Back to Front Page

Microsoft Word - የምዕራባውያን ተጽዕኖ በትግራይ ሠራዊት እስከ ምን ድረስ?.docx

የምዕራባውያን ተጽዕኖ በትግራይ ሠራዊት እስከ ምን ድረስ?

 

ያቤጽ ዘዳግም 1-4-22

 

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ሀብትና ንብረት ለርዕሰ ኃያላኑ አገራትና መንግስታት አሳልፎ እስከሰጠ ድረስ ምዕራባውያን አገራትና መንግስታት በትግራይ እየተፈጸመ ያለ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ቁሞ የመመለከት ከዚህ አልፎም በኢትዮጵያ ፈንታ ትግራይ ለመውጋት ማለትም የባለውለታቸው ሰው የዐቢይ አህመድ ዓሊ ስልጣን ለመጠበቅና ለማትረፍ ሲሉ ማንኛውም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ ግልጽ ያደረጉት ዛሬ ሳይሆን ትግራይን ለመውራት በሰባት አቅጣጫ የተመመው፥ በኢምሬት ዱሮኖች የታጀበ የኤርትራ፣ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ኢንተርሃምዌ ሚኒሻና ታጣቂ ከአብዛኛው የትግራይ ክፍል በኃይል ተጠራርጎ ከወጣና የትግራይ ሠራዊት አፈሩን አራግፎ ወደ ማኸል ማገስገስ በጀመረበት ቅጽበት ነበር። ይህን ያደረጉበት መንገድ አንዱ ትግራይ በከበባ ውስጥ እንድትገባ በመፍቀድና ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይህን የመሰለ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል በጠራራ ጸሐይ እንዲፈጽም ይሁንታቸው በመስጠት ነው። ቀደም ሲል በወረራ ዓላማው እንዲያስፈጽም የፈቀዱለት ምዕራባውያኑ በተመሳሳይ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ላይ ከባባ እንዲፈጽም ይሁንታቸው የሰጡበት ዓላማና ግብ ከመመልከታችን በፊት ግን ዐቢይ አህመድ ዓሊና የመርገም ጨርቅ የአማራ ልሒቃን ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው ሁለትና ሦስት ትውልድ የርዕሰ ኃያላኑ የገቢ ምንጭ የሚያደርጋት ስምምነት በመፈጸም ጦርነት የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ማወቁ አጅግ አስፈላጊ ነው። ይኸውም፥ በዋናነት አራት ምክንያቶች በአጭሩ ላስቀምጥ (ለወደፊቱ ራሱን ችሎ የሚቀርብ ጽሑፍ ነው)፥  

 

1.      ፍርሃት ነው። ጦርነቱ ትግራይ ሠራዊት የአማራ ክልል ቦታዎች እንደ ተቆጣጠረ ወደ ውይይት የተገባ እንደሆነ ትምክህተኞቹ አሁን ከተከናነቡት የውርደትና የክሽፈት ታሪክ የከፋ ስለሚሆን ነው። በነገራችን ላይ፥ ስዎቹ የፈለጉትን ሜክአፕ ቢቀባቧት ኢትዮጵያ ራስዋ በለኮሰችው ጦርነት የተሸነፈች አገር ናት። የተሸነፈችውም ኢትዮጵያ በቁጥር አምስት ከመቶ (5%) ነው በሚባለው በትግራይ ህዝብ ላይ ወረራ ለመፈጸም፥ ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከሶማሊያና ከኢምሬት ጋር በመምከርና በመዘከር ከዚህም ከዚያም የሰውና የጦር መሳሪያ አግበስብሳ በትግራይ ላይ ወረራ የፈጸመችበት ዕለት ብቻ ሳይሆን ዓላማዋ ማሳካት ሳትችል በመቅረትዋ ጭምር ኢትዮጵያ የሽንፈት ሽንፈት የተከናነበች የከሰረች አገር ናት።  

2.     ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን ኢትዮጵያን ሽጠው መቀመጫቸው ከመታደግ ውጪ ሌላ አማራጭ ስለሌላቸው ነው።

3.     ጥቅምና አጉል ጀብደኝነት ሲሆን 

4.     በትግራይ ላይ የፈጸመሙት ወረራና እያካሄዱት ያለ ጦርነት የውክልና ጦርነት ስለሆነ ሰዎቹ ኢትዮጵያን ሸጠው ከምዕራቡም ከምስራቁም ሊያገኙት የሚችሉት ዕርዳታ ሁሉ በመጠቀም ርዕሰ ኃያላኑ የትግራይ ሠራዊት ወደ ትግራይ እንዲመስለ ለማድረግ ተችላቸዋል። ይህን ያደረጉበት መንገድ ወደኋላ ከታሪክ ማለትም ምዕራባውያን በሴራ ፖለቲካ በሰርቦች ላይ ከፈጸሙት ጭፍጨፋ ጋር በማመሳከር አስረዳለሁ። አሁን ቀደም ሲል ወዳነሳነው ነጥብ ልመለስ።  

 

Videos From Around The World

ወደ ከበባው ልመለስ። የከበባ ዓይነቶችና አፈጻጸም ልዩ ልዩ ቢሆንም ይህን ዓይነቱ ስልትም አዲስ ሳይሆን በጥንት ዘመን የታወቀ ስልት ነው። በትግራይ የተፈጸመና አሁንም በቀጣይነት እየተፈጸመ ያለ ዓይነት ከበባ ታድያ በዓለማችን ታሪክ የኢየሩሳሌም ውድመት (Destruction/Siege of Jerusalem) ተብሎ የሚታወቀው በ70 ዓ/ም አይሁዳውያን ዘር ላይቀርላቸው ባቢሎናውያን በኢየሩሳሌም ላይ የፈጸሙት ከበባና ውድመት ምንም ልዩነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ከበባ ዓላማና ግቡም አንድን ህዝብ ወይም ማህበረሰብ እንደ ሰው ለመኖር የሚያስችለው መሰረታዊ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የነዳጅ፣ የገንዘብ ወዘተ አቅርቦቶች እንዳያገኝ በመከልከል እንደ ማህበረሰብ በርሃብ፣ በችጋርና በበሽታ ዘር ላይቀርለት ፈጽሞ እንዲረግፍ፣ እንዲጠፋና እንዲከስም ማድረግ ነው። ልብ ይበሉ፥ በተለይ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ፥ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም፣ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተባለ በተደጋጋሚ ሲነገርና ለዲሞክራሲና ለሰብአዊ መብት መከበር ቁመናል የሚሉ ምዕራባውያን መንግስታትና አገራትም ይህን ዓይነት ወንጀል ተፈጽሟል ባሉት አከባቢ በንጹሐን ዜጎች ደም እጃቸው ሲታጠቡ በተደጋጋሚ ተመልክተናል። ይህን የምዕራብያውያኑ የግብዝነት ታሪክ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ታድያ አንድን ህዝብ በማንነቱ እህል ውሃ እናዳያገኝ ከአንድ ዓመት በላይ በርሃብና በበሽታ እንዲረግፍ ከማድረግ በላይ በሰው ልጆች ላይ ሊፈጸም የሚችል የከፋ ወንጀል ምን ቢኖር ነው? የትግራይ ህዝብ በጥቂቱ እህል፣ መድኃኒት፣ ነዳጅ እንዳያገኝ በመከለከል አንድን ሕዝብ እንደ ህዝብ በርሃብና በበሽታ እንዲያልቅ በማድረግ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል በፊታውራሪነት እየመራ ያለ ብቸኛ የዓለማችን አረመኔ ዐቢይ አህመድ ዓሊ አይደለም ወይ? ኢትዮጵያና ኤርትራ ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለ ወንጅል የዘር ማጥፋት ወንጀል ካልተባለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ምንድ ነው? የኢትዮጵያ አብያተ ክርስትያትና የሃይማኖት ተቋምት ሳይቀር በይፋ በአደባባይ ሰይጣን ቢገዛን ይሻለናል! የሚል መርህ አነግበው ትግራዋይን መግደል ጽድቅ እንደሆነ፣ ትግራዋይ ለመግደል የሚሞተው ኢትዮጵያዊ ሁሉ መንግስተ ሰማያት እንደሚገባ፣ የትግራይ ህጻናት አንስትና ሽማግሌዎች መግደል ኃጢአትን እንደሚያስተሰርይ፣ እያበረታቱ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች እየመለመሉ ለሞትና ለዕልቂት ወጣቶችን ሲያሰማሩ ምድሪቱም የደም መሬት ሲያደርጓትና አተኳከስ ጭምር እያስተማሩ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመና እየተፈጸመ ያለ ግፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ካልሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ምንድ ነው? የእግዚአብሔር ባሪያዎች የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ነን የሚሉ ሰዎች አደባባይ ወጥተው መፍትሔው እርዳታን መቆለፍ ነው እያሉ ደምነትን ሲሰብኩና ዕልቂትና ሞት ሲያበረታቱ አሁንም ይህን ዓይነቱ ዘመቻና ተግባራት የዘር ማጥፋት ካልተባለ የዘር ማጥፋት ማለት ምን ማለት ነው? ብሎ ራሱን የሚጠይቅ አስተዋይ በርካታ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያጠራጥርም። ሐቁ ታድያ፥ ብዙውን ጊዜ ርዕሰ ኃያላኑ መንግስታትና አገራት የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚሉት የዘር ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ቢያንስ እነዚህ መመዘኛ ነጥቦች መሟላት ግድ ነው በማለት የሚዘርዝሩት ድርጊት በተጨባጭ ስለ ተፈጸመ ሳይሆን በዋናነት፥   

 

1.               አገራቱ የሚያስገኝላቸው ስትራቴጂክ ጥቅም ያለ እንደሆነ ነው (ይህ ማለት ለእነሱ የሚያስገኘው ጥቅም ከሌለው አይደለም አምስት ሚልዮን ህዝብ ሌላም እልም ብሎ ቢጠፋ ጉዳያቸው አይደለም፤ አንድም፥ ዛሬ ላይ የደረሱበት የዕድገት ደረጃ የደረሱ በመቶ ሚልዮኖች የሚቆጠሩ የንጽሐን ዜጎች ደምና አጥንት ፈጭተው እንደ ዱቄት በመበተን ነው)፤   

 

2.              ፈጻሚው አካል ታዛዥና አጋር ከሆነ፣ የፖለቲካ ዝንባሌና ጎራውም በተጨማሪ ታሳቤ ያደረገ ለመሆኑ በተደጋጋሚ በታሪክ በግልጽ አይተነዋል (ይህ ማለት፥ ወንጀል ፈጻሚው የርዕሰ ኃያላኑ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ የኋላ ኪስ ከሆነ ድርጊቱ ያሸልመዋል እንጅ አያስጠይቀውም)። በፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊቱ የሚጠየቀውና ሊጠየቅ የሚችለው ታድያ ከመቶ ዓመት በኋላም ቢሆን ከፈቃዳቸው ስንዝር ያፈነገጠ እንደሆነ ነው።

 

ለምሳሌ ያህል፥ ቱርክ በአንደኛ የዓለም ጦርነት (በአቶማን ኢምፓዬር ዘመነ መንግስት መሆኑ ነው) በአርመንያውያን የፈጸመችው እጅግ ሰቅጣጭ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ወደ ጸሐይ የወጣና እውቅና ያገኘ ዛሬ ከአንድ መቶ ዓመት በኃላ ነው። ለምን አሁን? ለሚለው ጥያቄ፥ ማለትም ይህ የሆነበት ምክንያት ቱርክ ከምዕራቡ ዓለም እያፈነገጠች በመምጣትዋና እስራኤል በጋዛና አከባቢ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ከበባ በፈጸመችበት ወቅት የቱርክ መንግስት የማንም ፈቅድና ይሁንታ ሳይጠብቅ፣ ድርጊቱም በምዕራቡ ዓለም እንደሚያስጠቃውና ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንደሚያስገባው እያወቀ ፍልስጤማውያን ለመርዳትና ለመታደግ አስፈላጊ የሆነ የመድሃኒትና የምግብ አቅርቦት ለመለገስ መርከቧን በማንቀሳቀስዋ ምዕራባውያን በማስቆጣቱ ነው። ከዚያ በፊት ታዲያ ቱርክ ለአእምሮ የሚከብድ ልዩ ልዩ አረመኔያዊ ስልቶችና አፈጻጸሞች በመጠቀም በአርመንያውያን ለፈጸመችው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም ልትጠየቅ ቀርቶ ይህን ጉዳይ የሚያነሳ ሁሉ በአንድም በሌላም መንገድ እንዲወገድ ሲሰሩ የነበሩ ከቱርክ በላይ የምዕራባውያን የደህንነት ተቋማት ናቸው። የቱርክ ለይቶላት ፍልስጤማውያን ለመርዳት እግርዋን ያነሳች ቅጽበት ታድያ በዓለም መድረክ ሊኖራት የሚችል ተቀባይነት ለማሳጠትና ለማሸማቀቅ አቧራ የበላው ፋይል አፈሩን አራግፈው ቱርክ በአርመንያውያን ለፈጸመች የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመቶ ምናምን ዓመታት በኋላ እውቅና የሰጡት። ኢትዮጵያ የውጭ መንግስታትና አገራት በመጋበዝ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመችው በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም፣ የጦርና የዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይም ተመሳሳይ ለመሆኑ የሚጠራጠር ሰው አይኑር። የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ጠብቆ ለጌቶቹ እየገበረ የሚኖር መሪ እስካለና ከዚህ የባርነት ድርጊትም እስካላፈነገጠ ድረስ የትግራይ ጉዳይ የአቧራ ቀለብ ሆኖ ይቆያል። 

 እንቁላል መስረቅ የለመደ ሌባ … 

 

እአአ ኦገስት 4 ቀን 1964 ዓ/ም ምን እንደሰሩ የሚያውቁ ሰዎች ኖቨምበር 4 ቀን 2020 ዓ/ም (ከ56 ዓመት በኋላ መሆኑ ነው) በትግራይ ላይ ለተፈጸመ ወረራ እንደ ምክንያት የቀረበ ሐሰተኛ ውንጀላና የፈጠራ ትርክት ማደባበስና ማሳለፍ አይሳናቸውም። አሜሪካ ከግዛትዋ ውጭ ካካሄደችባቸው ጦርነቶች መካከል የቬትናም ጦርነት ጎልቶ ይታወቃል። አሜሪካ በሰሜን ቬትናም ላይ የፈጸመችው ወረራና የከፈተችው ጦርነት መንስኤው፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሂቃን ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያና ከዐረብ ኢምሬት ጋር መክረውና ዘክረው ያገኙትና የቻሉትን የጦር መሳሪያና የሰው ኃይል ሁሉ አሰባስበውና አስከትለው በትግራይ ህዝብ ላይ ለፈጸሙት ወራራ እንደ ምክንያት የተጠቀሙት “ሰሜን ዕዝ ተጠቃ” የሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ውንጀላ ተመሳሳይ ነበር። ይኸውም፥ በሰሜን ቬትናም በቶንኪን የባህር ሰላጤ ላይ የነበረችው “የጦር መርከባችን USS Maddox DD-731 በቬትናም ባህር ኃይል ተጠቃች” በሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ትርክት ነበር። ይህ ከ58,000 ሺህ የአሜሪካ ወታደሮች ጨምሮ ከ3 ሚልዮን በላይ ቬትናማውያን ዜጎች ህይወት የቀጠፈ ጦርነት ዓላማውና ግቡ ሌላ ሆኖ ሳለ አሜሪካ ሰሜን ቬትናም የወጋችበት ምክንያት ግን፥ ከአርባ ዓመት በኋላ ለህዝብ ይፋ በተደረገ መንግስታዊ ምስጢሮች የያዘ የድምጽና የጽሑፍ ሰነዶች እንደሚያመላክቱትና ቀደም ሲልም እንደተመለከትነው “የጦር መርከባችን ተጠቃ” የሚል የተፈበረከ ትርክትና የፈጠራ ውንጀላ መሆኑ ነው። ከረጅም ዓመታት በኋላ “የጦር መርከባችን ተጠቃ” የሚለው ምክንያት ፈጠራና ውሸት እንደሆነ ምስክርነታቸው ከሰጡ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት መካከል በወቅቱ የመከላከያ ዋና ጸሐፊ የነበረ ሮበት ማክናማራ ይገኝበታል። በጣም የሚደንቀው ታድያ፥ ኦገስት 6 (ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሁለት ቀን በኋላ) የሴነት የውጭ ግኑኝነትቶችና የትጥቅ አገልግሎቶች ኮሚቴ በጋራ ባዘጋጁት ዝግ ችሎት ፊት ቀርበው “የሰሜን ቬትናም ባህር ኃይል በመርከባችን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለው ምክስርነታቸው ከሰጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ማካከልም ሮበት ማክናማራ አንዱ ነበር።  

 

ቁም-ነገሩ፥ ሃራልድ ላስወል (Harold Lasswell) የተባለ አሜሪካዊ የፖለቲካ ሳይንቲስትና የህግ መምህር “Propaganda Techniques in the World War” በሚል ርዕስ እአአ በ1927 ዓ/ም ባሳተመው ትልቅ መጽሐፍ ላይ በገጽ 81-82 ላይ፥ 

“A handy rule for arousing hate, and that "if at first they do not enrage, use an atrocity. It has been employed with unvarying success in every conflict known to man. Originality, while often advantageous, is far from indispensable. In the early days of the war of 1914 (later known as the World War I) a very pathetic story was told of a seven-years old youngster, who had pointed his wooden gun at a patrol of invading Uhlans, who had dispatched him on the spot. This story had done excellent duty in the Franco-Prussian war over forty years before.” ሲል እንደጻፈው፥ ርዕሰ ኃያላኑ ለዐቢይ አህመድ ዓሊ የሰጡት የትግራይ ህዝብ ዘር ላይቀርለት የማጥፋት ነጻ ፈቃድ ምን ድረስ ይሄዳል? ነው። የትግራይ ሠራዊት ከአማራና ከአፋር ክልሎች ወጥቶ ወደ ትግራይ እንዲመለስ በማስገደዳቸው ያቆማሉ ወይስ በናጋሳኪና በሂሮሽማ የፈጸሙትን ወንጀል እስከ መድገም ይደርሳሉ? 

 

ሐቁ፥ ዐቢይ አህመድ ቡራኪያቸው ተቀብሎ በትግራይ ላይ የፈጸመው ወረራ ተከትሎ ከትግራይ በኩል በቀናት ውስጥ የገጠመው ያልተጠበቀ ከባድ ወታደራዊ ሽንፈትና ኪሳራ ለመቅልበስ፣ ለማካካስና የኢትዮጵያ ወጣቶች ለመመልመል ያስችለው ዘንድም በማይካድራ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ የፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ አምስቱ ዓይናማዎቹ ጨምሮ ሌሎቹም ጠንቅቀው ያውቃሉ። ርዕሰ ኃያላኑ ዐቢይ አህመድ ጦርነቱ ለማፋፋምና ጥላቻ ለመቀስቀስ የሄደው ርቀት በተጨባጭ እያወቁ ግን በንጹሐን ዜጎች ደም ላይ ራሱ የፈጸመው ወንጀል ተመልሶ ሲጠቀምበት እየተመለከቱና እየሰሙም አይተው እንዳላዩ ሰምተውም እንዳልሰሙ በመሆን አልፈውታል። ይባስ ብሎም ግራና ቀኛቸው የማያውቁ ህጻናት፣ አቅመ ደካማ ሽማግሌዎችና አንስት ጨምሮ የትግራይ ህዝብ በመላ በሁሉም አቅጣጫዎች ከበባ ውስጥ አስገብቶ እየፈጸመው ያለ ወንጀል ለማስቆም የቃላት አኩራባት ከመጫወት ያለፈ አንዳች ተጨባጭ እርምጃ ሲወስዱ አልታዩም። ይልቁንም፥ በትግራይ ጉዳይ ላይ ምን እየሆነና እየተደረገ እንዳለ ለማወቅ እዚህ ላይ አንድ ጭብጥ ማውሳት እወዳለሁ፥ ርዕሰ ኃያላኑ የትግራይ ህዝብ፥ ጽኑ፣ ብርቱ ተዋጊ፣ በኃይልና በጉልበት የማይንበረከክ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጥንታዊ ስልጣኔ ያለው የፖለቲካ ንቃቱ በአከባቢው የላቀና ቀደምት ህዝብ ነው ብለው ያምናሉ (ይህ የእኔ ቃል አይደለም) በመሆኑም፥ ርዕሰ ኃያላኑ ዐቢይ አህመድ ዓሊን የፈለገው ወታደራዊ ድጋፍና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ቢያሳጥቁት የትግራይ ሠራዊት አዲስ አበባ ከመግባት ሊያስቆመው እንደማይችል በተመሳሳይ መንገድ አስምረውበታል። ከዚህ ጎን ለጎንም የትግራይ ሠራዊት አዲስ አበባ እንዳይገባ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግራይ እንዲመለስ ማድረግና ማስገደድ እንደሚችሉም በማመን ወደ ስራ ከተገባ ሰነባብቷል። ይህን ያደረጉበት መንገድና ሂደት ከማናገሬ በፊት ግን ጉዳዮ በሚገባ ጥርት ብሎ ይታየን ዘንድ ከቅርብ የታሪክ ማህደር አንዳንድ ክስተቶች አጠር ባለ መልኩ ለማካፈል እወዳለሁ።     

 

እአአ ማርች 21 ቀን 1999 ዓ/ም ኒውዮርክ ታይምስ ይዞት በወጣ ዘገባ እአአ ነሐሴ 1995 ዓ/ም በጡረታ የተገለሉ አሜሪካውያን የጦር መኮንኖች አማካኝነት የሰለጠኑ የክሮሽያ ጦር ሠራዊት በፈጸመው ጥቃት በአራት ቀናት ወስጥ ብቻ መቶ ሺህ ሰርቦች/Serbs (መቶ ሃምሳ ሺህ ነው የሚሉም አሉ) ደም ደመ ከልብ ሆኖ ቀርተዋል። ይህ ሁሉ ግፍና በደል በንጹሐን ዜጎች ሲፈጸም ታድያ አንድም የምዕራቡ ዓለም መንግስት ስለ ሰብአዊነት ሲል ቃል የተነፈሰ መንግስት የለም። እንደውም፥ የእልቂቱ አስተባባሪዎችና ፈጻሚዎች ለመሆናቸው በርካታ ጭብጦች ይቀርባሉ። በርግጥ፥ ፍትሕ፣ ፍርድ፣ እውነትና ጽድቅ የሚባሉ ነገሮች ከሰው የሚገኙ ነገሮች ቢኖኑ ኖር ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት ነበር ሚሎሶቪክ በምዕራቡ ዓለም ወንጀለኛ ተብሎ የቀረበበት ክሶች ማለትም በሰብአዊነት የሚፈጸም ወንጀል፣ በዘር ማጥፋትና በጦር ወንጀለኝነት መጠየቅ የሚገባው ሰው ነው። በአንጻሩ ግን፥ የሚፈለገው ሰርቦች ማክሰምና ማጽዳት ስለሆነ፥ ምዕራባውያን ያደረጉት ሰርቦች ፈጽመው ሊቀበሉት የሚችሉት መደራደሪያ ነጥብ በማቅረብ (ምክንያት ፍለጋ ሆነ ተብሎ የሚሰራ የፖለቲካ ሴራ መሆኑ ነው) “ሰርቦች ድርድሩን አንቀበልም በሏል” ተብሎ የኔቶ ተዋጊ ጀቶችና ተወንጫፊዎች በመላክና በማስወንጨፍ ህዝቡን ማክሰምና መጨፍጨፍ ነበር በታቀደው ዕቅድ መሰረትም ተግባራዊ የተደረገው ዕቅድ ይህንኑ ነበር። አንዳንድ የታሪክ ጸሐፊዎች ታድያ ይህን ዓይነቱ የምዕራባውያን ወንጀለኛ ባህሪይና የፖለቲካ ሴራ፥ “Negotiating for the impossible, and falsely accusing the other side of non-cooperation, is handy way to launch a defensive war” በማለት ይገልጹታል። ወያነም ዋዛ አይደለምና አዋራ ቂሱን፥ እኛም አውቀናል! ብሎ ለማሳለፍ በመወሰኑ በግሌ ህዝባዊ ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ነው ብዬ አምናለሁ። የሥልጣኔ ባለቤት የሆነ የትግራይ ህዝብም ይህን ሐቅ እንደማይስተውና የትግራይ ሠራዊት ውሳኔ እንደሚረዳ ነው የማምነው። የትግራይ ሠራዊት ወደ ትግራይ መመለስ በመጠኑም ቢሆን የትግራይ አመራር አስተዋጽዖ (ድካም) በተመለከተ ታድያ፥ አመራሩ መጀመሪያውኑ የተሳሳተ ስትራቴጂ መከተሉና ቀጥሎም ነገሮች ሙሉ በሙሉ በፖለቲካዊ ውሳኔዎች እንዲከናውኑ በማድረግ የፈጸመው ስህተት ቢኖርም ስህተቱ ጊዜው ሲደርስ በታሪክ መልክ እንወቃቀስበታለን። 

 

በተረፈ፥ እውነት ነው፥ ማንም ያሸንፍ ማንም የርዕሰ ኃያላኑ ችግር አይደለም። የርዕሰ ኃያላኑ የመንግስታት ዋና ዓላማና ግብ ቀለል ባለ አማርኛ ያስቀመጥነው እንደሆነ፥ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ ስም የአገሪቱ ተፈጥራዊ ሀብት ወደ ግል ይዞታዎች በማዘዋወር ቀጥተኛ ተጠቃሚዎና ባለቤቶች መሆን ነው። በርግጥ፥ የትግራይ ሠራዊት አዲስ አበባ የገባ እንደሆነ ይህ ሁሉ ህልማቸው የውሃ ሽታ እንደሚሆን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ደህና ትምህርት ቀስሟል። እልቂቱ የፖለቲካ ዕልባት እንዲያገኝ ለማድረግ ቀጥሎ የሚከናወነው ፖለቲካዊ ውይይት በተመለከተ፥ ከማንም በላይ የሚፈልጋት ታድያ ዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሂቃን ናቸው። ይህ የሆነበት ምክንያትም ሰዎቹ ሰላም ወዳጆች ስለሆኑ ሳይሆን ከዚህ በላይ መሄድ ስለማይችሉ ብቻ ነው። የምዕራባውያኑ ጥረትም ዐቢይ አህመድ ዓሊና በጥላቻ የታወሩ ተከታዮቹ “አሸንፈናል” ብለው እንዲያምኑ፣ እንዲረጋጉ፣ እንዲሰክኑና ነፍስ እንዲዘሩ በማድረግ አሁን የትግራይ ሠራዊት ወደ ትግራይ ስለ ተመለሰ መመወያየት ይቻላል! ብሎ በተበጃጀለት ቦይ በመዝለቅ ለሰላማዊ ውይይት መቀመጥና ዕርቀ ሰላም መፈጸም ነው። አሁንም ቢሆን ይህ ለትግራይ ድል ነው። አንድም፥ ትግራዋይ ያዋጣኛል የሚለው ሁሉ እየመረመረና እያደረገ ክብሩና ማንነቱን ጠብቆ ተከብሮ ይኖሯልና። መጀመሪያውኑም ቢሆን የትግራይ ሰራዊት የማንም ይዞቶ ለመውረር ዓላማ አድርጎ የተነሳ ሠራዊት አይደለምና። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የዘነጋው ታድያ፥ በዓለም ታሪክ ሆኖና ተደርጎ የማይታወቅ ነውራም ደርጊት በመፈጸም ማለትም የውጭ መንግስታትና አገራት በመጋበዝ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል አሲድ ቢደፋበት ፈጽሞ የማይደመሰስና የማይፋቅ፣ በዓለም መድረክ ስሙ በተወሳ ቁጥር በአረመኔነቱ የሰው መጨረሻ ሆኖ እየተወሳ መኖሩ ግን ሐቅ ሆኖ ይቀጥላል።   

 

ትግራይ ትስዕር! 

 


Back to Front Page