ጦርነት የማልወድ ... መግደል የምጸየፍ

የራሴን የማልሰጥ ... የሌላ የማልመኝ

በጥህሎ ጠንክሬ .. ሀምባሻ ቆርሼ በህብስት ያደኩኝ

ትግራይ ነኝ ትግራይ ... በለ አስራ አንድ ቁጥር

 

ለወዳጆቼ መሬት ... ለጠላቶቼ ረመጽ

ልዑላዊነት ክብሬ ... ባርነት ጠላቴ

ትግራይ ምንነቴ ... ምሳና እራቴ

አንገቴን የማልደፋ ... ፊቴን የማላዞር

በትግራይ የመጣ ... የማልደራደር

 

የወ/ ለምለም ልጅ ነኝ ... ከአሉላ የምሳብ ... ከነ አሞራ ዘር

የደደቢት ምሩቅ ... የሀውዜን ግፍ ምስክር

የአይደር ማህበረ ዴጎ ... የአክሱም ጽዮን ነጋሽ

መቐለ ማይጨው ... የኮረም አላማጣ ...

የቶጎጋ ... እዳጋ ሀሙስ .. ኢሮብ ዛላምበሳ

በድሮን በጀት ... በአራዊት ስራዊት ግፍ ... ትእግስቱ የሳሳ

ትግራይ ነኝ ትግራይ ... ቁስሌንና ጠባሳዬን ምንም የማልረሳ

ትግራይ ነኝ ትግራይ ... / ለምለም ልጅ

 

ትግራይ ትስዕርን ፈረቃን !!!

 

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

01-16-22

Videos From Around The World

 

Back to Front Page