|
እንዲህም ብሎ ነበር
ኢዮብ ከጮማ እምኒ 09-19-21
ግንቡን እናፍርስ ወያነ የሰራውን እንዲህም ብሎ ነበር ...
መዶሻ እንያዝ አካፋ አንርሳ ብሎ ነበር እሱም ገጀራ ቆንጨራ ሽመልስ አባ ዱላ ... ከዘራ ቢላዋ አትርሱ አደራ .... ብሎ ነበር እሱም ሌባና ፀጉር ለውጥ ...ጉንዳንና ጀዝባ የናት ጡት ነካሽ ... ባንዳ ጭልፊት ሽፍታ ብሎ ነበር እሱም ፍቅርና ፀሎት ማቀፍ መተቃቀፍ መያያዝ መፋቀር …ንግስና ምናምን ብሎ ነበር እሱም ንቀትና ጥጋብ ንግሥና አስክሮት የማይነካ ነካ አረከሰ ራሱን
አገሩን አዋርዶ ... ድህነት ሰቆቃ ስደትን አስፋፍቶ ሸንግሎና ዋሽቶ መርዝ የሆነ ችግኙን ... በአገሩውስጥ ተክሎ ዋልጌነትን ነውር ... ሀጢያት እንደዉረርሽኝ በየቦታው ዘርቶ ሽማግሌ አዛውንት ... ድሀና ሀብታሙን ከየስሩ ነቅሎ ይሄ አልበቃ ብሎት ... ረከሰ ወረደ ነካ የማይነካውን አራዊቶች አበራከተ ... በንግስናው ዘመን
ሀሉም ሲያጨበጭብ ...ቄሰና ዲያቆኑ ሼክና ፓስተሩ ወጣቱን ...ባረከው ስብከው የማይሆነውን ሰደዱት ወደ ትግራይ ሊያፋጥኑት ሞቱን
እንዲህም ብሎ ነበር ... ሲቀበር የላከው ለ መለማመጃ ነው ... ስንልካቹህ ትግራይ ዞር እንድትሉልኝ ... ፊታችሁን እንዳላይ ይሄ ሰባተኛው ... ንጉሥ ነኝ የሚለው የማይነካ ነክቶ ... ሲያጥር አየሁ እድሜው ።
ትግራይ ለጠላቶቿ ሁሌም ረመፅ ነች !!!
ትግራይ ትስዕርን ፈረቃን !!! ኢዮብ ከጮማ እምኒ
|