Back to Front Page

አብይ ሆይ! የዋይታዬ ዋጋው ስንት ነው?

 

 

አብይ ሆይ! የዋይታዬ ዋጋው ስንት ነው?

 

እባክህ ወዳጄ

መግደሉን ግደለኝ

በቁሜ ሸምቅቀህ

በእሱም ካልወጣልህ

ሽህ ጊዜ ሰንዝረህ ሽህ ጊዜ ዘንጥለኝ

ሲሻህ በገጀራህ…ከደክመህ ባረር…በጣጥሰህ ዘልዝለኝ፡

ደረትክን የሞላው ጥላቻህ ገንፍሎ…ሲዖልን ከሆነ ሰርተህ የደገስከው

ወይንም እንዳልተርፍብህ…ቅንጣት እንኳ እንዳልቀር

ከሆነ መሃላህ…ስለት የገባሃው

ቢኤሙን አዝንበው…አዝንበው አዝንበው

አውርድ አውርድና…ቋያ ይሁን ስፍራው፡፡

ቤትና መንደሬ

እስከ ዘር ማንዘሬ

አመድ እንሆናለን

ዳግምም አትሰማን፡፡

 

ግና እባክህን

“ወድጀሽ ወድጀሽ ልግደልልሽ” ባልካት

“ሰው መቼ ሆነና…ሃገር ማለት ርስት መሬት ነው ድንጋዩ”እያልክ በሞሸርካት

  በልጆቿ ስቅየት “ስርየትሽ አሁን ነው!”ብለህ ባነገስካት

 ገደል ላይ አቁመህ“ከፍታሽ ከፍታሽ” እያልክ ባዜምክላት

  በሷ ልማጸንህ…በሷ ተማለደኝ

አልሞትም አልልም…መግደሉን ግደለኝ

 ግና እባክህን…ዋይታዬን ተውልኝ!!

ተውልኝ ዋይታዬን…ተውልኝ ተውልኝ

ከሸበብከው አፌ…እጅህን አንሳልኝ!!

እባክህ ወዳጄ…አንሳልኝ እጅህን

በቀረች ትንፋሼ…ልጩኸው ልጩኸው…ልጩኸው መሞቴን!!

 


አ/አለሙ (ታህሳስ 2013)

 

መታሰቢያነቱ  በአረመኔው አብይ አህመድና በተባባሪዎቹ  በግፍ ለተገደሉና በመገደል ላይ ላሉ፤ ህይወታቸውን ብቻ ሳይሆን መሞታቸውንም ለተካዱ የትግራይ ወገኖቼ እንዲሁም  በኦሮሚያ፣ በደቡብ ህዝቦች፣ በአማራ፣ በመተከልና በሌሎች ክልሎች ለሚጨፈጨፉት ድምጽ አልባ ወገኖቼ በሙሉ ይሁን፡፡

Videos From Around The World


Back to Front Page