Back to Front Page

አገገምሽ ወይ ማማ ?

አገገምሽ ወይ ማማ ?

ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ

10-02-21

 

አገገምሽ ወይ ... ማማ
ከቁስልሽ ከህማምሽ ... ከሀዘን ከስቃይሽ
እንባሽ ታበሰ ወይ  ..  በቀሩት ልጆችሽ

ለአራዊት ፋሺስቶቹ ..  ምን ነበር መልእክትሽ  ...
ልጆችሽን... ለደፈሩ
ያረዱትን ያቃጠሉ ... በጭካኔ የተሙሉ
መሬትሽን የወረሩ ... በደጅሽ በምድርሽ ደምን ላፈሰሱ

የገፉሽን ያጠቁሽን ... ምን ብለሽ ረገምሻቸው
ምን ብለሽ አውገዝሽ ... ምን ቃላት ተጠቀምሽ
ልጆችሽን እንዳትቀብሪ ... የከለከሉሽን
ለአራዊት እራት ... የዳረጉብሽን
እስቲ እንወቀው ... እስቲ እንማረው

እንዴትስ ውለሽ ... እንዴትስ ታመሺያለሽ
እንዴትስ ቆመሽ ... ወጥተሽ ትገቢያለሽ
አለቀብሽ ወይ እንባው ... ፊትሽን ያጠበው
ልሳንሽ ተዘጋ ወይ ... ኡይይይ ብሎ የጮኸው

እስቲ ንገሪን ማማ ...
.... ምን ነበር መልሳቸው
ሲደፉ ልጆችሽን ... ሲያፈሱ ደማቸውን
ምን ነበረ ያሉሽ ... ምን ቃላት ወጣቸው
ምን ምክንያት ሰጡሽ ... ምን ነበር መልሳቸው
እስቲ ንገሪን ማማ ...  
ማን ያርሳል መሬትሽን ... ማንስ ዘራው ሰብልሽን
ተረፉ ወይ በሬዎችስ ... እንጀራ ሚመግቡሽ
ምን በልተሽ ትውያለሽ ... የሚጠጣስ ታገኚያለሽ 

ንገሪን እስቲ ማማ ... ሁሉ የሆነውን
ሀጢያትና ግፉን ... ጭካኔ በደሉን
ይመዝገብ እንዳይጠፋ ... ይነገር ለአለም
እያንዳንዱ ወንጀል ... እያንዳንዱ በደል
ስማቸው ይታወቅ ..  ፎታቸው ይለጥፍ
ተባረከው ተመርቀው ... በጥላቻ ሰክረው
ዘርሽን ሊያጠፉ ...  ምድርሽን ሊያራከሱ
ለአብይ ለኢሳያስ ... መሀላ የማሉ
... አገገምሽ ወይ ማማ ?
ትግራይ ትስዕር !!!

Videos From Around The World


Back to Front Page