Back to Front Page

ዱቄት

ዱቄት

ተብዬ ነበረ ያለቀለት ዱቄት ...

እርባና የሌለው ዱቄት ... ማያመጣ ውጤት

እርሱት ዱቄት ነው ... የትም የማይደርስ

በአየር ላይ ተብትኖ ... የጠፋ በነፋስ

ያለቀለት ነው ... ዳግም ማይመለስ

ዱቄት ነው ዱቄት  ... ማይታይ ማይዳሰስ

ዱቄት ነውዱቄት

 

ደገሙ ደጋገሙ ...  በሀጢያት የከበሩ

በመግደል የደቆኑ ... በመግደል የነገሱ

ደገሙ እንዲህ ብለው ...

... ዱቄት ነውዱቄት

እፍ ብሎ የጠፋ ...ማይጨበጥ ማይታፈስ

ያከተመ ያለቀለት ... ዳግም ማይመለስ

እርሱት የሌለውን ... ደምሰሱት ከመዝገብ

 

መልሴ እንዲህ ነበር ... ላሉኝ አንተ ዱቄት…

… አዎ  ...

... ዱቄት ነኝ አዎ ዱቄት ... ምርጥ የሆነ ዱቄት

በእርጉሞች አይን ... በፋሺስቶች እምነት

ተነነ ሲሉኝ ... የምዘራ ህይወት

ዱቄት ነኝአዎ ዱቄት

 

አዎነኝ ዱቄት ...

ሰብስቤ ዱቄቱን ... ከዚህና ከዛም

በእናቴ እንባ ... አብኩቼ ዱቄቱን

ግማሹን ወደ ... አምባሻ  ህይወቴን ለማዳን

ግማሹንዱቄት ደግሞ ...

... በታረደው ውንድሜ ...  በፈሰሰው ደሙ

አብኩቼ ዱቄቱን ... ቀይሬ ወደ ብረት

...ኮልሼ አምባሻ ... አንግቼ ብረቱን

... ቀምሼ ...  ተኩሼ ተኳከሼ

ገፍቼ ገፍትሬ ... ኮስትሬ ኮስታትሬ

ዱቄቱ ...  የበነነው የጠፋው የተበተነው

ስማ ቢሉኝ እኔን ... እላለሁእላለሁ ደጋግሜ

... እምቢ  ... ኣይሰምዕንየ ... እምቢኣይሰምዕንየ!

ትግራይ ስዒራ !!!

 

ኢዮብ ጮማ እምኒ

11-20-21

 

Videos From Around The World

Back to Front Page