Back to Front Page

አክብሩ ልደቱን

አክብሩ ልደቱን


ኢዮብ ከጮማ እምኒ

01-06-21


እናንተ  ስታከብሩ ... ባንድ  ላይ  ሆናችሁ ...
እኛ  ወሬ  አጥተን ... የሞተን  በህይወት  ያለን
እናንተ... ባንድ  ላይ  ስትሆኑ ... በዛ  በሞቀ  ቤት
እኛ ..  ቤተ  አልባ  ሆነን ... እደጅ  ተበትነን
ጦርነት  እና  እልቂት ...   በአዋጅ  ተፈርዶብን
እናንተ ...
በግ ፣ ፍየል  ሙኩቱን ... ስታርዱ  ለመብላት
እኛ  ስንታረድ ... በራችን  ፊት  ለፊት
ደማችን  ሲንቆረቆር ... ሲፈስ  ልክ  እንደ ከብት
ቢላውን  ስትስሉ ... ብሩንዶ  ልትቆርጡ
እኛ  ሽሮው  ናፍቆን... እንጀራና  ወጡ

እናን  ስትስክሩ ... በቢራ  በጠላው
እኛ  ወሀ  አጥተን ... ተጥምተን  ምንጠጣው 
ሙዚቃ  ከፍታችሁ ... ስትስቁ  ስትጨፍሩ
እኛ  መብራት  አጥተን ... በአገር  በሰፈሩ
ገንዘብ  ስትሸልሙ ... ለአዝማሪ  ደናሹ
እኛ ...
ባንኩን  ዘግተውብን ... ተከልክለን  ብሩን

የሀይማኖት  መሪዋች ... ሲባርኩ  ገናን
ብለው  እንደልማድ ... ሲባርኩ  ሁሉን
እኛ  ስንጮህ ... የፈጣሪ  ብለን
ዜጎች  እንዳልሆንን ... በሁሉም  ተረስተን
እናት  ስትደፈር ... በአራዊት  ሰራዊት
አባት  ሲገደል ... ልጅህን  ካልደፈርክ  በማለት
መቼ  ታይቶ  ያቃል ..  እንደዚህ  አይነት  ሀጢያት
ታርጋ  ተለጥፎ ... ለኛ  ለብቻችን
የምክንያት  ጋጋታ .. ክሱ  ሲቀርብብን
መራብ  መጠማት ... መገደል  መሰደዱን ...
ጥፋቱ  የኛ  እንደሆነ ... ሁሉም  ሲፈርድብን
የኛ  እናት  ስታለቅስ ... በልጇ  መታረድ
በባሏ  መገደል ... በእህቷ  መሰደድ
እናንተ  ስትጨፍሩ ... በኛ  እልቂት  መከራ
እናት  እንደ  ሌለው ... ለልጇ  የምትራራ
ጡሩምባውን  ስትነፉ ... ስታውለበልቡ  ባንዴራ
አንድ  አገር  መኖራችንን ... ሁላችን  እስክንረሳ
ጥያቄ  እንድንጠይቅ... እኛስ  ማነን  ብለን
ላለንበት  አገር ... ህይወት  እንዳልሰዋን
ቤታችን  ሲፈተሽ ..  ከስራ  ስንባረር
ማነው  የጮኸልን ... በድፍረት  የሚናገር ?

የጠፋን  መስሏችሁ ... ያለቅን  የሞትን
ልባችን  ተሰብሮ ... መታገል  ያቃተን
አዬ  አለምወቅ ... አይ  አለመታደል
ትግራይ  ልማዷ  ነው ... ትመጣለች  በድል!

ክብርና ሞገስ በግፍ ለተገደሉ ሰማዓቶቻችን !
ትግራይ ትዕወት !!!!




Back to Front Page