Back to Front Page

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መቋቋም አስፈላጊነት

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መቋቋም አስፈላጊነት

 

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 06-13-21

 

የጽሑፉ ዓላማ፥ ትግራይ የራስዋ ሲኖዶስ ማቋቋም ትችላለች ወይ? የሚል በኢ-ሜይል አድራሻዬ ለተላከ ጥያቄ አጭር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ ለመስጠት ተጻፈ።

 

መንደርደሪያ፥ ትግራይ የራሷ ሲኖዶስ ማቋቋም ትችላለች ወይ? ለሚለው ጥያቄ፥ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን የተከታዮችዋን መንፈሳዊ ደህንነትና መንፈሳዊ ህይወት መጠበቅና ማስቀጠል ያስችላት ዘንድ የየራሷ ሊቃነ ጳጳሳት ለመሾም ሆነ የየራሷ ሲኖዶስ ለሟቋቋም የሚከለክላትና የሚያግዳት አንዳች መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ስርዓትና ህግ የለም። ጥያቄው በራሱ የሚያመላክተው ግን፥ መንፈሳዊ ግንዛቤ ከማጣትና ካለማወቅ አንድም፥ በቅንነትና የዋህነት የተነሳ ጥያቄ በመሆኑ ማብራሪያ አክልበት ዘንድ ወደድኩ። ይኸውም፥ ሲኖዶስ ምንድ ነው? ጳጳስ ምን ማለት ነው? የሲኖዶስ መቋቋም ዓላማና ተልዕኮ ምንድ ነው? ሲኖዶስ የሟቋቋም ስልጣንና ኃላፊነት ያለውስ ማን ነው? የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎች መጠነኛ ማብራሪያ በመስጠት ልጀምር። ምክንያቱም፥ የእነዚህ ኃይለ-ቃላት ትርጉምና የሲኖዶስ ዓላማ ማወቅና በአግባቡ መረዳት መቻል በዙሪያው ሊነሱ የሚችሉ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች በልበ ሙልነት ምላሽ እንድንሰጥ ስለሚያስችለንና ስለሚረዳን ነው።

 

ሐተታ፥ ሲኖዶስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጓሜው በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተሰብስቦ የሚመክር፣ መመሪያ የሚሰጥና የሚከታተል ህብረት ወይም ጉባኤ ማለት ነው። ይህን ዓይነቱ ልምምድ በሐዋሪያት ዘመን ይሰጥ የነበረ መንፈሳዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ማዕከል የነበረችው የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን የተስተዋለ ልምምድ ቢሆንም አሁን የሚታየውና ያለው ሲኖዶስ የሚባል አካል የያዘው መልክና ቅርጽ ይዞ የተከሰተ ግን በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ የሃይማኖት መሪዎች የውስጥና የውጭ ፖለቲካ ሲያፋጃቸውና ሲያናቁራቸው በኃይማኖት ሽፋን እርስ በርሳቸው ለመናከስና ለመወጋገዝና በነገስታቱ አስተባባሪነት በ4ኛ ክፍለ ዘመን የታየ ስብስብ ነው። ጳጳስ የሚል ቃል በተመሳሳይ ቃሉ ኤጲስ ቆጵስ (episkapos) ከሚለው የግሪክ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜው የምእመናን ህብረት ወይም የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ የበላይ፥ ሽማግሌ ማለት ነው። በሮማይስጥም በዕብራይስጥም ከዚህ ውጭ ሌላ ትርጓሜ የለውም። ሽማግሌ የሚለው ቃል ረጅም ሽበታም ጺም ያለው በዕድሜ የገፋ ሰው ማለት ሳይሆን መንፈሳዊ ብስለትና አስተዳደርን የሚያመላክት ነው። በጥታዊትዋ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የሚለው ቃል መሪነትን የሚያመላክት እንጅ ከምንኩስና ሆነ ሌላ ተረት ተረት ጋር አንዳች የሚያገኝ ነገር የለውም። የሲኖዶስ ዓላማም በተመለከተ፥ በሐዋሪያት ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መሰባሰብ ዓላማና ተልዕኮ በዋናነት የጌታ ወንጌል ላልሰሙ የሚዳረስበት፣ የምዕመናን ህብረትና አንድነት ለመጠበቅ ያስችላቸው ዘንድ የሚመካከሩበት በመቀጠልም፥ ቤተ ክርስቲያን ለተከታዮችዋ የምትሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት አንድም፥ የቤተ ክርስቲያን አባላት የሚመግብ፣ የሚመራና የሚያስተዳድር መንፈሳዊ አገልጋይና አገልግሎት ለማስተባበር ያለመም ነበር።

 

ጳጳስ የመሾም ስልጣንና ኃላፊነት ያለው ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽና ቀጥተኛ ምላሽ ነው ያለው። የጳጳስ ሹመት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የማያሻማ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ ነው። እንዲህም ይነበባል፥ ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን። በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል እንዲል። ይህ እንግዲህ እኔ የጻፍኩት መመዘኛ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኩልል ብሎ የተቀመጠ ቃል እግዚአብሔር ነው። ከዚህ ውጭ የሚነግሮት ያለ እንደሆነ ግን ሓዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው የተረገመ ነው።

Videos From Around The World

 

ስለ ኃይለ ቃሎቹ ትርጓሜና ዓላማ ይህን ካልኩ ዘንዳ አሁን ደግሞ፥ ጳጳስ፣ ሲኖዶስ ወዘተ ሲባል በተለምዶ የምንሰማቸው አባባሎች፣ ፍቺዎችና አንድምታዎች ሐቀኝነት አብረን እንፈትሻለን። በርግጥ፥ ጳጳስ ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጳጳስ ሆኖ እንዳልተወለደ ማወቁ ብቻውን በላያችን ላይ የሰለጠነው ውሸትና ለዘመናት ጋረዶ ሆኖ ያሳወረን ጥቁር መጋረጃ እንድንቀነጥጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው አምናለሁ። ጳጳስ፥ መላዕክት ከሰማይ ወርደው የሚሾሙት ሰውም አይደለም። ጳጳስ የምትሾመው ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ በድንጋይ ላይ ድንጋይ የተነባበረበት ህንጻ ማለት ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ጌትነትና አምላክነት የሚያምን የምእመናን ህብረት ነው። ይህ ለመንፈሳዊ ህይወታችን መቃናት ቁልፍ ሚና አለው። ሌላው፥ መጽሐፍ፥ እውነቱን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል እንዲል፤ ጳጳስ ሲባል ከሰው የተለየ፥ ቅዱስ፣ ብጹዕ፣ የሚለው እምነትና አስተሳሰብ መንፈሳዊ ድርቀት የሚወልደው ድንቁርና መሆኑን ተገዝበን እይታችንን ልናስተካክል ይገባል። አንድም፥ ብጹዕ ማለት ብሩክ ማለት ሲሆን መቀደስም ለጌታ መለየት ነውና ቅድስናም ብጽዕናም በስሙ ለሚያምኑና በቅዱስ መንፈሱ ለተቀደሱ አማኞች ሁሉ የተገባ መጠሪያ መሆኑን አውቀን ከድንግዝግዝ ህይወት ወጥተን በቅድሳት መጻህፍት እወቀት ራሳችንን ልናስታጥቅ ይገባል። አለዚያ ጺሙን አስረዝሞ ጥቁር ቀሚስ ለብሶና መስቀል ይዞ፥ ቄስ፣ መምህር፣ ዘማሪ፣ አዝማሪ ወዘተ የሚሉ መጠሪያ ስሞች እየለጣጠፈ የሚመጣ ወንበዴ ሁሉ ከሚቀበሉ ይልቅ የሚሰጡ ብጹዐን ናቸው እያለ ጥላ እየዘረጋ ሲዘርፍህና ሲሳለቅብህ ይኖራል። አንድም፥ ሳብስክራይብ ያድርጉ፣ የአባልነት ክፍያ ይክፈሉ እያለ መሳለቂያቸው ያደጉሃል።

 

በነገራችን ላይ፥ በአሁን ሰዓት በእያንዳንዳችን እጅ የሚገኝ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁ በፖስታ ታሽጎ ከሰማይ የወረደ መጽሐፍ ሳይሆን (ከሰማይ የወረደ መጽሐፍ ነው ብሎ የሚያምን ምእመን ቁጥር ቀላል ስላደለ) በቀኖና እንደ አንድ ጥራዝ እንዲሰባሰብ ያደረገና ያስተባበረ የሊቀ ጳጳስ ልጅ ነው። መቼም ይህ ምስክርነት ሰበር ዜና ሆኖበት፥ ጳጳስ ይወልዳል እንዴ? መጽሐፍ ቅዱስ ጳጳስ እንዲያገባና ልጆች እንዲወልድ የሚፈቅድለት ከሆነስ ጳጳስ ማግባት የለበትም የሚል ትምህርት ከየት ተገኘ? በማለት የሚጠይቅ፣ እንደ ቤሪያ ሰዎች የሰጡት በየዋህነት የማይቀበል ጭምት ሰው አይታጣም። ጥያቄው ተገቢ ነው። ጳጳስ እንዳያገባና እንዳይወልድ የሚከለክል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም። ቀልዱና አዙሪቱ የሚጀምረውም እዚህ ላይ ነው። ከነተረቱም፥ ሊበልዋት የፈለጉ አሞራን ጃግራ ይሏታል እንደሚባለው፤ ለጵጵስና የሚታጭ ሰው ያላገባ ነው የሚለው አደገኛ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሴራ እንጅ የኦርቶዶክስ አስተምህሮም አይደለም። ሴራው ሲጠነሰስም እንዲሁ በድንገት ሳይሆን በዓላማ ነበር። ይኸውም፥ ቤተ ክርስቲያን አሁን ለምትገኝበት የአስተምህሮ መለያየትና እንደ አሜባ የመበጣጠስ ችግር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱና ምክንያት የነበሩ 4ኛ ክፍለ ዘመን ስራ ፈትተው ቃላት ስንጠቃ ላይ የተሰማሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መከፋፈል የፈጠረው አለመረጋጋት ከቤተ ክርስቲያን አልፎ ሌላ ግዛት ውስጥ በመግባቱ ከዚህ የተነሳም ጉዳዩ የሮማውያን ነገስታት ቀልብ በመሳቡ ይህን ተከትሎም ከክርስቶስ ይልቅ የፖለቲካ ዓላማ የበለጠባትና ያንገበገባት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሮማ ነገስታት ህልውናና ግዛት በቤተ ክርስቲያን በኩል ማስቀጠል የምትችለው ቤትና ትዳር ባላቸው አገልጋዮች አማካኝነት ሳይሆን ሙሉ ጊዜውን የሰጠ የራስዋ የሆነ ሠራዊት መፈልፈልና ማደራጀት ስለነበረባት ምንኩስና እንደ ሽፋን በመጠቀም መልካም የሚመስል ግን ደግሞ ትክክል ያልሆነ አዲስ ኢ-መጽሓፍ ቅዱሳዊ አስተምሮ በመጻፍ ነበር። ደግሞ በሚገባ ተስክቷላታል።

 

ምክንያታዊ ለማስመሰል የሚነገረው ትርክት ማለትም፥ የበለጠ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለን ዘንድ የሚል ፈሊጥ አንዱ ነው። ይህን ሐሰተኛ አባባል ለማወፈርም መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ባንዴራ ማውለብለብ የተለመደ ነው። ሐቁ ግን፥ ዮሐንስ በድንግልና ጸንቶ ጌታን አገለገለ እንጅ ቤተ ክርስቲያን ልምራ ብሎ በቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦታ አለመቀመጡ ብቻ ሳይሆን ዮሐንስ በአስተዳዳሪነት የመራት ቤተ ክርስቲያን ተብላ በመጽሐፍ ቅዱስ የምትታወቅ ቤተ ክርስቲያን ለመኖሯ ማስረጃ አጣቅሶ ሊሞግት የሚችል አንድም ሰባኪ የለም። ሰባኪ ያልኩበት ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ኃይማኖትን ጨምሮ በሁሉም መድረኮች የተማረ ጥጉን ይዞ ኮከብ ቆጣሪና ጠጠር ወርዋሪ ያለ ከልካይ የሚፈነጭባትና መድረኩን የተቆጣጠረባት አገር ስለሆነች ነው። በማን አለብኝነት ቃለ እግዚአብሔር በማሻሻልና በመለወጥ ለበለጠ ስጋዊ ፍላጎታቸውና ምኞታቸው ለማርካት ሲባል ያላገባ/መኖክሴ የሚለው ሴራ እንግዲህ ታሪኩ ይህን ይመስላል። በመሆኑም፥ ሲኖዶስ ሲባል ልዩ ምትሃታዊ ቋንቋ ሳይሆን ታሪካዊ አፈጣጠሩና አመጣጡ የቤተ ክስርቲያን መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ያቀፈ ጉባኤ (assembly) እንጅ አስኬማና ጥቁር ጀለቢያ ያጠለቁ የባሳን ላሞች የመሳሰሉ ግለሰቦች ጋር በተለየ መልኩ የሚያቆራኝ ነገር እንደሌለው ማወቁ አስፈላጊ ነው። በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ተብሎ የሚታወቅ መንፈስ ቅዱስ የተለየው የጠንቋዮችና የመተተኞች ስብስብ መዋቅራዊ አሰራርና ህልውና መጽሐፍ ቅዱሳዊት ከሆነችው የቀደመችው ሓዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን ፍኖት የሚከተል ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በሮማ ነገሥታቱ ይሁንታና ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተፈጠረችው ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተቀዳ ነው።

 

ሌላው፥ ጳጳስ ከሰው የተገኘ ስጋ ለባሽ ሰው ነውና መጽሐፍ እንደሚያዘው አይደለም አንድ ሊቀልባቸውና በአግባቡ ተንከባክቦ ሊያሳድጋቸው የሚችለው ያህል ልጆች የመውለድ መብት አለው። ልዩነቱ፥ የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች መጽሐፍ እንደሚያዘው የአንዲት ሚስት ባል በመሆን፣ በትዳራቸው በመጽናት፣ ለትዳራቸው ታማኞች በመሆን፣ በጓዳም በአደባባይም እግዚአብሔርን በመፍራት የቅድስና ህይወት ይመሩ የነበሩ ትጉ አገልጋዮች ሲሆኑ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በአንጻሩ ደናግል ነን እያሉ ቅዱስ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰኝ ለማለትና ለንስሃ በራቸው የምታንኳኳ ሴት ልጅ ሁሉ የሚያስነውሩ፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደናግል እህቶቻችን ክብረ ንጽህና የሚጋሰሱ፣ ቀሚስ የለበስች ውሻ የሚያሳድዱና የማይምሩ፣ በዝግ ቤት የደናግል እህቶቻችን ህይወት የሚያበላሹና የሚያራክሱ፣ ይህን ነውራም ተግባር በጨለማ ሲፈጽሙ ጽንስ የተፈጠረ እንደሆነ እንዳይደረስባቸው ጽንስ የሚያስወርዱና የሚያስጨነግፉ፣ አምልጦ የተወልደም አላውቅልሽም በማለት ሴቶቻችን የሚያባርሩና የተወለደ ህጻን አጠበገባቸው እንዳይደርስ ሩቅ ስፍራ የሚያሰፍሩ፣ ሰው ሸሚዝና ካልሲ ሲለውጥ ሴቶች ሲለዋውጡ የሚውሉ፣ ንጹህ የሚጠጣ ውሃ በሌላት አገር ተቀምጠው የአውሮፓና የአሜሪካ የአልኮል ዓይነት ሲጨልጡ የምንጭ ውሃ በማጣጣም የሚታወቀው የዱር እንስሳ ዋልያ የሚያስቀኑ፣ እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ በርሃብ አለንጋ ሲገረፍ እነሱ ያለ ልክ ሲበሉና ሲጠጡ ተዘርዝሮ በማያልቅ የበሽታ ዓይነት የጠሰጠሱና ሰይጣን የሚያስቀና ቆሻሻ ህይወታቸው፥ በመስቀል፣ በአስኬማና ጥቁር ጀለቢያ የሸፈኑ አገር በቀል ቁማርተኞችና ነውራሞች መሆናቸው ብቻ ነው። እንግዲያውስ፥ የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋም አስፈላጊነቱ የትግራይ ህዝብ ከዚህ ዓይነቱ የጨለማ ቀንበርና የእርግማን ሰንሰለት ለመገላገል ነው።

 

ሌላው፥ ሲኖዶስ የሐዋሪያት መንበር ነው፤ ሊቃነ ጳጳሳት የሐዋሪት ምሳሌ ናቸው! የሚለው የተበላ ዕቁብ አባባል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን እንደማይመለከት ልናውቅ ይገባል። ለምን? የሐዋሪያት መሰባሰብ ለጌታ ወንጌል መስፋፈት እንጅ በንጹሐን ዜጎች ላይ ወንጀል ለመፈጸምና ለማስተባበር አይነበረምና። አንድም፥ ሐዋሪያት የሚታወቁ በቅድስና ህይወታቸውና የጠፋችውን ነፍስ ፍለጋ በሰማዕትነት ያለፉ ቅዱሳን መሆናቸው እንጅ፥ ስራ አጥተው፣ ነፍስ አጥፍተው፣ በአቋራጭ ለመበልጸግ፣ ቢዝነስ ለመስራትና ሌንጀራቸውን አውልቀው የሙንኩስና ቆብ የደፉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ነፈሰ ገዳዮችና አመንዝሮች ዓይነት ግለሰቦች እንዳልነበሩ ማወቁ አስፈላጊ። በመሆኑም፥ በንጹሐን ዜጎች ደም የጨቀየ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ሓዋሪያዊ መሰረትና ውርሻ ሊኖረው ቀርቶ ስብስቡ የአመንዝሮችና የወስላቶች ጉባኤ ከለባት ነው (የውሾች ጉባኤ) የሚለው ምስክርነት የታመነ ነው።

 

ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮሃለች

 

ለሺህ ዓመት የተገረ ውሸት ከሺህ ዓመት በኋላም ውሸት ነው። ለውሸት ተላልፎ የተሰጠ ሰው በአንጻሩ የፈለገውን ጊዜ እውነት ቢነገረው በላዩ ላይ የሰለጠነበት ውሸት ለመጣል ፈቃደኛ እስካልሆነ ድረስ እውነትን የመቀበል አቅም የለውም፤ ከዚህ የተነሳም የውሸት ባሪያ እንደሆነ ወደ መቃብር ይወርዳል የሚገላግለውም አይኖርም። ኢትዮጵያ ስትባል ፖለቲካዋ ብቻ አይደለም በውሸት የተሰገሰገው ኃይማኖትዋም ሊነገርና ሊገመት ባመይቻለው ልክ በውሸትና በደም የታጨቀና የተጨማለቀ ነው። ይህ አባባል በተጨባጭ ማስረጃ ለማስደገፍ ያለፈውን የትናንት ታሪክ ማውሳት አይጠበቅብኝም። ዛሬ ዓይናችን እያየ ኢትዮጵያ ሦስትና አራት የሰው አገር ሠራዊትና መንግስታት ገዝታና ጋብዛ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸመችው ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል በማስተባበር ረገድ የድርሻቸው እየተወጡ ከሚገኙ ሀገራዊና መንግስታዊ ተቋማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት ለመሰለፍዋ የሚክድ ባለ አእምሮ ሰው አይኖርም፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ራስዋም አልካደችውም። ድጋፍዋን የገለጸችው በአደባባይ ነውና። በመሆኑም፥ ትግራዋይ በዚህ ሰዓት ምን ጉዳይ ቢኖረው ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተብላ በምትታወቀው የሲዖል መጋበሪ ስር የሚሰባሰበው? ምን ለማግኘት? ትግራዋይ የሚባል ዘር ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት ብለው ተማምለው ከተነሱ ከኢሳይያስ አፈወርቂና ከዐቢይ አህመድ ዓሊ ጎን በመቆም አዎ! መጥፋት አለበት እያለች በቀንና በሌሊት በተጋሩ ላይ በምታሟርት ቤተ ክርስቲያን ምን ጉዳይ አለህ? ድፍን ዓለም እየተመለከተ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋም አላውቅህም በማለት ለገዳይ አሳልፋ በሰጠችህ ቤተ ክርስቲያን ስር ምን ትሰራለህ? በእውነቱ ነገር እስከዚህ ድረስ ነው ወይ የደነዘዝነው?

 

ሌላው ይቅር ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት በታንክና በከባድ ብረት ሲፈራርሱ፣ ቅዱሳት መጻህፍት በእሳት ሲቃጠሉ፣ ካህናት በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲታረዱ፣ ገዳማውያን ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ በማንነታቸው ለስደትና ለግዞት ሲማገዱ፣ የካህናት ሚስቶችና መነኮሳት ክብረ ንጽህናቸው በህሊና ቢሶች የኤርትራ፣ የዐቢይ አህመድና የአማራ ሰራዊትና ምኒሻ ሲደፈርና ሲራከስ እያየችና እየሰማች አበጁ! የምትል፣ የተጋሩ ሞትና ዕልቂት ስትሰማ በታላቅ ደስታ የምታሸበሽብና የምታሸረግድ ቤተ ክርቲያን ምን አለህ? እስከ ዛሬ ድረስ ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መላሽ በመስጠት ጎራው ያለየ ትግራዋይ ያለ እንደሆነ አሁንኑ ራሱን ከእውነት ጋር እንዲያስታርቅ እጠይቃለሁ። የደቡብ አፍሪካና የአውሮፓ አብያተ ክርስቲያን በጾምና በጸሎት ስለ የትግራይ ህዝብ እግዚኦ እያሉ በሚማልዱበትና ምህረት በሚለምኑበት ዘመን ይህች ቤተ ክርስቲያን ያደረገችውና እያደረገችው ያለ ተግባር ኮ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ድምጻቸውን እንዳያሰሙ የቁም እስረኛ አድርጋ ማስቀመጥ ነው። ጎበዝ፥ ይህቺ የበሰበሰችና የገማች የሙውታን ቤት ጥለህ በመውጣህ ከሞት ወደ ህይወት መጣህ እንጅ አንዳች ነገር አይቀርብህም። የሚቀርብህ ሞት ብቻ ነው። እንጀራህን የሚበላ ውሻ ያንተ አይደለማና ትግራዋይ ሁሉ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያንናት መሪዎችና አባቶች ጎን በመቆም ልክ ከዚህ ቀደም አዲዮስ ኢትዮጵያ! በማለት አንድነታችን ለዓለም እንዳሳየንና እንደገለጥን አሁንም አዲዮስ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ! በማለት መስቀል የጨበጡ የሲዖል አጋፋሪዎችና አማሳኞች ልንለያቸው ይገባል።

 

የትግራይ ሲኖዶስ የማቋቋም ሥልጣንና ኃላፊነት ያለው ማን ነው?

 

መንፈሳዊ ስልጣን፥ የሚሸመት፣ በይግባኝ በደብዳቤ የሚሰጥና በልመና የሚገኝ ነገር አይደለም። መንፈሳዊ ስልጣን መንፈሳዊ ስጦታ ነው። የትግራይ ካህናት ተሰባስበው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያዘው ከመካከላቸው መመዘኛው የሚያሟላ (ጸጋ፣ እውቀትና ጥሪ ያለው) አገልጋይ በመምረጥ በሊቀ ጳጳስ ማዕረግ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መሾም ይችላሉ ብቻ ሳይሆን ግዴታም አለባቸው። ይህ ብንወድም ባንወድም ቢመቸንም ባይመቸንም ቢገባንም ባይገባንም ብንቀበለውም ባንቀበለውም፥ የማይሸረፍ፣ የማይሻሻልና የማይለወጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዝና መመሪያ ነው። የትግራይ ሲኖዶስ የማቋቋም ኃላፊነት ሆነ የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የመሾም ስልጣን ያለው የትግራይ ቤተ ክርስቲያን ናት። የትግራይ ቤተ ክርስቲያን የራሷ ሊቃነ ጳጳስ በመሾም የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ማቋቋምን በተመለከተ ከጸሐይ በታች የመቃወምና እንቅፋት የመሆን፥ ሞራላዊ፣ መንፈሳዊም ሆነ ህጋዊ መሰረት ያለው አንዳች ኃይል የለም። ትግራይ ወደ ቀደመ መንፈሳዊ ስፍራና ስልጣን ለመመለስ፣ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ደህንነትና የተከታዮችዋ መንፈሳዊ ህይወት ለመጠበቅ ከተፈለገ የእያንዳንዱ ትግራዋይ መንፈሳዊ መረዳትና ንቃተ ህሊና መታደስና ዓይኑን ከፍቶ ማየት ይጠበቅበታል። የኮልኮሌ መዓት ይዛ እየሰመጠች ያለችው መርከብ ላይ ተሳፍሮ አዲስ ነገር የሚጠብቅ ትግራዋይ ያለ እንደሆነ ግን ሲበዛ የዋህ ነው። የሚፈለገው የትግራይ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን ማዕከል አድርጎ መንፈሳዊ ግዴታው የሚወጣ የተደራጀ መዋቅራዊ አስተዳደር ያለው ጉባኤ መፍጠር፣ ማቋቋምና ማደረጀት ከሆነ ከእያንዳንዳችን የቤተ እምነቱ ተከታዮች የሚጠበቅብን ለማድረግ ዝግጅዎች ልንሆን ይገባል። ለምሳሌ፥

 

1.      ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ እነዚህ አመንዝሮችና ነፈሰ ገዳይ ሊቃነ ጳጳሳት ያሰበሰበ ሲኖዶስ የሚመራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ራሱን መለየት ይጠበቅበታል፤ ይገባልም። ይህ የምለው አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በትግራይ የሚገኙ ወገኖቻችን ይህን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ ስለማይገኙ ነው።

 

2.     መጽሐፍ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ እንዲል ትግራይዋይ ባለበት ሁሉ ሊሰበባሰብና ህብረት ሊፈጥር፣ በአቅራቢያው የራሱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መስርቶ ሊደራጅ ይገባል።

 

3.     የሚፈጠሩ ህብረቶችና መሰባሰብ ተከትሎ የትግራይ ካህናት በአጠቃላይ የአገልጋዮች ጉባኤ ማቋቋም።

 

4.    ይህ ተጋሩ የሥነ መለኮት ሙሑራን ያቀፈ የሚቋቋመው ጉባኤ የትግራይ ምእመናን መንፈሳዊ ህይወት ለማሳደግና ለመጠበቅ ይጠቅማል በማለት በጸሎትና በምክክር የሚሰጠው መንፈሳዊ መመሪያና አስተዳደር በመቀበል አገልግሎት መጀመርና መሰባሰባችን ማስፋት ነው። ይህን ማድረግ ስንችል የትግራይ ቤተ ክርስቲያን ለመምራት ያስችለን ዘንድ በአገልግሎታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ተመርጠው በሊቀ ጳጳስ ማዕረግ መሪዎች በመሾም የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ማቋቋም ብቻ ሳይሆን ቱንቢውን ጠብቆ የሚገነባ መንፈሳዊ ሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር ለመዘርጋት ያስችለናል። ይህን የመሰለ ተቀደሰ ሃሳብ፣ መንፈሳዊ ህብረትና የወንድማማች መዓድ የሚቃወም ታድያ የኃጢአት ጸሐፊ የሆነው ሰይጣንና ግበረአበሮቹ ብቻ ናቸው።

 

በዚህ አጋጣሚ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት ቢኖር፥ ጉዳያችን በማስመልከት አስተያየቱን እንዲያካፍለን የምንጠይቀው አካል ሊኖር ስለማይችል ስራችንን ስንሰራ አይቶና ሰምቶ መሬት ይያዝልኝ በማለት የሚያጓራ ጦቢያና ሰንበላጥ ቢኖር ሲደክመው ይተዋዋል የሚል ጽኑ እምነት ስላለኝ ሰዎች ምን ያላሉ በማለት ሰዎች የሚሉትን ለመስማት የሚባክን ጊዜ እንደሌለን ለማከል እወዳለሁ።

 

ይህን ያውቁ ኖሯል?

 

ጥቁር የራሱ ሊቀ ጳጳስ መሾም አይችል፤ የዋለው እንደሆነም የተረገመ ነው የሚል ቃል ሰማያዊ ቃል ነው እያለች ኢትዮጵያን ለዘመናት ስታገብር፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የፈርዖን ተረት ተረት እውነት ነው ብላ በመቅበል፤ ግብጽም ሼክ ይሁን ሱፊ የማይታወቅ ብቻ ግን መስቀል አስያዛ የምትልከው ግለሰብ እየተቀበለች መስቀሉን ስትሳለምና ስታሳልም የኖረች ቤተ ክርስቲያን ከገባችበት መንፈሳዊ አዘቅትና እስራት የገላገላትና ነጻ ያወጣት ሌላ ማንም ሳይሆን የህግጋት ሁሉ ምንጭና የዝማሬ መገኛ የሆነችው ከትግራይ የተገኙ የብሉያትና የሃዲሳት መጻህፍት አዋቂዎችና ሊቃውንት ተጋሩ ቅድሳት መጻህፍት የሚለው ሐቅ ይዘው ግብጽን አሻፈረን ማለታቸው ተከትሎ ነው። ሌላው ገና ለውሃ ጥምቀት የበቃ ህዝብ አልነበረምና። ኋላ የመጣ ዓይን አውጣ እንደሚባለው ግን የምስራቹን ቃል ሰብከን ያጠመቅናቸውና ስም ያወጣንላቸው ሰዎች ዛሬ ተገልበጠው እኛን ሊያስተምሩና ሊነግሩን አላፈሩም።

 

ጥጉ፥ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ሲኖዶስ ለማቋቋም ሆነ የራሷ ሊቃነ ጳጳሳት በመሾም የተከታዮችዋ መንፈሳዊ ህይወትና ደህንነት ለማረጋገጥ የማንም ፈቃድ አይሻትም። በርግጥ፥ ይህን ጽሑፍ አንብቦ ተጋሩ የራሳቸው ሲኖዶስ ሊያቋቁሙ አይችሉም፤ አይቻልም! የሚል ወፈፌና የጠንቋይ መዓት መነሳቱ የማይቀር ነው። አንድም፥ እነዚህ ትምክህተኞችና ግብዞች ለሚያሰሙት ጩኸት በምክንያት አስደግፈው የሚያቀርቡት ጭብጥ ኖራቸው ሳይሆን ሰዎቹ ሟሟራት የአባታቸው ስለሆነባቸው ብቻ ነው። ከዚህ ሁሉ ሞትና እልቂት በኋላም ኢትዮጵያ ተብላ ከምትታወቀው የሴሰኞችና የአመንዝሮች አገር ክፉ ልክፍት ያልተላቀቀች ነፍስ ካልሆነች በስተቀር ይህን ባደርግ ኢትዮጵያውያን ምን ይሉ ይሆን? በማለት ከስራው የሚስተጓገል ትግራዋይ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። በመስኮት ላይ መቀመጥ ይፈጅህ እንደሆነ ነው እንጅ አይበጅህምና ያልቆረጠና ያልለየለት ሰው ያለ እንደሆነ አሁንኑ ሊለይለትና ከእውነት ጋር ሊወግን ይገባል። ዘመኑ እዚህም እዚያም የምንረግጠበት ዘመን ሳይሆን ከእውነት ጋር በመወገን ላመንበት እምነት እስከ ሞት ድረስ በመታመን ቆመን የምንታገልበት ዘመን ነው።

 

በተረፈ፥ የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋም በትግራይ ህዝብ ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ዕድገትና ለውጥ በተጨማሪ የሚፈጠረው፥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መነቃቃት በቀላሉ የሚገመት አይደለም። በመሆኑም፥

 

1.      የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋም፥ ከምንም በላይ ለእውነትና ለጽድቅ መቆም ሲሆን፤ የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋም፥ ሀገረ ትግራይ በመንግስትና በቤተ እምነት መካከል ያለው መስመር በመጠበቅ ሁለቱም አካላት የተጣለባቸው ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ስለሚያችል ነው።

 

2.     የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋም፥ የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት ከሚባለው የምዋርተኞችና የምቀኞች የበከተ አስተሳሰብ በማላቀቅ፣ ዕውቀት መሰረት ያደረገ የበለጠ ስልጡን ትግራዋይና የበለጸገች ትግራይ ለመገንባት በሚደረገው አዲስ ጉዞ ላይ የማዕዝን ድንጋይ ማኖር ስለሆነ።

 

3.     የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለራሳቸው አይገቡ ሌላውን እንዳይጋባ የሚከለክሉ፣ በተቀመጡበት ስፍራ ሁሉ የሚያንኮራፉና የሚቃዡ፣ የሙውታን መስባሰቢያ ከመሆኑ በላይ በታሪክ በተደጋጋሚ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አባቶች የገደለና ያስገደለ ስብስብ መሆኑን ይታወቃል። በቀድሞ መጠሪያው አጠቃላይ ጉባኤ በአሁን ሰዓት ደግሞ ማህበረ ቅዱስን ተብሎ የሚታወቅ ቤተ ክህነትና ቤተ መንግስት በመጠቅለል የሽዋ መንግስትነት ለመመለስ እንቅልፍ ያጣ ፊደል የቆጠረ ደንቆሮ አስተባባሪነት ፓትሪያሪክ ቲዎፍሎስ ደርግ አብዮታዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው ሲኖዶሱ ለወታደራዊው የደርግ መንግስት በምስጢር ደብዳቤ ጽፎና ተፈራርሞ በጥይት ያስረሸናቸው ሲሆን፤ ለፓርቲያሪክ ጳውሎስም በወቅቱ ከዋሽንግተን እስከ አስመራ መሽገው የነበሩ ትግራይ ፎቢያ የጸናባቸው እንደ እነ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ የመሳሰሉ የግንቦት 7 የአረጣ ፖለቲካ ነጋዴዎች በመመሳጠር ቤንሻንጉል ጉምዝ ድረስ በመሄድ በምዋርትና በጥንቆላ ሲያቅታቸው በቤተ መቅደስ ቅዱስ ቁርባን ውስጥ መርዝ በመጨመር የገደለ ስብስብ ነው። በተመሳሳይ፥ ፓትሪያሪክ ብጹዕ አቡነ ማሪያስ በትግራይ ህዝብ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይናገሩና ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነትዋን እንዳትወጣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ከኮሚኒስቱ ከኢሳይያስ አፈወርቂና ከዐቢይ አህመድ ዓሊ ጋር በመተባበር ፓትሪያሪኩ የቁም እስረኛ ሆነው እንዲቀሙጡ በማድረግ ነፍሰ ገዳይ ማንነቱ ለዓለም አስመስክረዋል። የትግራይ ሲኖዶስ መቋቋም አስፈላጊነት እንግዲህ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ዓይነቱ አረመኔያዊና ሰይጣናዊ ድርጊትና ባህል ለመገላገል ነው።

 

ይህን መራራ እውነት ሲሰማ ዘራፍ! የሚለው ትምክህተኛ ታድያ በጉባኤ ያለፈ የመጻህፍት አዋቂ ሳይሆን፥ ነጠላ ለብሶ ጥላ ዘርግቶ መለመን ጽድቅ የሚመስለው የደርግ ወታደር ነበር ጡረተኛና ተረት ተረት በማውራት፣ በመጮህና ከበሮ በመምታት የእግዚአብሔር መንግስት የሚገባ የሚመስለው ሰንበቴ፣ ከሰንበት ት/ቤት ያላለፈ እውቀት ይዞ ዳሩ ግን መምህር፣ ዘማሪ፣ ሰባኪ፣ መጋቤ ምናምን እያለ ራሱን በቁልምጫ የቀሚስ ስሞች የሚጠራ (አባባሉ፥ አቅማቸውን አውቀው በቅንነት የሚያገለግሉ የሰንበት ት/ቤት አባላት አይመለከትም)፣ ያለ ዕውቀት ምክርን የሚያጨልም ያልበራለት ደንቆሮ ብቻ ነው። በርግጥ፥ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ለማድረግ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ ከዝግጅት አንጻር ለጊዜው የትግራይ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ማደራጀትና የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስትያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ማቋቋም በቂ ነው (እስከ አሁን ድረስ ያልተቋቋመ እንደሆነ)። ቀደም ሲል እንደተገለጸው ግን፥ የመጮህ አመል ያለበት፣ ተራጋሚ ዜጋ ካልሆነ በቀር የቤተ ክርስቲያን መሪ ስለ መሾም ሆነ ጉባኤ (ሲኖድ) ስለማቋቋም ግልጽ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ በመቃወም የተሻለ ሃሳብ አለኝ የሚል፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚያምጽ ሰው ቢገኝ ታድያ ያ ሰው የተወዳጀው ከእግዚአብሔር ሳይሆን የራሱ ልበ ወለድ ድርሰት እያጣቀሰ ጠፍቶ ከሚያጠፋ የሐሰት አባት የተባለው የሰይጣን ባለሟል ለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም። አዎ! ትግራይ የራሷ ሲኖዶስ ማቋቋም ትችላለች የሚለው የትግራይ ህዝብ እምነትና አቋም እየበረታ ሲመጣ ነፍሰ ገዳዩ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ የማይቀር ነው። እዚህ ላይ አንድ የማይገባኝ ነገር ቢኖር ታድያ፥ ነፍሰ ገዳዩ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ትግራይ የራስዋ ሲኖዶስ ማቋቋም አትችልም በማለት ዘራፍ ማለቱ ሳይሆን ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ እንደ ከብት አጋድሞ እያረደ ከሚገኘው ነፈሰ ገዳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በጎ ፈቃድ የሚጠብቅ ሰው የተገኘ እንደሆነ ብቻ ነው።

 

E-mail: mahbereseytan@gmail.com

Back to Front Page