ለካቲትን ሊያጠፉ... ራሳቸውን አጠፉ
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
2-19-20
ሲያውጅ ንጉሳቸው ... የሰሜንዋ ኮከብ ሆናለች በሻሻ
ጨብጨብ ጨብ ጨብ ... ከግራ ወደ ቀኝ
ከፊት ወደ ኋላ .. መሀል ላይ የነበሩ ...
... ጨብጨብ ጨብ ጨብ ... እልል አሉ በዜናው
በጥላቻ የታወሩ ... በቅናት የሰከሩ
መስሏቸው የእውነት ... ለካቲት የምትሆን በሻሻ
ለካቲት ... የበሻሻውን ...
... ፈትፍታ አጉርሳ ... ያወዛች ያወደለች
በሻሻን ሲመኝላት ... እሱ በሽሸ እንጂ ...
... መች ለካቲት በሸሸች
የበሻሻው ከሀዲ
... ዶ/ሩ ውሸታሙ ንዑሱ ኮረኔሉ
በዝና ሰክሮ ... ዝናሽን ረግጦ ... ጥንቆሏን አምኖ
ፋኖን ገዝቶ በገንዘብ ... በኢሱ ፍቅር ብን ብሎ መኖ
በሻሻን ንቆ ... ኤርትራን እፍቅሮ
በሽሾ በሽሾ ... በባዕድ ተማምኖ
ከህደቱን አሳየ .. ለካቲት የኛን አያፍርም ደፈረ
መክራ ጠብራ ... ልብ ግዛ ባለች
አራዊት ለቃቅሞ
... ሲያስደፍር ሲያሳርድ...
Videos From Around The World
|
... ሲያቃጥል ፍጡራት ...
እነ ሞናሊዛ ይናገሩ .. እነ ቅሳነት ይመስክሩ
አይቀርም የናት ያባታቸው ... እህት ወንድማቸው
ደማቸው ፈሶ …. አይቀር በከንቱ ...
... ይለቀማል አራጁ ... ነውረኛ ደፋሪው
የበሻሻው ፋሽስት ... የ በታትናቸው አጋር
ለማኝ ባልንጀራው ... ጨለማ አማካሪው
ሳጥናኤል ... የነፍስ አባቱ
የአሳ ምቀኛ .. የባህር አድራቂ ...
... የኢሳት ...የጭድ አጋር ...
በሻሻ የበሸሸው ...
ሰክረው አሰከሩት ... የበሻሻው በሻሻን
ፓርላማ ... ሲኖዶስ
... ነብይ ፓስተሮቹ
በመስቀል ... በዝማሬ... በትንቢት ... ቡራኬ
ጨብ ... ጨብ ጨብጨብ ... የጨብ ..ጨብ ሰይጣኖች ...
... ከነ ሰብኮ ያካበተ ... አዝማሪ ተዋዛዋዥ
ጨብጨብ ... ጨብ ...ጨብ ጨብጨብ ... እርጉሞች
ስብዕና ሲዋረድ ... ሀይማኖት ሲናናስ
ትግራይ ዱቄት ሆናለች ... ሲባል እልል የደስ ደስ ...
... ጨብ ጨብ ... ጨብጨብ ጨብጫቦች
ሲባል ...
ዱቄት የተበተነ ... የምትጨበጥ የምትዘገን
ንዑስ እሚነት ... ብን ብላ የጠፋች
ነገን የማታይ ... የትም የማትደርስ
የማትመጣ የማትመለስ ... ጨብ ... ጨብጨብ ...
... ጨብጨቦች
መች አዲስ ... መች አሮጌ
ያረጀ የጃጀ ... የነበረ የጨከነ ...
ልክ እንደሮው ... እንደተለመደው
ጭካኔ ... ካሀዲነት ... አብሯቹህ ያረጀው
ለካቲት አይበሽሽም ...
ለካቲት እኛ ነን ... ለካቲት ተፈጥሮ ለካቲት ትግል
ለካቲት የተወለደው ... ለካቲት ማህፀን ላይ ያለው
ለካቲት አገር በቀል ... ለካቲት ውጭ የሚኖር
ለካቲት እኛ ... የማንሸጥ የማንለወጥ
እኛ ለካቲት ... የምንበራ የማንጠፋ
ሞተን ምንነሳ ... ተርበን የምንጠግብ
ምን ግዜም የማንጠፋ ... !!!
ለካቲትን ሊያጠፉ ... ራሳቸውን አጠፉ
ክብርን ሞገስን ንሰማኣታትና !!!
ትግራይ ትስዕርን ፈረቃን !!!